uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 042 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 281-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 239-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 042 obunachiga ega bo‘ldi.

28 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 512 ga, so‘nggi 24 soatda esa -6 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.18% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.37% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 039 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 663 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 30 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 29 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 042
Obunachilar
-624 soatlar
+917 kun
+51230 kun
Postlar arxiv
እንኳን ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ✤፨✤ አቡነ መብዓ ጽዮን አቡነ መብዓ ጽዮን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል (ጥቅምት 27 ቀን) ጋር አብረው የሚታሰቡ ታላቅ የተጋድሎ አባት ናቸው፡፡ የጻድቁ አቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያቸው ከመድኃኔዓለም በዓል ጋር ስለሆነ በዚህ ጽሁፍ ሥር ታሪካቸውን ይዘን ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ! አቡነ መብዓ ጽዮን የተገኙት እግዚአብሔርን እያስደሰቱ ያለነቀፋ ከሚኖሩ ቅዱሳን ነው፡፡ በክህነታቱ፣ በየዋህነቱ ከሰዎች የተስማማው አባታቸው ሀብተጽዮን፣ በደግነቷና በቸርነቷ የምትታወቀው እናታቸው ጽዮንትኩና በሕግ በንፅህና በጋብቻ ተወስነው ሲኖሩ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይለምኑ ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ክርስቶስም መብዓ ጽዮን የተባለ ደግ ልጅ ሰጣቸው፡፡ መብዓ ጽዮን ከልጅነቱ ጀምሮ ማስተዋል እና የእግዚአብሔር ፍቅር ያደረበት ሰው እንደነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ ይኸውም በአንዲት ቀን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብሎ ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ይሄድ የነበረ ሰው እግሩን እንቅፋት ተመቶ ደሙ ከመሬት ሲፈስስ በአየ ጊዜ እውቀት በልጅነቱ የሞላ መብዓ ጽዮን የደማው ጣቱ እስኪደርቅ ድረስ ጠባው፡፡ በመሬት የፈሰሰ ደሙን ከአፈሩ ጋር በላ፡፡ ይህ ሥራው ከልጅነቱ የመስቀሉ ፍቅር በልቡ የቸነከረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ #ያገባ ሰው ሚስቱን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል፡፡ ያላገባ ግን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ሥራ ያስባል$ የሚለው የመጽሀፍ ቃል ያፀናው ወጣቱ መብዓ ጽዮን ከቤተሰቡ የመጣለትን የጋብቻ ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ ኃጢአትን ከመጨመር ውጭ ምን እጠቀማለሁ እያለ የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቃት፡፡ በዚህም ቤተሰቦቹ ተውት፣ እርሱም ራሱን ይበልጥ ለእግዚአብሔር አስገዛ፡፡ የምንኩስና እና ተጋድሎ ሕይወቱ የምንኩስ እና የተጋድሎ ሕይወት የጣመ የላመ የሌለበት ፍፁም ራስን ለእግዚአብሔር ማሳለፍ ነው፡፡ ይህንን የማይወድ ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ፍፁም ፈተናን ያበዛል፡፡ ቅድሳንም በረድኤተ እግዚአብሔር እና በተጋድሏቸው ያልፉታል፡፡ ሠይጣንን ድል ይነሡታል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮንም የምንኩስና ቀንበር ከተሸከመ ጊዜ ጀምሮ ከፈረስ፣ ከበቅሎ፣ ከአልጋ፣ ከምንጣፍ ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ መኖሩን ገድሉ ይነግረናል፡፡ ለዚህም ተጋድሎ ሕይወቱ ያግዘው እና ይረዳው ዘንድ ክህነትን አባ ገብርኤል ከተባለ ጳጳስ ተቀብሏል፡፡ ቄስም ሆኖ የመድኃኔዓለምን ሥጋው እና ደሙን እያቀበለ ብዙ ዘመን ኖሯል፡፡ የምንኩስና ሕይወቱና ትጋቱም ታላቅ አባት እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ትልቅ ድንጋይ በደረቱ ተሸክሞ ከምድር ከአመድ በተቀመጠም ጊዜ በራሱ ተሸክሞ፣ በሚሰግድም ጊዜ በጀርባው አዝሎ ስለ ክርስቶስ መከራ ያስባል፡፡ ራሱን ይበድላል፣ ስጋውን ያደክማል፡፡ ይኸውም ያለሰንበት እና ያለበዓላት በቀር በዚህ ተጋድሎ የምንኩስና ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከዛም ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ከአቡነ ተክለሃይማኖት መቃብር በረከትን እንደተቀበለ ገድለ መብዓ ጽዮን ይነግረናል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን ራሱን ለእግዚአብሔር በሰጠ ቁጥር መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋወደሙ እየተገለፀ፤ እመቤታችንም እየታየች ትመክረው ታስተምረው ነበር፡፡ ቅዱሳንን ማክበር በዓላቸውን መዘከር እንዲገባ ከምንማርባቸው ታሪኮች አንድ የአቡነ መብዓ ጽዮን ታሪክ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን እና የእናቱን የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል አብዝቶ ያከብር ነበር፡፡ በዚህም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከቅድሳን ጋር መጥቶ ባርኮታል፡፡ የመለኮት ምሥጢርም ሥርዓትም በአካባቢው ላሉ ሠዎችም ተሠጥቷቸዋል፡፡ መናፍቃን በዓል ማክበር አይገባም ቢሉ የበዓል ማክበር ውጤቱ እዚህ ድረስ መሆኑን እናያለን፡፡ በፀሎቱም #ኦ እግዚኦ አንተ ትብለኒ ሰአል ኩሎ ዘፈቀድከ ወአነ እሁበከ፣ ጌታ ሆይ አንተ የወደድከውን ሁሉ ለምን እኔ እሠጥሃለሁ አልከኝ፡፡ አሁንም የለመንኩን ግለጽልኝ$ በማለት የቀራንዮን መስቀል መከራውን ያሳየው ዘንድ ሁልጊዜ ይለምን ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን የሆኑ እጆቹን በመስቀሉ እንዲዘረጋ፣ እግሮቹም እንዲቸነከሩ፣ የሾህ አክሊልም በራሱ ተሸክሞ የጥቅምት 27 ቀን ታየው፡፡ ለሙሴ ሊታያቸው እንዳልቻለ አባ መብዓ ጽዮን ከመሬት ወደቀ፡፡ እንደ ሞተም ሆነ፡፡ ማንም የመስቀሉን መከራ ሕማሙን ማየት እንደማይችል ነገረው፣ በቸርነቱም አነሳው፡፡ የሞቱ ገናንነት የሚያስፈራ እና የሚያስደነግጥ መሆኑን አሳውቀው፡፡ መከራው ታላቅ በሰው አእምሮ አይታሰብምና ነው፡፡ ኃጢአትን ያልሠራ ሐሰትም በአፉ ያልተገኘበት ስለሠው ኃጢአት ስለሞተው ስለመድኃኔዓለም ክርስቶስ የሞቱ መታሰቢያ በምትሆን በዕለተዓርብ ታላቅ ተጋድሎን በማድረጉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለት በዓል በሚታሰብበት በ27 በመድኃኔዓለም ዕለት የአቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያ ተደረገ፡፡ ይኸውም ጥቅምት 27 ነው፡፡ /ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/ የጻድቁ የአባታችን የአቡነ መብዓ ጽዮን በረከት ከእኛ ጋር ትሁን!!! የመስቀሉ ፍቅር በልባችን ይኑር አሜን!!!

፨፨ በአዲስ አበባ የመድኀኔ ዓለም ክብረ በዓል ያለባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንጠቁማችሁ፤ (ስብስብ 4) (ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡) ✤ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ቤ.ክ ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምወደ.ት. ቅ. ገብርኤል ቤ.ክ ✤ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔዓለም፤ (ታቦተ ሕጉ ባይወጣም በሰዐታትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡)፤ 6 ኪሎ ✤አቃቂ ጋራው መድኀኔዓለም፤ ✤ረጲ መካነ ጎልጎታ መድኀኔዓለም፤ረጲ ✤መንበረ ሕይወት መድኀኔዓለም፤ አቃቂ ክ/ከተማ ✤ደብረ ቅዱስ ደብረ ቀራሜሎስ ካራአሎ መድኀኔዓለም ወአቡነ ገሪማ፤ የካ ክ/ከተማ ✤መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም፤ የካ ክ/ከተማ ✤ቦሌ ቡልቡላ ደብረ ገነት መድኀኔ ዓለም፤ቦሌ ቡልቡላ ✤ድልበር መድኀኔዓለም፤ ጉለሌ (ቶታል) ✤ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ.ክ ልደታ ሜክሲኮ ✤ደብረ ሳሌም ቦሌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን (የመድኀኔዓም ታቦት በድርብነት ይገኛል)፤ ቦሌ ✤ምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኀኔዓም ቤተክርስቲያን፤ቀበና ✤አያት መድኃኔዓለም፤ አያት ✤ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔዓለም፤ደቡባዊ አ.አ ✤ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡ ✤ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል ፡፡ ጎተራ ✤የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ወኢሉጣ ቤ.ክ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፤ ለገሃር ✤ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡ ✤ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም ቤ.ክ (የመድኀኔዓለምና የመብዓ ጽዮን ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ.ክ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ ኮተቤ(ሲምሲ) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል)

4. ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ (ስብስብ 3)፤ የ108 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ለዛ
+4
4. ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ (ስብስብ 3)፤ የ108 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ፡፡ (ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡) ስለ ታላቁ ደብር ብዙ ነገር ባወራን ደስ ባለን ነበር ….. የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ ያደረባት ደብረ ሰላም ብዙ ነገሮች አሏት፤ የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዛወሩ ካህናት ኹሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው፤ ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ኹሌም የሚደነቁበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡ ✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡)

በሃገራችን ከሚገኙ በመድኀኔዓለም ስም የተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት፤ ስብስብ 2፤ ጨነቅ ዋሻ መድኀኔዓለም፤ በቅዱስ ላሊበላ በዋሻ ውስጥ እንደገና ፎቅ ተደርጎ የተፈለፈለ፤ በሰሜን ተራሮች (በራስ ደጀ
+3
በሃገራችን ከሚገኙ በመድኀኔዓለም ስም የተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት፤ ስብስብ 2፤ ጨነቅ ዋሻ መድኀኔዓለም፤ በቅዱስ ላሊበላ በዋሻ ውስጥ እንደገና ፎቅ ተደርጎ የተፈለፈለ፤ በሰሜን ተራሮች (በራስ ደጀን) እግር ሥር የሚገኝ፤ በፓርክ ክልል ውስጥ በመኾኑ በብዙ ኢትዮጵያውያን የማይታወቅ፤ ነገር ግን ብዙ ተዓምራትን እጅጉን ፈዋሽ የኾነ ጠበል የሚገኝበት፡፡ 1. ✤መናገሻ ጋራ መድኀኔዓለም፤ ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቀድሞ የቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡ 2. ✤ገዳመ አባ ጽጌ ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡ 3. ✤ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ቤ.ክ፥ አዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡ (ነገር ግን በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል)

እንኳን ለጥቅምት መድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድ
+2
እንኳን ለጥቅምት መድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤ ፤ ስብስብ 1፤ ፠ ለየብቻቸው ያሉት፤ ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳምና ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም ቤ.ክ. ፠ አንድ ላይ ያሉት፤ ✤1. ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳም፤ ✤2.ላሊበላ መድኀኔዓለም ✤3. ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም ✤4. መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና ✤5. ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ ✤6. ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ ✤7.ቦሌ ደብረ ሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ፤ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብ አለ) ✤ 8.ድሬዳዋ መድኀኔዓለም ✤9.ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም

#በየቀኑ_ምግብ_ስንመገብ_የምናስባቸው_ታላቁ_አባት_ዛሬ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ነው፡፡ ምግብ ተመግበን ‹‹ስብሐት ካልን›› በኋለ ‹‹#በእንተ_አቡነ_አቢብ_ብለን የምናስባቸው፡፡ ✤✤ ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና በእንተ(ስለ) አባ ቡላ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን ማርልኝ ብለው ታላቅ ቃል ኪዳንን መድኀኔዓለም የሰጣቸው አባት ናቸው፡፡ በዚህም ኹል ቀን /ከተመገብን ‹‹ስብሐት ካልን›› በኋላ ስለ አባ ቡላ/አቢብ/ ብለን የምናዘክረው ታላቅ አባት ነው/ **** እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አባት አባ ቡላ (አቡነ አቢብ) በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ✤ አቡነ አቢብ በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነገሠ ዘመን የነበረ፤ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት የኾነና 3ት ጊዜ ሞቶ 3 ጊዜ የተነሣ (በተጋድሎ ሕይወቱ 10ር ጊዜ ሞቶ የተነሣ) ታላቅ ሰማዕተ ጽድቅ ነው፤ በሃገራችን በኢትዮጵያ በስማቸው 3ት ታላላቅና ጥንታዊ ገዳማት አሏቸው፡፡ ✣✣ #የስሙ_ትርጓሜ፣ ልደቱ፣ ጥምቀቱና እድገቱ፤ ቡላ ማለት አቢብ ማለት ነው፤ ቡላ ማለት ትርጓሜውም የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ሲኸን፤ አቢብ ማለት የብዙዎች አባት፥ የመልካም ሥራ ኹሉ ባለቤት ማለት ነው፡፡ ገድሉ አብ ክቡር፤ ወትሩፈ ትጋህ አባ ቡላ ዘውእቱ አቢብ መክብበ ኵሉ ሠናያት (የተከበረ አባት፥ በትሩፋት የተጋ፥ የመልካም ነገሮች ኹሉ አባት) ይለዋል፡፡ አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በሮም ሉፊ ከሚባል አውራጃ የካቲት 16 ነው የተወለደው፤ ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ ሲባሉ እጅግ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ልጅም አልነበራቸውም፤ በዘመነ ሰማዕታት በመክስምያኖስ ዘመን ስደት በሆነ ጊዜ በስደት በበረሃ ሳሉ በመልአክ ብሥራት ወለፉት፤ ቅዱሱ ሲጸነስም ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ በሮማይስጥ ቋንቋ "ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን" (‹‹ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው›) የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል:: ቅዱሱ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በመኾኑ ለ1 ዓመት ሳይጠመቅ ከቆየ በኋላ እመቤታችን ለሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ውደ በረሃ ወርዶ እንዲያጠምቀው አዘዝችው፤ ሊያጠምቀው ሲምል ሕፃኑ ተነስቶ እጆቹንም ዘርግቶ "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ …." ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕፃኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም በዛፉ ላይ የተገለጸውን ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ:: ✣✣ #ሰማዕትነት_ ውላጆቹ ገና የ10 ዓመት እድሜ ላይ እንዳለ ድንገት ሕዳር 7 ቀን ተከታትለው ዐረፉ፡፡ ቅዱሱን ሕፃንም ጎረቤቶች ማሳደግ ጀመሩ፤ ሃገረ ገዢውም ለጣዖት ስገዱ ብሎ አዋጅ ባስነገረ ጊዜ በሕፃን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት፤ ትላልቅ ችንካሮችን ቸንክረው በጅራፍ ገረፉት፥ በዘንግ ደበደቡት:፥ ቆዳውን ገፈፉት፥ በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት በሾተሎችና በጦሮች መካከል አድርገው በመንኮራኩር ውስጥፈጩት፡፡ ነገር ግን ኀይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከሞት ተነሳ፡፡ ዳግመኛም መኮንኑ የሕፃኑን ሰውነቱን አሥሮ በመሬት ላይ እንዲጎትቱት አዘዘ አሁንም ግን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አዳነው፣ ያለ ምንም ጉዳት ፍጹም ጤነኛ አደረገው፡፡ ቅዱስ ቡላ ዳግመኛም ወደ ሌላ ከሃዲ መኰንን ዘንድ ሄዶ እርሱንም ከነአምልኮ ጣዖቱ ገሠጸው፡፡ ያም ከሃዲ መኰንን ብዙ ካሠቃየው በኋላ ሚያዝያ 18 ቀን ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፤ ነገር ግን አሁንም ለ2ኛ ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ቅዱስ ቡላን ከሞት አስነሣው፡፡ ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ የምንኵስና ልብስንና አስኬማን በመስቀል ምልክት አለበሰውና ‹‹ከቅዱሳን ጻድቃን አንድነት ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር አዞሃል›› አለው፡፡ አባ ቡላም ከአንድ ደረቅ ተራራ ላይ ወጥቶ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነገሠ ጊዜ ሳያውቅ በመንገድ ሊያልፍ ሲል መልአኩ መጥቶ እንዲሰግድለት አድርጓል፡፡ ✣✣ #ገዳማዊ_ሕይወቱና_ተጋድሎው_ ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ:: ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል:: ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኰሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው:: አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታችን የመድኀኔ ዓለምን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር፤ የሚታየውም እንደ ተወለደ፥ እንደ ተጠመቀ፥ እንደ ተሰቀለ፥ እንደ ተነሳ፥ እንዳረገ እየሆነ ነበር፡፡ ስለ ጌታ ፍቅርም ብለው፤ ✤ ምንም ነገር ሳይቀምስ፤ መዝሙረ ዳዊትን ጥራዝ እስከ ጥራዝ (15ውን መዝሙራት) እየጸለየ ለ42 ዓመታት ጹሟል:: ✤ በአንዲት ዕለትም የጌታችንን መከራውን አስበው ሰይፍ አምጥተው ስለቱን ወደላይ አቁመው በአንጻሩ ከተከሉት በኋላ ናላው ፈሶ እስኪያልቅ ድረስ አንድ ዓመት በራሱ ተዘቅዝቆ ኑሯል፤ ‹‹ወኀልቀ ናላሁ›› እንዲል ገድሉ፡፡፡፡ ✤ ፊታቸውን እየጸፉ ሥጋቸው ተቆራርሶ እስኪወድቅ ድረስ ጀርባቸውን ሰባት መቶ ጊዜ እየገረፉ ኖሩ፡ ✤ ከረጅም እንጨት ላይ በመውጣት ከዚያ ላይ ራሱን ወደታች ሁልጊዜ ይወረውር ነበር፤ ጦርም ሰክቶ ከላይ ይወድቅበት ነበር፤ ነገር ግን ጦሩ እየተጣመመ አይገድለውም ነበር፤ በአንዲት ቀንም ከረጅም ዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን በረታበትና ገደለው፡፡ በአንዲት ቀንም ከረጅም ዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን በረታበትና ገደለው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ተገልጦለት ከሞት አስነሣውና ‹‹ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ (ሃቢብ) ተባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህ›› አለው፡፡ "እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ፤ ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ፤ ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ፡፡" እንዲል::

✣✣ #በዓለ_ዕረፍቱ_ አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎይን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ:: እመቤታችንም ከእልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክት ጋራ መጥታ ‹‹የእኔና የልጄ ወዳጅ አቢብ ሆይ! ሰላምታ ይገሃል›› አለቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ከበድናቸው ቃል ወጥቶ ‹‹የሰማይና የምድር ንግሥት እመቤቴ ሆይ! ሰላምታ ይገባሻል›› አላት፡፡ እመቤታችንም በከበሩ እጆቿ ዳሰሰቻቸውና ከሞት አስነሣቻቸው፡፡ ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና በእንተ(ስለ) አባ ቡላ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን ማርልኝ ብለው የለመኑትን ልመና አምላካችን ተቀብሎላቸው ዛሬም ድረስ፤ ወደፊትም በዚህ በቃል ኪዳናቸው የሚያስምሩ ሆነዋል፤ ጌታችንም ከድንግል እናቱ ከእልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክት ጋራ መጥቶ ልዩ የሆኑ አክሊላትን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ መጥቶ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ አቢብ ሆይ! ወደማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደ እኔ ልወስድህ መጣሁ፣ ስምህን ለሚጠራ፣ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንድ በራሴ ማልኩልህ፣ ወይም በስምህ ለተራቆተ የሚያለብሰውን፣ ለተራበ የሚያጠግበውን፣ለተጠማ የሚያጠጣውን፣ የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን የሚያነበውንና የሚሰማውን፣ በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ፤ አቅም ቢያጣ 'አምላከ አቢብ ማረኝ' ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን፤ በስምህ እንኳን ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ሰጣቸውና አቅፎ ቢስማቸው ቅድስት ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፡፡ የመላእክትን ዝማሬ እያሰማቸው በደረቱ አቅፎ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ወሰዳቸው፡፡ በዚሁ ዕት መታሰቢያ የሚደረግላቸው አባ ዕብሎይም የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ናቸው፤ የአቡነ አቢብና የአባ ዕብሎይ በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘተጸውዓ እምቅድም፤ በመርኅበ ቤቱ ለአብ ኀበ ዘበቈለ ኦም፡፡ አቢብ አቡየ ዝክረ ስምከ ጥዑም፤ በዘሊተ ሥጋሁ ወበዘዚአየ አጽም፤ ተጽሕፎ ይትረከብ በሐዳስ ዓለም፡፡›› /መልክአ አቡነ አቢብ ቀዳማይ/ /ምንጭ፤ የቃል ትምህርት በላስታ ላሊበላ አበው፤ ገድለ አቡነ አቢብ፤ የዲ.ን ዮርዳኖስና ከገድላት አንደበት ገጽ/ /ይህንን ታሪክ ከቦታው ድረስ ሂዶ ከገድሉና ከሌሎችም ጽሑፎች አቀነባብሮ ያዘጋጀልን ወንድማችንን አምላከ አቡነ አቢብ ወዕብሎይ በረድኤት በጤና ይጠብቅልን፡፡/ #ስዕሉ_፤ ✤✤ የአቡነ አቢብ ቤ.ክ በሃገራችን የሚገኝባቸው ቦታዎች፤ ✣ ላሰታ ዳሪያ አቡነ አቢብ፡፡ ከ1500ዓመታት በላይ ያስቈጠረ፤ ከደረቅ ዐለት ላይ ፈዋሽ ጠበል የሚፈልቅበት፤ ላስታ ዳሪያ አቡነ አቢብ ዋሻ ቤ.ክ.፤ ከላስታ ላሊበላ በቅርብ የሚገኝ ሲኾን፤ አፄ ካሌብ ከመንገሳቸውና በላስታ አካባቢ የሚገኙትን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት (ቂርቆስ፣ ዐርባዕቱ እንሰሳ፣ ብልብላ ጊዮርጊስ፣…) ከመፈልፈላቸውም 7 ዓመት ቀድሞ በአባ ሳዊሮስ (ታውረስ?) አማካኝነት በተዓምራት በሰይፍ ነው የገመሱት፡፡ በአቡነ አቢብ ቤ.ክ ውስጥ ብዙ ተዓምራቶች ሲኖሩ ማንኛውንም የጆሮ በሽታ የሚያድን ሴቴ ጭረት የሚባል ቄጠማ ነው፤ በመቅደሱ ውስጥ ከደረቅ ዓለት (ድንጋይ) ላይ የሚወጣ ተዓምራታዊ ጸበል አለ፡፡ በቅርቡ ምዕመናኑ ሁሉ ገብቶ እንዲያየው ተደርጓል፡፡ ………5ት አባቶና 1 እማሆይ አገልጋይ ብቻ ያሉት ገዳም፤ ቅዳሴ የሚቀደሰው በየወሩ በ25፣ በፍልሰታ በዓል፣ በሰንበት /በ15ቀን አንዴ፤ ከጃሮ ሚካኤል ጋር በፈረቃ/ ይቀደሳል፡፡……. በልደት ወደ ላሊበላ የምትሔዱ ምዕመናን፣ የጉዞ ማኅበራት ከላሊበላ በቅርብ ስለሚገኝ ተባርካችሁ ኑ፡፡ ✣ አቡነ አቢብ (ጎንደር አርማጭሆ ከደብረ መጕና አቡነ አብሳዲ ገዳም አጠገብ) ✣ አቡነ አቢብ (ጎጃም ዳንግላ አካባቢ)፡፡

#ጸሎተ_ምሕላ_ ከሰኞ - እሑድ (ከቅምት 24 -30) ለ፯ት ቀናት በማኅበረ ሥላሴ አባቶቻችን ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ጸሎተ ምሕላ በታዘዘው መሠረት በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም እንዲሁም በምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም አዳራሽ #ከጥቅምት_24 - ጥቅምት 30 #ከምሽቱ_12- 1 ሰዐት የምሕላ ጸሎት ስለሚደርስ ሁላችሁም እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት፨

#ከጥቅምት_24-30 #ጾም (እስከ 9 ሰዐት)፣ ጸሎት፣ ምሕላ፣ ስግደት፡፡ #እንኳን_ሰዉ_ከብቱ_ሥርዐት_ካለው_ድንቅና_ዕፁብ_የሆነው_የማኅበረ ሥላሴ ገዳም አበው አዘዋል፡፡
+4
#ከጥቅምት_24-30 #ጾም (እስከ 9 ሰዐት)፣ ጸሎት፣ ምሕላ፣ ስግደት፡፡ #እንኳን_ሰዉ_ከብቱ_ሥርዐት_ካለው_ድንቅና_ዕፁብ_የሆነው_የማኅበረ ሥላሴ ገዳም አበው አዘዋል፡፡

ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፬ኛ ሳምንት፥ዘጥቅምት ፳፫) በዓለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት፡፡ ✤፠ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤ ፠  ማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት
+5
ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፬ኛ ሳምንት፥ዘጥቅምት ፳፫) በዓለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት፡፡ ✤፠ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤ ፠  ማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል ዑራኤል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን፤ የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን(የሸዋን) የተከተለ ነው፤  የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ እያሳሰብን፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡

#ዝክረ_ሰማዕታት_ #ጥቅምት_16 #ከጸሎተ_ምሕላ_ወደ_ጸሎተ_ፍትሐት_ በሰሞኑን በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ በደረሰው ጥፋትና ግድያ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ምዕመናን ነገ እሑድ ጥቅምት 16/2
+3
#ዝክረ_ሰማዕታት_ #ጥቅምት_16 #ከጸሎተ_ምሕላ_ወደ_ጸሎተ_ፍትሐት_ በሰሞኑን በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ በደረሰው ጥፋትና ግድያ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ምዕመናን ነገ እሑድ ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም. በመላው በሃገራችንና በዓለም በሚገኙ አብያተ ክርስቲያኖችንና ጸሎተ ምሕላ እንዲካሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ፡፡ *በተለይም በአ/አ ከቅዳሴ መልስ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ #4#ኪሎ_በመንበረ_ጸባዖት_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ.ክ. ብፁዓን ወቅዱሳን ፓትርያርኮች ፥ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት፤ የታላላቅ ገዳማት አበምኔቶችና አባቶች በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐት ይከናወናል፡፡ **ስለሆነም በዕለቱ ምዕመናን የተዋሕዶ ልጆች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመገኘት ሰማዕታቱን በጸሎት እንድናስብ ቅድስት ቤ/ን ታሳስባለች፡፡ ***ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲሉ እስከ ሞት የታመኑ የታረዱላት የባሌ ሮቤ ሰማዕታት ክርስቲያኖችም ትናንት በታረዱለት በሙሽራው በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ንግሥ በዓል በቤተ ክርስቲያኑ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ ዘመነ ጽጌንና ፍሬ የሆኑትን ሰማዕታት፤ ወርኃ ጥቅምትና እንደ ማር ለቤተ ክርስቲያን ጣፋጭ የሆኑላትን፥ እንደ ሰምም ሆነው የበሩላትን፤ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስንና ስለ ቤተ ክርስቲያን ብለው ሙሽራ ሆነው የተሰየፉትን ፥ በገብረ ክርስቶስ ላይ ውሾች እንደቧጨሩትና ስለ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሲሉ በዱላ የተቧጨሩትን፥ የተደበደቡትን …… ሌሎችንም እያስማማችሁና እያመሣጠራችሁ ፠ ባለቅኔ መምህራን ቅኔ ተቀኙላቸው፤ ፠ ባለ ግጥም ገጣምያን ግጥሙን ሰድሩላቸው፤ ፠ ባለ ሥነ ጽሑፍ ጸሓፍያን ጽሑፍ ጻፉላቸው፤ ፠ ባለ ድርሰት ደራስያን ድርሰት ድረሱላቸው፤ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በክብር በሰማዕትነት አርፈዋልና፡፡ የአባቶቻችን አምላክ በምሕረቱ ይለመነን፤ ስለ አባቶቻችን ብሎ እርሱ ፍርዱን ይስጥ፨