cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
34 429
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+267 kunlar
+1 47430 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
የሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ሀይሎች ፤ የሀገሪቱ ጦር የህወሓት ታጣቂዎች ቀጥሮ እያዋጋ ስለመሆኑ ከሰሰ 👉🏼 ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ለዚህ ማስረጃ አለኝም ብሏል የሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ሀይሎች ፤ የሀገሪቱ ጦር የህወሓት ታጣቂዎች ቀጥሮ እያዋጋ ስለመሆኑ በትናንትናው እለት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጹ ካሰራጨዉ መግለጫ ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተከሰሱት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ሃይሎች አሁን ከሱዳን ጦር እና አጋር ታጣቂዎቹ ጋር ከተያያዙት ታጣቂዎች ጋር እየተዋጉ መሆኑን መረጃዎች አሉኝ ብሏል። የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ፤ የሀገሪቱ ጦር በዝርዝር ካልጠቀሳቸዉ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ ሲደረግለት ነበር ያለ ሲሆን የአየርሀይል ፣ ኢንጂነሪንግ ፣ የጦርነት መረጃ ፣ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን እና ሌሎች እርዳታዎች ይደረግከታል ሲል ወቅሷል። ከነዚህ መካከልም የህወሓት ታጣቂዎች አንዱ ናቸዉ ማለቱን ዳጉ ከመግለጫው ታዝቧል። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ህወሓትን የወነጀለበትን አመክንዮ ሲያስቀምጥ ፤ በህዳር እና ታህሳስ ወሮች በርካታ ቅጥረኛ ወታደሮች መሞታቸዉን እና ከነዚህ ዉስጥ የህወሓት ታጣቂዎች ስለመኖራቸው አመላክቷል። አላማችን ሀገራችንን በአዲስ እና ፍትሃዊ መሰረት ላይ መገንባት ያለዉ የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይሎች ፤ ሀገራችንን እና ዜጎቿን ለመጠበቅ ብቻ የሚተጋ ከርዕዮተ አለም ተጽእኖ የጸዳ አንድ የተዋሃደ ፕሮፌሽናል ሀገራዊ ሰራዊት ማቋቋም ነውም ብሏል የድጋፍ ሰጪ ሀይሎች የኦፊሴላዊ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በመግለጫው ማገባደጃ ላይ። ህወሓት ስለቀረበበት ዉንጀላ እስካሁን ያለዉ ነገር የሌለ ሲሆን ዳጉ ጆርናል ይህንን ተከታትሎ አዲስ መረጃዎች ከወጡ የሚያደርስ ይሆናል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
1 6570Loading...
02
የኮምፒውተር ጨዋታዎች ሱስ የያዛቸዉ ወንዶች የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ታየባቸው በኮምፒውተር ጨዋታዎች (computer games) ሱስ ምክንያት በወንዶች ላይ የወሲብ ፍላጎት መቀነስ እንደሚያስከትል ዶክተሮች አስጠንቅቀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዋና ዋና አደጋዎች የአኗኗር ዘይቤ፣ ከመጠን በላይ መብላት ወይም ጨዋታዎችን ሲጫወቱ የሚያስከትለው ረሃብ ናቸው። በመጀመሪያ ደረጃ የሚያስከትለው ችግር hypodynamia ነው፣ ይህ ማለት በአነስተኛ የአካል እንቅስቃሴ ምክንያት የሚመጣ የጡንቻ ጥንካሬ መቀነስ ነው። ታድያ መንስዔው በጨዋታው ውስጥ የማያቋርጥ ጭንቀት ነው ይላሉ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ዶክተሮች። ይህም ከመጠን በላይ ክብደት እንዲጨምር እና በዚህም ምክንያት የሆርሞን መዛባት እና የመራቢያ አካላትን በእጅጉ ይጎዳል ሲል men's health clinic (MHC) በድረ ገፁ አስነብቧል። በርካታ አለምአቀፍ ጥናቶችም በኮምፒውተር ጨዋታ ሱሰኞች ላይ ያለው ከፍተኛ መጨናነቅ የወሲብ ፍላጎታቸው እንደሚቀንሰው አረጋግጠዋል። Via @Showbizz21 #ዳጉ_ጆርናል
2 2591Loading...
03
በስሊንደር ፍንዳታ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የድሮው ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 9:30 በአነስተኛ መጠጥ ቤት አደጋው ማጋጠሙን ፖሊስ አስታውቋል በመጠጥ ቤቱ ውስጥ ተጥዶበት በነበረ ስሊንደር ላይ በተፈጠረው ፍንዳታ ዕድሜው 30 ዓመት የሚገመት አንድ ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በ3 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና መወሰዳቸው ታውቋል። ከአደጋው መከሰት ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮችን ለማጣራት ምርመራው የቀጠለ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በበዓላት ሰሞን የሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከል ሁሉም ሰው ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል። በተጨማሪም ከሲልንደር አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተነስቷል። #ዳጉ_ጆርናል
3 5411Loading...
04
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!! ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዬች በዓሉን የደስታ እና የሰላም ያድርግላችሁ!!🙏 #ዳጉ_ጆርናል
2 0452Loading...
05
የተቀቀለ ስንዴ እና ጤፍ እንዲሁም ሻወር የሚገባዉና የማያርሰዉ በሬ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ወጣለት ለፋሲካ ለገበያ የቀረበው የጅሩ ሠንጋ ዋጋ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረት እና ጅሩ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ግን ይህ የተለመደ ነው። በዚሁ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታደለ አስራት፣ ለዓመት ያህል ያደለቡት በሬ 550 ሺህ ለመሸጥ ማሰባቸውን ገዢ ግን 430 ሺህ ለመክፈል ጠይቆ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንዴት ይህንን ያህል ሊያወጣ ቻለ ተብለው የተጠየቁት አቶ ታደለ “በሬው እኮ የተቀለበው ከአምና ጀምሮ ነው” ይላሉ። በሬው ይህን ያህል ዋጋ ከመገመቱ በፊት ጤፍ እና ፉርሽካ እየተቀለበ ማደጉንም ጨምሮ ተናግረዋል። በርግጥ አቶ ታደለ ሲገዙት ጥጃ ሆኖ በ130ሺህ ብር መሆኑንም አልሸሸጉም። በሬው ዓመት ያህል ሲቀለብ ብቻ ሳይሆን “ሽልም” ብለው እንደሚጠሩትም ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ተናግረዋል። “በሬው እኮ ሁለት በሬ ያክላል” የሚሉት አቶ ታደለ “ከ500 ኪሎ በላይ ይገመታል” ይላሉ። ‘ሽልም’ የሚያድረው ሊሾ የተደረገ ቤት ውስጥ ነው። የሚመገበው ደግሞ እንደ መሰሎቹ ሳርከ እና ጭድ ብቻ ሳይሆን፣ ክክ ባቄላ እና የተቀቀለ ጤፍ ጭምር ነው። ‘ሽልም’ አያርስም መባሉንም ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። በዋናነት በሊሾው ቤቱ ውስጥ ሆኖ አልያም በተከለለት ስፍራ ቅቅል ጤፉን እና ክክ ባቄላውን እየበላ ከጉድጓድ በሚቀዳ ንፁህ ውሃ አልያም አተላ ያወራርዳል። የደለበ ስለሆነ ራቅ ያለ ቦታ ሄዶ ውሃ አይጠጣም ይላሉ የሽልም አሳዳሪ አቶ ታደለ። ጤንነቱን በባለሙያ ክትትል መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ገላውንም እንደሚያጥቡት ገልጸዋል። “ጠዋት ጸሐይ ይሞቃል፣ ቀን ደግሞ ወደ ማረፍያው ይሄዳል።” በሞረት እና ጅሩ ወረዳ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ አለማየሁ ይህ ከብቶችን የማድለብ ስራ በአካባቢው የተለመደ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። #ዳጉ_ጆርናል
3 47717Loading...
06
Media files
3 26216Loading...
07
ሪያል ማድሪድ የስፔን ላሊጋን ለ 36ተኛ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል 🏆 🤍 #ዳጉ_ጆርናል
3 3391Loading...
08
የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ                              ማንቸስተር ሲቲ 4-1 ዎልቭስ         ሀላንድ ⚽️⚽️⚽️ ሁዋን ⚽️         ~  ጎል አነፍናፊው እርሊንግ ብራውት ሀላንድ ሶስቴ ሰርቷል ግቦቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
3 8490Loading...
09
ፍየል ቤት አካባቢ በጎርፍ ተከበው የነበሩ 25 ሰዎችን በህይወት መታደግ ተቻለ በጎርፍ ተከበዉና ለመንቀሳቀስ ተቸግረዉ የነበሩ 25 ሰዎችን በሰላም ማውጣት መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። በጎርፍ አደጋውም አንድ የጤና ተቋም ህንጻ ምድር ቤት ላይ ጎርፍ ገብቶ በመድኃኒት መጋዘን ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። ዛሬ ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ በጣለዉ ዝናብ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፍየል ቤት እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በተፈጠር ጎርፍ በተሽከርካሪ ዉስጥ እንዳሉ  በጎርፍ ተከበዉ የነበሩ 25 ሰዎችን በሰላም  ማውጣት መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በዚያዉ በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 13 ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ በአንድ የጤና ተቋም ህንጻ ምድር ቤት ላይ ጎርፍ ገብቶ በመድኃኒት መጋዘን ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደህንጻዉ ዘልቆ የገባዉን ጎርፍ አስወግደዉ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል ተችሏል። በሌላ በኩል ዛሬ ከቀኑ 7:30 በአዲስ ከተማ ወረዳ 8 መሳለሚያ የካቲት 23 ት/ቤት አካባቢ ጉድጓድ ዉስጥ ገብቶ የነበረ 35 ዓመት የተገመተ ሰዉ የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቀላል ጉዳት ደርሶበት በህይወት ማዉጣት መቻላቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል። በትግስት ላቀው #ዳጉ_ጆርናል
4 61531Loading...
10
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም የቀድሞ ኃላፊ ጣሂር መሀመድ በግምገማ ከስልጣን ተነስተው እንጂ በፈቃዳቸው አይደለም - የቢሮው ምክትል ኃላፊ የአማራ ክልልን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ ጣሂር መሃመድ በራሴ ፈቃድ ነው ስራ የለቀቅሁት ማለታቸው ሐሰት ነው ተባለ። ጣሂር መሀመድ ከቀናት በፊት ሚያዝያ 22 በኃላፊነት ቦታቸው ላይ ሌላኛው የአብን አባል መልካሙ ፀጋዬ መሾማቸው ይፋ መደረጉን አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም። ይህን ተከትሎም ጣሂር መሀመድ ከስድስት ወራት በፊት መልቀቂያ አስገብተው በቤተሰብ ጉዳይ እንደሚለቁ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኀን በተለይ ለቢቢሲ አማርኛ ገልጸዋል። የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አየለ አናውጤ እንደገለጹት ጣሂር መሀመድ በራሳቸው መልቀቂያ ጠይቀው ሳይሆን በተለያዩ ጉዳዩች ተገምግመው ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጎ ነው። ኃላፊው እውነትን ለመደበቅ "የተደራጀ" የሚዲያ ስራ በመሰራት በግል ገጼ ለመጻፍ ተገድጃለሁ ብለው ካሰፈሩት ጽሁፍ አዲስ ማለዳ እንደተመለከተችው፤ ከኃላፊነት መነሳት ባሻጋር በተቋሙ ልዩ የኦዲት ምርመራ እንዲደረግ ከወር በፊት ለክልሉ መንግስት በደብዳቤ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። የቀድሞ ኃላፊው እንዲሁም አንዳንድ ሚዲያዎች "በግል ምክንያታቸው" አመልክተው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን በስፋት መዘገባቸውን "በዓላማ የተሰሩ ዘገባዎች መሆኑን አረጋግጫለሁ" ሲሉም የቢሮው ምክትል ኃላፊ ጽፈዋል። በተጨማሪም "ትክክለኛውን መረጃ ይንገሩን" የሚል ከሚዲያዎች ጥያቄ ቀርቦላቸው ትክክለኛውን መረጃ ቢሰጡም "እስካሁን" እንዳልተሰራጩ ጠቁመዋል። በመሆኑም ላለፈው አንድ ዓመት ተቋሙ በአንድ በኩል በአግባቡ እየተመራ ባለመሆኑ በሌላ በኩል ከፍተኛ የሃብት ብክነት አለ በማለት ተደጋጋሚ ግምገማዎችን መካሄዳቸውን አዲስ ማለዳ ተረድታለች። እንዲሁም ለሁለት ዓመታት ከ8 ወራት አዲስ አበባ ተቀምጠው በ3 ወር አንዴ እየመጡ ለዛውም ተደብቀው ገብተው ህገ ወጥ ድርጊት ፈፅመው ይሄዳሉ ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አየለ አናውጤ በፌስቡክ ገጻቸው አጋርተዋል። በመሆኑም በቢሮው ማኔጅመንት፣ የዘርፍ ማኔጅመንት፣ በክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ፣ በከተማ ክላስተር ደረጃ በርካታ ግምገማዎች የተደረጉ ሲሆን አንዳንድ የጥቅማጥቅም ጉዳዮችን ለመጨረስ ጊዜያቸው እንዲሞላ በጠየቁት መሰረት ጥቂት ሳምንታት በኃላፊነት እንዲቆዩ ተደርጎ እንጂ መልቀቂያ አስገብተው ቆይቶ እንዳልሆነ ተገልጿል። Via አዲስ ማለዳ #ዳጉ_ጆርናል
5 1052Loading...
11
Media files
5 3420Loading...
12
ልጅ ያሬድ ከስምንት ወራት እስር በኃላ ከማረሚያ ቤት ተለቀቀ #ዳጉ_ጆርናል
5 4046Loading...
13
ቡካዮ ሳካ በሁሉም ውድድሮች 𝟐𝟎 ግቦችን አስቆጥሯል 🌶️ አርሰናል 1-0 በርንመውዝ ⚽️ ሳካ ጎሉን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
5 5140Loading...
14
በእናቷ ታዝላ የነበረች የ 3 አመት ህፃን በጅብ ጥቃት ህይወቷ አለፈ   በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በለንፉሮ ወረዳ በረጴ ቀበሌ በትናንትናው እለት ሚያዚያ 24/2016 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 1/አንድ ሰዓት የ 3 አመት ህፃን በጅብ ተነክሳ ህይወቷ ማለፉን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነትና ሚድያ ጉዳዮች ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ከድር  ኤርጎሻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። የህፃኗ ወላጅ እናት እህል ለማስፈጨት በአካባቢው ካለ ወፍጮ ቤት ስትመለስ የ 3 ዓመት ህፃን ልጇን በጀርባዋ አዝላ በመጓዝ ላይ በነበረችበት ወቅት በእለቱ የቀኑ ብርሃን መጨላለሙን ተከትሎ ወጥቶ የነበረ የተራበ ጅብ  እናት በጀርባዋ አዝላት የነበረችውን የ 3 ዓመት ህፃን ልጇን ነጥቋት ሲሮጥ እናት ባሰማችው የይድረሱልኝ ጩሀት የአካባቢው ህብረተሰብ ተረባርቦ ቢያስጥለዉም የህፃን ህይወት ማዳን እንዳልተቻለ ኮማንደር ከድር ኤርጎሻ ለብስራት ተናግረዋል። የህፃኗ ህይወት ወዲያዉኑ ማለፉን የተናገሩት ኮማንደሩ ፤ ወቅቱ የዝናብ ወቅት በመሆኑ ህጻናትና አቅመደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
5 6085Loading...
15
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የባንኩን ስም እየጠሩ የሚሰሩ የሀይማኖት ሰባኪዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞክርበት የህግ አግባብ ካለ እንደሚያጣራ አስታወቀ 👉🏼 የባንኩ ፕሬዚዳንት " በጸሎት ገንዘብ እንዲበረክት እንጂ የሚጨመር ገንዘብ የለም" ብለዋል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የባንኩን ሂሳብ ደብተር ረግጠዉ ፣ አላስፈላጊ እና አዋራጅ ሊባል የሚችል ድርጊት የሚፈጽሙ የሀይማኖት ሰባኪዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞክርበት አግባብ ካለ እንደሚያጣራ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ለመንግስታዊዉ አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ቪዲዮዎችን መመልከታቸዉን ተናግረዉ በ 21ኛዉ ክፍለዘመን እንደዚ የሚያስብ ሰዉ ስለመኖሩ መገረማቸውን ተናግረዋል። በቅድሚያ ሀሰተኛ ቪዲዮ እንደመሰላቸዉ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ይህ ከሃይማኖታዊ ተግባር ያፈነገጠ እና የማይወክል መሆኑን አመላክተዋል። "ሰርተህ ለፍተህ ያገኘኸዉ ገንዘብ እንዲበረክት መጸለይ እንጂ በጸሎት ሂሳብ ላይ የሚጨመር ገንዘብ እንደሌለ ህዝቡ መገንዘብ አለበት" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ጉዳዩ ህግ ካለዉ እና ሊፈታ ከቻለ ባንኩ ጉዳዩን እንደሚመለከተዉ በቃለምልልሳቸው መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። ፕሬዝዳንቱ ህዝቡ አይሳሳት ሲሉም አሳስበዋል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
6 2234Loading...
16
በኡጋንዳ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመሰዊያ ዋይን መጠጥ እጥረት እንዳጋጠማት ተነገረ በኡጋንዳ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በመሠዊያ ዋይን መጠጥ እጥረት ውስጥ መሆኗን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። እጥረቱ ከየካቲት ወር ጀምሮ እንደቀጠለ ነው ተብሏል። በጋዛ ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች መዘግየት ችግር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ቤተክርስቲያኗ በዚህ ሳምንት ጉዳዩን አስመልክቶ ለሀገረ ስብከቶች አሳውቃለች። ቀደም ሲል ያለውን ምርት በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ መክራለች። ቤተክርስቲያኑ የወይኑን ምርቱ ከስፔን ታገኝ የነበረ ሲሆን በሜዲትራኒያን እና በቀይ ባህር በኩል ተጓጉዞ ወደ ዩጋንዳ ይገባል። ነገር ግን በጋዛ ግጭት የተነሳ የመንገድ ለውጥ ምክንያት በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሊደርስ የነበረው ጭነት በዚህ ወር መጨረሻ ላይ እንዲደርስ ተገዷል። መርከቦቹ ወደ ሞምባሳ ወደብ የመድረሻ ጊዜ በማራዘም እና መዘግየት የተከሰተባቸው በጋዛ ግጭት የተነሳ በቀይ ባህር ውጥረት የተነሳ በአትላንቲክ ውቅያኖስ እና በህንድ ውቅያኖስ በኩል ረጅም እና ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ እንዲወስዱ በመገደዳቸው ነው ሲሉ የቤተክርስቲያኗ  ማኔጂንግ ዳይሬክተር አባ አሲኩ አልፍሬድ ቱሉን ጠቅሶ ኦብዘርቨር ጋዜጣ ዘግቧል። የመሠዊያው ወይን ለቅዱስ ቁርባን ሥነ ሥርዓት አስፈላጊ አካል ነው። በዚህም ክርስቲያኖች የኢየሱስን ሞት መሥዋዕትን ለማስታወስ ጥቅም ላይ ይውላል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
6 9777Loading...
17
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ ተፈቱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ አሳውቀን ነበር። በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን እየገለጽን፣ በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት አፋጣኝ ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን። Via ማኅበረ ቅዱሳን #ዳጉ_ጆርናል
6 8723Loading...
18
ፖሊስ 89 ተጠርጣዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ በተለያዩ ጊዜ የተሰረቁ በርካታ የመኪና እቃዎችን ማስመለሱን አስታወቀ በልደታ ፤በአራዳና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዋሳኝ ወረዳዎች  የመኪና እቃ በሚሰርቁ ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቀውን የመኪና እቃ ከሌቦች በሚቀበሉ በአጠቃላይ ወንጀሉን ተደራጅተው ሲፈፅሙ በነበሩ  ህገወጦች ላይ  በተወሰደ  እርምጃ 89 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በተደረገ ምርመራ በልዩ ልዩ ጊዜ የተሰረቁ ከ1ሺ በላይ የሚሆኑ  33 አይነት የተለያዩ የመኪና እቃዎችን አስመልሷል፡፡ ፖሊስ የመኪና እቃ ስርቆትን ለመከለከልና ህገወጦችን ህግ ፊት ለማቅረብ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በተቀናጀ ኦፕሬሽን በተለምዶ ሱማሌ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህግን መሰረት አድርጎ በወሰደው እርምጃ 528 ልዩ ልዩ ፍሬቻዎችን ፣ 187 ስፖኪዮችን ፣ 113 የመኪና መብራቶች ፣ 172 የዝናብ መጥረጊያ  በአጠቃላይ 33 ልዩ ልዩ  1ሺ 269 አይነት የመኪና እቃዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡  የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን የሚገዙ እና የሚያሻሽጡ 89 ግለሰቦችንም በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን ገልጿል፡፡  የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን የሚገዙ ህገ-ወጦች ለወንጀሉ መስፋፋት ዋና መንስኤ በመሆናቸው ፖሊስ በእነሱ ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡ የተሰረቀባቸውን እቃ ከወንጀለኞች  የሚገዙ ግለሰቦችም በተዘዋዋሪ ለወንጀል ፈፃሚዎች ምቹን ሆኔታ እየፈጠሩ መሆኑን ተገንዝበው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ  አዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡ በተለያየ ጊዜ የመኪና እቃ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች በልደታ ፣  በአራዳና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎቸው በመቅረብ  ንብረታቸውን መምረጥ እንደሚችሉም ፖሊስ አስታውቋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
6 4236Loading...
19
Media files
6 7741Loading...
20
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሁለት ጭንቅላት ያለው ህጻን ተወለደ። በኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ ትላንት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ አንዲት እናት በተደረገላት የቀዶ ህክምና ከአንገት በላይ ሁለት ጭንቅላት  (Dicephalic parapagus) ያለው ወንድ ልጅ፤ ክብደቱ 4.2 ኪ.ግ የሚመዝን በሰላም ተገላግላለች። ልጁ የተወለደው በሲሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን በሆስፒታሉ የህጻናት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ቶኩማ ባይሳ የልጁን ቀጣይ ህይወት ለመወሰን ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል ሪፈር እንዲደረግ መወሰኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ቶኩማ አክለውም፥ እናትየው የመጀመሪያ ልጇ እንደሆነ ጠቅሰው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳለች ገልጸዋል። ዘገባው የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው። #ዳጉ_ጆርናል
6 25015Loading...
21
Media files
10Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
የሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ሀይሎች ፤ የሀገሪቱ ጦር የህወሓት ታጣቂዎች ቀጥሮ እያዋጋ ስለመሆኑ ከሰሰ 👉🏼 ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ለዚህ ማስረጃ አለኝም ብሏል የሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ሀይሎች ፤ የሀገሪቱ ጦር የህወሓት ታጣቂዎች ቀጥሮ እያዋጋ ስለመሆኑ በትናንትናው እለት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጹ ካሰራጨዉ መግለጫ ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተከሰሱት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ሃይሎች አሁን ከሱዳን ጦር እና አጋር ታጣቂዎቹ ጋር ከተያያዙት ታጣቂዎች ጋር እየተዋጉ መሆኑን መረጃዎች አሉኝ ብሏል። የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ፤ የሀገሪቱ ጦር በዝርዝር ካልጠቀሳቸዉ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ ሲደረግለት ነበር ያለ ሲሆን የአየርሀይል ፣ ኢንጂነሪንግ ፣ የጦርነት መረጃ ፣ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን እና ሌሎች እርዳታዎች ይደረግከታል ሲል ወቅሷል። ከነዚህ መካከልም የህወሓት ታጣቂዎች አንዱ ናቸዉ ማለቱን ዳጉ ከመግለጫው ታዝቧል። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ህወሓትን የወነጀለበትን አመክንዮ ሲያስቀምጥ ፤ በህዳር እና ታህሳስ ወሮች በርካታ ቅጥረኛ ወታደሮች መሞታቸዉን እና ከነዚህ ዉስጥ የህወሓት ታጣቂዎች ስለመኖራቸው አመላክቷል። አላማችን ሀገራችንን በአዲስ እና ፍትሃዊ መሰረት ላይ መገንባት ያለዉ የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይሎች ፤ ሀገራችንን እና ዜጎቿን ለመጠበቅ ብቻ የሚተጋ ከርዕዮተ አለም ተጽእኖ የጸዳ አንድ የተዋሃደ ፕሮፌሽናል ሀገራዊ ሰራዊት ማቋቋም ነውም ብሏል የድጋፍ ሰጪ ሀይሎች የኦፊሴላዊ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በመግለጫው ማገባደጃ ላይ። ህወሓት ስለቀረበበት ዉንጀላ እስካሁን ያለዉ ነገር የሌለ ሲሆን ዳጉ ጆርናል ይህንን ተከታትሎ አዲስ መረጃዎች ከወጡ የሚያደርስ ይሆናል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
🤔 11👍 10 1🔥 1😱 1
የኮምፒውተር ጨዋታዎች ሱስ የያዛቸዉ ወንዶች የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ታየባቸው በኮምፒውተር ጨዋታዎች (computer games) ሱስ ምክንያት በወንዶች ላይ የወሲብ ፍላጎት መቀነስ እንደሚያስከትል ዶክተሮች አስጠንቅቀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዋና ዋና አደጋዎች የአኗኗር ዘይቤ፣ ከመጠን በላይ መብላት ወይም ጨዋታዎችን ሲጫወቱ የሚያስከትለው ረሃብ ናቸው። በመጀመሪያ ደረጃ የሚያስከትለው ችግር hypodynamia ነው፣ ይህ ማለት በአነስተኛ የአካል እንቅስቃሴ ምክንያት የሚመጣ የጡንቻ ጥንካሬ መቀነስ ነው። ታድያ መንስዔው በጨዋታው ውስጥ የማያቋርጥ ጭንቀት ነው ይላሉ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ዶክተሮች። ይህም ከመጠን በላይ ክብደት እንዲጨምር እና በዚህም ምክንያት የሆርሞን መዛባት እና የመራቢያ አካላትን በእጅጉ ይጎዳል ሲል men's health clinic (MHC) በድረ ገፁ አስነብቧል። በርካታ አለምአቀፍ ጥናቶችም በኮምፒውተር ጨዋታ ሱሰኞች ላይ ያለው ከፍተኛ መጨናነቅ የወሲብ ፍላጎታቸው እንደሚቀንሰው አረጋግጠዋል። Via @Showbizz21 #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
በስሊንደር ፍንዳታ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የድሮው ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 9:30 በአነስተኛ መጠጥ ቤት አደጋው ማጋጠሙን ፖሊስ አስታውቋል በመጠጥ ቤቱ ውስጥ ተጥዶበት በነበረ ስሊንደር ላይ በተፈጠረው ፍንዳታ ዕድሜው 30 ዓመት የሚገመት አንድ ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በ3 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና መወሰዳቸው ታውቋል። ከአደጋው መከሰት ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮችን ለማጣራት ምርመራው የቀጠለ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በበዓላት ሰሞን የሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከል ሁሉም ሰው ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል። በተጨማሪም ከሲልንደር አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተነስቷል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😢 20👍 13👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!! ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዬች በዓሉን የደስታ እና የሰላም ያድርግላችሁ!!🙏 #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
17🙏 6👍 1
የተቀቀለ ስንዴ እና ጤፍ እንዲሁም ሻወር የሚገባዉና የማያርሰዉ በሬ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ወጣለት ለፋሲካ ለገበያ የቀረበው የጅሩ ሠንጋ ዋጋ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረት እና ጅሩ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ግን ይህ የተለመደ ነው። በዚሁ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታደለ አስራት፣ ለዓመት ያህል ያደለቡት በሬ 550 ሺህ ለመሸጥ ማሰባቸውን ገዢ ግን 430 ሺህ ለመክፈል ጠይቆ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንዴት ይህንን ያህል ሊያወጣ ቻለ ተብለው የተጠየቁት አቶ ታደለ “በሬው እኮ የተቀለበው ከአምና ጀምሮ ነው” ይላሉ። በሬው ይህን ያህል ዋጋ ከመገመቱ በፊት ጤፍ እና ፉርሽካ እየተቀለበ ማደጉንም ጨምሮ ተናግረዋል። በርግጥ አቶ ታደለ ሲገዙት ጥጃ ሆኖ በ130ሺህ ብር መሆኑንም አልሸሸጉም። በሬው ዓመት ያህል ሲቀለብ ብቻ ሳይሆን “ሽልም” ብለው እንደሚጠሩትም ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ተናግረዋል። “በሬው እኮ ሁለት በሬ ያክላል” የሚሉት አቶ ታደለ “ከ500 ኪሎ በላይ ይገመታል” ይላሉ። ‘ሽልም’ የሚያድረው ሊሾ የተደረገ ቤት ውስጥ ነው። የሚመገበው ደግሞ እንደ መሰሎቹ ሳርከ እና ጭድ ብቻ ሳይሆን፣ ክክ ባቄላ እና የተቀቀለ ጤፍ ጭምር ነው። ‘ሽልም’ አያርስም መባሉንም ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። በዋናነት በሊሾው ቤቱ ውስጥ ሆኖ አልያም በተከለለት ስፍራ ቅቅል ጤፉን እና ክክ ባቄላውን እየበላ ከጉድጓድ በሚቀዳ ንፁህ ውሃ አልያም አተላ ያወራርዳል። የደለበ ስለሆነ ራቅ ያለ ቦታ ሄዶ ውሃ አይጠጣም ይላሉ የሽልም አሳዳሪ አቶ ታደለ። ጤንነቱን በባለሙያ ክትትል መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ገላውንም እንደሚያጥቡት ገልጸዋል። “ጠዋት ጸሐይ ይሞቃል፣ ቀን ደግሞ ወደ ማረፍያው ይሄዳል።” በሞረት እና ጅሩ ወረዳ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ አለማየሁ ይህ ከብቶችን የማድለብ ስራ በአካባቢው የተለመደ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😁 38👍 16 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ሪያል ማድሪድ የስፔን ላሊጋን ለ 36ተኛ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል 🏆 🤍 #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 24🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ                              ማንቸስተር ሲቲ 4-1 ዎልቭስ         ሀላንድ ⚽️⚽️⚽️ ሁዋን ⚽️         ~  ጎል አነፍናፊው እርሊንግ ብራውት ሀላንድ ሶስቴ ሰርቷል ግቦቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 17😁 5👎 1
ፍየል ቤት አካባቢ በጎርፍ ተከበው የነበሩ 25 ሰዎችን በህይወት መታደግ ተቻለ በጎርፍ ተከበዉና ለመንቀሳቀስ ተቸግረዉ የነበሩ 25 ሰዎችን በሰላም ማውጣት መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። በጎርፍ አደጋውም አንድ የጤና ተቋም ህንጻ ምድር ቤት ላይ ጎርፍ ገብቶ በመድኃኒት መጋዘን ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። ዛሬ ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ በጣለዉ ዝናብ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፍየል ቤት እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በተፈጠር ጎርፍ በተሽከርካሪ ዉስጥ እንዳሉ  በጎርፍ ተከበዉ የነበሩ 25 ሰዎችን በሰላም  ማውጣት መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በዚያዉ በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 13 ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ በአንድ የጤና ተቋም ህንጻ ምድር ቤት ላይ ጎርፍ ገብቶ በመድኃኒት መጋዘን ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደህንጻዉ ዘልቆ የገባዉን ጎርፍ አስወግደዉ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል ተችሏል። በሌላ በኩል ዛሬ ከቀኑ 7:30 በአዲስ ከተማ ወረዳ 8 መሳለሚያ የካቲት 23 ት/ቤት አካባቢ ጉድጓድ ዉስጥ ገብቶ የነበረ 35 ዓመት የተገመተ ሰዉ የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቀላል ጉዳት ደርሶበት በህይወት ማዉጣት መቻላቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል። በትግስት ላቀው #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 50👏 8 5

😁 30👍 18👎 6 2