cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
35 734
Obunachilar
-224 soatlar
+9077 kunlar
+1 07730 kunlar
Postlar arxiv
ጀርመን ለቻይና ሲሰልል ነበር ያለችዉን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለች የጀርመን ፖሊስ ለቻይና በመሰለል የጠረጠረዉን የቀኝ አክራሪ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ረዳትን በቁጥጥር ስር አውሏል።አቃብያነ ህጎች በዛሬዉ እለት እንዳስታወቁት ጂያን ጂ በአውሮፓ ፓርላማ አሠራር ላይ መረጃን ለቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደጋጋሚ አሳልፎ ሰጥቷል ተብሎ ይታመናል:: እስሩ በሰኔ ወር ከአውሮፓ ኅብረት ምርጫ በፊት የዲሞክራሲ ስጋት ፈጥሯል የሚል ማስጠንቀቂያ የተነሳበት ሲሆን ቤጂንግ በበኩሏ ጸብ ጫሪ ብላዋለች፡፡ የጀርመን ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋለውን ሰው የቀጠረው የትኛው ፖለቲከኛ እንደሆነ አልገለፁም። ይሁን እንጂ ጀርመናዊው የማክሲሚሊያን ክራህ ረዳት እንደነበር ሚዲያዎች ዘግበዋል።ለመጪው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ የቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን (አፍዲ) ፓርቲ መሪ እጩ ናቸዉ። ክራህ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቼክ የስለላ ድርጅት በተከፈተው ክስ የሩሲያን ደጋፊ የሆኑ ትርክቶችን ወደፊት ለማምጣት ጉቦ በመውሰድ የተጠረጠሩ በመላው አውሮፓ ካሉ ፖለቲከኞች ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። ጂያን ጂ ሰኞ መገባደጃ ላይ በድሬዝደን ተይዞ በአፓርታማው ላይ ፍተሻ እንደተደረገበት አቃቤ ህግ አስታዉቋል። በጥር ወር የአውሮፓ ፓርላማ ድርድር እና ውሳኔዎች ላይ ሪፖርት ከማድረግ በተጨማሪ በጀርመን የሚገኙ የቻይና ተቃዋሚዎችን ይሰልል ነበር ተብሏል።የበርሊኑ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ፋዘር የስለላ ውንጀላ "እጅግ አሳሳቢ" ነው ብለዋል። በአውሮፓ ፓርላማ ውስጥ ለቻይና የስለላ ድርጅት ሰላይ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ በአውሮፓ ዲሞክራሲ ላይ የሚደረግ ጥቃት ነው ስትል የበርሊኑ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ፋዘር አክላለች፡፡የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤጂንግን ለማሳነስ እና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማፍረስ በሚያደርገዉ ጥረት ስማቸው ያልተጠቀሰ ሀይሎችን መወንጀል ተቀባይነት የለዉም ብሏል፡፡ በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 9💔 3👎 2 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
4
Photo unavailableShow in Telegram
#Breaking ህወሓት ብልፅግናን ሊቀላቀቀል ነዉ መባሉን ተከትሎ ከብልፅግና ጋር የጀመርኩት ንግግር የለም ሲል አስተባበለ የህወሓት እና የብልፅግና ድርድር ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው ያለው ህወሓት ፤ ህወሓት እና ብልፅግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች መሆናቸውን ገልጿል። አክሎም ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች አሉና በነዛ ዙርያ ውይይት እያደረግን ነው ማለቱን ዳጉ ጆርናል ከፓርሪዉ መግለጫ ተመልክቷል። ከዚህ ውጭ ግን እንደሚወራው ህወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል ንግግር ጀምሯል የተባለው ጉዳይ ሐሰት ነው ሲልም በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ፓርቲዉ አጋርቷል። በዛሬዉ እለት ህወሓት ብልጽግና ፓርቲን ሊቀላቀል መሆኑን ዳጉ ጆርናል የዋዜማ ሚዲያ ዘገባን ዋቢ በማድረግ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎም ህወሓት ይፋዊ መግለጫ አዉጥቷል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😁 26👍 19🤬 3🔥 1🤔 1
ለሰብዓዊ ተግባር በሚል ገንዘብ ሰብስቦ ለግል ጥቅም ማዋል እስከ አስር ዓመት በእስራት ያስቀጣል ተባለ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ደንጋጌ ላይ እንደተቀመጠው ማንም ሰው ለሰብዓዊነት በሚል የተሰበሰበን ገንዘብ ሆነ ቁስ ለግል ጥቅሙ ማዋል የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት ሆኖ መቀመጡን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ተናግረዋል፡፡ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ የሆኑት ጠበቃ ካሳሁን አውራሪስ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ድንጋጌ መሰረት አግባብ ካለው ተቋም ፍቃድ ኖሮት ሆነ ሳይኖረው ማንኛውም ሰው ኃይማታዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ሰብዓዊ ዝ ባህላዊ ወይም ማንኛውንም ጉዳይ ምክንያት አድርጎ  ከግለሰብ ወይም ከህዝብ ላይ ገንዘብ እና ቁስ ሰብስቦ በሙሉም ሆነ በከፊል ገንዘቡን ሆነ ቁስ ለተሰበሰበለት አላማ ሳይውል ለግል ጥቅሙ ያዋለ እንደሆነ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 701 ንኡስ ቁጥር 4 ስር በተቀመጠው መስረት ይቀጣል፡፡ ስለቅጣቱ በተለይም ግለሰቡ እርዳታ የሚያስፈልው ሰው ሆኖ እርሱን በማሳየት በስሙ ሰብስበው ገንዘቡን ለግል ጥቅም ካዋለ ቅጣቱ እስምን ድረስ ነው ሲል ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዢን ለህግ ባለሙያው ላነሳው ጥያቁ የህግ ባለሙያው ሲያብራሩ ፍቃድ አውጥቶ ገንዘቡን ሰብስቦ ለግል ጥቅሙ ካዋላ  በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 701 ንኡስ ቁጥር 4 ስር በተቀመጠው መስረት ከአስር አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከ30 ሺ ብር የማይበልጥ መቀጮ ገንዘብ እንደሚቀጣ ህጉ አስቀምጧል፡፡ ለሰብዓዊ እርዳታ ይሁን ለሌላ አላማ ገንዘብ ሲሰበሰብ ከሚመለከተው አግባብ ካለው ባለስልጣን ፍቃድ ሳይኖረው ሲሰበስብ የተገኙ ከሆነ ፍቃድ ሳያገኝ በመስብሰቡ ብቻ በተጨማሪ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 862 ላይ በተቀመጠው ህግ መሰረት ተጨማሪ ቅጣት ይጣልበታል፡፡ በአንቀጽ 701 አንደተደነገገ አንድ ሰው ጉዳት ሳይደርስበት ቸግር አለብኝ በማለት የሰበሰበ እዲሁም ሌላ ግለሰብም ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈለግው ሰውን በአደባባይ ይዞ የታመመ በማሰመሰል ሀሰተኛ መግለጫ በመስጠት በማጭበርበር በተለያዩ መንገድ ገንዘብ ከሰበሰቡ እስከ አምስት አመት እንደሚያስቀጣም ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ የሆኑት ጠበቃ ካሳውን ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ እንደህግ ባለሙያ ማብራሪያም ይህ ቅጣት ተግባራዊ የሚሆነው የሰብዓዊ እርዳታ የተሰበሰበለት ግለሰብ ወይም ድጋፉን ባደረጉ ሰዎች ክስ ሲመሰረት  እና ማስረጃ ሲቀርብ መሆኑን ህግ ይደነግጋል፡፡ በትግስት ላቀው #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 34😁 3 2
Photo unavailableShow in Telegram
1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ በአማራ ክልል ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ። ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ ም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መንስኤው እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በፓርኩ የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ነው የተገለጸው። እሳቱ በአካባቢው ሕዝብ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሣ በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች መያዛቸውን አመልክተዋል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሕግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ጉዳዩ የሚጣራ መሆኑን፤ ቃጠሎው ያደረሰው የጉዳት መጠንም ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግም ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኝበት አካባቢ ሦስት ዓይነት የአየር ጠባይ እንዳለና በየዓመቱም ተመሳሳይ የእሳት አደጋ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንደሚከሰት ነው ባለሥልጣኑ የገለጹት። ከቀናት በፊት የተነሳው እሳት በፓርኩ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደነበር በማመልከትም ፓርኩ ጓሳ እንደመሆኑ የተዳፈነ እሳት ንፋስ አቀጣጥሎት እንዳይነሳ ክትትል የማድረግ ጥረት መኖሩንም ተናግረዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር በ1978 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 15👏 5 3😁 2
በአርጀንቲና ቅድመ ክፍያ የፈፀምኩለት ተሽከርካሪ አልተሰጠኝም ያለው ግለሰብ በመኪና መሸጫ መደብር ውስጥ ለ15 ቀናት አልወጣም ማለቱ ተሰማ በደቡብ አሜሪካ አንድ አርጀንቲናዊ በመኪና መሸጫ መደብር ውስጥ ሌሊቱን ማደሩ የተሰማ ሲሆን ቅድመ ክፍያ የፈፀመበትን የጭነት ተሽከርካሪ ካልተሰጠው ስፍራውን ለቆ ለመውጣት ፍቃደኛ እንደማይሆን አስታውቋል። አልቤራዶ ኡሳንዲቫራስ የተባለው አርጀንቲናዊ ግለሰብ ከሁለት ሳምንታት በላይ ዓለም አቀፍ የዜና አርዕስተ ሆኖ ቆይቷል።በመኪና አቅራቢ ድርጅቶች በኩል የሚሰራውን ህገ ወጥ ድርጊት በመታገል ረገድም በተወሰነ ደረጃዋ ምልክት ተወስዷል። በሳልታ ነዋሪ የሆነው በአርባዎቹ አጋማሽ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው ይህው ሰው ከ15 ቀናት በፊት ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ወደ አርጀንቲና ዋና ከተማ ቦነስ አይረስ መጥታል። በጣም የሚፈልገውን የጭነት ተሽከርካሪ በወቅቱ ሊደርስለት ባለመቻሉ በቀጥታ አከፋፋዩን አግኝቶ ለማውራት ቢሞክርም ሳይሳካለት ይቀራል። ኡሳንዲቫራስ የሚፈልገውን መልስ ባለማግኘቱ እና ከባለቤቱ ጋር መገናኘት ባለመቻሉ ቃል የተገባለት ተሽከርካት ወይም ቢያንስ የከፈለውን ክፍያ ካልተመለሰለት ከመኪና መሸጫ መደብር ውስጥ እንደማይወጣ ይናገራል። ይህው የእርሱ ጉዳይ በፍጥነት ተሰራጭት የአቤላርዶ  ኡሳንዲቫራስ የመብት ትግል በሁሉም የላቲን አሜሪካ ሀገራት ውስጥ ትልቅ ርዕስ ሆኗል። ኡሳንዲቫራስ ባለፈው አመት አዲስ የጭነት መኪና ለመግዛት በመወሰን በቦነስ አይረስ ካለው አከፋፋይ ጋር ከተገናኘ በኋላ አሮጌውን የጭነት መኪናውን ለመሸጥ እና ለአዲሱ መኪና ሙሉ ክፍያ ለመፈጸም ይወስናል። እስከዚያ ድረስ ሁሉም ነገር ያለችግር ሄዷል። ነገር ግን የቅድሚያ ክፍያ ከፈፀመ በኋላ፣ ከአከፋፋዩ ሰምቶ የማያውቀውን ተሽከርካሪውን ለማስረከብ 120 ቀናት እንዲጠብቅ ቀነ-ገደብ ሲሰጥው እና ወደ ሌላ የአስተዳደር ክፍል ሲያመላልሱት ብስጭት ውስጥ ይገባል። ከታህሳስ ወር ጀምሮ ከአንድ ስልክ ወደ ሌላ ስልክ ደውል እያሉ ሲያንከራትቱኝ እና የኩባንያውን ተወካይ ስም እንኳን ሊነግሩኝ ፍቃደኛ አልነበሩም ሲል አቤላርዶ ኡሳንዲቫራስ ለጋዜጠኞች ተናግሯል። "እውነታው ግን የሌላቸውን የጭነት ተሽከርካሪ እንዳላቸው አድርገው ማስታወቂያ ሰርተዋል። ከዛም አገንዘብህን ተጠቅመው ሌላ ስምምነት ለማድረግ የሚጥሩበት የፋይናንስ ሥርዓት ነው ሲል አክሏል። አርጀንቲናዊው ግለሰን በከፈለው ገንዘብ ቅናሽ ሌላ መኪና እንደቀረበለት ተናግሮ አዲስ የጭነት መኪና ከፈለገ ተጨማሪ ክፍያ እንደሚፈጽም ቀድሞ ባልነበራቸው ውል መሰረት ተነግሮታል። ሴት ልጁን እና ትንሹን ወንድ ልጁን ጨምሮ መላውን ቤተሰቡን ወደ ቦነስ አይረስ እና እንዲሁም ለጭነት መኪናው የሚከፈለውን የቀረውን ክፍያ ካመጣ በኋላ አዲሱ መኪና ካልተሰጠው ከማከፋፈያ መደብሩ ውስጥ እንደማይወጣ አሳውቋል። በአካባቢው የሚገኙ ፖሊሶት ለሰዓታት ድርድር እና ሽምግልና ቢያደርጉም የአቤላርዶ ያልተለመደ የተቃውሞ አይነት መላው ሀገሪቱን አዳርሷል።ሌላው ቀርቶ አከፋፋዩን ‘መኪናውን አምጡልኝና እዚህ በጥሬ ገንዘብ ልክፈል ብላቸውም ሊሰሙኝ አልቻሉም፤ ምንም እንዳልገባኝ አድርገው ከገጠራማ አካባቢ የመጣ ሰው ነው ብለው ዝቅ ሊያደርጉኝ ቢሞክሩም አልተሸነፍኩም ብሏል። የቦነስ አይረስ የተሽከርካሪ አከፋፋይ በበኩሉ ኩባንያውን ከንግድ ውጪ ለማድረግ የተነደፈ የሚዲያ ዘመቻ ሰለባ ሆኛለው ብሏል። በኩባንያው ድረ-ገጽ ላይ የተለጠፈው መግለጫ እንደሚያሳየው የተካሄደብኝ "ቆሻሻ ስም የማጥላላት ጦርነት" አውግዟል በማለት ለደንበኞቼ ምርጡን አገልግሎት ለማቅረብ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ሲል አስታውቋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 29😁 24
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
ከየመን ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ የ16 ኢትዮጵያውያን ህይወት አለፈ ትናንት ምሽት ከየመን የባሕር ዳርቻ ልዩ ስሙ ‘አራ’ ከተባለ ቦታ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ-ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጎዶሪያ አካባቢ ተገልብጣ የ16 ወገኖች ሕይወት አለፈ፡፡ እንዲሁም አብረው በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩ 28 ኢትዮጵያውያን እስካሁን አለመገኘታቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡በሌላ በኩል 33 ፍልሰተኞች በሕይወት ተርፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኤምባሲው የተሰማውን ሐዘን ገልጾ÷ ከጂቡቲ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ጉዞዎች እጅግ አደገኛ ከመሆናቸውም በላይ በየጊዜው የዜጎችን ሕይወት እያሳጡ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ዜጎቻችን በሕገ-ወጥ ደላሎች የሐሰት ስብከት በመታለል ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ሲል አሳስቧል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😢 35👍 8💔 7 2😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ማላዊ 11 ኢትዮጵያዊያንን በእስራት እና በከባድ የጉልበት ስራ ቀጣች ማላዊ በህገወጥ መንገድ ሀገሬ ገብተዋል ያለቻቸዉን 11 ኢትዮጵያዊያንን በእስር መቅጣቷን ዳጉ ጆርናል ሰመቷል። የመዙዙ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኢትዮጵያዊያኑ በህገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብተዋል ያለ ሲሆን የኢሚግሬሽን ህግ አንቀጽ 21/1 በመጣስ ወደ ማላዊ ገብተዋል ሲል ወንጅሏል። ከ 11 ስደተኞች ዉስጥ ሰባት ያህሉ በካሮንጋ ወረዳ ሃንጋላዌ የባህር ዳርቻ ፓስፖርት ሳይዙ ባሳለፍነዉ ሳምንት በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑ ተነግሯል። ሰባቱ ኢትዮጵያን ከከባድ የጉልበት ስራ ጋር የሁለት ወር እስራት እንደተፈረደባቸዉ ዳጉ ጆርናል ከዘገባዎች ተመልክቷል። የተቀሩት አራት ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ሀገሪቱን ለቅቀዉ እንዲወጡ የሚደረግ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በመዙዙ እስርቤት እንደሚገኙ ተነግሯል። በቅርቡም ሌሎች 52 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በተመሳሳይ ማላዊ በህገወጥ መንገድ ድንበሬን ጥሰዉ ገብተዋል ስትል ዉሳኔ ሰጥታባቸዋለች። የጉልበት ስራ ተብሎ በኢትዮጵያዊያኑ ላይ የተላለፈዉ ዉሳኔ እስረኞች በማረሚያ ቤት ቆይታቸዉ መጸዳጃ ቤቶችን ማጽዳት ፣ የጉልበት እና ሌሎች ስራዎችን እንዲሰሩ የሚደረጉበት ነዉ። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😢 25👍 23💔 6👎 4🤔 4😁 3 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኔታንያሁ በእስራኤል ወታደራዊ ክፍል ላይ የሚጣለዉን ማዕቀብ እንታገላለን ሲሉ በድጋሚ ቃል ገቡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በእስራኤል ጦር ውስጥ "በአንድ ክፍል ላይ ማዕቀብ ሊጥሉ ይችላሉ" ብለው የሚያምኑ ሰዎች እንደገና ሊያስቡበት ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የአይሁድ ፋሲካ ሴደር በዓልን ለማክበር በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በተጋራዉ ንግግራቸዉ ኔታንያሁ የእስራኤል ሃይሎችን በሰብአዊ መብት ረገጣ ለመቅጣት የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ “በሙሉ ኃይሌ” እዋጋዋለሁ ሲሉ ተናግረዋል። "ወታደሮቻችን በጦር ሜዳ እኛን ለመከላከል አንድ ሲሆኑ በዲፕሎማሲው መስክም እነሱን ለመከላከል አንድ ነን" ብለዋል፡፡ኔታንያሁ አስተያየታቸውን የሰጡት ዩናይትድ ስቴትስ በዌስት ባንክ ፍልስጤማውያን ላይ በደረሰው የሰብአዊ መብት ረገጣ በአንድ የእስራኤል ጦር ክፍል ላይ ማዕቀብ ልትጥል መሆኑን ዘገባዎች እየወጡ መሆናቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሰኞ እለት እንደተናገሩት በእስራኤል ወታደሮች የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለማጣራት "ሂደቶች" እየተካሄዱ ነው፡፡በዌስት ባንክ ውስጥ የሚገኘው ኒታዝ ጁኡዳ ወይም "ዩሁዳ ለዘላለም" የተባለው የአይሁድ ወታደሮች ክፍል የማዕቀብ ኢላማ ሊሆን እንደሚችል ዘገባዎች ያመለክታሉ። በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር የጦር አውሮፕላኖቹ በደቡባዊ ሊባኖስ ላይ በአንድ ሌሊት ጥቃት መፈጸማቸው ተሰምቷል፡፡ ከሰሜን እስራኤል ጋር በሚያዋስነው የያሩ መንደር አካባቢ ሂዝቦላህ "የሽብር መሰረተ ልማት" ናቸው ያላቸውን አምስት ቦታዎችን ደብድቧል፡፡የእስራኤል የምድር ጦር ሃይሎች በቅርቡ በያሮው አካባቢ ስጋትን ለማስወገድ ጥቃት ሰንዝረዋል ሲል ወታደሮቹ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጡት ጽሁፍ ላይ በሊባኖስ ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት ህንጻዎች ሲፈርሱ የሚያሳይ ምስል አካተዉ ይፋ አድርገዋል፡፡ በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 17😁 14 2
Photo unavailableShow in Telegram
የካናዳ ኤምባሲ በሰሜን ፣ መካከለኛ እና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ዜጎቹ እንዳይቀሰቅሱ መከረ 👉🏼 ኤምባሲዉ በአዲስአበባ ጭምር ዜጎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል የካናዳ መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ በጥቅሉ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር እንዳይጓዙ ሲል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ዳጉ ጆርና ታዝቧል። በሕዝባዊ አመፅ ፣ ብጥብጥ ፣ በትጥቅ ግጭት እና የወንጀል ድርጊት ይበዛባቸዋል  ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ አላስፈላጊ ጉዞን ያስወግዱ ሲልም አሳስቧል። በዋነኛነት በሰሜን ኢትዮጵያ አማራ ፣ ትግራይ ከመቐለ ከተማ ዉጪ ወደ አዲግራት ፣ አቢ አዲ ፣ አድዋ ፣  ሽሬ እና ማይጨዉ አካባቢዎች እንዲሁም ወደ ቤኒሻንጉል ክልል ዜጎቹ አይጓዙ ሲል አስጠንቅቋል። በተጨማሪም መካከለኛዉ ኢትዮጵያ ክፍል ጋምቤላ እና ሲዳማ ክልሎች እንዲሁም ሰሜን እና ምዕራብ ሸዋ እና ወደ አራቱ የወለጋ ዞኖች ዜጎቹ እንዳይጓዙ ጠይቋል። እንዲሁም ኢትዮጵያን ከኬንያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሱዳን ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችም ዜጎቹ እንዲጠበቁ መክሯል። ኤምባሲዉ የካናዳ ዜጎች በአዲስአበባ ጭምር ራሱ ዜጎቹ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ከፍተኛ የተባለ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ማሳሰቡን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። በቅርቡ ካናዳን ጨምሮ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣሊያን ፣ ጃፓን ፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለዉ የጸጥታ አለመረጋጋት አሳስቦናል ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ማስታወቃቸዉ ይታወሳል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 27👎 9😢 5 2🥰 1😁 1
00:32
Video unavailableShow in Telegram
ማሌዥያ ውስጥ የባህር ሃይል ሄሊኮፕተሮች በአየር ላይ ተጋጭተው የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ የንጉሣዊው የማሌዢያ ባህር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ ላይ በነበረበት ወቅት ሁለት የባህር ሃይል ሄሊኮፕተሮች በአየር ላይ ተጋጭተው የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል።በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ላይ የታተመው ቀረጻ እንዳመላከቱ ሁለቱ ሄሊኮፕተሮች መሬት ከመጋጨታቸው በፊት አንደኛው የሌላውን ሮተር ቆርጧል። ድርጊቱ ያጋጠመዉ በማሌዥያ ሉሙት ከተማ ሲሆን ይህም የባህር ሃይል ሰፈር ነው፡፡ በአደጋዉ በሕይወት የተረፉ ሰዎች ስለመኖራቸዉ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡የሮያል የማሌዢያ ባህር ሃይል ሁሉም ተጎጂዎች በስፍራዉ መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን አስከሬን ለመለየት ወደ ሉሙት ወታደራዊ ሆስፒታል ተልኳል።የአደጋውን መንስኤ የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንደሚሰራም አክሏል። ከሄሊኮፕተሮቹ አንዱ የሆነው ኤም 503-3 ሰባት ሰዎችን አሳፍሮ በመንደርደሪያ መንገድ ላይ ወድቋል ተብሏል።ሌላው ፌንኔክ ኤም 502-6 ሌሎች ሶስት ተጎጂዎችን አሳፍሮ በአቅራቢያው በሚገኝ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ወድቋል።የግዛቱ የእሳት እና የነፍስ አድን ክፍል አደጋዉ ከባድ እንደነበር ገልጿል፡፡ በመጋቢት ወር የማሌዢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂ ሄሊኮፕተር በማሌዢያ አንጋሳ ደሴት በስልጠና  ላይ እያለ በባህር ላይ መዉደቁ ይታወሳል፡፡ፓይለቱ፣ ረዳት አብራሪው እና ሁለት ተሳፋሪዎች በአሳ አጥማጆች በመገኘታቸዉ ከሞት ተርፈዋል፡፡ በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
8.39 MB
👍 16😱 8💔 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከ1.5 ሄክታር በላይ ደን ያቃጠለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በባሌ ዞን ጎሮ ወረዳ ልዩ ስሙ ባሌ ጋዱላ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘዉን ሰፊ ደን በማቃጠል ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል፡፡ ተከሳሽ አብርሀም ጌታሁን የተባለው ግለሰብ በባሌ ዞን ባሌ ጋዱላ አካባቢ በሚገኘው የባሌ ተራራ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ በመግባት ከ 1.5 ሄክታር በላይ ደኖችን በማቃጠል እንዲወድሙ በማድረጉ በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎሮ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረዳት ኢንስፔክተር ፈቲ ሱፊያን ገልፀዋል። ፖሊስ ተከሳሹን በቁጥጥር ስር ካዋለው በኃላ በበቂ ምርመራ በማጣራት የምርመራ መዝገቡን  ለአቃቤ ህግ የላከ ሲሆን አቃቤ ህግም የዱር እንሰሳት እንክብካቤና የአካባቢ ጥበቃ አዋጅ በመተላለፉ ክስ መስርቶበታል። የተመሰረተውን ክስ ሲመለከት የቆየው የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ አብርሀም ጌታሁንን በአስር አመት እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የጎሮ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረዳት ኢንስፔክተር ፈቲ ሱፊያን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በመዓዛ ኃይሌ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 17👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
በናሚቢያ የባህር ዳርቻ 10 ቢሊዮን በርሜል ነዳጅ ዘይት ተገኘ በናሚቢያ 10 ቢሊየን በርሜል የሚገመት ነዳጅ ዘይት መገኘቱን የፖርቱጋል የነዳጅ ዘይት ኩባንያ ጋልፕ ኢነርጂ አስታዉቋል።ኩባንያው በናሚቢያ የባህር ዳርቻ በሞፔን መስክ ያደረገውን የነዳጅ ፍለጋ የመጀመሪያ ምዕራፍ ካጠናቀቀ በኋላ የነዳጅ ሀብቱን ማግኘቱን ገልጿል። በሞፔን ብቻ፣ ተጨማሪ ፍለጋ ጉድጓዶች ከመቆፈራቸዉ ፊት፣ የሃይድሮካርቦን ምርት እና ቦታው ላይ 10 ቢሊዮን በርሜል ነዳጅ ወይም ከዚያ በላይ ይገኛለ ሲል ኩባንያዉ አስታዉቋል፡፡ሞፔን በሚገኝበት በናሚቢያ ኦሬንጅ ተፋሰስ ውስጥ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሰፊ የነዳጅ እና የጋዝ ክምችት ተገኝቷል። ግኝቶቹ በደቡባዊ አፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ በአለም አቀፍ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንድትይዝ አድርጓታል።ሀገሪቱ በ2030 የነዳጅ ምርቷን በመጨመር ወደ ኦፔክ ወደ ዘይት አምራቾች ድርጅት ለመግባት እየጣረች ትገኛለች፡፡ በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 28 3
Photo unavailableShow in Telegram
የቻይና መንግስት ድጋፍ ያለዉ ፓርቲ በማልዲቭስ ምርጫ ከፍተኛ ድል በማግኘት አሸነፈ የማልዲቪያ ፕሬዝደንት መሀመድ ሙኢዙ ፓርቲ እሁዱ እለት በተካሄደዉ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፋቸዉን የቅድመ ምርጫ ውጤቶች አመላክተዋል፡፡ የህዝብ ብሄራዊ ኮንግረስ (ፒኤንሲ) ፓርላማውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ከሚያስችለዉ ከ93 መቀመጫዎች ዉስጥ ሰባዉን አሸንፏል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ውጤቱ ማልዲቪስ ከቀድሞ አጋሯ ህንድ ፊቷን ወደ ቻይና ልታዞር እንደምትችል አመላክቷል፡፡ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም መሀመድ ሶሊህ የሚመራውና በህንድ መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ የሚደረግለት የማልዲቪያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኤምዲፒ) በቀድም ፓርላማ 65 መቀመጫዎች የነበሩት ሲሆን አሁና ላይ በመቃወም 15 መቀመጫዎችን ብቻ ማግኘቱን የሀገር ውስጥ የዜና ምንጭ ሚሃሩ ዘግቧል።ከተወዳዳሪዎቹ 41 ሴቶች መካከል ሶስት እጩዎች ብቻ መመረጣቸውን ሚሃሩ ዘግቧል። ውጤቱን ለማፅደቅ አንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን አዲሱ ምክር ቤት ከግንቦት ወር መጀመሪያ አንስቶ ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ፒኤንሲ እና አጋሮቹ በስልጣን ላይ ባለው ፓርላማ ውስጥ ስምንት መቀመጫዎች ብቻ የነበራቸው ሲሆን ይህም ሙኢዙ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ በራሱ ፖሊሲ እንዳይራመድ አስቸጋሪ አድርጎታል።1,192 ትናንሽ ደሴቶች ያሏት ማልዲቭስ፣ በምድር ወገብ ላይ 800 ኪ.ሜአካባቢ ተበታትነው የሚገኙት በአየር ንብረት ቀውስ ምክንያት ለባህር ጠለል ከፍታ ተጋላጭ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ናት። የሀገሪቱ መሪ የ45 አመቱ የቀድሞ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ሙኢዙ፣ መሬትን መልሶ ማልማት እና ደሴቶችን መገንባት ችግሩን ለመፍታት እንደሚያስችል ቃል ገብተዋል፣ ነገር ግን የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች እንዲህ ያለው እርምጃ የጎርፍ አደጋን እንደሚያባብስ ይከራከራሉ። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 13🔥 2
ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ተባለ ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ – ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑን ዳጉ ጆርናል ፤ ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች አሰባስቤ ሰራሁት ያለችዉ ዘገባ ያመለክታል። ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል። ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም። አሁንስ እየተደረገባቸው ባለው ድርድር ሕወሓት የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል። ብልፅግና ግን ሕወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልፃል። የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግረዋል። በሕወኋት በኩል ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው …አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች ቢኖሩም ፣ ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ፀጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልፅግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ። Via ዋዜማ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 39😁 26👎 7🤬 5😢 5🕊 5 2🤯 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
4
Photo unavailableShow in Telegram
በአቡዳቢና ዱባይ የሚገኙ ኢትዮጲያዉያን ከጉዞ ሰነድና ቪዛ ጋር ተያይዞ ያሉ የአገልገሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲፈቱ ተጠየቀ በአቡዳቢና ዱባይ አካባቢ እየተሰጠ ባለው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎቶች ከዚህ ቀደም የሚነሱ ቅሬታዎች እየተፈቱ መሆኑን የኮሚኒቲ አባላት፣ ተወካዮችና አመራሮች ተናግረዋል።በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ልዑክ በአቡዳቢና ዱባይ ሚሲዮኖች የሚሰጡ የዜግነት አገልግሎቶችን ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቶ ከሚሲዮን መሪዎችና ኮሙኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ በሚሲዮኖቹ ከፓስፖርት እድሳትና ተያያዥ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ዜጎች ላቀረቡት ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ የሚደነቅ ቢሆንም፤ ከጉዞ ሰነድና ቪዛ ጋር ተያይዞ ያሉ የአገልገሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲፈቱ ተጠይቋል፡፡በተጨማሪም የመረጃ ልውውጥ ክፍተት፣ ሐሰተኛ ማስረጃ፣ የጉዞ ሰነድ (ሊሴ ፓሴ)፣ የበይነ-መረብ አጭበርባሪዎች መበራከት እንዲሁም ከዜግነት አገልግሎት ጋር ያሉ ክፍተቶች መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት÷ ተቋሙ 11 የሪፎርም አጀንዳዎችን ቀርጾ ወደ ስራ በመግባቱ ከዜጎች አገልግሎት ጋር በተያያዘ እየታዩ ያሉ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች መታየታቸውን ተናግረዋል።የሪፎርሙ ስራ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በዘርፉ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያስችልም ገልጸዋል። ከሰነድ አልባና ከዜግነት አገልግሎት ጋር ያሉ ስራዎች ከሀገር ደህንነት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ በመሆኑ በጥንቃቄና በህግ አግባብ ብቻ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።ልዑኩ ባደረገው ጉብኝት የዱባይ ሚሲዮን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ የሚከተለው አሰራር እንደተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን እንደተመለከተ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 16
ስፓይሲ ገርልስ በቪክቶሪያ ቤካም 50ኛ ዓመት የልደት በዓል ላይ ዳግም ተገናኙ አምስቱም የስፓይሲ ገርልስ አባላት እንደገና ተገናኝተዋል፣ ቅዳሜ ምሽት ቪክቶሪያ ቤክሃም፣ ሜላኒ ብራውን፣ ኤማ ቡንተን፣ ጌሪ ሆርነር እና ሜላኒ ቺሾልም በመባል የሚታወቁት የእንግሊዝ የድምፃዊያን ቡድን የቪክቶሪያን 50ኛ ዓመት የልደት በአል በለንደን ለማክበር ተገናኝተዋል። የባንዱ አባላት ልክ እንደ 1997 በማመሰል ታዋቂ የሆነውን ስቶፕ የተሰኘውን ስራቸውን አቅርበዋል። ዴቪድ ቤካም ስነስርዓቱን በኢንስታግራም ገፁ ላይ አጋርቷል፣ እንዲሁም አብሮ ሲዘፍን ታይቷል። የቪክቶሪያ ባል እና የ48 አመቱ የቀድሞ የእንግሊዝ ካፒቴን ቤካም ደስተኛ ሆኖ እንደነበር ማስተዋል ተችሏል። በሜይፌር በሚገኘው የኦስዋልድ የግል  ክለብ ውስጥ በተካሄደው የልደት ድግስ ላይ እንደ ቶም ክሩዝ፣ ሳልማ ሃይክ፣ ሮዚ ሀንቲንግተን-ዊትሊ እና ጎርደን ራምሴ የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ተገኝተውበታል። በሰምሃል አለባቸዉ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 18 5😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
65 በመቶው የሚሆኑ እስራኤላዉያን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ጥሩ እንቅልፍ እንደማይተኙ አንድ ጥናት አመላከተ የእስራኤል ዬዲዮት አህሮኖት ሚዲያ እና የሪችማን ዩኒቨርሲቲ የነፃነት እና ኃላፊነት ተቋም ባደረጉት የህዝብ አስተያየት 85 በመቶ የሚሆኑ እስራኤላውያን በመንግስታቸው ላይ እምነት የላቸውም።64 በመቶ ያህሉ እስራኤላውያን አገራቸው የህልውና ስጋት እንዳለባት የሚያምኑ ሲሆን 65 በመቶው ደግሞ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ጥሩ እንቅልፍ እንዳልተኙም ገልጿል። ቢያንስ 73 በመቶ የሚሆኑት እስራኤላውያን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በጭንቀት ተውጠዋል።በሌላ በኩል የዮርዳኖስ ሃሺሚት መንግሥት በሁለት ክልላዊ ኃይሎች እስራኤል እና ኢራን መካከል ክልላዊ ውጥረቱ እየጠነከረ ከቀጠለ ከባድ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዘዞች ሊገጥማቸው ይችላል በሚል የማሸማገል ሚናዉን እየተወጣ ይገኛል። ዮርዳኖስ ማንኛውም ክልላዊ እርምጃ በኢራን እና በእስራኤል መካከል ያለው ጠላትነት መባባስ ወይም እስራኤል ራፋህ ከወረረች በአገር ውስጥ ተቀጣጣይ ምላሾች ሊኖሩት ይችላል ብላለች።በሴናጎህ ዩኒቨርሲቲ የዮርዳኖስ ኤክስፐርት እና ከሬሲሊየንስ ቱ ሪቮሊሽን ፀሃፊ ሼን ዮም "ማንኛውም የማይቀር የኢራን እና የእስራኤል ጦርነት ዮርዳኖስን በጠባብ ገመድ ላይ ሊያስቀምጣት እንደሚችል ለአልጀዚራ ተናግሯል። ከአደባባይ ውዝግብ መራቅ እንዳለበት ከየትኛውም ተዋጊ ጋር መቆም እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡ በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😁 43👍 10👏 7🤔 6 4😱 1
Inter are celebrating their second star ⭐⭐   #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
12👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
🚨 ኢንተር የሴሪ ኤ ሻምፒዮንስ በታሪካቸው የሊጉን 20ኛ ዋንጫቸውን ተቀናቃኛቸው ኤሲ ሚላንን 2ለ1 በመርታት አሳክተዋል! 🔵⚫️ 77 ግቦችን በማስቆጠር ፣ 18ግቦች ተቆጥረውባቸው ፣ 1ድ ጨዋታ ብቻ ተሸንፈዋል ። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
30👍 14👏 2
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቀሲስ በላይ ጉዳይ ጋር ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ አስታወቀች ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል መባላቸውን ዳጉ ጆርናል ተከታታይ መረጃዎችን አድርሷል። ይህንኑ ተከትሎ ቀሲስ በላይ የተጠረጠሩበት ድርጊት መነጋገሪያ ሆኖ የቆየ ሲሆን ዶቼዌሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቀሲስ በላይ ጉዳይ ጋር ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ ማስታወቋን ዘግቧል። ስለሁኔታው የተጠየቀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግለሰቡ በቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚገለግሉ ቢሆንም፤ ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ አስታውቃለች፡፡ መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶመምስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመምበረ ፓቲሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ “ሊቀአዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች ማለታቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል፡፡ እስካሁን በተደረገው ክትትል ግን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው” ብለዋል። ኃላፊው በቀጣይ ግን ጉዳዩ የቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለወይ ለሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉን አመልክተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረገው የባንኮች መጭበርበርና አንድምታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ሚያዚያ 03 ቀን 2016 ዓ.ም. የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ጤናማነትን በመገምገም ይፋ ባደረገው ሪፖርት፣ የአገሪቱ ባንኮች በበይነ መረብ ማጭበርበርያ ሥልቶች፣ ከባንኮች የውስጥ ሠራተኞችና ከሦስተኛ ወገን በሚደርሱባቸው የምዝበራ ድርጊቶች እየተጋለጡ ነው ብሎ ነበር። ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ማለትም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ በሐሰተኛ ሰነዶችና በሌሎች የማጭበርበር ድርጊቶች ባንኮች አንድ ቢሊዮን ብር ማጣታቸውን፣ ብሔራዊ ባንክ በግምገማ ሪፖርቱ ገልጿል። ይህም ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው እጥፍ መሆኑ ነው፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 61😁 29 4👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
-2147483648_-210974.jpg0.47 KB
በአፋኞች ከታገተች አንድ ወር ያለፋት የ 16 አመቷ ታዳጊ ማህሌት ተክላይ አሁንም አለመገኘቷን ቤተሰቦቿ ተናገሩ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ከ 30 አካባቢ የቋንቋ ትምህርቷን ለመከታተል በወጣችበት የታፈነችዉ ታዳጊ ማህሌት ተክላይ አሁንም አለመገኘቷን ታላቅ ወንድሟ የሆኑት ሙሴ ተክላይ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በታገተች በቀናት ዉስጥ ከአጋቾቹ የስልክ ጥሪ ሲደርሳቸዉ የነበሩት ቤተሰቦቿ ካለፉት 25 ቀናት ወዲህ ግን የስልክ ግንኙነቱም መቋረጡን ነግረዉናል። ልጇቸዉ በእገታ ዉስጥ ከገባች አንድ ወር ማሳለፏንም ጠቅሰዋል። ከትምህርቷ ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ 30 የምትወጣ የነበረ መሆኑን የነገሩት ታላቅ ወንድሟ የሆኑት ሙሴ ፤ ዘወትር ይቀበሏት የነበረ ቢሆንም በእለቱ ወደ ትምህርት አለመግባቷን እንዳረጋገጡ ያስታዉሳሉ። በእለቱ አመሻሹን 2 ሰዓት 20 ደቂቃ አካባቢ ላይ በማህሌት ስልክ ወደ ወላጅ አቧቷ በመደወል ፤ አጋቾቿ 3 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸዉንም ይገልጻሉ። ከዚህ በኋላ በቀናት ልዩነት ዉስጥ ገንበዙን አጋቹ በሚያስቀምጠዉ መመሪያ መሰረት እንዲያስቀምጡ ትዕዛዝ ቢሰጣቸዉም ላለፉት ከ 25 በላይ በሆኑ ቀናት ግን የስልክ ግንኙነቱ መቋረጡን ፤ የልጃቸዉንም ሁኔታ እንደማያዉቁ ታላቅ ወንድሟ ነግረዉናል። ሙሴ ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ቢናገርም የደረሰበትን ደረጃ ግን ለማወቅም ተቸግረናል ይላሉ። የአድዋ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተስፋዬ አማረ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፤ የታዳጊዋ መታገት ሪፖርት ከቀረበላቸዉ መጋቢት 11 / 2016 ጀምሮ በወቅቱ ተጓጉዛበታለች ተብሎ የተጠረጠረዉ የባጃጅ አሽከርካሪን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዉሎ ቃላቸዉን ተቀብሎ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። አንዳንዶቹ ተጠርጣሪዎች እስካሁን በቁጥጥር ስር ሲገኙ ከፊሎቹ ቃላቸዉን ሰጥተዉ የተለቀቁም እንዳሉ ነግረዉናል። ፖሊስ የራሱን ጥረት እያደረገ ነዉ ያሉት አዛዡ እስከ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ድረስ ማህሌትን ለማስለቀቅ እየሰሩ ነዉ ብለዋል። የማህሌት ታላቅ ወንድም የሆኑት ሙሴ ተክላይ ታናሽ እህታቸዉ ከታገቱ ከአንድ ሳምንት በኋላ ከአጋቾቹ የስልክ ጥሪ ከደረሳቸዉ በኋላ ከአንድ ወር በላይ ላስቆጠረ ጊዜ የማህሌትን ድምፅ እንዳልሰሙ ተናግረዋል። የ16 አመቷ ማህሌት ተክላይ ዛሬ ላይም ከቤተሰቦቿ ከተለየች አንድ ወር ከ 4 ቀን ሆኗታል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😢 41👍 16💔 7 1
Photo unavailableShow in Telegram
2
Photo unavailableShow in Telegram
በሀረር ከተማ በስለት በማስፈራራት የስርቆት ወንጀል የፈጸሙት ሶስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በሀረር ከተማ ጀኒኢላ ቀበሌ 16 እና 14 በተለያዩ  ጊዜያት የመኖሪያ ቤት አጥር ዘለው በመግባት  በስለት በማስፈራራት የስርቆት ወንጀል የፈጸሙት  ግለሰቦች በእስራት ተቀጥተዋል። የጀኒኢላ ወረዳ ፖሊስ  ወንጀል ምርመራ  ክፍል ሃላፊ ኮማንደር አህሚ  አህመድ  ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ተከሳሽ ዋሌ ኮርሱ የተባለው ግለሰብ በአጥር ዘሎ በመግባት የቤቱን ባለቤት በስለት በማስፈራራት አልባሳት እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የዋጋ ግምታቸው ከ24 ሺህ ብር በላይ የሆነ ንብረት  ሰርቆ ለማምለጥ  ሲሞክር በቁጥጥር  ስር መዋሉን ተናግረዋል። ፖሊስ ምርመራው  አጣርቶ መዝገቡን ለዓቃቢ ህግ ልኮ ክስ መስርቷል ። የሀረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ በመመልከት በተከሳሹ ላይ የ2 ዓመት እስራት የወሰነበት መሆኑን ኮማንደር አህሚ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል። በሌላ በኩል  ሁለት ግለሰቦች  ተባብረው የመኖሪያ ቤት አጥር ዘለው በመግባት ቴሌቪዥን ፣ 2 ሞባይል  ፣ ጂፓስ ፣ የባጃጅ ጎማ እና 7 ሺህ ጥሬ ገንዘብ በአጠቃላይ 94 ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት ዘርፈው ለማምለጥ ሲሞክሩ በቁጥጥር  ስር ውለዋል። ዓቃቢህግ የመሰረተውን የክስ መዝገብ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በእያንዳንዳቸው ላይ በ1 ዓመት ከ5 ወር እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 18👎 4😁 4 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች:: የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው። ተቋሙ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ሰሌዳው ላይ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል። የዓለም አትሌቲክስ አካል የሆነው ይህ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ አትሌቷ ሁለት የተከለከሉ ንጥረ-ነገሮችን መውሰዷን አምናለች ብሏል። ዘርፌ፤ ቴስቶስቴሮን የተባለውን እና ኢፒኦ የተሰኘውን አትሌቶች በደማቸው ውስጥ የበለጠ ኦክሲጅን እንዲኖር የሚያደርግ ንጥረ ነገር መውሰዷን አምናለች። ዘርፌ በቶኪዮ ኦሊምፒክስ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ስምንተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 19😢 17😱 5😁 2🤬 2🤩 1
Photo unavailableShow in Telegram
የናይጄሪያ ጦር ወታደሮቹ መገደላቸውን ተከትሎ የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ ዛተ የናይጄሪያ ጦር ባለፈው ሳምንት በኒጀር ማዕከላዊ ግዛት የሰላም ተልዕኮ ላይ እያለ በደፍጣ ውጊያ ለተገደሉት ስድስት ወታደሮች የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። ወታደሮቹ ባለፈው አርብ በሽሮሮ አካባቢ በሚገኘው ካራጋ መንደር “በተዋጊ ፓትሮል” ላይ በነበሩበት ወቅት በጦር ኃይሉ “አሸባሪዎች” ተብለው በተፈረጁ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ደርሶባቸዋል። የጦሩ መግለጫ እንዳመለከተው በርካታ ጥቃት አድራሾች መገደላቸውን እና ሌሎችንም እየተከታተልን እንገኛለን ነው። ጦረ በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት እንደሚበቀልም ቃል ገብቷል። የተገደሉት ወታደሮች ሁለት ከፍተኛ መኮንኖች እና ሌሎች አራት ወታደሮች እንደሚገኙበት ሰራዊቱ ገልጿል። በጥቃቱ ወቅት ሁለት መኮንኖች ቆስለዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ አንድ መኮንን ታፍኖ መወሰዱን ከአካባቢው የወጡ ዘገባዎች ቢያመላክቱም ማረጋገጥ ግን አልተቻለም። ከጥቃቱ ጀርባ ማን እንዳለ ግልፅ ባይሆንም በአካባቢው ሽፍቶች በመባል የሚታወቁት የታጠቁ ወንበዴዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደረሰባቸው ጥቃቶች የጸጥታ ሃይሎችን ኢላማ አድርገዋል ተብሏል። ናይጄሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ከፍተኛ የአፍሪካ የፀረ-ሽብርተኝነት ጉባኤ በመዲናይቱ አቡጃ ስታስተናግድ ቆይታለች። በነዳጅ ዘይት በበለጸገው ደቡባዊ ዴልታ ግዛት በተቀናቃኝ ማህበረሰቦች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ሲዋጉ የነበሩ 16 ወታደሮች ከተገደሉ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ይህው የአድፍ ጥቃት መከሰቱን መረጃዎች አመላክተዋል።ናይጄሪያ ለእገታ ገንዘብ ለመቀበል በሚል ከፍተኛ የአፈና ማዕበል የተስፋፋባት ሲሆን የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች እያንሰራሩ ይገኛሉ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 16 3🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
የታጠቁ ኃይሎች የደህንነት ጥበቃ ተደርጎላቸው በአገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ ዝግጅት ተደርጓል ሲል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ በትጥቅና ሰላማዊ ባልሆነ መንገድ የሚታገሉ አካላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ እንደሚደረግ ኮሚሽኑ አስታወቀ። የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር እንደገለጹት ሰላማዊ ያልሆነ ትግል የሚካሄዱ አካላት ወደ ምክክሩ እንዲመጡ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል። ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ እንደገልጹት "እነሱ [ሰላማዊ ትግል የሚያደርጉ] መጥተው በሚሳተፉበት ጊዜ ለእነሱ የደህንነት ጥበቃ ተደርጎ ምንም ጉዳት እንደማይደርስባቸው" አጽንዖት ሰጥተዋል። ኮሚሽኑ እንደገለጸው በዚህ "ታሪካዊ አጋጣሚ" ተገኝቶ በሃሳብ ተፎካክሮ መተማመን ከጦርነት ኪሳራዎች መውጣት ይገባል ብሏል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😁 66👍 12🕊 6🤔 3👎 1 1🙏 1
በደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 02877 ኢቲ አባይ የህዝብ አዉቶብስ ከፍተኛ የሀገር አቋራጭ አውቶብስ ከአዲሳ አበባ 95 ኪሎ ሜትር ላይ ደብረ ሊባኖስ ቃሲም ቀበሌ ዋኬኔ መሶብ ተራ የተባለ አካባቢ ሲደርስ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 46285 አአ ከሆነ ሱዙኪ የቤት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው አደጋው መድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡ የደብረሊባኖስ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደጀኔ ስዩም ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት አደጋው የደረሰው ሰኞ 6፡30 ላይ ነው ፡፡በአውቶብስ ውስጥ ከነበሩት 65 ተሳፋሪዎች መካከል ሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ በአደጋው ወዲያውኑ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡17 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ቀሪዎቹ ተሳፋሪዎች ቀላል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ የአደጋው መንስኤ የቤት ተሸከርካሪዋ መንገዱ በመበላሸቱ ምክንያት መንገድ ለመምረጥ መስመሩን ሲለቅ በአውቶቡሱ አቅጣጫ በመግባቱ አደጋው ሊከሰት እንደቻለ ተናግረዋል፡፡ፖሊስ አሁንም አደጋውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በአደጋው በጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደብረ ጽጌ ሸረሮ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛሉ፡፡ሌሎቹ ደግሞ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጫሌ እና አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መላካቸውን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በዚህ አካባቢ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች በብዛት ስለሚጓዙ መንገዱ ከመበላሸቱ የተነሳ መንገድ ለመምረጥ ብለው ከአቅጣጫቸው ውጪ ወደ ሌላ አቅጣጫ እየገቡ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሆነ አቶ ደጀኔ ስዩም ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 16😢 14😱 5 1
Kirish qilib, tafsilotli ma'lumotlarga ega bo'ling

Biz sizga ushbu hazinani tasdiqlashdan so'ng ochamiz. Va'da qilamiz, tezroq!