cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
35 702
Obunachilar
-2124 soatlar
-997 kunlar
+97430 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
😁 11
የእስራኤል ወታደራዊ መረጃ ሃላፊ የጥቅምት ሰባቱን ጥቃት መከላከል አልቻሉም በሚል ከስልጣን ለቀቁ የእስራኤል ወታደራዊ መረጃ ሃላፊ የሆኑት አሮን ሃሊቫ በሃማስ ጥቃት ዙሪያ በተፈጠረው ውድቀት ምክንያት ስልጣን የለቀቁ የመጀመሪያው ባለስልጣን ሆነዋል፡፡ የእስራኤል ጦር በመግለጫው የወታደራዊው ዋና አዛዥ የሃሊቫን የስራ መልቀቂያ ተቀብሎ ለአገልግሎታቸዉ አመስግነዋል። እርምጃው ጥቃቱን ባለመከላከላቸዉ ምክንያት ጥፋተኛነቱን እንዲቀበሉ እና ከስልጣን እንዲወርዱ ያደረገ ሲሆን በርካታ የእስራኤል ከፍተኛ የጸጥታ ሃይሎች ተመሳሳዩን መንገድ ሊከተሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ሃሊቫ በጥቅምት ወር እንደተናገሩት የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን ለማስቆም ባለመቻሉ ሃላፊነቱን እንደሚወስዱ መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡ ቢያንስ 1 ሺ 1 መቶ 39 እስራኤላውያን በጥቃቱ ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተይዘው ወደ ጋዛ ተወስደዋል።ሜጀር ጄኔራል አሮን ሃሊቫ በስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ የወታደራዊው የስለላ ክፍሉ የተጣለበትን ኃላፊነት አልወጣም ብለዋል። ሃማስ በእስራኤል ግዛት ላይ ካደረሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት እንዲያመልጠን የሆነዉ ከፍተኛ የመረጃ ውድቀት እንዳለ እናውቃለን ብለዋል።ከአንድ አመት በፊት የእስራኤል የስለላ ድርጅት የጥቅምት 7ቱን ጥቃት እቅድ በትክክል ያስቀመጠ የሃማስ ሰነድ እጁ ላይ ገብቶ ነበር፡፡ ጥቃቱ ከመፈጸሙ ባሉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ በጋዛ ዙሪያ ካሉት ማማዎች የእስራኤል ወታደራዊ ስፔሻሊስቶች የሃማስ ሻለቃዎች ለአንድ ጥቃት ሲዘጋጁ ማየታቸውን እናውቃለን ሲሉ ደብዳቤዉ ላይ አስፍረዋል።ይህ ሁሉ በወታደራዊ እና በመንግስት ከፍተኛ አመራረፐች ደረጃ ችላ ተብሏል ምክንያቱም ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ፍላጎት የለውም ከሚል የተሳሳተ እምነት ነበረ። ሃማስ የበለጠ ጋዛን የማስተዳደር ፍላጎት አለዉ የሚለዉ በእስራኤል አስተዳደር በኩል አጋድሏል። ለዚህም የወታደራዊ መረጃ ሃላፊዉ ባልተወጣዉ ስራዉ ምክንያት ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ተቀብሏል። የጦር ኃይሎች መሪ ሌተና ጄኔራል ሄርዚ ሃሌቪ እና የአገር ውስጥ የስለላ ድርጅት ኃላፊ ሺን ቤት ኃላፊ ሮነን ባር ከጥቃቱ በኋላ ኃላፊነቱን ቢቀበሉም በጋዛ ያለዉ ጦርነቱ በመቀጠል ስልጣናቸዉን አይለቁም፡፡በአንፃሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሃማስ ለተፈጸመዉ ጥቃት እስካሁን ድረስ ኃላፊነቱን አልወሰዱም፣ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኞቹ እስራኤላውያን ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥረት ባለማድረጋቸው ግን ይተቿቸዋል፡፡ በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 26😁 13 3
በሸገር ከተማ በአበባ እርሻ ድርጅር ዉኃ ማጠራቀሚየ ዉስጥ የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ህይወት አልፎ ተገኘ ላፍቶ ሮዝ የተሰኘወ የአበባ እርሻ ድርጅት የሚጠቀምበት የተጠራቀመ ዉኃ  ዉስጥ ዕድሜዉ ዘጠኝ ዓመት የሆነ ታዳጊ ህይወቱ አልፎ  መገኘቱን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡ ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ-ከተማ "ላፍቶ ሮዝ" ዉስጥ አደጋዉ ማጋጠሙን የታዳጊዉን አስከሬን የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች በፍለጋ አግኝተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸው የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራጽ ሬዲዮ እና ቴሌቭዢን ተናግረዋል፡፡ ይህ የተጠራቀመ ዉሀ ከፍተኛ ስፋትና ጥልቀት ያለዉ ከመሆኑም ባሻገር ምንም ዓይነት ከለላ ያልተደረገለት ነዉ።በዚህ ቦታ ቀደም ሲልም ተመሳሳይ አደጋ መድረሱን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።በሌላ በኩል በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 አዲስ አበባ ኮንደሚኒየም ብሎክ 99 ስር ባሉ ሰባት የንግድ ቤቶች ዉስጥ ጎርፍ ገበቶ ከባድ ጉዳት ማድረሱን አቶ ንጋቱ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በንግድ ሱቆች የገባዉን ጎርፍ ለማስወገድ ሶስት ሰዓት የፈጀባቸዉ ሲሆን በጎርፍ አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😢 20👍 8 1
በሸገር ከተማ በአበባ እርሻ ድርጅር ዉኃ ማጠራቀሚየ ታንከር ዉስጥ የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ህይወት አልፎ ተገኘ ላፍቶ ሮዝ የተሰኘወ የአበባ እርሻ ድርጅት የሚጠቀምበት የተጠራቀመ ዉኃ ታንከር ዉስጥ ዕድሜዉ ዘጠኝ ዓመት የሆነ ታዳጊ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡ ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ-ከተማ "ላፍቶ ሮዝ" ዉስጥ አደጋዉ ማጋጠሙን የታዳጊዉን አስከሬን የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች በፍለጋ አግኝተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸው የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራጽ ሬዲዮ እና ቴሌቭዢን ተናግረዋል፡፡ ይህ የተጠራቀመ ዉሀ ከፍተኛ ስፋትና ጥልቀት ያለዉ ከመሆኑም ባሻገር ምንም ዓይነት ከለላ ያልተደረገለት ነዉ።በዚህ ቦታ ቀደም ሲልም ተመሳሳይ አደጋ መድረሱን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።በሌላ በኩል በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 አዲስ አበባ ኮንደሚኒየም ብሎክ 99 ስር ባሉ ሰባት የንግድ ቤቶች ዉስጥ ጎርፍ ገበቶ ከባድ ጉዳት ማድረሱን አቶ ንጋቱ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በንግድ ሱቆች የገባዉን ጎርፍ ለማስወገድ ሶስት ሰዓት የፈጀባቸዉ ሲሆን በጎርፍ አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ ባለፋት አራት ወራት አምስት ሰዎች በዝሆን ተረግጠው ህይወታቸው ማለፋ ተነገረ በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ በሰውና በዝሆኖች መካከል እየደረሰ ያለው ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል። በኢትዮጵያ በሚገኙ የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች ላይ በተለያዩ ጊዜያት በሰዎችና በዝሆኖች መካከል በሚፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ሰዎች ለአካል ጉዳት  እና ለህልፈት እንደሚዳረጉ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የሰውና የዱር እንስሳት ግጭት አፈታት ባለሙያ የሆኑት አቶ ኃይሉ ዘርፉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት  በሰውና በዝሆን መካከል የሚስተዋለው ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ  እንደ ሀገር ልዩ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል።  ግጭቱ  በአብዛኛው የሚከሰተው ከጥበቃ ቦታዎች ውጭ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ዝሆኖችም ለዚህ ችግር ይዳረጋሉ ተብሏል ።የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ችግሩን ከመሰረቱ ለመለየትና ለመከላከል የሚያስችል የመፍትሔ አማራጮችን ለመውሰድ የጥናት ቡድን በማደራጀት ላለፉት ወራት የዳሰሳ ጥናት ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል ፡፡ በተካሄደው የዳሰሳ ጥናትም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና የዝሆን መገኛ ከሆኑ ጥበቃ ቦታዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች በተገኙበት  የጋራ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የጥናቱ መረጃ  የዝሆን መገኛ ከሆኑት ከጨበራ ጩርጩራ፣ ኦሞ፣ ማጎ፣ ከቃፍታና ከጋምቤላ ብሔራዊ ፓርኮች እንዲሁም ከባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ አካባቢ ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መሆኑን  አቶ ሀይሉ ጨምረው ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡ በጥናቱ በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ግጭቱ  በተለይም በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ  ተጠቁሟል፡፡ባለፋት አራት ወራት ውስጥ በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ አምስት ሰዎች በዝሆን ተረግጠው መገደላቸውን የገለፁት አቶ ሀይሉ የህገወጥ ሰፈራ መበራከት ለችግሩ መፈጠር ዋነኛው ምክንያት መሆኑን አንስተዋል። ሰዎች ለእርሻና ለሌሎች ተግባራት በሚል በፈጠሩት ህገወጥ እንቅስቃሴ ምክንያት በዚሁ የዝሆኖች መጠለያ የነበሩት ዝሆኖች መቆሚያ በማጣታቸው  የተነሳ  የእነዚህ ሰዎች ህይወት ማለፋን ተናግረዋል። በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ እየተስተዋለ የሚገኘውን ህገወጥ ሰፈራ ለመከላከል በቀጣይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፣የምዕራብ ሀረርጌ ዞን መስተዳድር ቢሮዎችና ወረዳዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በጋራ  ሆነው የሚያደርጉት የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 16😁 8😢 5🤯 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቲክ ቶክ በአሜሪካ ሊታገድ መሆኑን ተከትሎ ኩባንያው የመናገር ነፃነትን ይጥሳል ሲል አስጠንቅቋል ቲክ ቶክ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመተግበሪያው ላይ እገዳ ሊጣል መሆኑን ተከትሎ የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያንን “የመናገር ነፃነትን ይረግጣል” ሲል ኩባንያው አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የመተግበሪያው ባለቤት ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቋረጠ ቲክ ቶክን እንዲያግድ ድምጽ ሰጥቷል። ህጉ የዩክሬን ርዳታን ያካተተ የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ፓኬጅ አካል ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል። በቅርብ ወራት ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ቲክቶክ በወጣቶች ዘንድ ስላለው ተወዳጅነት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። የቲክቶክ ባለቤት ባይቴዳንስ ለቤጂንግ አስተዳደር ታዛዥ ነው ስትል ዋሽንግተን ክስ ብታቀርብም ባይቴዳንስ ግን ክሱን ደጋግመው ውድቅ አድርገዋል።የቲክ ቶክ ህግ በሕግ አውጭዎች የጸደቀው፣ ለ61 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕርዳታን ወደ ዩክሬን እንዲሁም ለእስራኤል እና ለታይዋን ገንዘብ በሚልክ ጥቅል ውስጥ ተካቶ ነው። የተወካዮች ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በቲክ ቶክ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ድምጽ ሰጥቷል ። በተሻሻለው የዳይቭስት ወይም እገዳ ህግ ላይ 360 ለ58 ድምጽ ተሰጥቷል። ሴኔቱ በሚቀጥለው ሳምንት በህጉ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ህጉን እንደሚፈርሙ ተናግረዋል ። ይህው ረቂቅ ህግ ሆኖ ከፀደቀ ባይቴዳንስ ድርሻውን ለመሸጥ ዘጠኝ ወራት ይኖረዋል። ሽያጭ በሂደት ላይ እያለ ለሶስት ወራት ሊራዘም ይችላል።የቲክ ቶክ ቃል አቀባይ ህጉን አውግዘዋል፣ “የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያንን የመናገር መብት ይረግጣል፣ ሰባት ሚሊዮን ንግዶችን ይዘጋል፣ እንዲሁም በአሜሪካ ኢኮኖሚ ላይ ያለውን የ24 ቢሊዮን ዶላር አስተዋጽኦ የመድረኩ መታገድ ያስቀረዋል ሲሉ ተደምጠዋል። ቲክ ቶክ ባይት ዳንስ “የቻይና ወይም የሌላ አገር ወኪል አይደለም” ይላል። ባይት ዳንስ 60 በመቶውን የያዙትን በርካታ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ድርጅቶችን በማመልከት የቻይና ኩባንያ እንዳልሆነ አጥብቆ ተናግሯል። የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ለባይት ዳንስ ቲክቶክን ለቻይና ላልሆኑ ባለቤቶች እንዲሸጥ ወይም መተግበሪያው በአሜሪካ እንዲታገድ በመጋቢት ወር ድምጽ ሰጥቷል። ነገር ግን ይህ ህግ አሁንም የሴኔት ይሁንታ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 28😁 7
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በአሜሪካ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር መወያየታቸው ተነገረ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ኃላፊ የተመራ ልዑክ ቡድን በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ ከኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር መወያየቱ ዳጉ ጆርናል ከክልሉ ፓርቲ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል። በአማሪካ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ የተመራው ቡድን በኒውዮርክ ከተማ የሥራ ጉብኝትም አድርጓል። "የልዑክ ቡድኑ በሀገር ደረጃ እና ክልላዊ  የለውጥ ጉዞ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሔ መንገዶች ላይ" ውይይት አድርጓል የተባለ ሲሆን ክልሉን ወደ ተሟላ ሰላም ለማምጣት መንግሥት እያደረገ ስላለው ጥረትና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተደረገ ስላለው ጥረት ውይይት ማድረጉን አሳዉቋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም ስለክልሉ የሰላም ሁኔታ ፣ የልማት ሥራዎችና ድህነት ቅነሳ ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ ፣ የሀገራዊ አካታች የምክክር መድረክ ላይ የአማራ ክልል ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ሥራ እና ለሥራ እድል ፈጠራ ያለውን ምቹ ሁኔታ የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል ተብሏል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ጽሕፈት ቤት አምባሳደሮች ፣ ዲፕሎማቶች ፣ ኢትዮጵዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተወካዮች በዉይይቱ መሳተፋቸው ታዉቋል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👎 36👍 19😁 11 1
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንጨት እና ፊኒሺንግ ስራዎችን ጨምሮ 12 የሙያ ትምህርቶች ይሰጣሉ ተባለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ  በ2017 የትምህርት ዘመን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሙያ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር አስታዉቋል። ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከቢሮዉ ያገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተው ለተማሪዎች ይሰጣሉ የተባሉት የሙያ አይነቶችም ይፋ ተደርገዋል። በዚህም በክልሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተፈጥሮ ሳይንስ በ7 የሙያ አይነቶች እና በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በ5 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ ይሰጣል ሲል ቢሮዉ አሳዉቋል። በዚህም መሰረት በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የእንጨት ስራ ቴክኖሎጂ ፣ ፊኒሺንግ ኮንስትራክሽን ስራ ፣ ዌብ ዲዛይን እና ዴቬሎፕመንት ፣ ኮምፒውተር ጥገና ፣ አኒማል ፕሮዳክሽን ፣ ተፈጥሯዊ ሀብት አስተዳደር እና ማህበረሰብ ጤና የተሰኙ የሙያ ትምህርት አይነቶች ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹ ይሰጣሉ ብሏል። በተጨማሪም በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ጋዜጠኝነት ፣ ስነ ልቦናዊ ክብካቤ ፣ አካውንቲንግ እና ፋይናንስ ፣ ማርኬቲንግ እና ሽያጭ አስተዳደር ፣ ቮካል ፐርፎርማንስ እና ዳንስ መሆናቸውን ቢሮዉ ገልጿል። እንደ ሀገር በ 40 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሰው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከ12ቱ የሙያ ትምህርቶች በተጨማሪ ወደፊት ሌሎች የሙያ አይነቶች ወደፊት በተጨማሪነት እንደሚካተቱም አሳዉቋል። የሙያ አይነት ትምህርቶቹ ከቀለም የትምህርት አይነቶች ጋር ጎን ለጎን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጡ መሆኑን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 52👏 11😁 6 1🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
👏 6😁 6
አሜሪካ በእስራኤል ጦር ኃይሎች ላይ የምትጥለውን ማንኛውንም ማዕቀብ ውድቅ እናደርጋለን ሲሉ ኔታንያሁ ቃል ገቡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዩናይትድ ስቴትስ ለአንድ የጦር ክፍል የምትሰጠውን እርዳታ ለማቋረጥ ማቀዷን መዘገቡን ተከትሎ በእስራኤል ጦር ላይ የሚጣልው ማንኛውንም ማዕቀብ እንደማይቀበሉ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  "በሙሉ ኃይላችን እንታገላለን" ብለዋል። ቀደም ሲል አክሲዮስ የዜና ጣቢያ እንደዘገበው ዩናይትድ ስቴትስ በዌስት ባንክ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፀመዋል ያለቻቸውን የእስራኤል ኔትዛህ ይሁዳ ክፍለ ጦር ላይ ማዕቀብ ለመጣል ኢላማ አድርጋለች። በዌስት ባንክ የሰብአዊ መብት ረገጣ ክስ ለእስራኤል መከላከያ ሃይል ክፍሎች የሚሰጠውን ወታደራዊ እርዳታ ሊያቋረጥ እንደሚችል ዘገባዎች ባለፈው ሳምንት ሲወጡ ነበር። ይህንኑ በተመለከተ የተጠየቁት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ብሊንከን ውሳኔ ወስኛለሁ፤ እናንተም በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ይህንኑ ለማየት መጠባበቅ ትችላላችሁ ሲሉ ተደምጠዋል። ዋሽንግተን የእስራኤል ዋና አጋር ስትሆን ከዚህ በፊት ለእስራኤል ጦር ኃይሎች ክፍል የምትሰጠውን እርዳታ አቋርጣ አታውቅም። የእስራኤል ጦር ኔትዛህ ይሁዳ በአለም አቀፍ ህግ መሰረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። የተጣለውን ማዕቀብ የሚገልጹ ህትመቶች በስፋት መሰራጨታቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ጉዳዩን አያውቅም ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የእስራኤል ጦር ኃይል ማንኛውንም ያልተለመደ ክስተት በተግባራዊ መንገድ እና በህግ መሰረት ለመመርመር እንደሚሰራ ይቀጥላል ሲሉ የእስራኤል የመከላከያ ሚንስትር ዮአቭ ጋላንት የተናገሩ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ በኔትዛህ ይሁዳ ላይ ማዕቀብ የመጣል ፍላጎቷን እንድታቆም ጠይቀዋል። ዓለም የዩናይትድ ስቴትስ እና የእስራኤልን ግንኙነት ከምንጊዜውም በላይ በቅርበት እየተከታተለ ነው ያሉት ጋላንት በሰጡት መግለጫ አንድን አጠቃላይ ክፍል ለመተቸት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ በእስራኤል ጦር ኃይሎች ላይ ትልቅ ጥላ ይጥላል ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ለአጋሮቻችን ትክክለኛው መንገድ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።የዜና ወኪሉ አክሲዮስ ጉዳዩን ከሚያውቁ ሶስት የአሜሪካ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ብሊንከን በቀናት ውስጥ በኔትዛህ ይሁዳ ላይ የሚጥሉትን ማዕቀብ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። እርምጃው የሚወሰደው በዌስት ባንክ ውስጥ ተፈጽሟል በተባለው የመብት ጥሰት ሲሆን የ80 ዓመቱ ፍልስጤማዊ አሜሪካዊው ኦማር አሳድ በዌስት ባንክ በተደረገ ፍተሻ በእስራኤላውያን ወታደሮች ታስረው ህይወታቸው ማለፉ በእስራኤል ኃይሎች ላይ ቁጣን ፈጥሯል። በጥር 2022 በወቅቱ ዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ላይ “የተሟላ የወንጀል ምርመራ እና ሙሉ ተጠያቂነት” እንዲደረግ ጠይቃለች።የእስራኤል ጦር በአሳድ ሞት እንደተፀፀተ እና የኔታህ ይሁዳ አዛዥ ላይ "ተግሣጽ" እንደሚደረግበት አስታውቋል። ሁለት ወታደሮች በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ለሁለት አመታት እንዳያገለግሉ እንደሚከለከሉ ነገር ግን በህግ እንደማይጠየቁም አክሏል። የአሳድ ሞት የተከሰተው ቀደም ሲል በነበረው የጤና እክል መሆኑንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 24😁 11 2🔥 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
አባ ገዳ ጎበና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸ መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ተናገሩ የቱለማ አባ ገዳ የሆኑት አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ። ከአንድ ሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን መንግሥት ‘ሸኔ’ የሚለው ቡድን አባል ነው ያለው የአባ ገዳ ጎበና ልጅ “ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል” ብሎ ነበር። ይህን የዞኑ መግለጫን ተከትሎ በኦሮሞ ባሕላዊ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ስፍራ በሚሰጠው ገዳ ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸው የአባ ገዳ ጎበና ልጅ የመገደል ዜና ብዙዎችን ሲያነጋግር ቆይቷል። የቱለማ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ፀሐፊ የሆኑት አባ ገዳ ጎበና ሆላ፣ ፎሌ ጎበና የሚባለው ልጃቸውን መገደል የሰሙት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚሠራጨው ወሬ መሆኑን እና አስካሁን ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል። የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ፤ “የኦሮሞ ልጆችን ሕይወት ሲቀጥፍ የነበረው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ ላይ እርምጃ ተወሰዷል” ብሎ ነበር። የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጨምሮም፤ “ፎሌ ጎበና ሆላ የተባለው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ውስጥ የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ለመቅጠፍ ሲንቀሳቀስ” እንደነበረ እና በፀጥታ ኃይሎች “እርምጃ እንደተወሰደበት” አመልክቷል። አባ ገዳ ጎበና የልጃቸውን ሞት ባያረጋግጡም በእርግጥ ልጃቸው መንግሥት ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባል መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልጃቸው ፎሌ ዕድሜው ወደ 33 ዓመት እየተጠጋ መሆኑን እና ከልጃቸው ጋር ከተያዩ ስድስት ዓመታት ማለፋቸውን አባገዳው ገልጸዋል። “ከስድስት ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀናት በፊት ፎቶ ግራፉን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የተመለከትኩት። “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ውስጥ እንዳለ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ምንም ግንኙነት የለንም። የት እንዳለም አላውቅም። መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለሁ” ብለዋል። የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ይህ የአባ ገዳው ጎበና ሆላ ልጅ በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ግድያዎችን ሲፈጽም ቆይቷል ሲል ከሶታል። አባ ገዳ ጎበና ግን ልጃቸው ተገድሏል ከመባሉ በተጨማሪ መንግሥት ስለሚያቀርብበት ክስ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። “እኔ አባ ገዳ ነኝ አልዋሽም፤ ከልጄ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም። ስልክ አንደዋወልም። ከስድስት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፎቶግራፉን እንኳ የተመለከትኩት።” የአማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው እና የአባገዳው ሰባተኛ ልጃቸው የሆነው ፎሌ ጎበና ከቤት የወጣው የ26 ዓመት ወጣት ሳለ እንደነበረ አባቱ ገልጸዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አባ ገዳ ጎበና ልጃቸው ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ መግባቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በተደጋጋሚ መኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበር ማድረጋቸውን ሲናገሩ ነበር። ከጥቂት ወራት በፊት አባ ገዳ ጎበና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤታቸው ላይ ብርበራ በተደረገበት ወቅት ከወላጅ አባታቸው የወረሱት የጦር መሳሪያ መወሰዱን እና ክስተቱን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ተናግረው ነበር። አባ ገዳ ጎበና ከቀድሞ የቱለማ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ መስከረም 20/2011 ዓ.ም. በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ የሆነውን ባሕላዊ ሥልጣንን መረከባቸው ይታወሳል። በገዳ ሥርዓት መሠረት አባ ገዳ ጎበና የቱለማ አባ ገዳ ሆነው እስከ 2019 ዓ.ም. ድረስ በስልጣን ላይ ይቆያሉ። በአሁኑ ጊዜ ታጣቂ ቡድኖች ከሚንቀሳቀሱባቸው ክልሎች አንዱ በሆነው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ የአባገዳው ልጅ አባል የሆነበት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዋነኛው ነው። በተለያዩ የኦሮሚያ ክልፍሎች ውስጥ የሚንቀሳቀሰው እና መንግሥት ‘ሸኔ’ በማለት በሽብር ቡድንነት የፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሰላማዊ ሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ይከሰሳል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 51👎 4 4😢 4👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
አሳዛኝ ተሸናፊዎች Coventry 👌 #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 73😁 12👎 7 4
ቀያይ ሰይጣኖቹ በፍጹም ቅጣት ምት 4-2 ኮቨንትሪን በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙሪ አላፊ ሁነዋል 👉በኤፌ ካፕ ፍፃሜው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ይፋለማሉ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😁 35👍 14 6😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሰደድ እሳት አጋጠመ በሰሜን ጎንደር ዞን የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርቅ ዉስጥ ከ አራት ቀናት በፊት ያጋጠመዉን የእሳት አደጋ ለማጥፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። የእሳት አደጋዉ የተከሰተበት ምክኒያት አይታወቅም ያሉት ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በፓርኩ የሚሰሩ የስነ ምህዳር ባለሙያ ሲሆኑ ከሰሞኑ በሌሎች ሶስት አካባቢዎችም የእሳት አደጋዎች አጋጥመዉ እንደነበር ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ሶስቱን የእሳት አደጋዎች በነዋሪዎች ትብብር ማጥፋት መቻሉን የተናገሩት ባለሙያዉ ከአራት ቀናት በፊት በአምባራስ ቀበሌ ግፍ በተሰኘዉ አካባቢ ያጋጠመዉ እሳት ግን ለማጥፋትም ፈታኝ መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ ቀበሌ ያጋጠመዉ የእሳት አደጋ መነሻ መንስኤ እንደማይታወቅም ሲሉ ባለሙያዉ አክለዋል። እሳቱን ለማጥፋት ከቀበሌ እስከ ዞን አስተዳደር ድረስ በነዋሪዎች ርብርብ እየተደረገ ነዉ ያሉት ባለሙያዉ ፤ ሆኖም እሳቱን በማጥፋት የሚሳተፉ ሰዎችን ለማመላለስ የተሽከርካሪ ነዳጅ እና የምግብ አቅርቦት ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል። ባለሙያዉ ሄሊኮፕተር እና ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎችን እስከማሳተፍ የደረሰ አደጋ የለም ቢሉም የእሳቱ መስፋፋት ግን ያሰጋል ሲሉ ገልጸዉታል። በፓርኩ የእሳት አደጋ በተደጋጋሚ የሚከሰት ሲሆን ለከሰል ምርት ሲባል ከሚነሳዉ እሳት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ይገለጻል። ፓርኩ በአመት መጠናቀቂያ ወራት ላይ ከከሰል ምርት ጋር በተያያዘ የተለየ ቁጥጥርም ያደርጋል። አሁን ያጋጠመዉ የእሳት አደጋም ከቦታ ቦታ እየተስፋፋ አምባራስ ቀበሌ ላይ መድረሱን ባለሙያዉ ለብስራት ተናግረዋል። እስካሁን በእሳት አደጋዉ የደረሰዉ ጉዳት አለመታወቁንም ባለሙያዉ አክለዉ ተናግረዋል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 26😢 18😱 3🕊 2 1👏 1🙏 1
አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 ማራቶንን አሸነፈ አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 የማራቶን ውድድርን 2 ሠዓት ከ6 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት በበላይነት አጠናቀቀ፡፡ በተመሳሳይ በለንደን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡ እንዲሁም አትሌት ትዕግስት አሰፋ በለንደን የተካሄደውን የሴቶች ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ በለንደን ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኬንያውያን አትሌቶች ሲያሸንፉ በቪዬና በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ውድድርም ኬንያውያን አትሌቶች 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 50 5🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም የዳጉ ጆርናል ቤተሰቦች.... ቻናላችንን ምርጫችሁ ስላደረጋችሁ እያመሰገንን ተከታዮቻችንን ተሸላሚ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን በየሳምንቱ እናቀርባለን። ለጥያቄዎቹ ትክክለኛዉን መልስ ለምታስቀምጡ እና ለምትመረጡ 3 ተከታዮቻችን የ 100 ብር የሞባይል ካርድ ሽልማት አዘጋጅተናል። አሸናፊዎች ጥያቄ በቀረበበት መልዕክት በሚቀመጠዉ የአስተያየት መስጫ ላይ መልሶቻችሁን ማስቀመጥ የምትችሉ ሲሆን ትክክለኛዉን መልስ ያስቀመጡ አሸናፊዎችን ካለምንም መስፈርት የምንመርጥ መሆኑን እናሳዉቃለን። የዛሬዉ ጥያቄያችን የሚሆነዉ በመላዉ አለም በየእለቱ በተደጋጋሚ የሚጠራዉ ቃል ምንድነዉ? የሚል ሲሆን መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ አስቀምጡልን እኛ ካለመስፈርት እንመርጥና አሸናፊውን እናሳዉቃለን። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 31 7🔥 5👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም የዳጉ ጆርናል ቤተሰቦች.... ቻናላችንን ምርጫችሁ ስላደረጋችሁ እያመሰገንን ተከታዮቻችንን ተሸላሚ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን በየሳምንቱ እናቀርባለን። ለጥያቄዎቹ ትክክለኛዉን መልስ ለምታስቀምጡ እና ለምትመረጡ 3 ተከታዮቻችን የ 100 ብር የሞባይል ካርድ ሽልማት አዘጋጅተናል። አሸናፊዎች ጥያቄ በቀረበበት መልዕክት በሚቀመጠዉ የአስተያየት መስጫ ላይ መልሶቻችሁን ማስቀመጥ የምትችሉ ሲሆን ትክክለኛዉን መልስ ያስቀመጡ አሸናፊዎችን ካለምንም መስፈርት የምንመርጥ መሆኑን እናሳዉቃለን። የዛሬዉ ጥያቄያችን የሚሆነዉ በመላዉ አለም በየእለቱ በተደጋጋሚ የሚጠራዉ ቃል ምንድነዉ? የሚል ሲሆን መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ አስቀምጡልን እኛ ካለመስፈርት እንመርጥና አሸናፊውን እናሳዉቃለን። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
ቀሲስ በላይ መኮንን ከሰሞኑ "ተሳትፈዉበታል" በተባለው የማጭበርበር ድርጊት የተነሳ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተሰማ 👉🏼 ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በሀሰተኛ ሰነድ ልጭበረበር ነበር ያለ ሲሆን "ታማኝ" በተባሉ ሰዎች የተፈጸመው ሙከራ ወደፊት "በባለስልጣናት ላለመሞከሩ ማረጋገጫ ስለሌለኝ ነዉም" ብሏል ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል መባላቸውን ዳጉ ጆርናል ተከታታይ መረጃዎችን አድርሷል። ይህንኑ ተከትሎ ቀሲስ በላይ የተጠረጠሩበት ድርጊት መነጋገሪያ ሆኖ የቆየ ሲሆን ዘ ሪፖርተር ደግሞ አዲስ መረጃ አጋርቷል። ቀሲስ በላይ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከህብረቱ የሂሳብ ቁጥር ለግንባታ እና ሌሎች ስራዎች ክፍያ በሚል 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ስማቸዉ ያልተጠቀሰ የዘ ሪፖርተር ምንጭ ታድያ ይህንን ድርጊት ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተናግረዋል። ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በተጭበረበረ ሰነድ ከባንክ ሂሳቡ ሊወጣ የነበረ ገንዘብን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ያስታወቀ ቢሆንም "እምነትና እዉቅና" ባላቸዉ ሰዎች የተፈጸመዉ ተግባር ወደፊት በባለስልጣናት ለላመሞከሩ መተማመኛ የለኝም በማለቱ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ያለዉ ቅርንጫፉ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የተከፈተ ሲሆን በዋነኛነት የአፍሪካ ሒሳቦችን በተለይ ለማስተዳደር ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሪ ክምችት ያላቸዉ አካውንቶችን በማካተት ቁጥጥር ያደርጋል። ቀሲስ በላይ በወቅቱ ሀሰተኛ የህብረቱ ማህተም ያረፈባቸዉን ወረቀቶች በመያዝ ለግባታ እና የማሽነሪዎች አቅርቦት በሚል ክፍያዉን መጠየቃቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። ክፍያዉ ከመፈጸሙ በፊት ወደ ህብረቱ የስልክ ጥሪ ያደረጉት የባንኩ ሰራኞች የክፍያዉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሲሞክሩ የህብረቱ የፋይናንስ ክፍል የማያዉቀዉ መሆኑን እና ክፍያዉ እንዲታገድ ህብረቱ መጠየቁ መረጃዉ ይደርሳቸዋል። ህብረቱ ይህንን ተከትሎም ግለሰቡ እንዲያዙለት ጠይቆ ቀሲስ በላይ በህብረቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ በፌዴራል ፖሊስ ተላልፈዉ መሰጠታቸዉን ዳጉ ጆርናል መዘገቡ ይታወሳል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፋይናንሺያል አስተዳደር ዲቪዥን ኃላፊ ማዳሊስቶ ሙኡሶ ሎሌም ወዲያውኑ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ክፍል ደብዳቤ ጽፈዋል ብሏል ዘገባዉ። ኃላፊዉ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ከአፍሪካ ህብረት ሒሳብ ወደ አራት ግለሰቦች ሒሳብ እንዲዘዋወር የጠየቁ ሰነዶች ሁሉም ፎርጂድ ናቸው ብለዋል በጻፉት ደብዳቤ። ከዚህ ክስተት በኋላ የህብረቱ እና የባንኩ  ሰራተኞች ለፖሊስ ቃላቸዉን መስጠታቸው በዘገባዉ ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ለዜና ምንጩ ከሰጡት ቃል ዳጉ ጆርናል እንደተመለከተው "በመሠረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሊሰጥ አይችልም ። ለማጭበርበር የሞከረዉም ግለሰብ መጥቶ መጠኑን በጥሬ ገንዘብ ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር ማለታቸዉን ነዉ። አክለዉም " ግለሰቡ እዚህ አገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም እንኳ የትም ሊደርስ አይችልም።  አጭበርባሪዎች በየቀኑ ወደ ባንካችን ይመጣሉ።  ባንክ ስለምንሰራ የተለመደ ነው።  እኛ ግን ሁልጊዜ ከመሳካታቸው በፊት እናጣራለን።  ለፍርድም እየወሰድናቸው ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።  ያንንን እያደረግን ነው።  የአፍሪካ ህብረትም እስካሁን ድረስ ቀጥተኛ ቅሬታ አላቀረበብንም" ሲሉ አቶ አቤ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል። "ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው" ያሉት ስማቸው ያልተጠቀሱት የዜና ወኪሉ የአፍሪካ ህብረት ምንጭ" አሁን ማጭበርበሩ በተከበሩ ሰዎች እየተሞከረ ስለሆነ ተጨንቀናል" ብለዋል። ይህ ድርጊት  "ባለስልጣናት አንድ ቀን ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸዉ ምንም አይነት ዋስትና የለንም" ያሉም ሲሆን  "እምነት እያጣን ነው" ብለዋል። ባለስልጣኑ አክለዉም በዚህ የተነሳ "ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ(የዉጪ ምንዛሪ ) ለመያዝ ወስነናል ፤ የድርጅቱን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ውጭ ማቆየት እንድናስብ ያስገድደናል" ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣን መናገራቸውን ዳጉ ጆርና ከዘገባው ተመልክቷል። Via The Reporter #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 65😁 48😢 15 9🤔 4😱 2🔥 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በ1500 ሜትር ታሪክ 3ኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አትሌት ጉድፍ ፀጋዬ አሸነፈች አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በዋንዳ ዳይመንድ ሊግ 3 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ በ1500 ሜትር ውድድር አሸንፋለች። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 83 15🥰 4👏 4🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጲያዊቷ አትሌት ከ10 ዓመታት በፊት ያሸነፈችበትን የቦስተን ማራቶን 100 ሺ ዶላር እስካሁን ድረስ አልተሰጣትም የ36 ዓመቷ ኢትዮጲያዊቷ አትሌት ብዙነሽ ዲባ የረጅም ርቀት አትሌት ስትሆን እኤአ በ2014 በቦስተን ማራቶን ብታሸንፍም በአሸናፊነቷ ሊሰጣት ይገባ የነበረው 100 ሺ ዶላር እስካሁን እንዳልተሰጣት ከሲቢኤስኒውስ ኒውዮርክ ጋር ባደረገችው ቆይታ ተናግራለች። በወቅቱ በውድድሩ ብዙነሽ ዲባ ሁለተኛ ወጥታ የነበረ ቢሆንም አንደኛ የወጣችው አትሌት ውድድሩ ከተደረገ ከሁለት ዓመት በኃላ በ2016 በዶፒንግ አበረታች መድኃኒት በመውሰድ ያገኘችው ውጤት ተሰርዞ አንደኝነቱን አትሌት ብዙነሽ ዲባ አግኝታለች። ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገችው አትሌቷ የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ዳግም ወደ ልምምድ መመለሷን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። አትሌቷ በካሊፎርኒያ ዓለም አቀፍ ማራቶን፣ በሳንዲያጎ ማራቶን፣ በሎስ አንጀለስ ማራቶን፣ በግራንድ ማ ማራቶን፣ በቦስተን ማራቶን እና በቲዊን ሲቲ ታ ማራቶን አሸናፊ ነች። በኒውዮርክ ሲቲ ማራቶን ሶስት ጊዜ ምርጥ አስር ሆና አጠናቃለች። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
🤔 43👍 21 4🤬 4
Photo unavailableShow in Telegram
ናይጄሪያዊው ግለሰብ ቼዝን ለረጅም ሰዓታት በመጫወት ክብረ ወስኑን   ለመስበር እየሞከረ ይገኛል በኒውዮርክ ታዋቂው የታይምስ ስኩዌር ስር ናይጄሪያዊው የቼዝ ማስተር ቱንዴ ኦናኮያ ረጅሙን የቼዝ ማራቶን ክብረ ወሰን ለመስበር ትልቁን ፈተና እየሞከረ ይገኛል። ለተከታታይ 58 ሰአታት ለመጫወት እና 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለበጎ አድራጎት ለማሰባሰብ አላማ አለው። የሚሰበሰበው ገንዘብ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ህጻናት የቼዝ ትምህርት ለመስጠት ይውላል። የናይጄሪያውን አፍሮቤያትስ ኮከብ ድምፃዊ ዴቪዶን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች የቼዝ ማስተሩን ሲያበረታቱ ታይተዋል። በኒውዮርክ የሚገኙ የናይጄሪያ ማህበረሰብ ለአገራቸው ሰው ድጋፍ በማድረግ ኦናኮያ ሙዚቃ በማቅረብ እና ተወዳጅ የሆነውን የጆሎፍ ሩዝን ጨምሮ የናይጄሪያን ምግቦችን በማቅረብ ድጋፍ አድርገዋል። በናይጄሪያ በተመሳሳይ ለኦናኮያ ድጋፋቸውን በርካቶች እየሰጡ ሲሆን ክብረወስኑን እንዲሰብር እያበረታቱ ይገኛል። የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ በኤክስ ላይ ባጋሩት መልዕክት " ኦናኮያ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ለሚገኙ ናይጄሪያውያን የልህቀት እና የጽናት ምልክት ነው፤ ሂዱ፣ ታሪክ ሰሩ እና ስማችንን በወርቅ ፃፉ።" ሲሉ ሀሳባቸውን አስፍረዋል።የሌጎስ ግዛት አስተዳዳሪ ባባጂዴ ሳንዎ-ኦሉ ለኦናኮያ እንደተናገሩት ሌጎስ ድጋፏን እየሰጠችህ ነው ብለዋል። ኦናኮያ ለ39 ሰዓታት መጫወት የቻለ ሲሆን ከ42,000 ዶላር በላይ እስካሁን ሰብስቧል። ለ58 ሰዓታት ለመጫወት እና ከዙህ ቀደም እኤአ በ2018 በ56 ሰአት ከዘጠኝ ደቂቃ ከ37 ሰከንድ የተመዘገበውን የኖርዌጂያዊውያኑን የሁለት ግለሰቦች ሃልቫርድ ሃግ ፍላቴቦ እና ስጁር ፈርኪንግስታድ ክብረወስን ለመስበር እየተጋ ይገኛል። የ29 አመቱ በሌጎስ የተወለደ ሲሆን ከአስከፊ ድህነት ራሱን ለማውጣት ቼዝ ውድድር እንደረዳው ይመሰክራል። መንግሥታዊ ባልሆነው ቼስ ኢን ስሉምስ አፍሪካ ድርጅቱ ከድሃ ማህበረሰብ የመጡ ልጆችን በማስተማር እና በትምህርታቸው በመደገፍ ይረዷቸዋል።ኦናኮያ በተጨማሪም የዩናይትድ ስቴትስ ለትርፍ ያልተቋቋመ "The Gift of Chess" የቦርድ አባል ሲሆን ይህም በቼዝ ህይወትን ለመለወጥ የሚሰራ እና በ2030 አንድ ሚሊዮን የቼዝ ሰዎችን ለማሰባሰብ በማቀድ እየሰራ ይገኛል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 20 3
Photo unavailableShow in Telegram
ኢራን አፋጣኝ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እቅድ የላትም ሲሉ አንድ የኢራን ባለስልጣን ተናገሩ አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት "ኢራን በእስራኤል ላይ አፋጣኝ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እቅድ የላትም" ሲሉ እስራኤል በኢራን ኢስፋሃን ከተማ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተከትሎ ተናግረዋል፡፡ ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ጥቃቱ ከእስራኤል የመጣ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን ቢናገሩም እስራኤል ኃላፊነቱን ለመዉሰድ ወዲያዉ መግለጫ አላወጣችም ነበር።አንድ ኢራናዊ ተንታኝ ለኢራን መንግስት ቲቪ እንደተናገሩት "በኢስፋሃን በአየር መከላከያ የተተኮሱ ሚኒ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ ኢራን ውስጥ ሰርጎ ገቦች ገብተዋል" በማለት እስራኤል ጥቃቱን ፈጽማለች የሚለውን ዘገባ አሳንሰዉ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል እስራኤል በኢራን ላይ የበቀል ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ በእስራኤል ለሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞቿ እና ቤተሰቦቻቸው “ከከፍተኛ ጥንቃቄ የተነሳ” የጉዞ ገድብ ጥላለች።ኤምባሲው ሰራተኞቹ ከታላቋ ቴል አቪቭ ክልል ውጭ  ወደ ሄርዝሊያ ፣ ኔታንያ እና ዩሁዳን ጨምሮ ወደ እየሩሳሌም እና ቢየር ሼቫ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል፡፡ በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 17 5
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ በተገነቡ ማዕከላት ከመደበኛው ገበያ የጤፍ ዋጋ ላይ የ3 ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው ተገለፀ በአዲስ አበባ ከተማ ተገንብተው አምራችን ከሸማቾች የሚያገናኙ ሶስት ማዕከላት ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው አሁን ላይ በዋነኛነት የገበያ ማዕከላት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን የተናገሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እንደተገነቡ ተናግረዋል። ከተማ አስተዳደሩ በእነዚህ ማዕከላት አምራቾችን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ ለሸማቾች ከማሳ የተሰበሰቡ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ እያቀረበ ነው ብለዋል።እነዚህ ማዕከላት በሸማቹ እና በአምራቹ መሀል የነበረውን ህገ ወጥ ደላላን መስበር የቻለ ነው። ከዋጋም አኳያ ከእሁድ ገበያ አንፃር የተሻሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።ምርቶች በበቂ ሁኔታ በገበያ ማዕከላት ቢገቡም ህብረተሰቡ ስለ ማዕከላቱ በቂ ግንዛቤ ስሌለው የሚበላሹ  ምርቶች አሉ በተለይ ደግሞ  የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ብልሽት እንደሚገጥማቸው ተናግረዋል። ሸማቹ ወደ እነዚህ ማዕከላት በመምጣት ሁሉንም ምርቶች በአንድ እንዲሁም በቅናሽ ዋጋ ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።ከመደበኛ ገበያዎች የጤፍ ዋጋ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የ3ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው አንስተዋል። እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችም ከእሁድ ገበያው ቅናሽ እንዳለውም አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል። ማዕከላቱ በኮልፌ ፣በአቃቂ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ይገኛሉ ተብሏል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 33👎 6 1😁 1
በህንድ በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ምርጫ የምርጫ አስፈጻሚዎች ወደ ጣቢያዎች ለመጓዝ ሄሊኮፕተር፣ ዝሆን፣ በቅሎ እና ጀልባን መጠቀማቸዉ ተሰማ ህንዳውያን በሰባት ደረጃ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በመጀመሪያ ደረጃ በዛሬዉ እለት ድምጽ እየሰጡ ዉለዋል። ወደ 167 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች በ187 ሺ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ ለመስጠት ብቁ ናቸው ተብሏል። ከእነዚህ መራጮች መካከል 84 ሚሊዮን ወንዶች ሲሆኑ፣ 82 ሚሊዮን ደግሞ ሴቶች ናቸዉ፡፡የ1,625 እጩዎች እጣ ፈንታ ዛሬ ይወሰናል። የሴቶች እጩዎች ከዚህ ቁጥር ውስጥ እጅግ ያነሰ ሲሆን 134 ያህል ብቻ ናቸዉ፡፡ወደ 1.8 ሚሊዮን የሚሆኑ የምርጫ አስፈፃሚዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ይቆጣጠራሉ፡፡ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ሠራተኞችን ለማጓጓዝ 41 ሄሊኮፕተሮችን፣ 84 ልዩ ባቡሮችን እና ወደ 100 ሺ የሚጠጉ ተሽከርካሪዎችን አገልግሎት ላይ ዉለዋል፡፡ የሕንድ ምርጫ ኮሚሽን “የሁሉም መራጮች ድምጽ ይቆጠራሉ” ይህ መፈክር ብቻ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።ባለሥልጣናቱ ለመድረስ አስቸጋሪ ወደሆኑት ምርጫ ጣቢያዎች ለመድረስ ሄሊኮፕተሮችን፣ ጀልባዎችን፣ ፈረሶችን፣ ዝሆኖችን እና በቅሎዎችን ተጠቅመናል ብለዋል፡፡እ.ኤ.አ በ 2019 አጠቃላይ ምርጫ አምስት የምርጫ አስፈፃሚዎች በአውቶብስ እና በእግር ለሁለት ቀናት በመጓዝ የ39 ዓመቷ ሴት በሰሜን ምስራቅ አሩናቻል ፕራዴሽ ግዛት ድምጽ መስጠት ችላ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የተቃዋሚ መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ መንግስት ተቃዋሚዎቹን ለመምታት እና ፍትሃዊ ምርጫ የመካሄድ እድሎችን ለመቀነስ የፌደራል ኤጀንሲዎችን በማስታጠቅ ከሰዋል።ምርጫው ከመጀመሩ ሳምንታት ቀደም ብሎ ባለስልጣናት የዴሊ ዋና ሚኒስትር አርቪንድ ኬጅሪዋልን በሙስና ክስ በቁጥጥር ስር አውለዋል ብለዋል። በምርጫዉ ናሬንድራ ሞዲ ሰፊ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 21 3😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል በኢራን እስፋሃን ከተማ በፈፀመችው ጥቃት የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ጉዳይ አለመድረሱን ቴህራን አስታወቀች የኢራን አየር መከላከያ ሶስት ትናንሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በማዕከላዊ እስፋሃን ከተማ ላይ ከአየር እንዳወረደ አስታውቋል። የኢራን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ይህንን የዘገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ብሮድካስተሮች ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናትን ጠቅሰው ከሰአታት በፊትላ የእስራኤል ሚሳኤሎች በኢራን ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ ነው።የኢራን መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የአየር መከላከያ ስርዓቱ በንቃት ላይ መሆኑን በመግለፅ ዛሬ ረፋድ ድረስ ዋና ከተማይቱን ቴህራን እና ኢስፋሃንን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በረራዎች መቋረጣቸውን ዘግቧል። አደጋው ከደረሰ ከአራት ሰአት ተኩል በኋላ የአየር ክልል የተከፈተ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። የኢስፋሃን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን ሁለተኛ ብርጋዴር ጄኔራል ሲያቫሽ ሚሃንዱስት ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የአየር መከላከያ ስርዓቶች አጠራጣሪ ነገር ማሳየታቸውን ተከትሎ የተሰነዘረው ጥቃት ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም ብለዋል። ቀደም ሲል ኤቢሲ ኒውስ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው እስራኤል ኢራን ውስጥ በሚገኝ ቦታ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መሰንዘሯን አስታውቋል። የአውሮፓ ህብረት ዋና ፀሀፊ ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ፈፅማለች የሚለውን ዘገባ ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ውጥረት እንዳይከሰት ለመከላከል ጠይቀዋል።የቻይና መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን እንደተናገሩት ቤጂንግ “አግባብነት ያላቸውን ሪፖርቶች” አስተውላለች በማለት ውጥረቱን የበለጠ የሚያባብሱ ማንኛውንም እርምጃዎችን ትቃወማለች ሲሉ ገልፀዋል። የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢራብ ኢስፋሃን ከተማ ላይ የተፈፀመውን "የእስራኤል ጥቃት" በማውገዝ መግለጫ አውጥቷል። ኦማን "በተጨማሪም የእስራኤልን ተደጋጋሚ ወታደራዊ ጥቃቶችን እንደምታወግዝ አስታውቃለች። የባህረ ሰላጤ ሀገር የሆነችው ኦማብ በኢራን እና በምዕራባውያን ሀገራት መካከል ለረዥም ጊዜ የሸምጋይነት ሚና ስትወጣ ቆይታለች። የኢራን መንግስት የዜና አውታር ፕረስ ቲቪ እንደዘገበው በኢስፋሃን ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ምንም አይነት ፍንዳታ ወይም ጉዳት በጥቃቱ አልደረሰም ብሏል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 24👏 6🔥 2👎 1🕊 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.