የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
Kanalga Telegram’da o‘tish
5 831
Obunachilar
+224 soatlar
+87 kun
+930 kun
Postlar arxiv
+1
የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን ጎብኝቼ ነበር። ይህ ተቋም ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የልማት ርዕይ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አለው።
ኢትዮጵያ እጅግ ከፍተኛ በሆነ እምቅ አቅሟ እና በተትረፈረፈ ተፈጥሯዊ ሀብቷ ለረጅም ጊዜ ትታወቃለች። አዲሱ ምዕራፍ ደግሞ እነዚህን ሀብቶች ወደ ተጨባጭ ልማት፣ የቴክኖሎጂ እድገት እና ወደ ጋራ ብልጽግና መለወጥ ላይ ያተኩራል።
አስተማማኝና ዘላቂ የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ፣ ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለዲጂታል መሠረተ ልማትና ለአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ማዕከላዊ ሚና አለው። የኒውክሊየር ቴክኖሎጂ ደግሞ የኃይል ዋስትናን በማጠናከር እየገሰገሰ ያለውን ፍላጎት ለማሟላት ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ፤ ከኃይል ምርት ባለፈ በጤና፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ለሀገራዊ ልማትና ለቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ መሠረታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ለብሔራዊ የኒውክሊየር ኃይል ፕሮግራም አስፈላጊ የሆኑትን ተቋማዊ እና ቴክኒካዊ መሠረቶች በመጣል ይህንን ርዕይ ለማሳካት ስትራቴጂካዊ ሚና አለው። ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት፣ ሳይንሳዊ ምርምርን ማስፋፋት እና የተቋሙን ዕውቀት ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ወሳኝ ተግባራት ናቸው። ይህም ብሔራዊ አቅምንና ልዩ ሙያዊ ብቃትን በማዳበር የኒውክሊየር ኃይል ልማት ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና ዘላቂ በሆነ መንገድ በኃላፊነት ስሜት እንዲከወን ያደርጋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን)፤ የነፃነት፣ የሉዓላዊነት እና የወዳጅነት ቀን!
Guyyaa Mashujaa (Goototaa), guyyaa bilisummaa, kan birmadummaafi guyyaa michummaa!
Mashujaa Day, the day of freedom, sovereignty, and partnership!
የነገ አገር ተረካቢ የሆኑትን ሕፃናት መንከባከብ ለአገር እድገት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቆመ
( ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም )
የ90 ቀን እቅድን መሠረት በማድረግ በአራዳ ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተዘጋጀው የሕፃናት ማቆያ ክፍሎች ዛሬ ተመረቁ
ለሕፃናቱ ማረፊያ የሆኑትን ክፍሎች መርቀው የከፈቱት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የምዘና ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አለልኝ ወንዴ ባስተላለፍት መልዕክት እንደገለጹት ለአገር እድገት ትልቁ ሚና ያላቸው ሕፃናት በመሆናቸው በከተማችን በአሁኑ ሰዓት ለሕፃናት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ብዛት ያላቸው መጫዎቻዎች እና ማረፊያ በማዘጋጀት በርካታ ተግባራት እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጽዋል፡፡
በዚህም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከ90 ቀን እቅድ ውስጥ የሆነውን ለቅርንጫፍ ሠራተኞች ልጆች ማረፊያ የሚሆን በግብአት እና በአደረጃጀት የተሞላ ክፍሎችን ማዘጋጀቱ የሚያስደስት ስራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወደፊት አገር የሚረከቡ እና ለአገር እድገት የሚሰሩ ትውልድ የምናፈራው ሕፃናት የሚያስፈልጋቸውን ነገር ከወዲሁ በማሞላት እና ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአራዳና ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እጅጋየሁ አድማሱ ባስተላለፍት መልዕክት እንደገለጹት ለሠራተኛው ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና ሕፃናት ልጆች ያሏቸው ሠራተኞች ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ ለማስቻል የሕፃናት ማቆያ መዘጋጀቱን ገልጽዋል፡፡
ክፍሎቹንም ለማዘጋጀት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ማኔጅመንት እና ሠራተኞች ቢሮዎችን ሽግሽግ በማድረግ እንዲሁም ለክፍሉ የሚያስፈልጉ ግብአቶች በተሟላ መልኩ ተሞልተው ስራ እንዲጀምር መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በማዕከል ያሉ አመራሮች እና ሠራተኞችን ለስራው መሳካት ላደረጉት ጥራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በምረቃ መርሐግብሩ ላይ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮች እና የቅርንጫፍ ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
በመጀመሪያ ሩብ አመት የተገኘውን አፈፃፀም በማጠናከር በውጤት የሚለካ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ ፡፡
( ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም )
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት መድረክ ላይ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጥራት ዘርፍ ኃላፊ እና ምከትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ ባስተላለፍት መልዕክት እንደገለጹት
የ1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጸጸም በውስን የሰው ኃይል ተቀናጅቶ በመስራት ውጤታማ የተሆነበት አግባብ መኖሩን የጠቀሱ ሲሆን አገልግሎት አሰጣጣችን የከተማውን አቅጣጫ መሠረት በማድረግ ከቁጥር ባለፈ በተገልጋይ ላይ ያመጣው የአገልግሎት እርካታ ውጤታማነት ማየት እንደሚገባ ገልጽዋል፡፡
የ1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ስንለካ የነበሩብንን ክፍተቶች በማረም እና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጥራት ያለው አገልግሎትን መስጠት እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን መልካም አስተዳደርን በማስፈን እና ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ በትብብር እና በአንድነት በአዲስ መንፈስ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የምዘና ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አለልኝ ወንዴ በበኩላቸው ባስተላለፍት መልዕክት እንደገለጹት
በየወቅቱ በየደረጃው የስራ አፈጻጸም መገምገም ለምንሰራው ስራዎች ውጤታማነት ወሳኝ በመሆኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም እርስ በእርስ ለመማማር እና ተሞክሮ ለመውሰድ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በዘጠና እቅድ ውስጥ የደም ልገሳ የተደረገ ቢሆንም ከእቅድ አንፃር የሚጎለውን ዩኒት ለማሳካት በቀጣይ የደም ልገሳ የሚካሄድ ሲሆን ለዚህም ተግባር ስኬት በቅንጅት መንፈስ በትኩረት መስራት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል በሌላም በኩል በምዘና ዘርፍ የቭርዥን ዝግጅት የማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን ጠቅሰው ለምዘናው ዘርፍ ውጤታማነትም 120 መዛኞችን የሰለጠኑበት አግባብ መኖሩን ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት አቶ አሸናፊ መለሰ የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃጸም ሪፖርት እንዲሁም በቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የአቃቂ ቃሊቲ እና የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የእቅድ አፈጻጸማቸው የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ቀርቧ ውይይት እና አስተያየት ተሰጥቶበታል ፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የበላይ አመራሮች ፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኬንያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ልማት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖች ክብር በሚሰጥበት የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ በዓል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት ለመታደም ኤልዶሬት፣ ኬንያ ገብተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም ውጤታማ እንደነበረ ተገለፀ
(9/2/2019)
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የበላይ አመራሮች እና ሠራተኞች በተገኙበት የመጀመሪያ ሩብ አመት የተለያዩ የእቅድ አፈጻጸሞች በተገመገሙበት ወቅት
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት አቶ አሸናፊ መለሰ የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃጸም ሪፖርት እና የ90 ቀን እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት
በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለማከናወን በእቅድ ከተያዙት ተግባራት መካከል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተከናወነ በመሆኑ አፈፃፀሙም 97.08% መሆኑን ገልፅዋል፡፡
በዚህም ለ155 የትምህርትና ስልጠና ተቋማት አዲስ እውቅና እውቅና ፈቃድ መስጠት መቻሉ፣ በ136 የትምህርት ስልጠና ተቋማት ላይ ድንገተኛ ኢንስፔክሽን፣ በ30 የኢንዱስትሪ ማዕከላት ላይ መዛኝ ማፍራት መቻሉ፣ የግል ትምህርት ተቋማትን በማስተባበር ከ20 ሚሊዬን ብር በላይ በማሰባሰብ ለአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግ መቻሉ፣ በመትከል ማንሰራራት መርህ 4,120 የተለያዩ ችግኞችን መትከል መቻሉ፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ መርህን የጋራ በማድረግ ከ2,455,000 ብር በላይ በማሰባሰብ 400 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት ስራዎች መሰራታቸውን አሳውቀዋል፡፡
የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምላኩ ተበጀ የለውጥ ስራዎች አፈፃጸም ድጋፍና ክትትል ግኝቶች እና የ2019 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት ወርቃማ ሰኞ አተገባበር አቅርበዋል
የወርቃማ ሰኞ መርሐግብር ሳይቆራረጥ በአግባቡ መካሄዱ እና መረጃዎች በአግባቡ በምስል እና በቃለ ጉባኤ የተደራጀበት አግባቡ መኖሩን ጠቁመው አቅራቢዎች ከአመራር ፣ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች መሆናቸው ከአመራሩ ጋር የመቀራረብ መንፈስን የፈጠረ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በሂደቱ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዩች አብራርተዋል፡፡
በቀረቡት ሰነዶች ላይም ሠራተኛው ሃሳብ እና አስተያየት በማንሳት ውይይት ከተደረገ በኃላ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የበላይ አመራሮች ባስተላለፍት መልዕክት እንደገለፁት
የ1ኛ ሩብ አመት አመራሩ እና ሠራተኛው በርብርብ ሥራዎችን በመስራት ከቁጥር ባለፈ በጥራት ስኬት የተመዘገበበት በመሆኑ ይህን በማስቀጠል የሚቀሩ ስራዎችን ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር መስራት የሚገባ ሲሆን በ1ኛ ሩብ አመት በሁሉም የስራ ክፍሎች በድጋፍና ክትትል የታየበት አግባብ በመኖሩ የተሰጡትን ግብረ መልሶች በመያዝ ያሉብንን ክፍተቶች ማረም እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡
እንዲሁም ለተገልጋዩ ምን ያህል የተጨበጠ ለውጥ አመጣን የሚለውን በየግዜው እየገመገምን መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በዕለቱ በወርቃማ ሰኞ አቅራቢ ለነበሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
ቀዳማይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አብ ወድዓዊ ኹነታት ሀገር አድሂቦም በቋንቋ ትግርኛ ምስ ኮርፖሬሽን ብሮድካስት ኢትዮጵያ (EBC) ዝገበርዎ ፃንሒት ሙሉእ ትሕዝቶ ሎሚ ምሸት ስዓት 2:30 ክቀርብ እዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ጋር በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በትግርኛ ቋንቋ ያደረጉትን ቆይታ ዛሬ ምሽት 2:30 ይከታተሉ።
What we have seen in Addis Ababa is more than what we have expected. We have seen that we have to think of how to adopt those experiances to Accra.
-Michael Kpakpo Allotey : Mayor of Accra
እንደ ሀገር የሚጠበቀውን ተቋማዊ የግልጽነት፣ ተጠያቂነትና የመልካም አስተዳደር ስርዓት አልፎም የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የእቅም ማጎልበቻ ወቅቱን የሚመስሉ ስልጠናዎች አስፈላጊ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
(ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የውስጥ የኦዲት ዳይሬክቶሬት በግዥ፣በንብረት፣ፋይናንስ፣እቅድ እንዲሁም ኦዲት አስራር ስራዓት ዙሪያ ላይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ፡፡
የባለስልጣኑ አማካሪ አቶ ብርሀኑ ተሾመ በመርኃ-ግብሩ ላይ መክፈቻ ንግግራቸው ባስተላለፉት መልዕክት ተቋማዊ የግልጽነት፣ ተጠያቂነትና የመልካም አስተዳደር ስርዓት ለማሰፈን እንዲሁም ለስራዎች ወጥነት ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን ሙያዊ ስነምግባር በተሞላበት ወደ ተግባር መቀየር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ትዕግስት ጌታነህ የባለስልጣኑ የውስጥ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለጹት የስልጠናው አላማ በተለይም ከሪፎርም በኃላ አዳዲስ ባለሙያዎች ወደ የዳይሬክቶሬቱ የገቡበት አግባብ በመኖሩ አቅማቸውን መገንባት የሚከወኑት ስራዎች ወጥነት እንዲኖራቸው የአሰራር ስራዓት ልዩነት እንዳይፈጠር ማለትም የተሻሻሉ መመሪያዎች ደንቦች ግድፈት እንዳይኖር የተሻሻሉት ምንድን ናቸው የነበሩትስ ምን ይላሉ የሚለውን ግልጽነት የመፍጠርና የአሰራር ስርዓት ወጥነት ክፍተት እንዳይፈጠር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑን ገልጸው
በተጨማሪም ከብልሹ አሰራር ከግኝት አንጻር እንዴት መሰራት እንዳለበት የሚወገዱ ንብረቶች እንዴት መወገድ እንዳለበት የውስጥ ቁጥጥር እንዴት መሰራት አለበት የሚሉትንና ሌሎች መሰል አስፈላጊ ነገሮች በስልጠናው በዝርዝር የተካተቱ መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡በስልጠናው የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናነስ ቢሮ የተለያዩ ባለሙያዎች ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም የ9ኙ ቅ/ጽ/ቤትና የማዕከል ሰራተኞች መሆናቸው ተውቋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ እና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የኢፌዴሪ መንግሥት የትግራይ ክልልን የሚያጸና ውሳኔ ወስኗል።
እንደሚታወቀው፣ በትግራይ ክልል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት ለመፍታት የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት በሕወሐት ዕንቅፋትነት የተነሣ ሳይሳካ ቀርቷል።
ሰላምን ያልፈለገው የሕወሐት አመራር ለአራተኛ ጊዜ የጀመረው አውዳሚ ጦርነት ለአራተኛ ጊዜ በሕወሐት ሽንፈት ተጠናቋል። የትግራይ ሕዝብ የራቀውን ሰላም እንዲጎናጸፍ፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ እንዲረጋገጥ፣ እንዲሁም ላለፉት በርካታ ዓመታት ያላገኛቸውን የልማት ትሩፋቶች ለማጣጣም እንዲችል ከግጭት አዙሪት መውጣት አለበት።
ለዚህ ደግሞ በፌዴሬሽኑ ውስጥ የሚገባውን ቦታ አግኝቶ ሰላሙን ማስከበር፣ ትኩረቱን በልማት ላይ ማድረግና ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ጸንቶ መኖር አለበት። እነዚህን ሁኔታዎች ባጠረ ጊዜ ለማመቻቸት እንዲቻል የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መሠረት ተመሥርቷል፡፡
ይህ የትግራይ ክልል የፊዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ለሚቀጥሉት 6 ወራት ትግራይን የሚያስተዳድር ይሆናል። ዋና ተግባሩ፦
1. በትግራይ ክልል ውስጥ ተፈጥሮ ያለውን የሰላምና የመረጋጋት ችግር በፍጥነት በመፍታት የተረጋጋ ሁኔታን መፍጠር፣
2. የፈረሱ የመንግሥት መዋቅሮችን መልሶ በመዘርጋት ሕዝቡ የመደበኛ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ መፍጠር፤
3. በጦርነት ምክንያት የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን በመጠገንና ፈጥነው ወደ ሥራ እንዲገቡ በማድረግ በሀገር ደረጃ የሚታዩ የልማት ትሩፋቶች ትግራይ ውስጥም መስፋፋት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
4. የተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ወደየቀያቸው መመለስ፤
5. በክልሉ ውስጥ ተቋርጠው የነበሩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ ማድረግ፤
6. እንዲሁም የተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ ተፈጥሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ነጻና ግልጽ ምርጫ ተከናውኖ ትግራይ የፌዴሬሽኑ መደበኛ አካል የምትሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
7. ከፌዴራል የመከላከያ፣ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት እንዲሁም ከትግራይ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ከክልል እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈጠር፣ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በማስረከብ ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱና ተሐድሶ እንዲያደርጉ ሁኔታውን ማመቻቸት፣ የክልሉን የጸጥታ መዋቅር እንደ አዲስ የማዋቀር ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
8. ሰላም እንዲጸና ፣ የሕዝቡ ሥነ ልቡና እንዲስተካከልና ወደ ልማትና የመልሶ ግንባታ ሥራ ለመግባት የሚያስችለው ዝግጁነት እንዲኖረው ማድረግ፤
9. የሚዲያ ሥራዎችን የማስተባበር፤ በየደረጃው የሚደረጉ የሕዝብ መድረኮችን የማዘጋጀት፤
10. ለቀጣዩ ምርጫ ሰላማዊና አካታች እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት አለበት፡፡
የባለአደራ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው ሁሉም ተግባራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች፣ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት፣ የትግራይ ሕዝብን መሠረታዊ ጥቅሞች መሠረት ማድረግ አለበት። በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት እስከሚቋቋም ድረስ የክልሉን የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች ከማቅረብና ለቀጣይ ምርጫ አስቻይ ሁኔታዎችን ከመፍጠር በዘለለ ረዘም ያለ ስትራቴጂያዊ አንድምታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ አይንቀሳቀስም፡፡ ተግባሩንም ከፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫ እና መመሪያ መሠረት ያከናውናል።
የባለአደራ አስተዳደሩ ዋና አስፈጻሚዎች
1. አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ
2. ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ ወ/ሥላሴ - የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ
3. ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ - የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ
4. አቶ ረዳኢ ኃለፎም ወ/ሥላሴ - የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ
5. ዶክተር ሽሻይ አማረ - የመቐለ ከተማ ከንቲባ
በመሆን ተሹመዋል።
ለሚያከናውኗቸው ሁሉም እንቅስቃሴዎች የፌዴራል መንግሥቱ መመሪያ፣ አቅጣጫ፣ ድጋፍና ክትትል ይደረግላቸዋል።
+8
"አንችልም" ወይም "ጊዜ ይወስዳል" የሚሉ አሉታዊ አስተሳሰቦች የለወጠችው አዲስ አበባ
የከተማችን የኮሪደር ልማቱ፣ የፓርኮች ግንባታ እና የከተማዋ ውበት እድሳት በነዋሪው ዘንድ አዲስ የመተማመን የመንሰራራት ስሜት ፈጥሯል። አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ክብርና ምቾት በሚጠብቅ መልኩ በመገንባቷ፣ ነዋሪው በከተማው የመኩራትና የባለቤትነት ስሜቱ እንዲያንሰራራ አድርጎታል።
"አንችልም" ወይም "ጊዜ ይወስዳል" የሚሉ አሉታዊ አስተሳሰቦች ተስብረው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን አቅዶ በጥራት ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተግባር ያሳየችው አዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌትና የዜጎቿን የነገ ተስፋን በእጅጉ በማጠናከር ማንሰራራትን በተግብር እየገለጠች ነው፡:
