cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

Publicaciones publicitarias
3 269
Suscriptores
+324 horas
+367 días
+8230 días
Archivo de publicaciones
በተመሳሳይም ቀደም ባሉት ግዜያት በውጪ አቅም የሚጠናውን ጥናት በተመለከተ ጥናቱ የሚያተኩርባቸው ጉዳዩች እስከ መቼ መጠናት አለበት እና የጥናቱ አሠራር በተመለከተ ጥናቱን ለማስጀመር ከማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይት መደረጉ ታውቋል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
በውስጥ አቅም የተሰሩ ሁለት የጥናት ግኝቶች ላይ ውይይት ተደረገ፡፡ (ሰኔ 7/2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በትምህርት ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክተር የተዘጋጀውን ጥናት ለባለስልጣኑ የበላይ አመራሮች እና ከተጠናው ጥናት ጋር ተያያዥነት ካላቸው የስራ ክፍል ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህርት ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አንዋር ሙላት ጥናቶችን አስመልክቶ እንደገለፁት በ2016 ዓ.ም በውስጥ አቅም የተሰሩት ሁለት ረቂቅ የጥናት ግኝት መሆናቸውን ጠቅሰው ጥናቶቹ የሙያ ብቃት ምዘና ተመዛኞች ውጤት የማጣት ምክንያቶች በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ያለበት ደረጃ በሚሉ ርዕሶች ላይ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ የጥናቶቹም የመጀመሪያ ረቂቅ ላይ ውይይት በማድረግ ለጥናቱ ግብአት የሚሆኑ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን ጥናቱም የተሰጡትን አስተያየቶች መሰረት በማድረግ ተጠናቆ በቀጣይ ለባለድርሻ አካላት እንደሚቀርብ ገልጸዋል፡፡
Mostrar todo...
የውይይቱ ተሳታፊ የግል ትምህርት ቤት ባሀብቶችም ሆኑ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች ሜቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እያከናወነ የሚገኘውን የበጎ አድራጎት ተግባር መደገፍ የሚሰጠው የመንፈስ እርካታ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ማዕከሉን በቋሚነት ለመርዳት የአባልነት ፎርም በሙላትም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ምንጭ፡-ት/ቢሮ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
የግል ትምህርት ተቋማት ለሜቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ እንዲያደርጉ የማዕከሉ መስራች ወጣት ዶ/ር ቢኒያም በለጠ ጥሪ አቀረበ። (ሰኔ 7 /2016 ዓ.ም) የማዕከሉ መስራች ጥሪውን ያስተላለፈው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ከግል ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተገኝቶ ባለሀብቶቹ ወላጆችን ጨምሮ የትምህርት ቤት ማህበረሰቦቻቸውን አስተባብረው ለማዕከሉ ድጋፍ የሚያደርጉበትን ፎርም እንዲሞሉ በተደረገበት ወቅት ነው። ሜቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 28 ቅርንጫፎች ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን ከ7,500 በላይ የሚሆኑ አረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማንን ከወደቁበት በማንሳት እየረዳ እንደሚገኝ የማዕከሉ መስራች ቢኒያም በለጠ ጠቁሞ የማዕከሉ የቀን ወጪ 1.5 ሚሊዮን ብር አከባቢ መሆኑን እና ምንም አይነት ቋሚ ገቢ ሳይኖረው በደጋግ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እዚህ ደረጃ መድረሱን በመግለጽ የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች የተማሪዎችን እና ወላጆቻቸውን ጨምሮ መምህራንን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን አስተባብረው ለማዕከሉ በቋሚነት በየወሩ አቅም በፈቀደ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። ወጣት ዶ/ር ቢኒያም መልዕክቱን በመቀጠል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ ሌሎች የቢሮው እና የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮች ማዕከሉን ለመርዳት እያደረጉ ለሚገኘው አስተዋጽኦ በራሱና ድጋፍ በሚደረግላቸው ወገኖች ስም ምስጋና አቅርቦ ተማሪዎችና መምህራን ወደ ማዕከሉ በመምጣት የበጎ ፍቃድ ተግባራትን በማከናወን ወገኖቻቸውን እንዲያበረታቱም ጥሪ አቅርቧል።
Mostrar todo...
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም ትምህርት ተቋማት የ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ተማሪ ምዝገባ ከሰኔ 24 እስከ 30 እንዲሁም የአዲስ ተማሪ ምዝገባ ከጳጉሜ 1 እስከ 5 መሆኑን እና የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መስከረም 6/2017 ዓ.ም በይፋ እንደሚጀመር ለ2017ዓ.ም በተዘጋጀው የትምህርት ካላንደር መቀመጡን ገልጸዋል። ቢሮው ከበባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጋራ በመሆን የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋማት በተመሳሳይ የትምህርት ካላንደር ወጥ የሆነ ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ ሲገልጹ በትምህርት ፖሊሲው በተቀመጠው ስርአተ ትምህርት ላይ ጥሰት በፈጸሙ 27 የግል ትምህርት ተቋማት የዕውቅና ፍቃድ መሰረዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስከያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ አስታውቀዋል። ምንጭ፡-ት/ቢሮ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ካላንደር እና በመጽሐፍ አቅርቦት ዙሪያ ከግል ትምህርት ቤት ባለሀብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ። (ሰኔ 7 /2016 ዓ.ም) ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በመርሀ ግብሩ የሁለቱ ተቋማት አመራሮችና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የግል ትምህርት ተቋማት ከመንግስት ጋር በአጋርነት በትውልድ ግንባታ ሂደቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ወቅቱ የ2016ዓ.ም የማጠቃለያ ምዕራፍ እንደመሆኑ ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ ውይይቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል። በ2017ዓ.ም የተማሪ መጽሐፍ ጥምርታን አንድ ለአንድ ለማድረግ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን እና ለዚህም እንዲሆን ከስምንት ሚሊዮን ኮፒ በላይ መጽሐፍት ታትመው ስርጭት ላይ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ገልጸው ተቋማቱ የዘንድሮውን ትምህርት ሲያጠናቅቁ ለተማሪዎች መጽሐፍ በመስጠት ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባቸው አስረድተዋል።
Mostrar todo...
02:25
Video unavailableShow in Telegram
ልጆች እንዴት ይማራሉ?(ሰኔ 6/2016 ዓ.ም) #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
ልጆች___ክፍል___2__Children_Education__Lijoch(720p).mp47.09 MB
ቋሚ ኮሚቴው ክትትልና ድጋፍ አደረገ፡፡ (ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የስራ አፈጻጸምን ክትትልና ድጋፍ አከናወነ፡፡ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ የባለስልጣኑን እቅድ ክንውን የዝግጅት ምዕራፍ ስራ ፣ቁልፍ ተግባራት ፣አበይት ተግባራት ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተፈቱበት አግባብን በዝርዘር ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል፡፡ ከዚህም በላይ ግልጽነትን የሚሹ ሃሰቦችን አብራርተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር እንደተናገሩት የቀረበው ዝርዝር ሪፖርት ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ ለውጥ እያመጣ መሄዱን የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸው ድጋፍና ክትትል መደረጉ ደግሞ ተቋሙ ያሉትን ክፍተቶች ለማሳየትና በጋራ ስራን ለማከናወን እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡ በድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እና የስራ ክፍል ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱት ጥያቄዎችና ግልጽነት ለሚፈልጉ ሃሳቦች ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
ባለስልጣኑ ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚካሄደውን የሠራተኞች የማነቃቂያ እና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር አከናውኗል፡፡ (ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም) በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሰኞ ማለዳ የሚቀርበው የማነቃቂያና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር የአስተሳሰብ ቅኝትና ራስን ማታለል በሚል ርዕስ በዛሬው ዕለትም የባለስልጣኑ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ የመወያያ ሃሳቡን ያቀረቡት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ሲሆኑ ራስን ማታለል ማለት ራስን ማጭበርበር ውሸት የሆነ ወይም ያልተረጋገጠ የራስን ስሜት፣ሀሳብን ወይንም ሁኔታን ትክክል እንደሆነ አድርጎ ራስን የማሳመን እርምጃ እና ህሊናችን ከሚነግረን በተቃራኒ ማድረግ ነው ፣ ለዚህም ብዙ እምቅ መነሻዎች አሉት ያሉ ሲሆን የኛ አስተዳደግና ባህል ፣በራስ የመተማመን ስሜት ማጣት፣ሌሎችን ለማስደሰት መፈለግ፣ሌሎችን ለመማረክ መፈለግ፣የሚያሰቃዩ ሀሳቦችን ወይም ገጠመኞችን ለማስወገድ መፈለግ የሚሉት ሀሳቦች መነሻ ናቸው ብለዋል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
01:28
Video unavailableShow in Telegram
ልጆች ለምን ይማራሉ? (ሰኔ 3/2016 ዓ.ም) #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
ልጆች_ክፍል_1_Children_Education_Lijoch_part_1720p.mp44.13 MB
ዛሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ የሚገነባ ህንፃ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠናል። ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር፤ በማፍረስ ሂደትም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ህንፃዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ የሆነ ምላሽ ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ። በዚህ አጋጣሚ ከቤተክርስቲያንቱ ለቀረበልኝ ምስጋናም እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mostrar todo...
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህርት ምዘናና ምርምር ጥናት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ በቃሉ ያየህ በበኩላቸው እንደገለፁት ከተማ አቀፍ የሂሳብ ስሌት ምዘና በ110 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በናሙና ምዘናው የሚካሄድ ሲሆን በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ የትምህርት ተቋማትም ተጨማሪ ሲሆኑ በምዘናውም ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡ በአነስኛ ክፍሎች ላይ የሚካሄደው ጥናት እና ምርምር ለትምህርት ስራው እና ለፖሊስ አውጪዎች እንደ ግብአት የሚያገለግል እንዲሁም ተማሪዎች በአነስተኛ ክፍሎች ያለውን ችግሮች በመለየት የትምህርት ስርዓትንና መማር ማስተማርን ሂደትን ለማሻሻል ጥናቱ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ክፍሎች ላይ ማንበብና የሒሳብ ስሌትን በአግባቡ የማይችሉ ከሆነ በትምህርታቸው ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚፈጥር ከዚህም የተነሳ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል በየሁለት አመቱ ጥናት እንደሚደረግ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
ከተማ አቀፍ የሒሳብ ስሌት ምዘና ለማካሄድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ (ግንቦት 30/2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት የአነስተኛ ክፍሎች በ2ኛና በ3ኛ ክፍሎች የሚካሄደውን የማስላት ብቃት ለመመዘን የሚያስችል ገለፃ በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡ ለሁለት ቀን በቆየው የውይይት መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የባለስልጣኑ ተግባራት ጥራትና ተገቢነት ማረጋገጥ የምዘና ልህቀት እንደመሆኑ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ደግሞ የበቃ ትውልድ በማነጽ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በመፍጠር ሀገራችንን በማበልጸግ ወደ ከፍታ ማማ እናሳድጋት ብለዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ጥናት መካሄዱ ለትምህርት ስራው ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመው በጥናቱ ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላትም በአግባቡ በኃላፊነት መንፈስ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
Mostrar todo...
የቅ/ጽ/ቤቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ እታገኝ ተሰማ የክትትልና ቁጥጥር የትንተና ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም ላይ የክትትልና ቁጥጥር ኢንስፔክሽን ትንትናው ዓላማ፣ የትንተናው ወሰን፣ የክትትል እና ቁጥጥር ፋይዳ እንዲሁም ዝርዝር የትኩረት ነጥቦችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም በ2016 የውጭ ኢንስፔክሽን በእቅዱ ተካተው የክትትል እና ቁጥጥር ሽፋን ያገኙ የቴክኒክና ሙያ የመንግስትና የግል ተቋማት መርሃ ግብር ተይዞላቸው 15 ተቋማት እንደተሰራ ገልጸዋል፡፡ የ2016 ዓ.ም የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ግኝት ትንተና ሰነድ ያቀረቡት የቅ/ጽ/ቤቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያ አቶ አብይ ገመቹ የድንገተኛ ኢንፔክሽን ዓላማ ፣የትንተናውን አስፈላጊነት፣የትኩረት ነጥቦችን በዝርዝር አቅርበዋል፤ በተጨማሪም በሪፖርቱ እንደተገለጸው የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ምዘና ሽፋኑ ከታቀደው አንጻር 100% ተከናውኗል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም በመድረኩ ላይ ለተነሱ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ እና የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ዓለሙ ምላሽ ሰጥተውበታ፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...