uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

Kanalga Telegram’da o‘tish

↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya

Ko'proq ko'rsatish
3 819
Obunachilar
-524 soatlar
+1617 kun
+15530 kun
Postlar arxiv
“ህመምተኞቻችሁን በሶደቃ አክሙ።” ~ አቡበክር አልኹባዚይ እንዲህ ይላሉ፦ "የሆነ ጊዜ አደገኛ ህመም ታመምኩኝ። አንድ ደግ ጎረቤቴ አየኝና ' 'ህመምተኞቻችሁን በሶደቃ አክሙ' የሚለውን የአላህ መልእ
“ህመምተኞቻችሁን በሶደቃ አክሙ።” ~ አቡበክር አልኹባዚይ እንዲህ ይላሉ፦ "የሆነ ጊዜ አደገኛ ህመም ታመምኩኝ። አንድ ደግ ጎረቤቴ አየኝና ' 'ህመምተኞቻችሁን በሶደቃ አክሙ' የሚለውን የአላህ መልእክተኛን ﷺ ንግግር ተጠቀም' አለኝ። ወቅቱ በጋ ነበር። ብዙ ሃብሃብ ገዛሁ። በርካታ ድሃዎችና ህፃናት ተሰብስበው በሉ። ከዚያም እጆቻቸውን ወደ አላህ አንስተው እንዲያድነኝ ዱዓእ አደረጉልኝ። ከዚያ ወላሂ! ከአላህ - ተባረከ ወተዓላ - ጥሩ ጤና ያገኘሁ ሆኜ እንጂ አላነጋሁም።" 📖 [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 18/44] = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor * የዋትሳፕ ቻናል፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M * ፌስቡክ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL

የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ
የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ! ምናልባትም እንዲህ ዓይነቱ ቡድንተኝነት የወለደው ከንቱ ሙገሳ ይሆናል ልባቸውን አሳብጦ ገደል እየከተታቸው ያለው። አንደኛውንም "ሸይኹል ኢስላም" እያሉት እንደሆነ ሰምቼ ነበር። እውነት ይሆን? ከቅጥፈቱ በላይ የገረመኝ ጠሀ ኸዲር ይህንን አሳፋሪ ወሬ ቁም ነገር አድርጎ መለጠፉ ነው። ሰዎቹ ግን እኛ ከምንገምታቸውም በጣም የራቁ ናቸው። = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

ሲጋራ ~ ሲጋራ ጎጂ የሆነ ሱስ ነው። ጎጂ ነገር በኢስላም ሐራም ነው። ስለሆነም ጎጂ ነገርን መጠቀምም በጎጂ ነገር መነገድም ሐራም ነው። ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ "ለ
ሲጋራ ~ ሲጋራ ጎጂ የሆነ ሱስ ነው። ጎጂ ነገር በኢስላም ሐራም ነው። ስለሆነም ጎጂ ነገርን መጠቀምም በጎጂ ነገር መነገድም ሐራም ነው። ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ "ለማንም ሰው ሲጋራ ሊሸጥ አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ሲጋራ የተከለከለ ነውና። አላህ አንድን ነገር ከከለከለ የሽያጭ ዋጋውንም ነው የሚከለክለው። እንዲሁም ሲጋራን መሸጥ በወንጀልና ወሰን በመተላለፍ ላይ መተባበር ነው።" [አሊቃኡ ሸህሪይ፡ 22/57] ኢብኑ ባዝ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፦ "ሲጋራ ማጨሱም፣ መሸጡም፣ በሱ መነገዱም አይፈቀድም። በዚህ ላይ ከባድ ጉዳትና መጥፎ ፍፃሜ አለበትና።" [አልፈታዋ፡ 6/456] = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor * የዋትሳፕ ቻናል፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M * ፌስቡክ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 5 ~ ያያያዝኩት የባህሩ ተካ ፅሁፍ ነው። እንደምታዩት ከካ'ፊሮች ጋር አንድነት ወደ መፍጠር እየተጣራ ነው። ይሄ የወላእና በራእን ዐቂዳ የሚፃረር ብልሹ ስብከት ነው። ከስላሴ አማኞች ጋር ምን አይነት አንድነት ለመመስረት እንደሚጣራ አላህ ይወቅ። ሠላሠቱል ኡሱል የቀራ ህፃን እንኳ ከሺርክ እና ከሙሽሪኮች መጥራት እንዳለበት ያውቃል። እዚህ የምናየው ግን ሌላ ነው። በዚህ የግንዛቤ መጠን የሆነ ነው እንግዲህ ሰርክ ስለ ተምይዕ የሚያወራው። ምናልባት ተምይዑ ከነሷራ ጋር ሲሆን ሌላ ሑክም ይኖረው ይሆን? ነው ወይስ ተምይዑ የናንተ ሲሆን ቅዱስ ነው? ይሄ ከነሷሪዎች ጋር አንድነት ወደ መፍጠር የተጣራው ከነሱ የተለየ ሰው ቢሆን ብላችሁ አስቡ። ባህሩም፣ ያ ከባባድ ውንጀላዎችን ለመለጠፍ ለአፍታ ቆም ብሎ ማሰብ የማይሻው ጭፍራም ጩኸቱ ከባድ ነበር። ችግሩ "የኛ" የሚሉት ላይ ሲሆን ግን "ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ" ይሆናሉ። ከዚህ በፊት ከውስጣቸው ከዚህ ባነሰ ጉዳይ እንኳ በ "ወሕደተል አድያን" ስብከት የሚከሱ ገጥመውኛል። በነገራችን ላይ ይሄ ስብከት ኢኽዋኒዮች የሚታወቁበት ስብከት ነው። የሚያልሙትን መስለሐ ያስገኝልናል ብለው እስካሰቡ ድረስ የወላእና በራእ ዐቂዳ ጉዳይ አያስጨንቃቸውም፡፡ በሕሩም ተመሳሳይ ጥፋት ነው የፈፀመው። እንደሚታወቀው ነብያችን ﷺ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃገር ከሚጋሯቸው የመካ አጋሪዎች ጋር አንድነት ወደ መመስረት አልተጣሩም። ከኢስላማዊ ግንዛቤ የራቀ ፖለቲከኛ ቢያደርገው ቃላቱን በሸሪዐ የመመዘን ትኩረቱ አናሳ ነውና ብዙም አይደንቅም። በዚያ ላይ ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ የሚያስተዳድረውን ህዝብ ይለያያል እንዳይባል 'ሙጃመላ' ያደርጋል። በሕሩ ተካስ ምንድነው የሚያልምበት? ከነሷራ ጋር አንድነት ወደ መፍጠር የሚሰብክ ሰው ነው እንግዲህ ሲለው የሰው ንግግር እየቆለመመ፣ ሲያሰኘው ደግሞ ከመሬት አንስቶ በሃሰት እየከሰሰ ሙስሊሞችን የሚያጠለሸው። የውጭ አልጋ፣ የቤት ቀጋ ማለት እንዲህ ነው። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

"አምላካችሁም እግዚአብሔር #ከእናንተ_ጋር_የተማማለውን_ቃል_ኪዳን #እንዳትረሱ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።" (ኦሪት ዘዳግም 4:23) "በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር #የማናቸውንም_ምሳሌ #የተቀረጸውንም_ምስል ለአንተ አታድርግ፤" (ኦሪት ዘዳግም 5:8) " #ለተቀረጸ_ምስል የሚሰግዱ #ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት።" (መዝሙረ ዳዊት 97:7) (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 28/2011) = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor * የዋትሳፕ ቻናል፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M * ፌስቡክ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL

የማርያም ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለንም! ~ ሰሞኑን #እስቴ ላይ መስጂዶች የተቃጠሉት በአንድ የሙስሊም ሰርግ ቤት ለዲኮርነት በተበተነ ወረቀት ላይ "የማርያም ምስል" መገኘቱ ነው። በርግጥ ወረቀቱ ባህርዳር ከተማ ውስጥ ከሚገኝ ማተሚያ ቤት የተገዛ ሲሆን በተበተነው ወረቀት ውስጥ የተገኘው ዘግይቶ ከሰአት በኋላ ነው። ሆን ተብሎ አልተፈፀም ማለት ነው። · በርግጠኝነት ይሄ ወረቀት የተገኘው ከአንድ ክርስቲያን ሰርግ ላይ ቢሆን የአራት የአምስት ሰዎች አጀንዳ እንኳን መሆን አይችልም ነበር። ስለዚህ ጉዳዩ ያ ሁሉ ጥፋት የተከተለው አጀንዳ የሆነው ከሙስሊም ቤት መገኘቱ ነው። ወይ ሙስሊሞች ሆነ ብለው ለትንኮሳ አድርገውታል ብሎ ከማሰብ ወይም ለማርያም ክብር የላቸውም ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው። በርግጥ እኛ እንደ ሙስሊም የማንም ምስል ቢሆን ለስእል ክብር የለንም። የእየሱስም ተባለ የሙሐመድ፣ የማርያምም ተባለ የዓኢሻ ለኛ ልዩነት የለውም። ነገር ግን ይህንን አቋማችንን ለትንኮሳና ለብጥብጥ አናውለውም። · ስለ ማርያም ያለን እምነት ግን በአክብሮት የተሞላ ነው። አክብሮታችንም ከቁርኣንና ከነብያችን (የአላህ ሶላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) አስተምህሮት የተቀዳ ነው። ለምሳሌ ያክል ጥቂት ብናይ:– ① ማርያም በአምላካዊ እንክብካቤ ስር በሥርዓት ተኮትኩታ ያደገች እንደሆነች ቁርኣን ይመሰክራል (وَأَنْبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنًا) "(ጌታዋም) በመልካም አስተዳደግ አሳደጋት፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 37] ② ማርያም ጌታዋን ፈሪ፣ ህጉን አክባሪ፣ የተሟላ ስብእና ባለቤት ነች ይላል የፈጠራት ጌታ (وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَى نِسَاءِ الْعَالَمِينَ * يَا مَرْيَمُ اقْنُتِي لِرَبِّكِ وَاسْجُدِي وَارْكَعِي مَعَ الرَّاكِعِينَ ) "መላእክትም ያሉትን (አውሳ)፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነፃሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» «መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፡፡ ስገጂም፡፡ ከአጎንባሾቹም ጋር አጎንብሺ፡፡» [ኣሉ ዒምራን: 42–43] ስለዚህ ማርያም የከበረች ሙስሊማ ነች። ሙስሊም ማለት ለፈጣሪ እጅ የሰጠ፣ ለትእዛዙ ያደረ ማለት ነው። ማርያም ደግሞ በሚገባ ለጌታዋ እጅ የሰጠች ነበረች። ③ ማርያም ከተወነጀለችበት የዝሙት ወንጀል ፍፁም የራቀች፣ ይልቁንም በአምላክ ፈቃድ በተአምር ፀንሳ የወለደች ናት። አላህ በቁርአን እንዲህ ይላል:– (إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ ) "መላእክት ያሉትን (አውሳ)፡- ‘መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በሆነው ቃል ስሙ መሲሑ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በሆነ (ልጅ) ያበስርሻል፡፡’ " [ኣሉ ዒምራን: 45] ④ ልጇም የዝሙት ልጅ ሳይሆን ከታላላቅ የፈጣሪ መልእክተኞች እንደሆነ በቁርአን ተመስክሯል። ( إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَى مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِنْهُ ) "መሲሑ የመርየም ልጅ ዒሳ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት ‘የሁን’ ቃሉ እና ከእርሱ የሆነ መንፈስም ነው፡፡" [አኒሳእ: 171] ⑤ ማርያም የእውነተኞች ተምሳሌት ናት። ፈጣሪ እንዲህ ይገልፃታል:– (مَا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ) "መሲሑ የመርየም ልጅ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡" [አልማኢዳህ: 75] ⑥ ባጠቃላይ ማርያም የጌታ ተአምር ነች ማለት ይቻላል። በቁርአን እንዲህ ተገልፃለች: – (وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً ) "የመርየምን ልጅ እና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው፡፡" [አልሙእሚኑን: 50] ⑦ መርየም ከታላላቅ የጀነት (ገነት) ሴቶች ውስጥ እንደሆነች ነብያችን መስክረዋል ። [ሙስነድ አሕመድ: 2668] · ይሄ እምነታችን ከቁርኣን የወሰድነው፣ ከቀደምቶቻችን የወረስነው ነው። ይሄ ሐቅ ሙስሊሞች በጣም ጥቂትና ደካሞች በነበሩበት የመካ ዘመን ጀምሮ ሃገር እስከመሰረቱበት የመዲና ዘመን ድረስ የፀና ነው። በአንድ ወቅት የቁረይሽ ዐረቦችን ክፋት ሸሽተው ወደ ሐበሻ ተሰደው ይኖሩ የነበሩት ሙስሊሞችን የኢትዮጵያው ንጉስ ስለ ዒሳ ሊጠይቃቸው ፈልጎ ሰው ላከባቸው። ንጉሱ በጊዜው አልሰለመም ነበርና ምን ብለው ሊመልሱለት እንደሚገባ ለመመካከር ተሰባሰቡ። "ስለ ዒሳ ከጠየቃችሁ ምንድነው መልሳችሁ?" ተባባሉ። "ወላሂ! በዚህ ጉዳይ ላይ የፈለገ አካል ቢመጣ ስለሱ አላህ የተናገረውን ፣ ነብያችን ያደረሱንን ነው የምንናገረው!" ተባባሉ። ንጉሱ ዘንድ እንደገቡም "የማርያም ልጅ ስለሆነው እየሱስ ምን ትላላችሁ?" የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። እየመራቸው የገባው የነብዩ የአጎት ልጅ የሆነው ጀዕፈር እንዲህ አለ:– "ስለሱ ነብያችን ያመጣልንን ነው የምንለው። እሱ (ዒሳ) የአላህ ባሪያና መልእክተኛ ነው። እርሱ ከፈጠራቸው ነፍሶች ውስጥና ወደ ድንግሏ መርየም የጣለው የሁን ቃሉም ነው።" ንጉሱ በዚህን ጊዜ በእጁ መሬቱን መታና እንጨት አንስቶ የመርየም ልጅ ዒሳ ከተናገርከው ይቺን እንጨት የምታክል አላለፈም" አለ። [ሙስነድ አሕመድ: 1742] · ይህ ነው ስለ ማርያም ያለን እምነት። ድንበር ማለፍ የሌለበት፣ እሷን ወደ ማምለክና ወደ መማፀን የማይሻገር ፍፁም አክብሮት። ይሄ ስለሷ ብቻ ሳይሆን ስለሌሎችም ፃድቃን ያለን እምነት ነው። በእርግጥ "የማርያም ምስል" ተብሎ አሁን ክርስቲያኖች ዘንድ የሚገኘውን ስእል በተመለከተ እሷን ለመምሰሉ ማንም ማረጋገጫ ሊያቀርብለት አይችልም። ምክንያቱ ለማንም አይሰወርም። · በነገራችን ላይ ስእሎችን ማክበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የለውም። ለምሳሌ ያክል ጥቂት ጥቅሶችን እንይ:– "በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር #የማናቸውንም_ምሳሌ፥ #የተቀረጸውንም_ምስል ለአንተ አታድርግ።" (ኦሪት ዘጸአት 20:4) " እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ #የተቀረጸም_ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።" (ኦሪት ዘሌዋውያን 26:1) "#እንዳትረክሱ! #የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ … ምሳሌ እንዳያደርጉ።" (ኦሪት ዘዳግም 4:16–18)

የባህሩ ተካ እና አምሳዮቹ ውሸት ሲጋለጥ ክፍል —8 የቴሌግራም ቻናል፡‐ https://t.me/fejir_tube የዋትሳፕ ቻናል: — https://whatsapp.com/channel/0029VaFiaPJ1NCrMw2SOqP1n

የአቢሲኒያ ባንክ የአለም ገና ቅርንጫፍ ኃላፊ ኡስታዝ ሙሐመድ ኸዲርን ከደዕዋ ሊያስቆም ሲታገል በአንድ ቪዲዮ ላይ ብዙ ሰው አይቶታል። በሙስሊም አስተማሪዎች ላይ እስከ እስራት የሚያልፍ መሰል ማዋከብና እንግልት ሲደርስ ማየት የተለመደ ነው። እዚህ አገር ላይ ያለው እብሪት ግን የተለየ ነው። በየጎዳናው ከሚርመሰመሱ ሰባኪዎች መሀል ሙስሊም አስተማሪዎች ተለይተው የሚከለከሉበት ምክንያት ምንድነው? ፖሊሱም፣ ባንከሩም እንዲህ ለይቶ ሲዳፈር ማየት የሚገርም ነው። በአንድ ሃገር ላይ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ የሚሆንበት አካሄድ የትም እንደማይደርስ ማወቅ ይገባል። እስኪ አሁን የአንድ የግል ባንክ ኃላፊ እንዲህ አይነት ተግባር ውስጥ መግባት ምን ይባላል? ኧረ እንደ ዘመናችሁ ኑሩ። Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

ደርስ ~ * መንሀጁ ሳሊኪን * ክፍል:- 1️⃣8️⃣ * የደርሹ መነሻ፦ أوقات النهي * የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ * የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

✅ አዲስ የተጠናቀቀ ደርስ 📚 የኪታቡ ስም :- አልዑቡዲያህ / العبودية ✍ የኪታቡ አዘጋጅ :- شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله- ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ -ረሒመሁሏህ- 🎙 በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም -ሐፊዘሁሏህ- 🎶 ከክፍል/01 እስከ ክፍል/37 ሊንኩን በመጫን ሙሉውን ደርስ ማግኘት ይችላሉ👇👇👇 https://t.me/SheikhMuhammedZain/2127

ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣4️⃣2️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 417፣ باب تجويز صلاة الضحى من ارتفاع الشمس * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ
የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ! ምናልባትም እንዲህ ዓይነቱ ቡድንተኝነት የወለደው ከንቱ ሙገሳ ይሆናል ልባቸውን አሳብጦ ገደል እየከተታቸው ያለው። አንደኛውንም "ሸይኹል ኢስላም" እያሉት እንደሆነ ሰምቼ ነበር። እውነት ይሆን? ከቅጥፈቱ በላይ የገረመኝ ጠሀ ኸዲር ይህንን አሳፋሪ ወሬ ቁም ነገር አድርጎ መለጠፉ ነው። ሰዎቹ ግን እኛ ከምንገምታቸውም በጣም የራቁ ናቸው። = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

+1
ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣4️⃣3️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 421፣ ሐዲሥ ቁ. 1158 * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

አንድ ነጥብ ~ የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የሚታወቅ ነው። ሰሞኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ሰዎች ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው እርዳታ ማድረጋቸው ጥሩ የድጋፍ ስራ መሆኑን አውስቼ "አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው" ብል ይሄ ስሜት ያሰከረው መንጋ ሲንጫጫ ነበር። ከዚህ በፊት የመስጂድ ቦታ ለሰጡን አካላት ምስጋና ስገልፅ ምንም ያላሉት እነዚያ ሙስሊሞች ስላልሆኑ ነው። አንዳንድ ሰዎች ዘንድ "እናመሰግናለን፣ አላህ ይስጥልን" ማለት ለሙስሊሞች ሲሆን የቢድዐን አካል ማወደስ፣ የመንሀጅ መንሸራተት ሲሆን ለካፊሮች ሲሆን ግን ችግር የለውም። እንዲያውም እንደ ንቃት ነው የሚቆጠረው። ነገሮች እንዴት እየተያዙ እንደሆነ ቆም ብለን እናስተውል። በተረፈ የመጅሊስ ሰዎች አካሄድ እንከን የለሽ ነው የሚል አቋም የለኝም። ባደባባይ ከሚታዩ ችግሮቻቸው ውስጥ በአንድ ሁለቱ ላይ ከዚህ ቀደም በግልፅ ፅፌያለሁ። ለማንኛውም አንድ አካል ችግር ቢኖርበት እንኳ በመልካም ስራው ላይ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ማለት አቧራ የሚያስነሳ አይደለም። 1- ኢብኑ ባዝ - ረሒመሁላህ - ከሙሐመድ አልገዛሊ "መዐ'ላህ" ኪታብ በረጅሙ ከወሰዱ በኋላ መጨረሻ ላይ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ነቅዱል ቀውሚየቲል ዐረቢያ] [መጅሙዑ ፈታዋ፡1/317] 2- ሸይኹል አልባኒይም - ረሒመሁላህ - አሕመድ ዲዳትን ትልቅ ጂሃድ ላይ እንዳሉ በመግለፅ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር] 3- ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደምም እንዲሁ ከዩሱፍ አልቀርዳዊ "ፊቅሁ ዘካ" ኪታቡ ረዘም ያለ ክፍል ከወሰዱ በኋላ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ዘኺራ፡ 22/168] አለፍ ብለውም እንዲህ ሲሉ ስራውን ከማድነቅ ጋር ዱዓእ ያደርጋሉ:- انتهى ما كتبه الدكتور القرضاويّ شكر اللَّه سعيه، وهو بحثٌ نفيسٌ جدًا. የቀርዷዊ ማንነት የሚታወቅ ነው። አሁንም ሸይኹል አልባኒይ ለሙሐመድ አልገዛሊይ እና ዩሱፍ አልቀርዷዊይ አድናቆታቸውን ከገለፁ በኋላ ለቀርዷዊ "አላህ ይጠብቀው። ሙስሊሞችንም ይጥቀምበት" ብለዋል። [ጋየቱል መራም፡ 7] አልባኒይ የነዚህን አካላት ብልሹ አካሄድ በመተቸት የታወቁ ናቸው። ከመሆኑም ጋር "በመልካም ስራቸው" ላይ አላህ እንዲመነዳቸው ዱዓእ ሲያደርጉ እናያለን። መሰል አካሄድ ብንፈልግ ሌሎችም ጋር እናገኛለን። "ሙብተዲዕን ማድነቅ ይቻላል" እያልኩ አይደለም። ይልቁንም ነገሮችን መለየትና በልክ መያዝ እንልመድ እያልኩ ነው። ያያያዝኩት በሕሩ ተካ በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ላይ የነበረን ሁከት ተከትሎ የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ርስቱ ይርዳውን፣ የፍትህ ሚኒስቴርን፣ አስተዋይና ሚዛናዊ ብሎ የገለፃቸውን ክርስቲያኖችን፣ የጉንችሬና የእነሞር አመራሮችን ያደነቀበትና ያመሰገነበት ነው። ለሽፋን ከሚቀርቡ ሰሞንኛ ግርግር ውጭ እነዚህ የተጠቀሱት አካላት ለአካባቢው ችግር ወይ ጠንሳሽ ናቸው። ወይ አፍራሽ ሚና የነበራቸው ናቸው። ወይ ደግሞ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ችግሩ እንዲቀጥል ያደረጉ ናቸው። (የተነሳውን ነጥብ ጥለው በማስቀየስ ላይ እንደሚጠመዱ እጠብቃለሁ።) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣4️⃣4️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 426፣ باب استحباب قيام رمضان * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ኢስራእ እና ሚዕራጅ መቼ ተካሄደ? ~ ብዙ ሰዎች በተለይም ሱፍዮች አካባቢ ኢስራእ እና ሚዕራጅ ረጀብ 27 እንደተካሄደ ያምናሉ። ግና ይህን የሚያስረዳ ሶሒሕ ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም ። ክስተቱ በምን ቀን፣ በምን ወር፣ በየትኛው አመት እንደተፈፀመ በውል አይታወቅም። በዚህም ሳቢያ የዑለማዎች ሐሳብ ተለያይቷል። ጊዜውን የሚጠቁም አንድም ሶሒሕ ማስረጃ በሌለበት ረጀብን እየጠበቁ የሚያከብሩ ሰዎች የሚገርሙ ናቸው። ረጀብ ነው የሚለውን "ግልፅ የሆነ ውሸት ነው" ብለው የገለፁት አሉ። አመቱን በተመለከተ ① ከሂጅራ በፊት ስድስት ወር ቀደም ብሎ፣ ② ከሂጅራ አንድ አመት በፊት ③ ከሂጅራ ከ 3 አመት በፊት፣ ④ ከሂጅራ ከ5 አመት በፊት፣ ⑤ ከመላካቸው በፊት፣ ወዘተ የሚሉ አሉ። ከሂጅራ ከ8 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ11 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ15 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ17 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ18 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ20 ወር በፊት እና ሌሎችም። ወሩን በተመለከተነው ① ረቢዑል አወል ወር ነው የሚል ዘገባ አለ። [ጦበቃት ኢብኒ ሰዕድ: 1/213–214] ② ዙል ቂዕዳ ወር ያሉ አሉ። [አልቢዳያ ወኒሃያህ: 3/109] ③ ረጀብ ወር ነው ያሉ አሉ። ④ ረመዳን ነው ያሉም አሉ። ⑤ ረቢዑል ኣኺር ያሉም አሉ። ⑥ ሸዋል ወር ያሉም አሉ። ከነዚህ ውስጥ አመቱንም ወሩንም የሚጠቁም አንድም ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ያሉት ማስረጃዎች በሙሉ ደካማ ናቸው። ስለዚህ ኢስራእና ሚዕራጅ አላህ ለነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዋለው ትልቅ ተአምር ቢሆንም ጊዜው በትክክል አይታወቅም። ይህም በሱፍዮች እንደሚደረገው አመት እየጠበቁ ክስተቱን ማክበር ቀደምቶች ዘንድ እንዳልነበር በቂ ማስረጃ ነው። ሰለፎች ዘንድ ቢከበር ኖሮ ጊዜው በውል ይታወቅ ነበርና። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 16/2009) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ሙሓደራ ክፍል 189 አዲስ ሙሓደራ ክፍል 01 ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇 ““የ አብዱል ሀሚድ አልለተሚይ እና  ሁሰይን ሙሀመድ ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““ 🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም) https://t.me/UstazKedirAhmed

ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣4️⃣3️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 421፣ ሐዲሥ ቁ. 1158 * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ትግራይ ላይ ያደረጉት መልካም ስራ ይበል የሚያሰኝ ነው። ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ። አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor