uz
Feedback
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Kanalga Telegram’da o‘tish

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council analitikasi

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council (@eiasc1) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 11 288 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 8 061-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 963-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 11 288 obunachiga ega bo‘ldi.

26 Iyul, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -73 ga, so‘nggi 24 soatda esa -7 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 16.91% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 9.89% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 1 909 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 116 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 0 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 27 Iyul, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

11 288
Obunachilar
-724 soatlar
-277 kunlar
-7330 kunlar
Postlar arxiv
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የኡለማ ጉባዔ ምክትል ፕሬዝደንት በጅግጅጋ ከተማ የሥራ ጉብኝት አካሄዱ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ል | ሰፈር 10/1448 ዓ.ሂ بِسْمِ
+4
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የኡለማ ጉባዔ ምክትል ፕሬዝደንት በጅግጅጋ ከተማ የሥራ ጉብኝት አካሄዱ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ል | ሰፈር 10/1448 ዓ.ሂ بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ጅግ ጅጋ| የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ በጅግጅጋ ከተማ የስራ ጉብኝት አደረጉ። ​ምክትል ፕሬዝደንቱ በጉብኝታቸው በሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እየተገነባ የሚገኘውን መስጂድ የግንባታ ሂደት አሁናዊ ደረጃ ከሰወራ ኃላፊዎች ጋር ሆነው ተመልክተዋል። ​ሸይኽ ጁነይድ በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር የክልሉ መጅሊስ እያከናወናቸው ያሉት የልማት እና የዳዕዋ ሥራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸው ለክልሉ መጅሊስ አድናቆት እንዳላቸው አመላክተዋል። ​የሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሸይኽ አህመድ ሙሀመድ አሊ በበኩላቸው ፌዴራል መጅሊሱ እያደረገ ያለው ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል የክልሎችን የመፈጸም አቅም እየገነባ መሆኑን ገልጸዋል። ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ በነገው ዕለትም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ሌሎች የልማትና ስራዎችን በመጎብኘት ከክልሉ መጅሊስ አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ለመጅሊስ አመራሮችና ለዱዓቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ል | ሰፈር 7 /1448 ዓ.ሂ بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሻሸመኔ | የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማእ ጉባዔ ከኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና ከቡኒያን ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለክልልና ለዞን መጅሊስ የሥራ ኃላፊዎችና ዱዓቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሻሸመኔ መስጠት ጀምሯል። በስልጠናው ላይ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ከሲዳማ ክልል መጅሊሶች የተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ዱዓቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ። የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማእ ጉባዔ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሙሀሙድ ሁሴን በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በሻሸመኔ ከተማ በተጀመረው የአቅም ግንባታ ስልጠና በእስላማዊ እውቀት፣ በዳዕዋ፣ በሰላም ግንባታ፣ በማኅበራዊ ኃላፊነት እና በአመራር ክህሎት ላይ ትኩረት ማድረጉን ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም የሕዝበ ሙስሊሙን የሰላም፣ የልማት፣ የአንድነት እና የአብሮነት ኢስላማዊ እሴቶችን በማጠናከር ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ኃላፊው አክለው ገልጸዋል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየሰጠ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና በቀጣይ ሳምንትም እንደሚቀጥል ተመላክቷል። ••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

የኢትዮጵያ ዑለማዎች ጉባኤ ለኮሌጅ መምህራን የሰጠው የማስተማር ብቃት ማበልጸጊያ ስልጠና ተጠናቀቀ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሐምሌ/13/2018 ዓ.ል| ሰፈር 6/1448 ዓ.ሂ بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ━━━━━━━━━━━━━━━━ አዲስ አበባ | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዎች ጉባኤ የትምህርትና ሥርዓተ ትምህርት ዘርፍ ከሱና ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለኢስላማዊ ኮሌጅ መምህራን ሲሰጥ የቆየውን ሥልጠና አጠናቀቀ። ሥልጠናው ውጤታማ የዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሲሆን በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የዑለማ ጉባኤ ጽፈት ቤት ኃላፊ ሸይኽ ዓሊ መሐመድ ትምህርትን በስልጠና በመደገፍ ከዘመኑ ጋር አብሮ መራመድና የትምህርት ጥራትን ከፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ስልጠናው በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የአረብኛ ቋንቋና የስርዓተ ትምህርት ሊቃውንት የተሳተፉበት የተሳተፉበት መሆኑን በመጥቀስ እንዲህ ዓይነቱ የስልጠና መድረክ ጠቀሜታው ከፍተኛ እንደሆነ አብራርተዋል። የጠቅላይ ምከር ቤቱ ዑለማእ ጉባኤ የትምህርትና ሥርዓተ-ትምህርት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አብዱላህ ኸድር በሰጡት ማብራሪያ ስልጠናው መምህራን የማስተማር ማስተማር ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማና ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ ያግዛቸዋል ብለዋል። በመጨረሻም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚና የመስጂዶች ጉዳይ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ እድሪስ አሊ ለሠልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት ሙያን በሥልጠና ማበልጸግ ከዘመኑ ጋር መራመድ መሆኑን ነው ያሉ ሲሆን ሰልጣኞች ባገኙት ዕውቀት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አደራ ብለዋል። ስልጠናው በአፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የዐረብኛ ቋንቋ ተመራማሪና የሥርዓተ-ትምህርት ባለሙያ ፕሮፌሰር አል-ሲዲቅ አዳም በረካት የተሰጠ ሲሆን ሸይኽ እድሪስ አሊ እና የሙስሊም ወጣቶች ዓለም አቀፍ ጉባኤ (WAMY) ተወካይ ለሠልጣኞች የሜዳሊያና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል። •••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ ​ ​«ሁላችንም የአላህ ነን፤ ወደ እርሱም ተመላሾች ነን።» (ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን) ​በእኔ፣ በኢትዮጵያ እስልምና
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ ​ ​«ሁላችንም የአላህ ነን፤ ወደ እርሱም ተመላሾች ነን።» (ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን) ​በእኔ፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በመላው የኢትዮጵያ ህዝበ ሙስሊም ስም፣ ለተከበሩት የሀገረ ኳታር አሚር ሸይኽ ታሚም ቢን ሀማድ አል ታኒ፣ ለኳታር መንግሥት እና ለኳታር ሕዝብ፣ በክቡር አሚር ሸይኽ ሀማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ህልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ልባዊ እና ጥልቅ ሐዘን እገልጻለሁ። ​ክቡር አሚር ሸይኽ ሀማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ለኳታር ብቻ ሳይሆን ለሀገራት ሁሉ ሰላም በተለይም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አርዓያ መሪ ነበሩ። ​የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና መላው ሕዝብ ለሟቹ አሚር ታላቅ ክብርና መልካም ትውስታ ያለው ሲሆን ክቡር አሚር የኢትዮጵያ እና የኳታር ታሪካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ሚና ነበራቸው። በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለው ሃይማኖታዊና ሰብዓዊ ትስስር ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ደማቅ አሻራ አሳርፈዋል። ​ለክቡር አሚር ሸይኽ ሀማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ምሕረቱንና እዝነቱን እንዲለግሳቸውና ማረፊያቸውን በጀነት እንዲያደርግላቸው አላህን እንማጸነዋለን። ለተከበረው የሀገረ ኳታር መንግስትና ህዝብ እንዲሁም ለወዳጆቻቸው ሁሉ አላህ መጽናናትንና ሰላምን እንዲሰጥ ዱዓችን ነው። ​ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የኡለማ ጉባኤ ፕሬዝደንት

ለኢማሞችና ለዑስታዞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ሐምሌ 03/2018 ዓ.ል | ሙሐረም 24/1448 ዓ.ሂ بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ አሶሳ | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማእ ጉባዔ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና ከቡኒያን ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ ዑለማዎችና ዑስታዞች በአሶሳ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ። በአቅም ግንባታ ስልጠናው ላይ 50 ኢማሞችና 50 ዑስታዞች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው በእስላማዊ እውቀት፣ በዳዕዋ፣ በሰላም ግንባታ፣ በማህበራዊ ኃላፊነት እና በአመራር ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ንግግር ያደረጉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ተግባራዊ በማድረግ ማህበረሰቡን በብቃት እንዲያገለግሉ አደራ ብለዋል። ኢማሞችና ዑስታዞች የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላም፣ አንድነት እና ኢስላማዊ የስነ ምግባር እሴቶችን በማጠናከር ውጤታማ ሥራ እንዲሰሩም ጠይቀዋል። ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በቀጣይም የኢማሞችና የዑስታዞች አቅም ለማጠናከር መጅሊሱ እንደሚሰራም ፕሬዝደንቱ ልጸዋል። በምርቃት መርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ መጅሊስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሐጅ አኑር፣ ሸይኽ ሷሊህ ሙሐመድ እና ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

የጠቅላይ ምክር ቤት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ለኮሚሽነሮች እና ለባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ። •••••••••••••••••••••••••••••••• ሰኔ 30 /2018 ዓ.ል| ሙሀረብ 22/1448 ዓ.ሒ سْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• አዳማ | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በአዳማ ከተማ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደር መጅሊስ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽነሮች እና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ። በሥልጠናው በተግባር ልምምድ ታግዞ ሲሰጥ የቆዬ ሲሆን ሰላጣኞቹ በስልጠናው ባገኙት ክህሎት መሰረት የኦዲት እና ኢንስፔክሽን መመሪያ እንዲሁም ዓመታዊ ዕቅድ አዘጋጅተው ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የኦዲትና ኢንስፔክሽን በማቅረብ አስገምግመዋል። ስልጠናው ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የተጠናቀቀ ሲሆን በማንኛውም ደረጃ የሚሰበሰብ ገቢና ወጪ የፋይናንስ ሕግና እና ሥርዓትን ተከትሎ እንዲከናወን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ በስልጠናው ማሳረጊያ ቃል ተገብቷል። የሕገ መጅሊሱ ማስፈጸሚያ ደንቦችና መመሪያዎች ሳይሸራረፉ ሥራ ላይ እንዲውሉ ተቋማዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባም በአቋም መግለጫው ላይበተካቷል። የጠቅላይ ምከወር ቤቱ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሸይኽ ኢልያስ አወል በስልጠነው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የስልጠናው ዓላማ በመጅሊስ መዋቅሮች ውስጥ ግልጽነትን እና ተጠያቂነት ማስፈን ነው። ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ለተቋሙ ስኬት አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱም ሸይኽ ኤሊያስ አወል አደራ ብለዋል። ••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤትን ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያን ይከታተሉ | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማእ ጉባዔ የሞሮኮ ንጉስ ሙሀመድ ስድስተኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን ጋር በትምህርትና ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ሰኔ 30/2018 ዓ.ል| ሙሀረም 22 /1447 ዓ.ሒ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• አዲስ አበባ | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማእ ጉባዔ ከሞሮኮ ንጉስ ሙሀመድ ስድስተኛ የአፍሪካ ዑለማእ ፋውንዴሽን ጋር በትምህርትና ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። በጠቅላይ ምክር ቤቱ የተደረገውን የፊርማ ሥነ ሥርዓት የዑለማእ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ እና የሞሮኮ ንጉስ ሙሀመድ ስድስተኛ የዒማሞችና ዱዓቶች ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት ዳይሬክተር ዶክተር አብዱሰላም ላዛር ተፈራርመዋል። በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሀምዛ የሞሮኮ ንጉስ ሙሀመድ ስድስተኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን የዒማሞችን አቅም ለማጎልበት የመግቢያ ፈተና ያለፉ ሃያ ስምንት ዒማሞችን ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ለማስተማር ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። ፋውንዴሽኑ በቀጣይም የምዘና ሌሎች ዒማሞችን በማወዳደር የትምህርት እድሉ ተጠቃሚ እንዲያደርግ የዑለማእ ጉባዔው በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ፕሬዝደንቱ አክለዋል የሞሮኮ ንጉስ ሙሀመድ ስድስተኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን እና ጠቅላይ ምክር ቤቱ የጋራ በሆኑ ሃይማኖታዊ እና ልማታዊ ስራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ዶክተር አብዱሰላም ተናግረዋል። ••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤትን ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ይከታተሉ | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ለክልል መጅሊስ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽነሮች የስልጠናና ምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተጀመረ። ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ሰኔ 28 /2018 ዓ.ል| ሙሀረብ 20/1448 ዓ.ሂ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• አዳማ | ​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ከ"ጋይድ ላይት ኮንሰልቲንግ" ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአቅም ግንባታና የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥ መድረክ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል። ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መርሐ ግብር ላይ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ የመጅሊስ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽነሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። የአቅም ግንባታ ስልጠናውንና የምክክር መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዑለማእ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ የተከበሩ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ናቸው። ​ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በ2017 ዓ.ም "ምርጫችን በመስጂዳችን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሀገራዊ የመጅሊስ ምርጫ በምሁራን ዘርፍ በርካታ አዳዲስ ምሁራንና ባለሙያዎች የመጅሊስ የአመራር መዋቅሮችን መቀላቀላቸውን አስታውሰዋል። ​ፕሬዝደንቱ የአቅም ግንባታ ስልጠናው ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርገው በመጅሊሱ ውስጥ መስተካከል ያለባቸውን ክፍተቶች ለመድፈን ስህተቶችን ለማረምና ዘመኑን የዋጀ አሰራርን ለማስረጽ ትልቅ በር የሚከፍት መሆኑን ገልጸው ይህ ስልጠና በተለያዩ ክልሎች መካከል ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን በመጋራት የጋራ አቅምን ለመገንባት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል። የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በመልክታቸው መጨረሻ በስልጠናው የተገናኙት ባለሙያዎች ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያሸጋግሩ ጥሪ አቅርበው ለሥራቸው ስኬታማነት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በዚህ የስልጠና መረሀ ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሸይኽ ኤልያስ አወል የስልጠናውን ዋና ዓላማና አስፈላጊነት በሰፊው አብራርተዋል። ተቋሙን ዘመናዊ ለማድረግ አዲስና ሰፊ የሰው ኃይል አደረጃጀት የተፈጠረ ሲሆን፣ የሐጅና ዑምራ ኮሚሽን በገለልተኝነትና ራሱን ችሎ መቋቋሙ ለዚህ ስኬት ዋነኛው የለውጥ መነሻ መሆኑ ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በደረጃው እንዲደራጅ የሚያስችለው ማቋቋሚያ ደንብ፣ መመሪያና መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅተው በጠቅላይ ምክር ቤቱ እንዲጸድቁ መደረጉን መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ገልጸዋል። ​ የተጀመረው አገራዊ የለውጥ አጀንዳ ግቡን እንዲመታና የሕዝበ ሙስሊሙን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ ሁሉም ክልሎችና አጋር አካላት በኅብረትና በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ ቀርበዋል። በመጨረሻም በክልል መጅሊሶች ደረጃ የሚስተዋሉ የፋይናንስ አያያዝ፣ የንብረት አስተዳደርና የኦፕሬሽን አሠራር ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመሙላት ዘመኑን የዋጀ አሰራርን ለማስረፅ እንዲህ ያሉ የስልጠና መድረኮች ወሳኝ መሆናቸው አስታውሰዋል። ​ይህ መድረክ ተሳታፊዎቹ በስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር፣ በየክልሎቻቸው የሚገኙትን የመጅሊስ መዋቅሮች የአሠራር ጥራትና ታማኝነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል። በስልጠናው የመክፈቻ ስነስረአት ላይ የተከበሩ ኡስታዝ አብዱልቃድር ማህ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ እና ዑምራ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ምክትል ኮሚሽነር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤትን ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ይከታተሉ | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ኢማም አል ሻፊኢ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ ከኒዳዑል ኢህሳን አል ኸይሪያ ዓለም አቀፍ ተራዕዶ ድርጅት ጋር በመተባበር በተያዩ የሸሪዓ የዕውቀት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ስድስት መቶ ሠልጣኞችን አስመረቀ። •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ሰኔ 25 /2018 ዓ.ል| ሙሀረም 17 /1447 ዓ.ሒ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• አዳማ | ኢማም አል ሻፊኢ ኢስላማዊ ዩንቨርስቲ ከኒዳዑል ኢህሳን አል ኸይሪያ ዓለም አቀፍ ተራዕዶ ድርጅት ጋር በመተባበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተመለመሉ ኢማሞችን፣ ዱዓቶችንና ቃዲዎችን በተያዩ የሸሪዓ የዕውቀት ዘርፎች አሰልጥኖ አስመረቀ። የኢማም አል ሻፊኢ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ መስራችና የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ኢማም አል ሻፊኢ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ እዚህ በመድረሱ መደሰታቸውን ገልጸው ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ለነበራቸው ባለ ድርሻ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። በተያዩ ሸሪዓዊ ዕውቀቶች የአቅም ግንባታ ክህሎት ሥልጠና ያጠናቀቁ የዛሬ ተመራቂዎች በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ሕዝበ ሙስሊሙን እንዲያገለግሉም ፕሬዝደንቱ አዳራ ብለዋል። የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ የፈተዋ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ሸይኽ ጀይላን ኸድር በበኩላቸው ጉባዔው በተያዩ የሸሪዓ ዕውቀት ዘርፎች የሰለጠነ የሰው ኃይል ለመፍጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ታጁዲን ኸድር በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ኢማም አል ሻፊኢ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ በሸሪዓ ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪ የሰለጠነ የሰው ኃይልን እያፈራ የሚገኝ አንጋፋ የሸሪዓዊ ትምህርት ተቋም ነው። ዩኒቨርስቲው እየሰጠ ያለውን ተከታታይ ስልጠና አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ አባልና የትምህርትና ካሪኩለም ዘርፍ ኃላፊ ተባባሪ ፕሮፌሰር አብደላ ኸድር ናቸው። የኢማሙ አል ሻፊኢ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ሙሀመድ ከማል ቲልሞ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን ያለውን የኢልም ሽግግር ከማስቀጠል ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰው ዩንቨርስቲው ከመደበኛ ስራው ባሻገር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የመህበረሰብ ክፍሎች ከሃያ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ ተናግረዋል። ዋና መቀመጫውን አዳማ ከተማ አድርጎ ለዓመታት በርካታ ተማሪዎችን በተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች በማስተማር ላይ የሚገኝ ዩንቨርስቲው በዘንድሮው የትምህርት ዘመንም በአራት ፋኪሊቶዎች 300 ወንዶችን እና 205 ሴት ሰልጣኞችን በዲግሪ መርሀ ግብር ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል። በስልጠናው ከፍተኛ ውጤት ላስመዝገቡ ሶስት ሰልጣኞች ነጻ የዑምራ ሽልማት የተሰጣቸው ሲሆን በምርቃት መርሀ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማእ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍን ጨምሮ የዩንቨርስቲው እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል መጅሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ታላላቅ ዑለማዎች፣ ዑስታዞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤትን ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ይከታተሉ | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1