cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

በዚ ቻናል ደብዳቤዎች - ወግ ትረካዎች ግጥሞች -በድምፅ፣ በፅሁፍ አነቃቂ ንግግሮች አስተማሪ ታሪኮች እና ሀሳቦች ይቀርቡበታል። "መኖር ጥሩ ነው.... ሀሳብና አስተያየት እቀበላለው (ኪያብ) @Jerrysisayyy @itsmejerrymejerry

Ko'proq ko'rsatish
Efiopiya6 860Amxar6 264Toif belgilanmagan
Reklama postlari
643
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-57 kunlar
-3030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼            ~~~ እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ: ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ። እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን::                                                    መልካም አዲስ ዓመት!        🌼እንቁጣጣሽ                                                                🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በሰላም ብርሀን ያማረ፥ ጤናን ከደስታ ያጣመረ፥ በስኬት በድል የታጀበ...ዓዲስ ዓመት ይሁንልን🙏        ✍ #ዮቶራዊት     @Mahder_Kasahun
Hammasini ko'rsatish...
🌿#አንጀት_አርስ_እውነታ! ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡ እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡ አስታውሳለሁ ፥ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝ ዝና ፥ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 አመት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡ አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 አመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡ ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡ እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡ @Human_intelligence
Hammasini ko'rsatish...
...........................🍂 ኪያብ🔉 አብርሃም ፍቅሬ የቅዳስ ልጅ
Hammasini ko'rsatish...
1.44 KB
.................................. ከረጅም አመት ቡኋላ እመጣለው…የዛኔም ግን እንደድሮ ሆኜ አደለም…አንቺ ማነሸ?…የት ነበርሽ?…ትለኝ ይሆናል…እኔም አንገቴን ደፍቼ እምልህ ነገር ቢኖር…"እያለሁ መች ነበርክ? ነው ስኖርልክ መቼ ኖርክልኝ ነው መልሴ
Hammasini ko'rsatish...
ስላንተ ነው የማወራው ስላንተ ብጣሽ ሀሳብ ብጣሽ ልብ የለኝም የነበረኝ ፍቅር ረቂቅ መሆኑ አሁን ድረስ ያስገርመኛል ባይገርም ቆፍጣና ሆኛለው ማለቴ ልበ ደንዳና ጀግንነት አይደለም አውቃለው ግን መልካም ነው ይመቻል ኪያብ
Hammasini ko'rsatish...
; የተሰላቸ ስሜት ይሰማኛል አዲስ ነገር ማጣት: ከደስታ መራቅ.. ከሰዎች ጋር ማውራት መሳቅ መጫወት እነዚ እኔጋ አለመኖራቸው ስልቹ አድርጎኛል..ራሴን መሸወድ ላይም የተካንኩ እንድሆንኩ ታዝቢያው..... ከጠፋችው ኪያብ🍂
Hammasini ko'rsatish...
ክፍል ፬         በ #ሄኖክ_በቀለ ✍     ታላቁ ልጄ እንደምታውቁት የቀኝ እጁ አራት ጣቶች ቆራጣ ናቸው። የእርሱ ታናሽ ደግሞ እጁም እግሩም ላይ ስድስት ስድስት ጣት አለው። ይህ እንዴት ሆነ? ሲቀለድብኝ መሆኑ ነዋ! .....አንድ ቀን ጠዋት የጀመርሁ ሥራ ፍለጋ ስንከራተት ውዬ ሰውነቴ ዝሎ አመሻሽ ላይ ቤት ደረስኩ። ምንም ምንም ሳልል፤ እህልም ሳልቀምስ፤ ልብሴንም ሳላወልቅ መጥረቢያዬን ቆጥ ላይ ሳልሰቅል ተኛሁ። ብዙም አልቆየ ታላቅ ልጄና ነፍሰጡር ሚስቴ በጩኸት ቤቱን ሲያናጉት ብትት ብዬ ተነሣሁ። ሳይ ከልጄ መዳፍ ላይ ደም እንደወራጅ ውኃ ይንዠቀዠቃል። ዘልዬ አፈፍ ሳደርገው አራት ጣቶቹ ተራ በተራ ጠብ፣ ጠብ ብለው እንደጉድፍ መሬት ላይ ወደቁ። ያ መጥረቢያ ከንፈሩ ደም ጠግቦ ተጋድሟል። የሆነው ወዲያው ገባኝ። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ከረፈደ ዕውቀት የቀደመ ጠርጣራነት እንደሚበልጥ ማን አስተምሮኝ  ያኔ? ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር አይደለሁ። አንድ ቀን መጥረቢያዬን ማራቅ ብረሳ... ። ዛሬም ድረስ አውራ ጣቱ በመዳፉ ላይ ብቻዋን ፍርፍር ስትል ሳያት እንባዬ ይመጣል። ጠማማ ዕድሌን መግራት ተስኖኝ እንዳጎደልሁት ይሰማኛል!”     "ይበቃል ተብለሀል።"      “አይበቃኝም ገና መች ጀመርኩትና?! ኋላ ስንቀዠቀዠ ቤቱ ሄድኳ። ምነው ፈጣሪ ምነው ሳምንህ ጉድ ሠራኸኝ? ስል አለቀስሁ። ስለትህን አጉድዬ አውቃለሁ? የምበላው ባጣ እንኳ አሥራትና መባህን ነክቼ አውቃለሁ? ውለታ አታውቅም? አምላክ አይደለህም ተንደርድረህ ከሰው ልታንስ ነው? ምነው እኔን እንዳሻህ ብታደርገኝ? ምነው ልጆቼን ብትተውልኝ?” አልኩት። ሞኝ፣ የሞኝ ዘር አይደለሁ? ...የሰማኝ መሰለኝ። “አይዞህ ያለኝ መሰለኝ። “ይቅርታህን! የዛሬን ብቻ እለፈኝ ትቼሃለሁ” ያለኝ መሰለኝ። “ታርቀናል” ብዬ እንባዬን ጠርጌ ተነሣሁ። ቤት ስደርስ ያቺ ወረግቡ ሚስቴ ስታምጥ ደረስኩ። ቀበቶዬን አላልቼ የምትሰጥም አንተ፤ የምትነሣም አንተ ተመስገን!” አልሁት። ክፋቱን ረሳሁለት። ሚስቴ ምጥዋ ሳይጠና ተገላገለች። ቆንጅዬ ወንድ ልጅ በጨርቅ ጠቅልለው አሳቀፉኝ። ሳይደግስ አይጣላም!” ይሉ የለ የእኛ ሀገር ሰዎች? ...ደጋጎቹ። “መከራዬን አይተሃልና ኀዘኔን በሳቅ፣ ለቅሶዬን በደስታ ቀይረሃልና” ስል ስሙን ካሣ አልኩት። የካሠኝ መስሎኝ! አይ ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር ...ቶሎ አይነቃም እኮ።      ያዋለደችው ሴት በደስታ የምሆነውን ሲያሳጣኝ ፊቷን ጨምታ ስታየኝ ጠረጠርኩና ጨርቁን ገለጥሁት። በእጆቹ በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች አሉ። ስድስተኛ ሆነው የበቀሉት እንደሌሎቹ ጠንካራ ስላልሆኑ ወዲያና ወዲህ ተንከርፍፈዋል። ደነገጥሁ። ከማዘን ማበድ ቀረበኝ። ጣቱ ስድስት መሆኑ አይደለም፤ ነገረ-ሥራው ገርሞኝ እንጂ። የታላቁን አራት ጣት ነሳኸኝ ብዬ “ምነው?” ስላልኩት ካሣ ላይ መመለሱ ነው? ይሄ ቀልድ እንጂ ሌላ ምን ይሆናል? ድርቅ በጎርፍ ይካሣል? ሥርጉዳት በእባጭ ይሣሳል? ኧረ እንዲህም አድርጎ ቀልድ የትም የለ!      ሽማግሌው የግራ ጆሯቸውን፤ ከፊቶች አንዱን እያከኩ ተነሡ።      “እንግዲህ ሰማንህ 'ዕድሉ'። ለሰሚ የቸገረ ነገር ነውና የሸንጎውን ሐሳብ አድምጠን ፍርዱን ለዋናው ዳኛ እንሰጣለን።  ወደ ሸንጎው ዞረው  ፈጣሪና መጥረቢያ አጥፍተዋል። ፍርድ ይገባቸዋል? የምትል እጅህን አውጣ ተብለሃል!”            ይቀጥላል.........     @Mahder_Kasahun🦋
Hammasini ko'rsatish...
የሰካራም ግጥም 🎤Hሀበሻman
Hammasini ko'rsatish...
2.37 MB