cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የስብዕና ልህቀት

በዚህ ቻናል ⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች ⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች ⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች ⚡ውብ የጥበብ ስራዎች በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ። #ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ko'proq ko'rsatish
91 364Obunachilar
-2724 soatlar
-2607 kunlar
-1 59630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Обуначиларнинг ўсиш даражаси

Ma'lumot yuklanmoqda...

“ጅል አይሙት እንዲያጫውት!” ከአሌክስ አብርሀም መፅሀፍ-አልተዘዋወረችም በአገራችን ባህል የዝምታ ትርጉም ግራ የገባው ነው፡፡ እውነት በአደባባይ ሲደፈጠጥ እያዩ አፍን መሸበብ፤ ግን ደግሞ በስሚ ስሚ ለመጣ አሉባልታ ነፍስን ጭምር መስጠት። ጮኾ የማያወራ፣ ሐሳቡን የማይገልጽ ሕዝብ የሐሜት ጫካ ነው። በየጋራና ሸንተረሩ ጥይት ከማስጮኸ የበለጠ፣ ጮኽ ብሎ ያመኑበትን መናገር የሚከብደው ሕዝብ ጀግንነቱ ከባድ ጥያቄ ውስጥ ነው፡፡ በዝም አይነቅዝም ብሒል የነቀዘ ሕይወት እንመራ ዘንድ የፈቀድን ሕዝቦች መሆናችን ሳያንስ ይኽንንም ባህል አድርገን ልንኮራበት ይዳዳናል፡፡ ይኼ ተወልጄ ያደግሁበት ሕዝብ በሹክሹክታ ያወራል፣ ጓዳ ለጓዳ ያወራል፣ እውነት ይሁን ውሸት አግበስብሶ ያወራል፣ እንደ ወረርሽኝ ወሬ በብርሃን ፍጥነት ያዛምታል፣ በአደባባይ ግን ዝምተኛን ያደንቃል- ያበረታታል፡፡ በተረቱ “ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም” እያለ  ዝንብ ፈርቶ ዝም (እንዴት _ ለዝንብ ዝም ይባላል? ለምን ሰፈራችሁን አጽድታችሁ እንደልባችሁ አታወሩም? የሚል የማሪያም ጠላት ነው!) መንግሥትን ፈርቶ ዝም (እንዴት ዝም በሉ ለሚል መንግሥት ዝም ይባላል አፋኝ መንግሥት እጁን ከአፋችን ላይ እንዲያነሳ መንገር የለብንም ወይ? የሚል የአገር ጠላት ነው) ይሉኝታን ፈርቶ ዝም (እንዴት በይሉኝታ እንለቅ? ብንል የባህል ጠላት መባል ይመጣል፡፡) ሁሉም ስሕተትና ፍርኃታችን እንደ ትልቅ ሐብት በእሳት ሰይፍ ተከቦ የሚጠበቅ ቅርስ ነው፤ እውነት ብቻ ነው ራቁት፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም እውነት የእብዶችና ሰካራሞች ልፈፋ ተደርጋ በየመድረኩ የምትሳለው፡፡ እብዶች እውነቱን እንዲናገሩለት “ጤነኛው' ከፍሎ ይታደማል፡፡ ይኼ ባህላችን ሲሆን ከያኒ የነፍሱን ጥሪ ጥሎ የጅሎች አፈቀላጤ ይሆናል፡፡ ታዲያ የዚህ ሁሉ ምክንያት ፍርኃታችን ቢሆንም፣ ይኼንንም በሰበብ ስንጀቡነው (መቼም ሰበብ አናጣ) “ዝምታችን ትዕግስት የወለደው፤ ትዕግስታችንም አምላካችንን የምንፈራ ሕዝቦች ስለሆንን የተጎናጸፍነው ጸጋ ነው” እንላለን፡፡ እውነታው ግን አምላክን መፍራታችን ሳይሆን ፍርኃትን ማምለካችን ነው። በዚህ ሁሉ ዝምታ ውስጥ የታቀፈ ጅልነት ድርጊት ሆኖ ሲፈለፈል ከግለሰብ እስከ አገር ስንት የጨነገፈ ኑሮ ፈጠረ!? ታዲያ የራሳችን ዝምታ ተጠራቅሞ ሲከብደንና አላራምድ ሲለን፤ በየዘመኑ ጊዜና ሁኔታ እየጠበቅን በጋራ እንጮኻለን። የጨረባ ተዝካር! ይኼን ዓይነቱን ጩኸት አብዮት እንለዋለን (የታዘዙትን ሁሉ እሺ! እያሉ አብዮት አለ ወይ?!) ነገሩ ልክ ውሃ ውስጥ የተነከረ ውሻ፣ ውሃውን ከላዩ ላይ ለማራገፍ በደመነፍስ እንደሚርገፈገፈው ዓይነት ነው፤ ውሃው ቢራገፍም ውሻው ያው ውሻ ነው፡፡ አጯጯኻችን በአንድ ላይ በየአፋችን ስለሆነ ማንም ማንንም አይሰማም፤ ማንም የማይሰማው ጩኸት ደግሞ ከዝምታ እኩል ነው፡፡ ይኼ ዝምታ፣ የጅል ባንዲራ እንጂ ጨዋነት አይደለም። ባንዲራችን ከፍ ብሎ የሚውለበለበው ለዘመናት በተከመረና በደደረ ጅልነታችን ላይ ይመስለኛል፡፡ የባንዲራችንን ቀለም እየጠቀስን የማንሰጠው ትርጉም የለም። ሁሉንም ቀለም እንደ ዳማከሴ ጨቅጭቀን ብንጨምቀው ከጀግንነታችንም በፊት፣ ከኩሩነታችንም በፊት፣ከአገር ፍቅራችንም በፊት የሚንጠባጠበው ጅልነታችን ሳይሆን ይቀራል?! እሱን እየተቀባን ስንት ጊዜ ከዘመን በሽታ ተፈወስን ብለናል?! ፈውሳችን ሐሰት ነበርና ምስክርነታችን የታተመበት ቀለም ሳይደርቅ፣ ብዙዎች በነጠላም በጅምላም የጅል በትር ሰለባ ሆነው ወደ መቃብር ወርደዋል፡፡ የተረፍነው እንዴት ተረፍን? እያልኩ ሳስብ፣ አንዳንዶች “ምሕረቱ በዝቶልን'' ቢሉም እኔ ግን ፈጣሪም ከዚህች ከኛ ምድር በተዋሰው ተረት “ጅል አይሙት እንዲያጫውት!” ብሎ ለአጫዋችነት ትቶን ይሆናል እላለሁ፡፡ አገሬ ጨዋታና ተጨዋች ይበዛታል፡፡ እንደ አገር ልጅነታችንን አልጨረስንም ይሆን? እስከምል ድረስ የአገሬ ጨዋታ ወዳድነት ያስደምመኛል፡፡ ጅልነቴ ከሕዝብ ባሕር የተቀዳ ነው ስል፣ ለጥፋቴ ሌላ የሕዝብ ክንብንብ ውስጥ መደበቄ አይደለም፤ ምንስ ቢሆን ሕዝብ የሚባለው አጀብ ለሚሊዮኖች ቢሰነጣጠር አንዱ ስንጣሪ መሆኔ አይቀር፡፡ ሕዝባዊ ጀግንነት፤ ሕዝባዊ ታሪክ እንዳለ ሁሉ ከየቤታችን አዋጥተን አገራዊ ያደረግነው ሕዝባዊ ጅልነት አለመኖሩን ማን አጥንቶ ነገረን?! ጅልነት ቀለም ነው፤ ታሪካችን እኛም በግልና በጅምላ አማርን ብለን የተቀባነው የተኳኳልነዉ ጠይም ቀለም፡፡ በዚህ ጠይምነት በኩል ስለተገለጠ ግለሰባዊ ጅልነቴ በጸጸት አወራለሁ... በጓዳዬ ለአገር ያዋጣሁት የጅልነት ድርሻ... ይኽም ከንስሓ ይቆጠር እንደሆን እንጃ፡፡ @zephilosophy @zephilosophy
Hammasini ko'rsatish...
👍 50 5👏 2😢 2
ጣፋጩ ገዳይ መርዝ! በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል። ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም። ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው:: በተቻለህ መጠንም ከስራህ እና ከማሰብ ከሚያስተጓጉሉህ ነገሮች ሁሉ ለማራቅ ሞክር። ድብቁ አእምሮ ድብቁ ኃይል @Human_Intelligence
Hammasini ko'rsatish...
👍 90🔥 30 8
👍 93 17🙏 5🔥 3
ለፍልስፍና አፍቃሪዎች ድንቅ ቻናል 👇👇👇 @Zephilosophy ፍልስፍና ለነፃ አስተሳሰብ https://t.me/joinchat/RVzIu0-BTYG_XaN8 👆👆👆 በዚህ ቻናል ከተለያዪ የአለም ዳርቻዎች የተነሱ የታላላቅ ፈላስፋዎች አስተሳሰቦች እና ፍልስፍናዎች ይቀርባሉ።ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ፤ ከሰሜን እሰከ ደቡብ የአለምን የአስተሳሰብ ኮምፓስ የቀየሩ ፈላስፋዎች እና ሃሳቦቻቸው ከየመፅሀፉ እየተጨለፉ ለናንተ ይቀርባሉ። ከሶቅራጥስ እስከ ኒቼ ፤ ከቡድሃ እስከ ኦሾ ፤ ከማርክስ እስከ ሌኒን አለም ላይ የማይፋቅ አሻራዎቻቸውን ያሳረፋ ሰዎች ፤ ከክርስትና እስከ ቡዲሂዝም ፣ከእስልምና እስከ ሂንዲይዝም ፣ከሶሻሊስት እስከ ካፒታሊስት በዘመናት ውስጥ የተፈጠሩ ሀይማኖቶች ፣ስርዓቶች ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉ ይዳሰሳሉ። ለዓለም ያስገኙት ሞራላዊና መንፈሳዊ ትሩፋቶች ይወዳሳሉ። ታሪካዊ ህፀፆቻው ደግሞ ያለምህረት ይተቻሉ ፣ይወቀሳሉ። ፍልስፍናን ከተደበቀችበት ጓዳ አውጥተን በአደባባይ እናሰጣታለን። ማህበረሰቡ የሚሳሳላቸው ባህሎቹ እና እምነቶቹ በነፃነት ይጠየቃሉ ፣ይመረመራሉ ይፈተናሉ። እንደ ጣት ቁስል የተፈሩ እውነቶች መሀረባቸው ይገለጣል። እንደ ማህበረሰብ በጉያችን የጋረድናቸው እባጮች የግንባር ስጋ ይሆናሉ።ከግለሰብ እስከ ቡድን ፤ከሀይማኖት እስከ ርዕዮተ -ዓለም ፤ ከኋለቀር ባህሎች እስከ ዘመናዊ ስልጣኔዎች ያለምንም ፍርሃት በግላጭ ይሞገታሉ፣ ይመረመራሉ፣ይጠየቃሉ ውስጣቸው የተደበቀው እውነት እስኪገለጥ ድረስ በአውድማው ላይ መንሽ እየተፈለገ ፍሬው ከገለባ ይለያል። መንሻችን የሰላ አምክንዮዊ አእምሮ፣ የሰከነ የሞራል ልዕልና እና ንፁህ ሰዋዊ ህሊና ናቸው። Join 👇👇👇👇 @Zephilosophy @Zephilosophy
Hammasini ko'rsatish...
👍 25 2🔥 1
ለትናንት ማንነትህ ደብዳቤ ፃፍለት! (Note to self) (እ.ብ.ይ.) በዓለማችን በተለያየ የሙያ ዘርፍ ላይ አንቱ የተባሉና የስኬት ጫፍ ላይ የደረሱ አብዛኞቹ ሰዎች ለራሳቸው የማስታወሻ ደብዳቤ የመፃፍ ልማድ አላቸው፡፡ ደብዳቤው አንደኛ ራሳቸውን አይዞኝ ለማለትና ለማነቃቃት ጠቅሟቸዋል፤ እንደገናም ትናንትናቸውን በጥራት እንዲያዩት አጉሊ መነፅር ሆኗቸዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ልማድ ከነበራቸው ታዋቂ ሰዎች መካከል የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር፣ ታላቋ ተዋናይትና የቲቪ ሾው አቅራቢዋ ኦፕራ ዊንፍሬይ እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የታዋቂ ሰዎችን የግል ማስታወሻ ደብዳቤ በመሰብሰብ በመፅሐፍ መልክ ያሳተመችው ደግሞ የሲቢኤስ ዜና (CBS News) ጋዜጠኛ የሆነችው ጋይል ኪንግ (Gayle King) ነች፡፡ መፅሐፉንም ‹‹Note to self›› በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ 2018 ዓ.ም. ወርሃ ግንቦት ላይ ለአንባብያን አቅርባለች፡፡ በዚህ መፅሐፍ ከተጠቀሱት የማስታወሻ ደብዳቤዎቹ ውስጥ ቀልቤን የሳበው የምርጧ የቴሌቪዥን ሾው አዘጋጅና የፊልም ተዋናይት የነበረችው የአሜሪካዊቷ የኦፕራ ዊንፍሬይ ደብዳቤ ነው፡ ኦፕራ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት የወጣትነት ጊዜዋን ፎቶ እየተመለከተች ለራሷ ደብዳቤ ፅፋ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ሆና ትናንቷን ስታስታውስ ራሷን በራሷ እንዲህ ብላታለች፡- ‹‹ውዷ ባለቡናማ ቆዳዋ ቆንጅዬዋ ሴት ሆይ...›› ‹‹ቆንጆ የሚለውን ቃል ለራስሽ ተጠቅመሽ እንዳማታውቂ አውቃለው፡፡ በዓይኖችሽ ውስጥ የሕይወቴን ብርሃንና ተስፋ አይቻለሁ፡፡ የመጀመሪያውን የዜና ዘጋቢነት ስራ ስታገኚ ደስተኛ ነበርሽ፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ትጨነቂ እንደነበርም አስታውሳለሁ፡፡ በዛን ጊዜ ላንቺ የምልሽ የነበረው ‹‹አይዞሽ! በርቺ... ሁሉም ነገር በጎ ይሆናል (Relax, It’s going to be OK)›› የሚል ነበር፡፡ ይሄን ስራ በማግኘትሽ ሞራልሽና በራስ መተማመንሽ ጨምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ርግጠኛ አልነበርሽም፡፡ ገና የ10ኛ ክፍል የሃይስኩል ተማሪ በመሆንሽ ትምህርቱንና አዲሱን ቋሚ ስራሽን እንዴት አቀናጅተሸ እንደምትመሪው ግራ ተጋብተሸ ነበር፡፡›› ‹‹ከፊል የህይወት ዘመንሽን ያሳለፍሽው ሌሎች የሚፈልጉትን ለመሆንና እነሱን ለማስደሰት ነበር፡፡ ያ ነገር ለምን እንደሆነ ዛሬ እረዳሻለሁ፡፡ ገና በአፍላው እድሜሽ በዘጠኝ ዓመትሽ ተደፍረሽ፣ እስከ አስራአራት ዓመት እድሜሽ ድረስ እንወድሻለን ይሉሽ በነበሩ ዘመዶችሽና ወገኖችሽ እየተሰደብሽና እየተገፋሽ እንደኖርሽ አውቃለሁ፡፡ በስድባቸውና በንቀታቸው እንኳ የምትናደጂበትና የተቃውሞ ሃሳብ የምታሰሚበት አቅም አልነበረሽም፡፡ ጥሩ ያልሆነውን ስሜትሽን እንኳን ለመግለፅ የፈቀደልሽ የለም፡፡ ሁሉም ረጋሚሽና አውጋዥሽ ነበር፡፡ ይሄ ሁሉ ለራስሽ የሚኖርሽን ክብርና አመለካከት እንደሚንድ አውቃለሁ፡፡ አሁን ላይ ግን ብዙ ነገር ገብቶሻል፡፡ መከራውን ተሻግረሽ እዚህ ደርሰሻል፡፡ በራስሽ ልብ ራስሽን ወድደሻል፤ በገዛ ዓይኖችሽ ራስሽን አይተሻል፡፡ ሁሉን ነገር በአምላክሽ ደጋፊነት ችለሽ እዚህ ደርሰሻል፡፡ አሁን ላይ ሆኜ የህይወት ጉዞሽን ሳየው የምትፀፀቺባቸው ነገሮች ኢምንት ናቸው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ህይወትን ጥሩ አድርገሽ ኖረሻታል ማለት ነው፡፡ ስኬት ሂደት መሆኑንና ከታላቅ ድል በተቃራኒ መቆም አለመሆኑን ተረድተሻል፡፡ ውዴ ሆይ.. በአንቺ እንድኮራ አድርገሽኛል ....... ›› በማለት ያለፈችበትን የሕይወት ውጣውረድ መንገድ በዓይነህሊናዋ ተመልክታ በራሷ ኮርታለች፡፡ አዎ ትናንትናቸውን የተገነዘቡ አዋቂዎች፣ ዛሬአቸውን የተረዱ ብልሆች፣ ልብ ያላቸው አስተዋዮች፣ ወደውስጥ ማሰብ የሚችሉ ጥልቅ አሳቢዎች፣ ከራሳቸው ጋር መከራከርና መወቃቀስ የሚወዱ ምክንያታዊ ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው ለማየት ለራሳቸው ደብዳቤ ይፅፋሉ፡፡ ማስታወሻው አንድም ከትናንቱ ሕይወታቸው የሚጠቅመውን ልምምድ ለማስቀጠል፤ አንድም ካለፈው ውጣውረድ ትምህርት ለመቅሰም፤ አንድም ኋላቀር አስተሳሰባቸውን አስወግደው ወደፊት የሚያሻግራቸውን አመለካከት ለመፍጠር፤ አንድም የሚደነቀውን ማንነታቸውን ለማድነቅ ነው፡፡ ወዳጄ ሆይ.. ለትናንትናው ማንነትህ፣ ለልጅነት ሕይወትህ፣ ለትኩሱና ለወጣቱ አንተነትህ የምትጽፍለት ማስታወሻ ምንድነው? የምትናፍቀው ማንነት የለህም? የምትፀፀትበት አንተነትህ የየትኛው ዕድሜ ማንነትህ ነበር? ሕይወትን በራስህ መንገድ ኖረሃል? ራስህን ለማስደሰት ነው ወይስ ለሌሎች ደስታ ነው አቅምህን የጨረስከው? በሰው ሃሳብ ነው እድሜህን የገፋኸው? የትናንት አንተነትህን ታስታውሰዋለህ? ዛሬ ላይ ሆነህ ለትናንቱ ራስህ የምትለው ነገር የለም? እንዴት ነበር ንዴትህን የምትገልጸው? ከሀዘንህ በምን ጉልበት ነበር የምትፅናናው? ማግኘትና ማጣትን እንዴት አስተናገድካቸው? ሀዘንህን እንዴት አለፍከው? ድንገቴ ውድቀትህን በምን ተቋቋምከው? ጉርምስናህን በምን አመክንዮ ነው ያስተዳደርከው? ይዘህ የኖርከውን ሃሳብና ማንነት በማስታወሻህ አልገመገምከውም? የመጣህበት መንገድ ጎርበጥባጣ ነበር? በወፍ በረር ቅኝት ራስህን፣ ህይወትህን፣ ትናንትህን፣ ትዝታህን፣ ልጅነትህን፣ ጉርምስናህን፣ ጉልምስናህን፣ እሳቱ ጊዜህን መለስ ብለህ አይተኸዋል? እስቲ ለራስህ የማስታወሻ ደብዳቤ (Self note) ፃፍለትማ.......! ቸር የሕሊና ማስታወሻ! ኢትዮጵያና ኢትጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ! _____ እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.) @Human_Intelligence
Hammasini ko'rsatish...
👍 61 24🙏 1
48👍 21
የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ! ሕይወታችንን ማስመለስ ማለት በአጭሩ ሲተረጎም በአንድ ሰው፣ ሁኔታ ወይም ልምምድ ምክንያት ከደረሰብን ቀውስ የተነሳ በትክክል ማሰብ፣ መስራት፣ መተኛትም ሆነ መኖር እስከማንችል ድረስ የደረሰውን ሁኔታችንን እንደገና ወደቀድሞው ጤናማ ሁኔታ ማስመለስ ማለት ነው፡፡ •  የጎዳችሁና እስክትበቀሉት ድረስ ውስጣችሁን የሚያናድደው ሰው የወሰደባችሁን ሕይወታችሁን አስመልሱ! •  ሰዎችን አምናችሁ በተወሰደባችሁ ቁሳቁስ ወይም ገንዘብ ምክንያት ዘወትር ከመቆጨታችና ከመቆዘማችሁ የተነሳ የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ! •  አፍቅራችሁ ትንሽ ከተጓዛችሁ በኋላ ያ ሰው ለእናንተ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ብትደርሱበትም ካላችሁ የስሜት ትስስር የተነሳ ልትረሱት ባልቻላችሁት ሰው የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!   •  ማንኛውንም ሰውም ሆነ ሁኔታ ከመፍራታችሁ የተነሳ ወደፊት መራመድ እስከማትችሉ ድረስ በመሆናችሁ ምክንያት የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ! ወደራሳችሁ ተመለሱ! ወደቀደመው ሰላማችሁ ተመለሱ! ወደእውነተኛው ማንነታችሁ ተመለሱ! ከምንም ሁኔታና ከማንም ሰው ጫና ውጪ ወደነበራችሁበት ሚዛናዊ ሕይወት ተመለሱ! ንቁ! ወስኑ! ምክርና እገዛን ፈልጉ! የድሮውን ጤናማ ማንነታችሁን እንደገና የራሳች አድርጉ እንጂ የሰውና የሁኔታዎች ሰለባና መጫወቻ አትሁኑ! መልካም ቀን! Dr eyob
Hammasini ko'rsatish...
👍 79 30👏 2
#የተፈጥሮ_ዑደት በተፈጥሮ ዑደት ውስጥ ድል ማድረግም ሆነ ድል መሆን የሚባሉ ነገሮች የሉም። ያለው እንቅስቃሴ ብቻ ነው:: ክረምት ከሁሉም የበላይ ሆኖ እስከመጨረሻው ለመዝለቅ ይጣጣራል:: ሆኖም ጊዜውን ጠብቆ የፀደይን ተተኪነት ከመቀበል በቀር አማራጭ አይኖረውም፡፡ ፀደይም አበቦችን እና ፍካትን እንዲሁም ደስታን ይዞ ከተፍ ይላል። በጋውም ቢሆን ሞቃታማ ቀናቱን ለዘለዓለም ለማዝለቅ መውደዱ አይቀርም:: ነገር ግን የበልግን መምጣት ተቀብሎ ስፍራውን አስረክቦ ዘወር ይላል:: በልግም ምድሪቱ ታርፍ ዘንድ እድል ይሰጣታል:: አጋዘን ሳርን ብትበላም እርሷ ራሷ የአንበሳ ምግብ ናት:: ይህ የጥንካሬ ጉዳይ አይደለም:: ማን ይበልጥ ይበረታል ስለማለትም አይደለም:: ይልቁን አምላክ የሞትንና የትንሳኤን ዑደት ለእኛ የሚያሳይበት መንገድ ነው:: በዚህ ዑደት ውስጥም አሸናፊም ተሸናፊም የለም:: መታለፍ ያለባቸው ደረጃዎች ብቻ እንጂ። የሰው ልጅ ልብ ይህንን እውነታ ሲረዳ ነፃ ይሆናል፤ አስቸጋሪ ወቅቶችን ለማለፍ አያዳግተውም፤ በድል አድራጊነት የሞቅታ ስሜትም አይታለልም:: ሁለቱም አላፊ መሆናቸውን አይዘነጋም:: አንዳቸው በሌላቸው ይተካሉ:: ዑደቱም ይቀጥላል:: ስለዚህ የፍልሚያ ቀለበት ውስጥ ያለ ቡጢኛ (የራሱ ምርጫ አሊያም ሊመረመር የማይችል እጣ ፈንታ እዚያ ያስገኘው) ከፊት ለፊቱ በሚጠብቀው ፍልሚያ ተስፋ በደስታ ስሜት ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፡፡ ክብሩንና ግርማውን መጠበቅ ከቻለ ፍልሚያውን ቢሸነፍም እንኳ ተሸናፊ ሊባል አይችልም:: ምክንያቱም መንፈሱ ምንም አልተሸራረፈምና። ስለደረሰበት ነገር ሁሉ ሌሎችን መውቀስን ሙጥኝ አይልም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍቅሮ፤ የፍቅር ጥያቄው ውድቅ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ይህ ውድቀት በእርሱ የማፍቀር ችሎታ ላይ ያመጣው አሉታዊ ለውጥ እንደሌለ ያውቃል:: በፍቅር ውስጥ እውነት የሆነው ሁሉ በጦርነት ውስጥም ይሰራል። ፓውሎ ኮሆልዮ @Human_Intelligence
Hammasini ko'rsatish...
👍 72 17👏 4
ልክ እንደ ቡናው! በአንድ ወቅት አንዲት ወጣት ወደ እናቷ በመሄድ ኑሮ እንደከበዳትና ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ ላይ እንዳለች ነገረቻት፡፡ “አንዱ ችግሬ አበሳጭቶኝ ሳልጨርስ ሌላ ይተካል፣ በእርሱኛው ደግሞ ውስጤ ተጎድቶ ገና ሳላገግም ሌላ ይጨመርብኛል” በማለት ከፍቅር ሕይወቷ ጀምሮ እስከ ሌሎች አስቸጋሪ ገጠመኞቿ ስሜታዊ በሆነ መልኩ አንድ በአንድ ገለጠችላት፡፡ በጥበቧ የምትታወቀው እናት፣ ወደ ልጇ ጠጋ በማለት ዳበስ አድርጋት ፍቅሯን ከገለጠችላት በኋላ አሁን ለጊዜው ተረጋግታ ስራ እንድታግዛት ጠየቀቻት፡፡ ልጅ ፈቃደኝነቷን ከገለጸች በኋላ እናት ምንም ጊዜ ሳታባክን አንድን ነገር እነድታደርግ ለልጇ አዘዘቻት፡፡ “ሶሰት ድስቶችን ውኃ በመሙላት በምድጃው ላይ ጣጂ” አለቻት፣ እናት፡፡ ልጅ የተባለችውን ለመፈጸም ወዲህ ወዲያ ማለት ጀመረች፡፡ ያንን ካደረገች በኋላ በመቀጠልም በእያንዳንዳቸው ውስጥ የተለያዩ ነገሮችን እንድትጨምርባቸው ነገረቻት፡፡ “በአንዱ ድስት ውስጥ አንድ ካሮት ጨምሪበት፡፡ በሚቀጥለው ድስት ውስጥም እንደዚሁ አንድ እንቁላል ጨምሪበት፡፡ በሶስተኛው ውስጥ ደግሞ የቡና ዱቄት ጨምረሽ ነይና ንግግራችንን እንቀጥል”፡፡ ልጅ የተነገራትን ካደረገች በኋላ ወደ እናቷ መጥታ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡ ከተገናኙ ሰንበት ስላሉ ብዙ የሚነጋገሯቸው ነገሮች ነበሩና ሳያስቡት ቆየት አሉ፡፡ ይህንን ሁሉ ስታደርግ እናት ምን ለማድረግ እንደፈለገች በሚገባ ታውቅ ነበር፡፡ ከዚያም እናት በድንገት ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው፣ “የጣድሻቸውን ድስቶች ረሳሻቸው እኮ!” በማለት ልጇን አስታወሰቻት፡፡ ልጅ በፍጥነት ወደድስቶቹ በመሄድ ምድጃውን አጠፋችና ወደ እናቷ ተመለሰች፡፡ እናትም፣ በይ ተመለሺና ያበሰልሻቸውን ሶስቱንም ነገሮች አንድ በአንድ ይዘሽ ነይ አለቻት፡፡ ልጅም ሳህን ካመጣች በኋላ ካሮቱንና እንቁላሉን በጥንቃቄ ከድስቱ ውስጥ በማውጣት አመጣች፡፡ ተመልሳ ቡናውን ለማምጣት ከመሄዷ በፊት እናት ለልጇ በእንቁላሉ እና በካሮቱ ላይ ያየሽውን ለውጥ ንገሪኝ አለቻት፡፡ ልጇም በመጀመሪያ ካሮቱን ከነካካችና ካጤነች በኋላ፣ “ወደ ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ጠንካራ ነበር አሁን ግን በጣም ለስላሳ ሆኗል” አለቻት፡፡ በመቀጠልም እንቁላሉን ከነካካች በኋላ ቀድሞ እንደነበረ ስላገኘችው፣ “እንቁላሉ ምንም ለውጥ የለውም” አለቻት፡፡ እናት ግን በመመለስ፣ “የእንቁላሉን ላይ ላዩ እንጂ ውስጡን አላየሽውም” አለቻት፡፡ ልጅም እቁላሉን ሰበር ስታደርገው ውስጡ ጠንክሮ አገኘችው፡፡ ስለዚህም፣ “ወደ ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ውስጡ ፈሳሽ እንደነበረ እርግጠኛ ነኝ፣ አሁን ግን ጠንክሯል” አለቻት፡፡ በመጨረሻም ለልጇ፣ “አሁን የቡናውን ዱቄት ከድስት ውስጥ አውጪና አምጪው” አለቻት፡፡ ልጅ ትንሽ ግር አላት፡፡ “ቡናው ከውኃው ጋር ተዋህዷል፣ እንዴት አመጣዋለሁ?” ብላ አሰበች፡፡ በዚህ ሃሳብ ተመስጣ ወደ ቡናው ስትሄድ፣ መዋሃድ ብቻ አይደለም ቡናው የውኃውን መልክ፣ መዓዛና ጣእም ሙሉ ለሙሉ ለውጦታል፡፡ ከዚያም ቡናውን በሁለት ስኒዎች በመቅዳት ወደ እናቷ ወስዳ እያጣጣሙት መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡ ልጅ እናቷን፣ “ምን አስበሽ ነው ይህንን ሁሉ ያስደረግሽኝ?” አለቻት፡፡ “አየሽ”፣ አለች እናት፤ “እነዚህ ሶስት ነገሮች አንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለፉት፣ በፈላ ውኃ ውስጥ፡፡ ካሮቱ ካለፈበት ሁኔታ ምንም ነገር መቋቋም እስከማይችል ድረስ እጅግ ለስላሳ ሆነ፡፡ እንቁላሉ ደግሞ ካለፈበት ሁኔታ የተነሳ ውስጡ ጠነከረ፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች በገቡበት ሁኔታቸው ተጽእኖ ስር በመሆን ባህሪያቸው ተለወጠ፡፡ ቡናው ግን በገባበት ሁኔታ ላይ ተጽእኖ አመጣ፡፡ የገባበትን ቦታ ጣእም፣ ጠረንና እንዲሁም ቀለም እንደለወጠው ተመልክተሻል፡፡”  እናት በመቀጠል እንዲህ አለቻት፣ “አንቺም በምታልፊበት ሁኔታ ያለሽ ምርጫ ከሶስቱ አንዱ ነው፡፡ 1.  ልክ እንደካሮቱ አጉል ልፍስፍስና በሁሉም ነገር የሚጎዳ አይነት ሰው እንዳትሆኚ ልታስቢበት ይገባል፡፡ 2.  በተቃራኒው የምታልፊበት ሁኔታ ልክ እንደ እንቁላሉ ውስጥሽን አጉል ጠንካራና ደንዳና እንዳያደርገው ተጠንቀቂ፡፡ 3.  ከእነዚህ ሁኔታዎች ይልቅ የተሻለው መንገድ በምታልፊበት ሁኔታ ሁሉ በቀላሉ የሚነካና የሚፈርስ ደካማ ወይም ከጉዳት የተነሳ አጉል “ጠንካራ” እና አትንኩኝ ባይ ሳትሆኜ ልክ እንደ ቡናው ሁኔታውን የምትለውጪ የተጽእኖ ሰው ልትሆኚ ይገባል”፡፡ ዶ/ር እዮብ ማሞ @Human_Intelligence
Hammasini ko'rsatish...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👍 25 4
በ1237 ዓ.ም አካባቢ ከሦስት መቶ ዘመናት የዛግዌያን አገዛዝ በኋላ ሥልጣን በቤተክርስቲያን ጠንካራ ተጽዕኖ ከዛግዌ ነገሥታት ወደ የዘር ሀረጋቸውን ከሰሎሞን ዘር እንመዛለን ለሚሉ ሰሎሞናዊ ነገሥታት ተዛወረ፡፡ የዛግዌ ነገሥታትን ሥልጣኑን ለሰሎሞናዊው ገዥ ይኩኖአምላክ እንዲያስተላልፉ በመወትወት፣ በመገሰጽ አቡነ ተክለኃይማኖት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል፡፡ በሂደቱም ቤተክርስቲያን እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ የዘለቀ የክፍለዘመናት የሢሶ መንግሥትነት ፈላጭ ቆራጭነቷን አጸናች፡፡ ጥቂት ቆይቶ በ330 ዓ.ም አካባቢ የሰሎሞናዊ ስርወመንግሥቱን በትርክት እና በሕግ ለማጽናት ሲባል ‹ክብረነገሥት› የተሰኘው መጽሐፍ የመጻፉ አስፈላጊነት ታመነበት፡፡ መጽሐፉ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ ሥልጣን ባለቤቶች የዘር ሀረጋቸውን ከንጉሥ ሶሎሞን እና ከቀዳማዊ ምኒሊክ ዘር የሚመዙ ብቻ መሆናቸውን በማያሻማ ኹኔታ ይደነግጋል፡፡ በዚህም መጽሐፍ የተነሳ ኢትዮጵያን ሀገራቸውን እንደዳግማዊት ኢየሩሳሌም እንዲመለከቷት ተበረታተዋል፡፡ ለዘመናት በክርስትና እምነት መነሻነት በተገነባው በዚህ ትርክት እና በክርስትው ኃይማኖት ምክንያት ከኢትዮጵያ ውጭ በኢትዮጵያዊያን (በሰሜነኛው ክርስቲያን) አዕምሮ የታተመች ሌላ ከተማ (ሀገር) ብትኖር ኢየሩሳሌም ብቻ ናት፡፡ በዚህ ሰበብ ይመስላል ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት ከውጭው ዓለም የመጣውን ሰው በተለይ ክርስቲያኑን ሁሉ የኢየሩሳሌም ሰው እንደሆነ ይቆጥሩ እንደነበር በልዩ ልዩ ተጓዦች ማስታዎች ላይ ተዘግቧል፡፡ በዚህ መልኩ በአስራ አራተኛው መቶ ክፍለዘመን መጀመሪያ የተጻፈው ክብረነገሥት ከፊውዳል ሥርዓቱና ከቤተክህነቱ ጋር ተቀይጦ በኢትዮጵያ የሥነ መንግሥት ታሪክ ሰባት መቶ ዘመናት ድረስ የዘለቀ ገዥ ትርክትን ፈጠረ፡፡ ይህ ትርክት በተለይ ከሞላ ጎደል በአንድ አገዛዝ ሥር የሚያድር፣ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን የሚናገር በአብዛኛው የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነውን ሰሜነኛ ሕዝብ ለሰባት ክፍለዘመናት ያስተዳደረ መሪ ትርክት ሆኖ አሳለፈ፡፡ ዳግማዊ ምንይልክ የተበታተነውን የዳር ሀገር ሕዝብ ሁሉ በአንድ አጠቃለው በዘውዳዊ ሥርዓቱ ሥር ካስገቡትም በኋላ በዚህ ትርክት ሥር እንዲመላለስ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ሙሉ ለሙሉ የሰመረ ነበር ባያስብልም ቢያንስ በእሳቸው ዘመን ትርክቱ የአንድነት ስሜት በመፍጠሩ የአድዋ ጦርነትን የመሰለ በተባበረ ከንድ የተገኘ እጅግ አንጻባራቂ ገድል ለመከወን መሣሪያ ሆኗል፡፡ ኢጣሊያኖች ኢትዮጵያን ዳግም የወረሩ ሰሞን በቅኝ ገዥ ሴራ ሕዝቡን ለመከፋፈል አማርኛ ተናጋሪውን ሕዝብ በጅምላ የፊውዳል ሥርዓቱ ተጠቃሚ እና ጨቋኝ ገዥ መደብ እንደሆነ ፈርጀው ትርክታቸውን ማጠንጠን ጀመሩ፡፡ ይህ ትርክት በተለይ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ድፍን ሃያ ሰባት ዓመታት በሕገመንግሥት፣ በመንግሥት በጀት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃናት በይፋ እና በስውር እንደ አስፈላጊነቱ ይቀነቀን ነበር፡፡ በበኩሌ ሰሜነኛው ሕዝብ ለፊውዳል ሥርዓቱና ለአገዛዙ በነበረው ጂኦግራፊያዊ ቅርበት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ በተለዬ ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ ከሁሉም በላይ በሥርዓቱ ይበደል እንደነበር አስባለሁ፡፡ ከ2010 ዓ.ም በኋላ የመጣው አስተዳደር በመደመር ግራ የገባው ቅኝት እዚያ እና እዚህ እየረገጠ ምንም የትርክት ለውጥ ሳያስፈልገው የጨቋኝ ተጨቋኝ የትርክት ንጥቂያ እና ቁማርን ማስቀጠሉን ለመረዳት ብዙ የፖለቲካ ብስለት የሚጠይቅ አይመስለኝም፡፡ እኛ ግን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ትርክት ቀማሪነት የታጨን ሆነን ሳለን የራሳችን የቤት ሥራ እንኳን ሰርተን ያልጨረስን መሳቂያ የመሆናችን ነገር ያሳዝናል፡፡ ታላቁ ጥቁር የተሰኘ በንጉሴ አየለ ተካ የተጻፈ መጽሐፍ ያነበበ ሰው ሁሉ ንጉሠ ነገሥቱ አጼ ኃይለሥላሴ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ለነበሩ ጥቁር ሕዝቦች ሁሉ እንደምን ይታገሉ እንደነበር መታዘብ ይችላል፡፡ ታሪካችንን አላወቅነውም፡፡ መናናቂያ አድርግነዋል፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘነውን በሰው ዘርን ሁሉ ፊት በግርማ ሊያስጠራን የሚችል ዕድል እንደዘበት አምልጦናል፡፡ እናስ ያቆሙን መሰረቶች ምን ያህል ጽኑዓን ነበሩ? እንደ ኅብረተሰብ የአቋራጩ፣ ልክፍተኞች ሆነን ለመገኘታችን ምክንያቱ ምንድን ነው? የምንዋቀሰው፣ የምንናናቀው በድንቁርናችን ልክ አይደለምን? ለፍጥረት ሁሉ ከሚተርፍ በረከት፣ ኅሊና እና ርህራሄ ጋር ተፈጥረን ሳለን ዘመኑን ስላለመዋጀታችን በሰንደቅ ዓላማ ለሚያስለምን ችጋር ራሳችንን አላጨንምን?
Hammasini ko'rsatish...
👍 51 11
Kirish va batafsil ma'lumotga kirish

Biz sizga kirlanganingizdan so'ng bu kunodaliklarni ochamiz. Biz va'da qilamiz, bu tez!