የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Ko'proq ko'rsatish2 756
Obunachilar
+124 soatlar
+97 kunlar
+4330 kunlar
Postlar arxiv
አዘክሪ ድንግል
አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን /2/
ካንቺ መወለዱን አዘክሪ
በቤተልሔም አዘክሪ
በጨርቅ መጠቅለሉን አዘክሪ
መኝታው ግርግም አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በዚያ በብርድ ወራት አዘክሪ
የገበሩለትን አዘክሪ
የአድግና የላም አዘክሪ
እስትንፋሣቸውን አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በግብጽ በረሃ አዘክሪ
መሠደድሽን አዘክሪ
የአሸዋውን ግለት አዘክሪ
ርሃቡና ጥሙን አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በመቃብሩ ዘንድ አዘክሪ
ባነባሽው እንባ አዘክሪ
አሳስቢ ድንግል ሆይ አዘክሪ
ገነት እንድንገባ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
አዘክሪ ድንግል
አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን /2/
ካንቺ መወለዱን አዘክሪ
በቤተልሔም አዘክሪ
በጨርቅ መጠቅለሉን አዘክሪ
መኝታው ግርግም አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በዚያ በብርድ ወራት አዘክሪ
የገበሩለትን አዘክሪ
የአድግና የላም አዘክሪ
እስትንፋሣቸውን አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በግብጽ በረሃ አዘክሪ
መሠደድሽን አዘክሪ
የአሸዋውን ግለት አዘክሪ
ርሃቡና ጥሙን አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በመቃብሩ ዘንድ አዘክሪ
ባነባሽው እንባ አዘክሪ
አሳስቢ ድንግል ሆይ አዘክሪ
ገነት እንድንገባ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
+8
የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል ጥቅምት 14/2018ዓ.ም በፎቶ (4)
+9
የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል ጥቅምት 14/2018ዓ.ም በፎቶ
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
የጽ/ጽ/ሐ/ጎላ ቅ/ሚ/ቤ/ክ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ከዚህ በታች ባሉት ክፍት የስራ መደቦች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
የሥራ ቦታ ፡- የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
1.የሥራው ዓይነት፡- ጊዜያዊ የሕንጻ አስተዳደር
ተፈላጊ ችሎታ:- በማንኛውም የት/ት መስክ ዲፕሎማ እና ከዛ በላይ ያለው/ያላት
ብዛት:-1
2.የሥራው ዓይነት :-ጊዜያዊ የቤተ መጻህፍት ክፍል ኃላፊ
ተፈላጊ ችሎታ:- በስነ-መለኮት ወይም በማንኛውም ት/ት ዘርፍ ዲግሪ ያለው/ያላት
ብዛት:-1
3.የሥራው ዓይነት :-ጽዳት
ተፈላጊ ችሎታ:- 8ኛ ክፍል እና ከዛ በላይ
ብዛት:- 1
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን
ለሁሉም የሥራ ዓይነቶች ደሞዝ በስምምነት
የሰ/ት/ቤት አገልጋይ የሆኑ ይበረታታሉ
የማመልከቻ ጊዜ:- ከዛሬ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 (አስር) ቀናት
ለበለጠ መረጃ:- የሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ወይም በስልክ ቁጥር..
+251983753030
+251911458862
''ትምህርተ ሃይማኖት ''
ክፍል ሁለት
በዲ/ን ሞገስ አብርሃም
የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር
ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
+9
የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል 2018 ዓ.ም በደብራችን በፎቶ
+9
የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ ።
የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ የተሠወሩበት ዓመታዊ ክብረ በዓል በዛሬው እለት ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት አዕምሮ ምስጋናው እና ሌሎችም የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ጻድቁአቡነ አረጋዊ
ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚህች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት ነው።
እኚህ አባት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ
አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግስት እድና ይባሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳዊ ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድርያ ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓረገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡
የንጉሳዊ የቅንጦት ኑሮ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ ማዕረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል።
በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችን ኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም ከአባ ፍሬምናጦስ በኋላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ተሸክሞ አክሱም አድርሷቸዋል፡፡
ተመልሰውም ሄደው ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱም ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡
አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀ መዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሰዋል፡፡
ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/91፥11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስድሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡
ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስቲያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላም ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡
ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርስሃለሁ ብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት ሾመውላቸው በዚህች ዕለት በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ ተሰውረዋል።
የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከት አይለየን!!
