uz
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ህብረተሰቡ በአረንጓዴ አሻራ ለሚተከሉ ችግኞች ጽድቀት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባል አዲስ አበባ፣ሐምሌ 8/2017 (ኢዜአ)፦ህብረተሰቡ በአረንጓዴ አሻራ የነቃ ተሳትፎን በማጠናከር ለሚተከሉ ችግኞች ጽድቀት ተገቢውን እንክብካቤ ሊያደርግ እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት እና ሌሎች ተቋማት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በእንጦጦ ፓርክ አካባቢ አካሂደዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ መጠበቅ ባለመቻላችን ለልዩ ልዩ ተፈጥሯዊ አደጋዎች ተጋላጭ ሆነን ቆይተናል ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተጽዕኖ ለመቋቋም መንግስት ባለፉት ሰባት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። መርሀ ግብሩ ዜጎችን ለጋራ ዓላማ በንቃት ያሳተፈ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህም ጉልህ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። በቀጣይም ዜጎች በአረንጓዴ አሻራ የሚያሳዩትን የነቃ ተሳትፎ በማጠናከር ችግኝ ከመትከል ባለፈ ለፅጽቀትም ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽነር ይመር ከበደ በበኩላቸው፤ አረንጓዴ አሻራ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገርን የምንገነባበት ትልቅ ተነሳሽነት ነው ብለዋል። በመሆኑም ሁላችንም ለችግኝ ተከላ እና እንክብካቤ የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን መቀጠል አለብን ነው ያሉት። የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሴ፤ በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ለፍሬ እንዲበቁ እንሰራለን ብለዋል። በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የየካ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ኒቆዲሞስ ቡቼ በበኩላቸው፤ በተፈጥሯዊ አደጋዎች ሳቢያ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል አረንጓዴ አሻራን ባህል ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች አሻራቸውን አኖሩ። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ በስፋት ተግባራዊ እየሆነ ባለው የአረንጓዴ አሻራ ልማት የማሳረፍ ስራችን፣ የደን ሽፋናችንን በማሳደግ፣የአየር ንብረትና የስነ ምህዳር ሚዛንን በማስጠበቅ ረገድ የመጣዉን ተአምራዊ ለዉጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በመትከል ማንሰራራት "በሚል መሪ ቃል 7ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሐ ግብር በዛሬዉ እለት በእንጦጦ ፓርክ አከናውኗል። በአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሀ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ በመዲናችን ችግኝ የመትከል ስራን አጠናክረን በማስቀጠላችን ፣የአየር ንብረት ሚዛንን ከማስጠበቅ፣የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተትን በመከላከል የደን ሽፋናችንን በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ ውጤታማና ከፍተኛ ለዉጥ ማስመዝገብ የቻለ ስራ ማከናወን ችለናል ሲሉም ገልፀዋል። አያይዘዉም ይህንን ተአምራዊ ለውጥ በይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከለዉን የመንከባከብና የማፅደቅ ስራ የሁላችንም ሀላፊነት መሆኑን በመገንዘብ በቀጣይ በዚህ ረገድ ሰፊ ስራ ማከናወን ይጠበቅብናል ሲሉም እመልክተዋል። በዚሁ የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮች፣የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ፣የፅዳትና የዉበት አምባሳደሮች እና ተፅእኖ ፈጣሪዎች በእንጦጦ ፓርክ በዛሬው እለት ሐምሌ 8 ቀን 2017 አ.ም አረንጓዴ አሻራቸውን በጋራ አኑረዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ህይወት አድን ስራ በፈጣሪም በሰዉም ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለዉ። ዛሬ ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ170 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለኩላሊት ህሙማን 20 የዲያሊሲስ ማሽን እና 10 ዘመናዊ አልጋዎችን በማቅረብ ለ180 ታካሚዎች ለ3 አመት የሚሆን የዳያሊስስ ግብዓቶች ከወንበሮች ጋር አስረክቦናል። ከፍለዉ መገልገል ለማይችሉ 144 ታማሚዎች በምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ እና ዘዉዲቱ ሆስፒታሎች በየአመቱ እስከ 25 ሚሊየን ብር በመመደብ የዛሬ አምስት ዓመት ያስጀመርነዉ ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ የዛሬዉ ድጋፍ ሲጨመርበት አገልግሎቱን በእጥፍ ለማሳደግ ስለሚያስችለን ለታካሚዎቻችን ትልቅ እፎይታ ነው። የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በህሙማን፣ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም እጅግ አድርጌ እናመሰግናለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ቆሻሻን ወደ ሀብት በመቀየር ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ተገኘ በአዲስ አበባ በ2017 በጀት ዓመት ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ሥራ ላይ የተሰማሩ 325 ማህበራት ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን፤ የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ ሙላት ተገኝ ለኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል። በመዲናዋ የነዋሪው የቆሻሻ አወጋገድ ባህል በየጊዜው እየተሻሻለ ቢሆንም፤ አሁንም የሚቀሩ ተግባራት መኖራቸውንም ነው ኃላፊው የተናገሩት። ቆሻሻን ለይቶ በማስወገድ ረገድ ከ200 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ መቻሉንም በቆይታቸው አንስተዋል። አሁን እየተሰሩ ካሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ጋር የተናበበ ዘመናዊ የፅዳት አሰራር በመዘርጋት ላይ መሆኑንም ያነሱት አቶ ሙላት፥ የተጨማሪ የማፅጃ ማሽኖች ግዢ በ2018 ዓ/ም እንደሚፈፀም ተናግረዋል። ከዛም ባለፈ ስማርት ሲቲ ለመሆን እየተጋች ላለችው አዲስ አበባ የሚመጥን ቀልጣፋ የፅዳት ስራ ለማከናወን፤ የግል አጋርነት በሙከራ ደረጃ በተመረጡ አካባቢዎች ተግባራዊ መደረጉን አመላክተዋል። ከኤጀንሲው ባሻገር ነዋሪው ስልጡን የፅዳት ባህል ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ አቶ ሙላት ጥሪ አቅርበዋል። ኢቢሲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአደጋ ስጋትን ለመቀነስና በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም እየተገነባ እንደሆነ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ ። የእሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጥሪ መቀበያ ማዕከልን ለማዘመን በተደረገው ጥረት ቀደም የነበረውን የአገልግሎት መስተጓጓል ለመቀየር በቴክኖሎጂ እንዲተካ በመደረጉ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ መመዝገቡን አስታውሰው በአደጋ ጊዜ የተቀናጀ ምላሽ ለመስት እንዲቻል ከፖሊስና ከጤና ተቋማት ጋር የሚሰጡ አገልግሎ ቶችን በአንድ ማዕከል ለማስተሳሰር በ 2018 ዓ.ም ዕቅድ መያዙንም አመላክተዋል ። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የኢትዮጵያ ብልፅግና ከዳር እስከ ዳር እስኪዳረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራታችንን እንቀጥላለን ! በዛሬው የአሶሳ ጉበኝታችን አዲሰ አበባ ላይ ከዓመት ዓመት ባህል እየሆነ የመጣውን የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ፣ የምገባ ማዕከል ማቋቋም ፣ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አካል የሆነው የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ግንባታን እና የፅዱ ኢትዮጵያ ሥራዎችን አሶሳ ከተማ ላይ አስጀምረናል ። በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የስራ አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባን አሮጌ ገጽታ እና የድህነት ታሪክ ለመቀየር በመልሶ ማልማት እና በኮሪደር ልማት ስራ ከህዝብ ውይይት እስከ ትግበራ 24/7 በመስራት እንዲሁም ህዝባችንን የልማቱ ባለቤት በማድረግ ያመጣነውን ተጨባጭ ወጤት እና ተሞክሮዎቻችንን አካፍለናል። ወደ ክልሎች እየተስፋፋ ያለውን እና በአሶሳ ከተማ እየተሰራ ያለዉን የኮሪደር ልማት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አሻድሊ ሃሰን አስጎብኝተውናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማምሻዉን የምዕራቧ ኮከብ በሆነችው በቤኒሻንጉል አሶሳ ከተማ ከወንድሜ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራችንን አኑረናል :: በአሶሳ ከተማ "ሀለዋ የአግሮ ኢንዱስትሪ" መንደር በ60 ሄክታር ላይ ያረፈውን የሌማት ቱሩፍት የሆነውን የዶሮ ፣ የእንቁላል እና የወተት ተዋፅኦ በቀላል መንገድ በማልማትና የአካባቢ ሀብትን በመጠቅሞ እንዴት ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል ተዘዋውረን ጎብኝተናል:: አዲስ አባባ ከክልሎች ጋር የምርት አቅርቦት ትስስር በመፍጠር ምርትን ወደ ከተማዋ እንዲገባ እየሰራች ትገኛለች በቀጣይም በኮሪደር ልማት የተሰሩትን ስራዎች ልምድ ልዉዉጥም የምናደርግ ይሆናል። ስለ ተደረገልን ደማቅ አቀባበል እናአመሰግናለን ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አሰኪያጅ ፅ/ቤት በሰኔ ወር የተከናወኑ ተግባራትን የያዘ የሰኔ ወር ዜና መፅሔት ለንባብ በቅቷል። የዜና መፅሄቱን ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ገፃችን ያንብቡ https://t.me/aacitymanageroffice ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ እና ማብራሪያ። Gaafilee fi yaadota miseensota mana maree Finfinnee irraa ka'aniif deebii fi ibsa laatame.

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ተጠናቀቀ :: በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን የተለያዩ ሹመቶች አፅድቋል። በዚህም መሰረት 1-አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን :-በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፍይናስ ቢሮ ሃላፊ መሆናቸውን ለምክር ቤቱ እንዲያውቀው ተደርጓል:: 2. አቶ ኦልያድ ስዮም :-የከተማ ቦታ ማስለቀቅ ጉዳዮች እና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል ። 3-አቶ መኮንን ያኢ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል ።