uz
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የከተማ አስተዳደሩ የ2018 በጀት ዓመት በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ለምክር ቤት ቀርቦ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል፡፡ ምክር ቤቱ በሁለተኛው ቀን ወሎ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ለ2018 በጀት ዓመት 350 ቢሊዮን ብር በእቅድ መያዙን አቅርበዋል:: ከተመደበው በጀት ውስጥ ለካፒታል በጀት 249.9 ቢሊዮን ብር እና ለመደበኛ ወጪ 100.1 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡ ባቀረቡት የበጅት ድልድል የ2018 በጀቱ በዋናነት ለደህነት ቅነሳ፣ ለዘላቂ ልማት፣ የስራ እድል ፈጠራ ለትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ከከተማው ነዋሪ በተለያዩ መንገድ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለሚሰጡ አገልግሎቶች ፣ ለአቅርቦት ድጎማዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጠባን መሰረት ያደረገ ስራ ላይ የሚውል ነው ብለዋል፡፡

የከተማው ካቢኔ በአራት ተቋማት አወቃቀር ላይ አፅድቆ በላከው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት በአቀረበው በደንብ ቁጥር 13/2016 መሰረት በረቂቅ ደንብ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል፡፡ የቱሪዝም ኮሚሽን ለብቻው ወጥቶ መደራጀትን አስመልክቶ አስፈላጊነቱ ላይ በአፅንኦት ተወያይቷል:: በዚህም መሠረት 1-ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፤ 2-የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት ጋር እንዲወሀድ:: 3 ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲወሃድ:: 4-የከተማ ውበትና አረንጋዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት ተግባር ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ላይ ምክርቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡ በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::

በአዲስ አበባ ምክር ቤት 2ኛ ቀን ውሎ በ 2017 በጀት ዓመቱ ፍርድ ቤቶች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት ረገድ የተሻለ የፍትህ ሥርዓት አፈፃፀም እንደነበራቸው ተገልጿል ። የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች 2017 ዕቅድ አፈፃፀም ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ መለሰ ቀልጣፋ ፣ውጤታማና ተደራሽት ያለው አገልግሎትን መስጠት የፍርድ ቤቶች ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ መዛግብት የማጥራት ዕቅድ 97 በመቶ ለመፈጸም ታቅዶ 98 በመቶ መከናወኑንም አስታውቀዋል፡፡ የቅልጥፍና መለኪያ በተቀመጠው ጊዜ መሠረት ለጉዳዮች ውሳኔ መስጠት ነው፤ በዚህ መሠረትም በስታንዳርድ መሠረት 89 በመቶ የፍትሀብሔር ጉዳዮች ውሳኔ አግኝተዋል ብለዋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመት ውሳኔ ሳያገኙ ወደ ቀጣይ በጀት ዓመት የተላለፉት በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 3ሺ 32 ጉዳዮች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡ 18 ዓለም አቀፍ የአገልግሎት እርካታ ደረጃ ምዘና መስፈርት መሠረት ከ85 በመቶ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገብ ከፍተኛ መሆኑን ያስገነዘቡት ፕሬዝዳንቱ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ውጤት የተገኘባቸውን ክንውኖችም በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡ ባለ ጉዳይን ያለ ምንም ልዩነት በትህትና እና አክብሮት ማገልገል፣ የዳኞች እና ሰራተኞች ያለ ጉቦ ማገልገል፣ የፍርድ ቤቶች ኃላፊዎች ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመካላከል ያላቸው ተነሳሽነት ፣ የሥነ- ምግብር ጉድለት ያሳዩትን ተጠያቂ ለማድረግ ያለው ቁርጠኝነት እና በመሳሰሉት መስፈርቶች ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ በአንፃሩ ግልፅ ችሎት አለመኖር፣ የቀረቡ ክርክሮችና ማስረጃዎችን በአግባቡ አለመመዘን፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ውስንነት፣ ተደጋጋሚ ቀጠሮ መስጠት፣የቋንቋ አስተርጓሚ አለመኖር፣ ነፃ የህግ አገልግሎት አለመኖር እንዲሁም ጉዳዮች በእርቅ እንዲያልቁ በፍርድ ቤት ተገቢው እድል አለመስጠት በሚሉት መመዘኛዎች ደግሞ ፍርድ ቤቱ ከዓለም አቀፍ ምዘና በታች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የከተማ ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ሥራዎች በትግበራ ላይ እንደሚገኙ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ በዓመቱ በጥንካሬ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና በክፍተት የተለዩትን ደግሞ በበማረም ለተሻለ ውጤት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ የፍርድ ቤቶችን ሥራ በተለይም በቴክኖሎጂ ማስደገፍ ላይ የታየውን ውስንነት ለማሻሻል በሪፎርሙ በስፋት እየተሰራበት ይገኛልም ብለዋል፡፡ የበጀት አመቱን የፍርድ ቤቶች የአፈፃፀም ሪፖርት ያዳመጠው ምክር ቤቱ በቀረበዉ ሪፖርት ላይ የተሰጡትን የአባላቱን ሀሳብ እና አስተያየት ካዳመጠ በኋላ ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን መሠረት ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተካሄደ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ወርሃ ክረምቱን ምክንያት በማድረግ "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም!" በሚል መሪቃል የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን ፣ ቱቦዎችን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን እና ማንሆሎችን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ያካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ጃክሮስ አካባቢ በድምቀት ተካሂዷል። በመርሀግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ የአንድ ከተማ ዕድገትና ስልጣኔ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ፅዳት መሆኑን ገልፀው የአካባቢን ፅዳት ለመጠበቅ ለሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አብራርተዋል። አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብት በመቀየር የተለያዩ ቁሳቁሶችና ጌጣጌጦችን ከመስራት በተጨማሪ ወደ ውጪ ሀገር በመላክ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። እያንዳንዱ ደረቅ ቆሻሻ የሚመነጨው ከእያንዳንዳችን መኖሪያ ቤት ነው ያሉት አቶ ገዛኸኝ የምናመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመያዝና በየዘርፉ በመለየት በአካባቢያችን ለተመደቡ ማህበራት ልናስረክብ ይገባል ብለዋል። ይህን በማድረግ ቆሻሻን ወደ ወደ ሀብትነት ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ አስረድተዋል። የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌትነት አይናለም በበኩላቸው የፅዳት ስራ የዘውትር ተግባራችን መሆን እንዳለበት ገልፀው ፅዱ፣ ውብ እና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማን ለትውለድ ለማስተላለፍ የሁሉም ህብረተሰብ ቅንጅታዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል በፅዳት ንቅናቄ ስራው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የመዋቅሩ ሰራተኞች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። ሀምሌ 5/2017የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን መሠረት ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተካሄደ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ወርሃ ክረምቱን ምክንያት በማድረግ "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም!" በሚል መሪቃል የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን ፣ ቱቦዎችን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን እና ማንሆሎችን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ያካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ጃክሮስ አካባቢ በድምቀት ተካሂዷል። በመርሀግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ የአንድ ከተማ ዕድገትና ስልጣኔ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ፅዳት መሆኑን ገልፀው የአካባቢን ፅዳት ለመጠበቅ ለሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አብራርተዋል። አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብት በመቀየር የተለያዩ ቁሳቁሶችና ጌጣጌጦችን ከመስራት በተጨማሪ ወደ ውጪ ሀገር በመላክ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። እያንዳንዱ ደረቅ ቆሻሻ የሚመነጨው ከእያንዳንዳችን መኖሪያ ቤት ነው ያሉት አቶ ገዛኸኝ የምናመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመያዝና በየዘርፉ በመለየት በአካባቢያችን ለተመደቡ ማህበራት ልናስረክብ ይገባል ብለዋል። ይህን በማድረግ ቆሻሻን ወደ ወደ ሀብትነት ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ አስረድተዋል። የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌትነት አይናለም በበኩላቸው የፅዳት ስራ የዘውትር ተግባራችን መሆን እንዳለበት ገልፀው ፅዱ፣ ውብ እና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማን ለትውለድ ለማስተላለፍ የሁሉም ህብረተሰብ ቅንጅታዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል በፅዳት ንቅናቄ ስራው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የመዋቅሩ ሰራተኞች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። ሀምሌ 5/2017

የወደቀው ስማርት ፖል፤ አጀንዳ መፍጠር በሚፈልጉ ግለሰቦች ሆን ተብሎ የተፈፀመ መሆኑ ተገለፀ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ አውታር አንድ የስማርት ፖል ሲወድቅ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስልን አስመልክቶ እንደተናገሩት የወደቀው ስማርት ፖል አጀንዳ መፍጠር በሚፈልጉ ግለሰቦች ሆን ተብሎ የተፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በማብራሪያቸው ለስማርት ፖሉ መውደቅ መነሻው በዕለቱ ንፋስ የቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ተፅዕኖ ነው የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም በቦታው በተጣራው መረጃና በተቃራኒ በኩል ባለ ካሜራ ላይ የተገኘው ተንቀሳቃሽ የምስል ማስረጃ ግለሰቦች ጨለማን ተገን አድርገው ብሎኑን አላልተውት የሄዱ ሰዎች ስለነበሩና በዕለቱ በነበረው ንፋስ የቀላለቀለ ከፍተኛ ዝናብ ግፊት ሊወድቅ እንደቻለ አንስተዋል፡፡ ክብርት ከንቲባ በከተማችን የተፈፀመው ይህ ድርጊት አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተው ከዚህ በላይ ሌሎች በርካታ አብነቶችን ማሳየት እንደሚቻል ለተከበረው ምክር ቤት ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በከተማችን ነዋሪዎች ተሳትፎና በፀጥታ ሀይላችን በተቀናጀ ሁኔታ የሚሰሩት ጠንካራ ስራዎች እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ መሰረተ-ልማቶችም የከተማውን ሰላም በመጠበቅ በኩል ውጤቶች ማስገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ህዝቡ ልማቱ ወደ ኋላ እንዲመለስበት አይፈልግም ያሉት ክብርት ከንቲባ የህዝቡ አጀንዳ ልማትና ሰላም ነው፤ ተጠቃሚነቱም ከዚህ በላይ እንዲጎላ ሰፋ ያለ ፍላጎት ያለው መሆኑን አንስተው ተጨማሪ ስራ እንዲሰራ እንጂ የተሰሩ መሰረተ-ልማቶች እንዲዘረፉ እንዲሰረቁ አይፈልግም ብለዋል፡፡ እነዚህም መሰረተ-ልማቶች ለፀረ ሰላም ኃይል ተጋላጭ እንዲሆኑ ብሎም እንዲወድሙበት አይፈልግም ብለዋል፡፡ ህብረተሰቡ ገንዘቡንም ጉልበቱም አውጥቷል፤ ባለቤትነት ስሜትንም አዳብሯል፤ ተጠቃሚም ሆኗል ያሉት ክብርት ከንቲባ ይሄን መነሻ በማድረግ ህዝቡ ራሱ እየተከንባከበውና ሰላሙን በማስቀጠል ከሌሎች ዘራፊዎችና በተለያየ መንገድ በመሰረተ-ልማቱ ላይ ጉዳት በሚያደርሱ አካላት ከፀጥታ አካላችን ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም የፀጥታ አካላችን ከፌደራልና ከሸገር ከተማ ጋር በተቀናጀ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን አንስተው ወንጀል የሰሩ አካለት መደበቂያ መሸሸጊያ እንዳያገኙ በተቀናጀ አግባብ ከምን በላይ የሀገር ጥቅምን በማስቀደም እየተሰራ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡ በተያያዘም በካሳንቺስ አንድ ፖል በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትና ጉዳት ያደረሰው አካል በፖሊስ ተይዞ አስፈላጊውን ማጣራት እየተደረገበት ቢሆንም በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ መረጃውን ለርካሽ ጥቅምና ለፀረ ልማት ሀይል መሳሪያ በመሆን፤ መረጃውን ለህዝብ አዛብተው በንፋስ የወደቀ አድርገው አቅርበዋል፡፡ የተሰራጨው መረጀ ሀሰት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አየገለፀ ባለስልጣን መ/ቤቱ ህብረተሰቡ ሀሰተኛ መረጃዎቹ ሲሰራጩ ምንጩ ከየት ነው ብሎ ቆም ብሎ በመጣራት ለተሳሳተ ድምደሜና ድርጊት እንዳይጋለጥ እያሳወቀ ሀሰተኛ መረጃ ከሚያሰራጩ አከላት ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ ይህ አንዱና ትልቁ ማሳያ መሆኑን ባለስልጣኑ በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ ይወዳል ሲል አስታውቋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮ

በመትከል ማንሰራራት ! ዛሬ ጠዋት ከምክር ቤት አባላት ጋር በእንጦጦ ተራራ ላይ ችግኝ ተክለናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ የቀረበውን የከተማ አስተዳደሩን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2017 በጀት አመት የኦዲት ሪፖርት ያዳመጠ ሲሆን በኦዲት ሪፖርቱ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የምክር ቤቱ ጉባኤ በነገው እለትም ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች ምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀደቀ፡፡ በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት ምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች የተሰጡ ምላሾችን አካቶ የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል ።

ህብረተሰቡ ጉቦ መስጠት የሚጸየፍና ለመብቱ የሚታገል መሆን አለበት፡፡ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ከማስተካከል አንጻር ለውጡ ከህብረተሰባችን መጀመር አለበት፡፡ እንደ መንግስት ሲቪል ሰርቪሱን ሪፎርም ለማድረግና ተቋሞቻችን ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረቶች እያደረግን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር አገልግሎቶች መንግስት በተቀያየረ ቁጥር የሚቀያየር እንዳይሆንና አገልግሎት አሰጣጡ መሰረት እንዲይዝ ለማድረግና በሚሰራው ስራ ላይ በቂ እውቀት ያለው ሲቪል ሰርቫት ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው፡፡ ይሄን ለማሳካት ባደረግነው ጥረት ውስጥ የተለያዩ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸውም የሚታወስ ነው፡፡አሁንም ቢሆን ህዝቡ በመታገልና የአፈጻጸም ችግር ያለባቸውን በማጋለጥ ለአገልግሎት መሻሻል የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ለውጡን ማፋጠን አለበት፡፡