uz
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የ2017 ዓመተ ምህረት ሲጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን እድገት እና ለውጥ የሚያንፀባርቁና በአመቱ ያከናወኗቸው ቁልፍ ተግባራትን በሚከተለው መንገድ ተመልክተናል። #PMOEthiopia

ጽዱ፣ውብ እና ደህንነቷ የተጠበቀች አዲስ አበባ! መልካም አዲስ አመት!

የኢፌዴሪ የገቢዎች ሚኒስቴር የ2018 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ ለተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠቃሚዎች ማእድ አጋርተዋል:: በተስፋ ብርሃን ቁጥር 26 የምገባ ማዕከል በተካሄደው የምሳ ግብዣ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ባደረጉት ንግግር የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ወገኖችን በቀን አንድ ጊዜ የተሟላ የምገባ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የተናገሩት ሚኒስትሯ፣ የገቢዎች ሚኒስቴርም በዚህ የተቀደሰ ተግባር በመሳተፍ የድርሻውን አስተዋጽኦ በማበርከቱ ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማው ገልጸዋል፡፡ “ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖች በምግብ አቅርቦት ተጠቃሚ እንዲሆኑ 26 የምገባ ማዕከላትን ከፍቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን አውስተው፣ በዚህ ተግባር የተለያዩ ተቋማት ተባባሪ በመሆን ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በልዩ ልዩ መስኮች ከተገኙት ስኬቶች ጎን ለጎን በሰው ተኮር ሥራዎች የበርካቶችን ሕይወት ለመለወጥ መቻሉን የተናገሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙት ሁለት የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በርካታ ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸውን በመግለጽ ይህ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀደማዊት ዝናሽ ታያቸው፣ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በቤተ መንግሥት ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ። #PMOEthiopia

አዲስ አመትን ከወገኖቻችን ጋር ! ወትሮም እንደምናደርገዉ አዲስ አመትን በከተማችን በሚገኙ 26 የምገባ ማዕከላት ጧሪ ፣ ደጋፊ ከሌላቸዉ አቅመ ደካምች ፣ በጉብዝናቸዉ ወራት ለአገራቸዉ ዉለታ ከዋሉ አረጋዉያን ፣ የአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ከሆኑ ወገኖቻችንን ጋር መአድ ማጋራት አብረን አክብረናል ። መልካም አዲስ አመት ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ/አደረሰን ! አዲሱ የ2018 ዓ.ም የአገልግሎት አሰጣጣችን ቅልጥፍና እና ጥራት የምናጠናክርበት፣ ቅንጅታዊ ስራችን የምናጎለብትበት፣ በዘርፋችን ያሉ እድሎችን በማስፋት ለህዝባችን ይበልጥ ተደራሽ የምንሆንበት፣ እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን በተጠናከረ መሠረትና በላቀ ውጤታማነት የምናስቀጥልበት እንደሚሆን ያለኝን እምነት እገልፃለሁ። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታችን በመላ ኢትዮጵያውያን አንድነትና ጽናት የተሞላበት ትጋት ታላቅ ህልምን ወደ እውንነት መቀየር እንደሚቻል አገራችን ኢትዮጵያ ለአለም እንዳረጋገጠች እንዲሁ በመዲናችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለከተማችንና ለነዋሪዎቿ የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ስማርትና ዘመናዊ ለማድረግ በ2018 እጅግ የላቀ ስኬታማና ውጤታማ ስራዎች እንደምናከናወን በዚህ አጋጣሚ እየገለፅኩ መልካም አዲስ አመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ! ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ See less

እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን በ2017 በርካታ ስኬቶች አግኝተን፣ የኢትዮጵያ መጪ ብሩህ ዘመን ገላጭ የሆነውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ በማስመረቅ ወደ 2018 ዓ.ም በድል ታጅበን እየተሻገርን ነው። አዲሱ የ2018 ዓመት የእቅዶቻችንን ፍሬዎችን የምናይበት፣ አዳዲስ መልካም የተግባር ዘሮችን የምንዘራበት፤ በትጋት እና በቁርጠኝነት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል የምንፈጽምበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ!! መላው ኢትዮዽያዊያን ፣የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃትና ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ !! መልካም አዲስ ዓመት አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የዘንድሮውን ዘመን ስናበቃ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ መሆኑን ለማረጋገጥ የነበረን ቁርጠኝነት እንደቀጠለ ነው። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከፌደራል አገልግሎቶች ወደ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ ይገኛል። በአዲሱ አመት ዋዜማ በአስራ ሶስት ተቋማት አንድ መቶ ሰባት የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ተመልክተናል። ይኽ አገልግሎት አሰጣጥን የመልካም አስተዳደር የማዕዘን ድንጋይ የማድረግ እና ዜጎች ወቅቱን የጠበቀ፣ ግልጽ እና ተደራሽ አገልግሎት የማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን የሚያንፀባርቅ ነው። በአዲሱ አመት ገና ብዙ ማዕከላት ይኖሩናል። በድጋሚ መልካም አዲስ አመት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

በአዲስ አመት ለከተማችን ነዋሪዎች እነሆ ገፀ በረከት “አዲስ-መሶብ”! የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ እንዲሆን በቁርጠኝነት መስራታችንን ቀጥለናል:: ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት "አዲስ መሶብ "የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ አስጀምረን በአዲሱ አመት ዋዜማ እነሆ ገፀ በረከት ብለናል። በአስራ ሶስት ተቋማት ፤ መቶ ሰባት አገልግሎቶችን የሚሰጠው አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የነዋሪዎቻችን እንግልት የሚቀንስ ፣ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አዲስ ብስራት ይዘን መጥተናል። በአዲሱ አመት በብዙ ብርታት እና ትጋት ልናገለግላችሁ ቆመናል ። መልካም አዲስ አመት ! ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኢትዮጵያውያን ብሎም የአፍሪካውያን ኩራት የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድባችን እኛ ኢትዮጵያውያን ስንተባበር እና በጋራ ስንቆም ተአምር መስራት የምንችል ህዝቦች መሆናችን ለአለም ያረጋግጥንበት ብሔራዊ ኩራታችን ነው ሲሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ ደስታቸውን በገለፁበት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የአሁኑን አዲስ አመት ልዩ የሚያደርገው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታችንን በተሰፋ ጀምረን በሰኬት ማጠናቀቅ የቻልንበት፣በትውልድ ቅብብሎሸ በመላው ኢትዮጲያውያን የጋራ ተሳትፎ ግድባችንን እውን ማድረግና ሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ የሰኬት ምእራፍ የጀመረችበት፣ሁላችንም በጋራ ያሰባሰበ አዲስ የመቻል ትርክት የተፃፈበት አመት በመሆኑ ነው ሲሉ ገልፀዋል ። አክለውም የአባይ ግድብ በግንባታው ሂደት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ከጫፍ ጫፍ በቁጭት ያንቀሳቀሰ በአንድነት ያሰባሰበ የጋራ መልካችን ነው ሲሉም በአፅንኦት ተናግረዋል ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እየተጠናቀቀ ባለው የ2017 ዓ.ም በከተማችን የተለያዩ የልማት ስራዎችና እንዲሁም የሰዉ ተኮር ስራዎችን ማከናወን የቻልንበት ነው ሲሉ ገልፀው በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን፣ የመንገድ ዳርና የውስጥ ለውስጥ መስመሮች መብራት መሠረተ ልማቶች ዝርጋታን በሁሉም አካባቢ ተደራሽ በማድረግ፣ ህዝባችን ያለ ስጋት እንዲንቀሳቀስ ከማድረግና ከተማችንን ፅዱ፣ ምቹ ዉብ እና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ ረገድ ሰፋፊ ስራዎች የተከናወነበት አመት ነበር ሲሉም አመልክተዋል። በመዲናችን የጎርፍ አደጋና ስጋት መከላከልን ጨምሮ የቅድመ አደጋ መከላከል ስርአት የሚያጠናክሩ ሰፋፊ ስራዎችን በቅንጅት ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ በዚህም በተለይም እየተገባደደ ባለው ክረምት የነዋሪዎቻችን ህይወት ከጎርፍ አደጋ ስጋትና ጉዳት መታደግ ችለናል ሲሉም ተናግረዋል። አያይዘውም በከተማችን የዜጎች የማንነት መለያ ስርአት እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጡን የሚያጎለብቱ ሰፋፊ ስራዎችን በማከናወን አመርቂ ዉጤት ማስመዝገብ የቻልንበት አመት ነበር 2017 ዓ.ም ሲሉም አመልክተዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በማጠቃለያቸው መጪውን አዲስ ዓመት ያስመዘግብናቸዉን የልማት ዉጤቶችን እጅ ለእጅ ተያይዘን የምናስቀጥልበት፣ከተማችንን በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስማርት የምናደርግበትና የዘመነና የላቀ አገልግሎት በመስጠት የከተማችን የስማርት ሲቲ ግንባታ ጉዞ ለማፋጠን በጋራ የምንተጋበት አመት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉ ለፅ/ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager