Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ጳጉሜ 5 2017
በዘመን መለወጫ በዓል ወቅት ውሃ ከቧንቧ እንዳይጠፋ፣ መብራት ሄደ እንዳይባል ዝግጅት መደረጉን ተቋማቱ ተናገሩ፡፡
የድንገተኛ እና የእሳት አደጋዎች እንዳይከሰቱ፤ ከተከሰቱም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ሰምተናል፡፡
ለበዓል የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንዳይከሰት ዝግጅት አድርጌያው ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጡ ቢከሰትም በአፋጣኝ መፍትሄ የሚሰጥ ቡድን ተቋቁሟል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ውሃ ፍሳሽ ባለስልጣንም ውሃ እንዳትጠፋ እየሰራሁ ነው ሲል አስረድቷል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/t7u/
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የጥንቃቄ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አወራር ኮሚሽን የዘመን መለወጫ በዓል ያለ አደጋ ክስተት ተከብሮ እንዲያልፍ ህብረተሰቡ
ለአደጋ የሚያገልጡ አሰራሮችን ተረድቶ አደጋን ለመከላላል እንዲችል በአዲስ አበባ በተመረጡ ቦታዎች የጥንቃቄ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው ።
መላው የከተማው ነዋሪ እየተላለፉ የሚገኙ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንዲተገብር ኮሚሽኑ አሳስቧል ።
ለእሳት ለሌሎች ድንገተ ኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የነገው ቀን
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ
ትናንትን በመጠቀምና በማረም፣ ዛሬ ላይ ተግተን በመሥራት፣ ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ ተነሥተናል፡፡ በአናሎግ ዘመን የነበሩ ችግሮች በዲጂታል ዘመን አይደገሙም፡፡ ነገ “ዲጂታል ኢትዮጵያ” ፕሮጀክት ከመሆን አልፎ ባህል ይሆናል፡፡ ንግድ እና አገልግሎታችንን በማቀላጠፍ፣ መረጃዎቻችንን ተደራሽ በማድረግ፣ አንድ ሰው አንድ እንዲሆን በማስቻል፣ የፋይናንስ ሥርዓታችንን ይበልጥ ተደራሽ ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን በየአቅጣጫው በማስፋፋት፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ እንዲሳካ የሁላችንን ጥረትና ትኩረት ይፈልጋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተከናወነ የችግኝ ተከላ ተጠናቅቋል።
ጉባ !
“የኢትዮዽያ ፣ የአፍሪካ ፣ የመላዉ ጥቁር ህዝቦች የብርሃን ዘመን ማብሰሪያ ምድር “
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ክንቲባ አዳነች አቤቤ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቀቀ!
የኢትዮጵያ ቁርጠኝነት እና የአፍሪካ መፃኢ እድል ጮራ ነው!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
መጪው የአዲስ አመት በአል ወሳኝ የሆኑ ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶችን በተሻለ የቅድመ ዝግጅት ስራና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተመለከተ::
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ከአዲሱ አመትና በቀጣይ ከሚከበሩ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በአላት አከባበር ጋር ተያይዞ ለነዋሪው መሠረታዊና ወሳኝ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ከሚከውኑ ተጠሪ ተቋማት ማለትም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ከፅዳት አስተዳደር ፣ከኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር እና እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በዛሬው እለት በከንቲባ ፅ/ቤት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል::
በመግለጫው በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለፁት ለአዲስ አመት በአል እና በቀጣይ ለሚከበሩ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ፅ/ቤቱ ግብረሐይል አቋቋሞ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሆነ አስገንዝበዋል::
ግብረ ኃይሉ ከእሳት አደጋ፣ከኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ከፅዳት እና ከውሃና ፍሳሽ ከማእከል እስከ ዲስትሪክትና ቅርንጫፎች እንዲሁም ከፅ/ቤቱ የክ/ከተማ መዋቅር ጋር በመቀናጀት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት መቆራረጦችን በተቻለ መጠን ለመቀነስና ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የእርድ ተረፈ ምርት ቆሻሻ የከተማዋ ፅዳት እንዳይጎድፍ በፍጥነት ከማንሳት አንፃር የተደረገውን ዝግጁነትና እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል::
የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ሪጅን ማስተባበሪያ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ ጂሳ ካሳ በቀጣይ የሚከበሩ በአላትን አስመልክቶ የአገልግሎት ሽያጭና ቅሬታ እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ ችግርን ለመቀነስ በሃይል መጨናነቅ ሳቢያ የሚቆራረጡ መስመሮች ልየታና ጥገና እንዲሁም ያረጁ መሠረተ ልማቶችን በአዲስ የመቀየር ስራ ሲከናወን መቆየቱን ገልፀው ይህ ተግባር የሀይል መቆራረጡንም የሚቀንስ መሆኑን አመልክተዋል።
መጭውን የአዲስ አመት በአል አስመልክቶም የበአሉ ዋዜማ እና የእለቱ ቀን ለካርድ ተጠቃሚ ደንበኞች በአራቱም የአዲስ አበባ ሪጅን በ30 የአገልግሎት መስጫ ማአከላት አገልግሎት ለመሰጠት ዝግጁ መደረጋቸውን ገልፀው በበአሉ ወቅት የትኛውም የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ ቢያጋጥም የአስቸኳይ ጥገና ማከአላት ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው በማወቅ በ905 የጥሪ ማአከላ እና በመደበኛ ስልኮች በወደወል አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል ገልፀዋል ፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ በበኩላቸው በቀጣይ የሚከበረዉ የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል ህብረተሰቡ ከአደጋ ተጠብቆ እንዲያከብር አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀው አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና በደረሰም ጊዜ ፈጥኖ ለመቆጣጠር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ከማእከል እስከ ሁሉም ቅርንጫፎች መደረጉን አረጋግጠዋል።
አክለውም ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብር ራሱንና አካባቢዉን ከእሳትና መሰል አደጋዎች እንዲጠብቅ አሳስበው አደጋዎች ካጋጠሙ ግን ፈጥኖ ለመከላከል በሁሉም ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አብራርተው በመሰከረም ወር የሚከበሩ ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ በአላትን ባማረና በደመቀ መልኩ እንዲከበር በተቋቋመው ግብረ ሀይል አማካይነት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ አርጋዉ በበኩላቸው ባለስልጣኑ በቀጣይ የሚከበሩ በአላት የውሃ አቅርቦቱ ሳይቆራረጥ ለማቅረብ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወኑን ገልፀዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ ጁናይድ ከማል እንደገለፁት ከተማዋን ውብና ብርሐናማ ለማድረግ የተዘረጉ የመብራት መሠረተ ልማት ስራዎችን ህብረተሰቡ እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
በአፍሪካ ግዙፉ የታዳሽ ሃይል ምንጭ ለሆነው፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ርብርብ፣ ላብና ደም ለተገነባው፣ መለያችንና ኩራታችን እንዲሁም ብሔራዊ የትውልድ ተሻጋሪ ፕሮጀክታችን ለሆነው፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ምርቃት እንኳን አደረሰን/ እንኳን አደረሳችሁ !
ይህ ግድብ እኛ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ለአገር አንድነትና ነፃነት ፈተና ሳይበግረን፣ በፅናትና በቁርጠኝነት በአባቶቻችን የተከፈለው መስዋእትነት ዳግም በዚህ ትውልድ የተሰራ ዳግማዊ የድል ማህተማችን ነው።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እውነነት፣ ፅናት፣ በሳልና ጥበብ የተሞላበት አመራር የሰጡ አመራሮቻችን፣ የበረሐው ሃሩር ሳይበግራቸው ፣ ያለእረፍት በታታሪነትና ሌት ተቀን የተጉ ሠራተኞችና መላ ኢትዮጵያውያን የዚህ ትውልድ ጀግነንትና የአርበኝነት ምልክትና የኢትዮዽያ ማንሰራራት ተምሳሌት ለሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችንን ተጠናቆ ለማስመረቅ በመብቃታችን እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
መጪው ጊዜ የኢትዮጵያ የላቀ ከፍታና ብልፅግና የሚረጋገጥበት ነው!
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
