Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የዓለም የጽዳት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ
እለቱ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተካሄደ ልዩ የፅዳት ንቅናቄ ነው የተከበረው፡፡
በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በዚሁ ወቅት በመዲናችን በዛሬው እለት አየተከበረ ያለውን የዘንድሮው የአለም አቀፍ የጽዳትን ቀን ልዩ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች በሚል በሁሉም መስክ ከተማዋ በከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ላይ ባለችበት ወቅት መሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም አዲስ አበባ በጽዳትም የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች፤ ለዚህ ደግሞ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ለከተማዋ ጽዳት የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከዩኤን ሃቢታት ወ/ሮ ሐረገወይን በቀለ ባስተላለፉት መልዕክትም የዓለም የጽዳት ቀን ከማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ትልቁና አንዱ መሆኑን ገልጸው ይህ የጽዳት እንቅስቃሴ በዓለማችን ባሉ 180 አገራት እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡
በጽዳት ንቅናቄው ላይ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች፣ የአራዳ ክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና የወረዳው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
ይህ ዓለም አቀፍ የጽዳት ቀን የጻዳት ንቅናቄ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ተካሂዷል፡፡
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት
የጳጉሜ እና የአዲስ አመት ማግስት አበይት የስራ ክንውኖች በምስል ሲቃኝ:-
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
የዘንድሮ ሩዝ ምርት ከአምናው በጅጉ የሰፋ ነው::
የዘንድሮ ሩዝ ምርት ከአምናው በጅጉ የሰፋ ነው::
Homishni ruuzii baranaa kan bara darbeerra baay'ee bal'aadha.
This year's rice production is much larger than that of last year.
See less
የመስቀል ደመራ ክብረ-በዓል ነባር ኃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ
የመስቀል ደመራ ክብረ-በዓል ፤ነባር ኃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም በየደረጃው የሚገኙ የባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የጋራ አረዳድ እንዲኖር የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮና የአዲስ አበባ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በውይይት መረሃ-ግብሩ ላይ እንዳሉት:-የመስቀል ደመራ ክብረ-በዓል፤የአደባባይ በዓል እንደመሆኑ መጠን በምናከብርበት ወቅት አብሮነትን፤ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን፣ሰላምንና አንድነትን አጽንተን በመገኘት ለተቀረው ዓለም አጉልተን ልናሳይ ይገባል ብለዋል ።
የመስቀል ደመራ ክብረ-በዓል፣ በዩኒስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ ዓለም አቀፋዊ ክብረ በዓል እንደመሆኑ ከኃይማኖታዊ ትውፊቱ ወጪ የሆኑ አጀንዳዎች ማራመጃ እንዳይሆን ከወዲሁ ጥብቅ ክትትል ማድረግ ይገባል ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ ከውስጥም ከውጪም ተናበው የበዓሉን ሰላማዊነትና የሀገርን ገጽታ ለማጉደፍ የሚሰሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በንቃት መከታተልም የሁላችን ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው ክብረ-በዓሉ ኃይማኖታዊ እሴቱን እና የኢትዮጵያውያንን ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ልማድ አጎልብቶ ማሳየት የሚጠበቅበት ከመሆኑም በላይ በተጓዳኝ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ጥቅማችንን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳውን የሚያስጠብቅ እንዲሆን ተቀናጅቶ መስራት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል ።
በውይይት መረሃ-ግብሩ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ኃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች የበዓሉን ሰላማዊነት ለማስጠበቅ ተቀናጅቶ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል ።
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስን ጨምሮ የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ዋና ጻፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ተገኝተው በጋራ መክረዋል።
መጪዉ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቁ በሚያስችል ሰነድ ላይ ዉይይት ተካሄደ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች በመጪዉ ቀናት የሚከበሩት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ከማናቸዉም አደጋ ተጠብቀዉ እንዲከበሩ በሚያስችሉ ዝግጅቶችን የተመለከተ ዉይይት ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂደዋል።
በዓላቱ የአደባባይ በዓላት በመሆናቸዉ በርካታ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ሀገራት ዜጎች የሚታደሙበት በመሆኑ ከሚኖሩ ሰፊ መርሀ ግብሮችና እንቅስቃሴዎች አንጻር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ድንገተኛ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲያስችል በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ ሰፊ ዉይይት ተካሂዷል።
ኮሚሽን መ/ቤቱ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሚከበሩበት ቦታ የበዓል መርሀ-ግብሩ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊዉን ጥበቃ እንደሚያደርጉ የተገለጸ ሲሆን በዓላቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ ከባለድርሻ የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተመላክቷል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በዓላት በአብሮነትና በድምቀት እንዲከበሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል - ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአደባባይ በዓላት የቱሪስት መስህብ በመሆን ላቅ ያለ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳም አለው ተብሏል ።
ለአብነትም የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት ከሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ ፋይዳቸው በተጨማሪ ዲያስፖራዎች እና በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የሚሳተፉባቸው የሀገር ሀብት ናቸው::
በዓላት እሴቶቻቸው ተጠብቆ እንዲከበሩ እና የህዝባችንን ማህበራዊ መስተጋብር እንዲያጠናክሩ እንደ ፓርቲም እንደ መንግስትም የተጀማመሩ አበረታች ስራዎች ወንድማማችነት እና እህትማማችነት እንዲጠናከር አስችለዋል።
የበዓላት ሀይማኖታዊ ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለሀገረ መንግስት ግንባታውም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በጀመርነው አዲስ ዓመትም ቅንጅታዊ ርብርቡ ይጠናክራል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የመስቀል ደመራን እና የእሬቻ በዓላትን በሰላምና በድምቀት ለማክበር እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዝግጅቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲከበሩ የፀጥታ አካላት እና ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅቶን እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ሁሉም አካባቢውች ከስጋት የራቁ ሰላማዊ ሆነው እንዲዘልቁ ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዓላት በአብሮነትና በድምቀት እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በዓሉ ወንድማማችነትን እህትማማችነትን እና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት እንዲከበር የፀጥታ መዋቅሩ እስከ ብሎክ ከሚገኘው የሰላም ሰራዊት እና ከሁሉም ህብረተሰብ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት በቂ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ክፍለ ከተሞችም አረጋግጠዋል።
"ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ።
ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ። ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ዶ/ር እንደምን አደርክ እኛ ደህና ነን ለአመት በአል ስሙ ቤተሰብ ጋር ስትመጣ እንገናኛለን ብለን ነበር ነገርግ አልተገናኘንም፡፡ አብርሃም 1 ኬሞ ወስዶ ተሽሎታል እቤት ንፁ አየር እንዲያገኝ አድርጉት ብለው ቅዳሜ ወጧል ሁኔታው በጣም ጥሩ ነበር አሁን ግን ምግብ አልበላኝ ብሎኛል ያስመልሰኛል፣አልፎ አልፎ ትኩሣት አለኝ ብሎኛል ምን ብናደርግ ይሻላል አንተም ጠፋህ የምትረዳበት መንገድ ካላ እርዳው እናቱ ተቸገራለች
ህዝበ ሙስሊሙ የተጀመሩ ልማቶችን በማፋጠን ሰላም፣ ልማትና አንድነትን እንዲያጠናክር ጥሪ ቀረበ
1499ኛው የነቢዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) ልደት (የመውሊድ) በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼይኸ አብዱልከሪም በድረዲን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መውሊድ ለሀገር ሰላም፣ ልማት እና አብሮነት የጎላ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ልማቶች መጠናቀቃቸውን እና እየተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት ምክትል ፕሬዚደንቱ ህዝበ ሙስሊሙ ከምንጊዜውም በላይ ከመንግሥት ጎን በመቆም የተጀመሩ ልማቶችን በማፋጠን ሰላም፣ ልማትና አንድነትን እንዲያጠናክር ጥሩ አቅርበዋል።
በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ለነቢዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል እና ለመጅሊስ 50ኛ የምስረታ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ነቢዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) በህይወት ዘመናቸው ያከናወኑትን መልካም ተግባራት በመውሰድ ራስን ለበጎ ተግባር በማዘጋጀት እና ለሠው ልጅ የሚበጅ መልካም ስራ በመስራት ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሀገርና ከተማን በመገንባት አንዱ ለሌላው ጋሻና መከታ የመሆን ባህልን አጠናክሮ መቀጠል ይገባልም ብለዋል።
ነቢዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) ለሰላም የነበራቸውን አስተምህሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው የመውሊድ በዓል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያዊያን እርስ በርሳችን በመደጋገፍ የጋራ ጉዳይ ላይ ካተኮርን ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ ናት ብለዋል።
የነቢዩ መወለድ ዋና ዓላማ ለሰው ልጆች እዝነትና ፍቅርን ማስተማር መሆኑን የገለፁት ዋና ጸሀፊው ህዝበ ሙስሊሙ ከሎሎች ወንድሞች ጋር በመሆን ለሀገር ልማት የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በሀገር ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ጥቅምን ለማስከበር እያደረጉት ላለው አስተዋፅኦ ለማሕበራዊ ሚዲያ አንቂና የአባይ መብቶች የኢትዮጵያ ተሟጋች ለኡስታዝ ጀማል በሽር እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የአባይ ግድብ ተሟጋች መሀመድ አል አሩሲ ምስጋና አቅርበዋል።
በበዓሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የአባይ ግድብ ተሟጋች መሀመድ አል አሩሲ አማካኝነት የአባይ ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን በተመለከተ በአረብኛ ቋንቋ መልዕክት ተላልፏል።
AMN
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1499ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በአሉ የደሰታ፣ የሰላም፣ የበረከት እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!
መልካም በዓል !
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
