uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ። የመውሊድ በዓል መጠራታችንን የምናስብበት ቀን ነው። ነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመጡበትን ተልዕኮ፤ የሠሩትን ሥራና ያመጡትን ውጤት እናስባለን። ሰው ዝም ብሎ ወደ ዓለም አይመጣም። ተልዕኮ አለው። ታላላቅ ሰዎች የምንላቸው ሁሉ የመጡበትን ተልዕኮ ያወቁ፤ ዐውቀው ተልዕኳቸውን ለማሳካት የሠሩ፤ ለተልዕኳቸው ስኬትም ተገቢውን መሥዋዕትነት የከፈሉ ናቸው። የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) መምጣት ዓለምን በፊት ከነበረችበት መልክና ጠባይ ቀይሯታል። መምጣታቸው የዓለም ታሪክ መክፈያ ሆኗል። በዘመናቸው መሥራት ያለባቸውን ሥራም ሠርተዋል። ለምን ወደዚህች ዓለም መጣሁ? የእኔ ተልዕኮ ምንድን ነው? ያ ተልዕኮስ የሰው ልጅን ሕይወት ወደ በጎ ምእራፍ የሚለውጥ ነው ወይ? ያንን ተልዕኮስ እያሳካሁት ነው ወይ? የሚለውን ካሰብን፣ ሀገር ብዙ ታላላቅ ሰዎችን ታተርፋለች። የሰው ልጅ ጉዞም መልካምን ጎዳና በሚሠሩ ሰዎች የተነሣ የተቃና ይሆናል። በዚህ የመውሊድ በዓል የሕይወት ተልዕኳችንንና የተልዕኳችንን ስኬት እያስተዋልን በዓሉን እንደምናከብር ተሥፋ አደርጋለሁ። የዘንድሮው በዓል ድርብ በዓል ነው። የዛሬ ሃምሳ ዓመት መጅሊስ የተቋቋመው በመውሊድ በዓል ቀን(ረቢ አል አወል 12ኛ ቀን) ነውና። በድጋሚ እንኳን ለነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል(መውሊድ) እና ለመጅሊስ ሃምሳኛ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ መስከረም 4፣ 2017 ዓ.ም

ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት ተጀመረ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና የአመራር አቅምን በሚገነቡ ወቅታዊ ጉዳየች ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል፡፡ ስልጠናውን የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) አስጀምረዋል። "የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በይፋ በተጀመረው ስልጠና፣ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በላቀ ስኬት በመፈፀምና ተሞክሮን በማስፋት፣ ተግዳሮቶችን ወደ እድል በመቀየር የህዝብና የሀገርን ጥቅም ለማረጋገጥ በአመራሩ አቅም የሚያዝባቸው ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል። የብልፅግና ፓርቲ ከህዝቡ ጋር በመሆን በፈፀማቸው ተግባራት የተጎናፀፋቸውን አንፀባራቂ ድሎች ይበልጥ በማጎልበት በቀጣይ የሚያከናውናቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ አቋምና ዝግጁነት እንደሚፈጠርበትም ይጠበቃል። በጠንካራ ፓርቲ ጠንካራ የመንግስት አፈፃፀምን እዉን በማድረግ ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል በተጨባጭ ለማሣካት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር እንደሚሆን የብልፅግና ፓርቲው መረጃ ያመለክታል። ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት ተጀመረ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና የአመራር አቅምን በሚገነቡ ወቅታዊ ጉዳየች ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል፡፡ ስልጠናውን የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) አስጀምረዋል። "የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በይፋ በተጀመረው ስልጠና፣ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በላቀ ስኬት በመፈፀምና ተሞክሮን በማስፋት፣ ተግዳሮቶችን ወደ እድል በመቀየር የህዝብና የሀገርን ጥቅም ለማረጋገጥ በአመራሩ አቅም የሚያዝባቸው ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል። የብልፅግና ፓርቲ ከህዝቡ ጋር በመሆን በፈፀማቸው ተግባራት የተጎናፀፋቸውን አንፀባራቂ ድሎች ይበልጥ በማጎልበት በቀጣይ የሚያከናውናቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ አቋምና ዝግጁነት እንደሚፈጠርበትም ይጠበቃል። በጠንካራ ፓርቲ ጠንካራ የመንግስት አፈፃፀምን እዉን በማድረግ ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል በተጨባጭ ለማሣካት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር እንደሚሆን የብልፅግና ፓርቲው መረጃ ያመለክታል።

በነገው ዕለት የሚከበረው 1499ኛ የመውሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ በታላቁ የአንዋር መስጂድ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት እና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት መሐል መርካቶ በሚገኘው የታላቁ አንዋር መስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ 1499ኛ የመውሊድ በዓልን አስመልክቶ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል። በፅዳት መርሃ-ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው የፅዳት አምባሳደር ሐጅ ሸምሱ ሐባስ፥ በዓላት የጋራ አብሮነታችንን እና እሴቶቻችንን የምንገልፅባቸው በመሆናቸው ምንም እንኳን የተለያየ እምነት ብንከተልም የጋራ የሆነችውን ሀገራችንን በማሰብ አንድነታችንንና አብሮነታችንን የበለጠ ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል። የታላቁ አንዋር መስጂድ ዋና አስተዳዳሪ ሼህ መርዋን አብዱልከሪም በበኩላቸው፥ ህዝበ ሙሰሊሙ የነብዩ መሀመድን ልደት የሚያከብረው የእሳቸውን የደግነት ሥራዎች ተግባራዊ ለማድረግና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን ጠቁመው በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተካሄደው የፅዳት ዘመቻም ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ኢትዮጽያዊ አብሮነትና መተሳሰብን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ብለዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ከሚሰራባቸው አከባቢ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ በልደታ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ከሚሰራባቸው አከባቢ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ እና የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አበባ እሸቴ ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች ልማቱን እንደሚደግፉ አመላክተው በካሳ ክፍያና በምትክ አሰጣጥ በፕሮጀክቱ አፈጻጸምና ለሀገር ስላለው ፋይዳ ሀሳብና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንዳሉት በመጀመሪያ ዙር የተሰራው ኮሪደር ልማት ስራ ቀጣይ ለሚተገበረው ልማት ምቹ ሁኔታንና መደላድልን የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው ህዝቡ በቂ ግንዛቤ ካገኘ የልማቱ ተባባሪ ብቻ ሳይሆን ባለቤት እንደሚሆን ማሳያ መሆን የቻለ ነው ብለዋል። በ2ኛ ዙር የሚሰራው ኮሪደር ልማት በቂ ጥናት የተደረገበት ዝርዝር ዓላማና እቅድ የተዘጋጀበት እና ከወዲሁ ኮሪደሩ ከሚሰራባቸው አካባቢ ነዋሪዎች ጋር መግባባት ለመፍጠር እንቅስቃሴ የተጀመረበት መሆኑን ገልፀዋል። የካሳና ምትክ ቦታ በጥናት ላይ የተመሰረተና ጥራት ባለው አግባብ እንደሚሰራ በመግለፅ የኮሙኒኬሽን አግባቡ ኮሪደሩን ከሚያስተባብሩ አካላት ውጪ መሆን እንደሌለበት አመላክተዋል። Lideta sub-city communication office

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሰጡንን የስራ መመሪያ ተቀብለን በቢሾፍቱ ከተማ በመገኘት የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተናል። ከከተማዉ አመራሮች፣ አባገዳዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ሀደ ስንቄዎች እንዲሁም ከነዋሪ ተወካዮች ጋር በተያዙ እቅዶች እና በቅንጅት በምሰራበት አግባብ ዙሪያ ተወያይተናል። በቢሾፍቱ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በአምስት አካባቢዎች ሰፊ በሆነ ቦታ ላይ የሚከናወን ሲሆን በውስጡም የመንገድ ስራ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ ስራ፣ የህዝብ መዝናኛ ፓርክ እንዲሁም መንገዶችን የማስዋብ ስራን ያካተተ ነው። በእርግጥ ቢሾፍቱ በተፈጥሮ የታደለች ከሰባት ሀይቆች በላይ ያላት የቱሪስት መዳረሻ ከተማ ናት። የኮሪደር ልማት ስራው ሲጠናቀቅ ይበልጥ የቱሪስት መስህብነቷን የሚጨምር ሲሆን የከተማዋን የወደፊት እድልም ከፍ የሚያደርግ ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ትላንት አበባየሆሽ ዛሬ ደግሞ ሽኖዬ እና ጎቤን በባህላችን ደምቃችሁ በመጨፈር ለአዲሱ ዓመት መልካሙን ሁሉ ለተመኛችሁልን ወጣቶች እና ልጃገረዶች ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ:: መልካም አዲስ ዓመት! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲሱ አመት :- አዲስ አበባችን በጽዳት እና ውበቷ ይበልጥ የምትፈካበት፣ ከማንኛውም የአደጋ ስጋት የምትጠበቅበት፣ በብርሃን የምትደምቅምበት አመት እንዲሆን በአዲስ መንፈስ፣በላቀ ትጋት፣ ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት እንተጋለን! በድጋሚ መልካም አዲስ አመት! የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

ዓመታዊው የአዲስ ዓመት ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት በቤተ መንግሥት።