Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የአዲስ አበባን የጽዳት ተምሳሌትነት በአርያነት ለማስቀጠል የሚያስችል ከተማ አቀፍ የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ማስወገድ ላይ ያተኮረ የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ።
ህዳር 22/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ "እንገነባለን፤ እናፀዳለን!" በሚል መሪ ቃል በቀጣይ 10 ተከታታይ ቀናት የሚከናወን የግንባታ ተረፈ ምርቶቸችን መሠረት ያደረገ ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
ይህም የፅዳት ንቅናቄ ትኩረት የሚያደርገው የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ከመንገድ እና ከእግረኛ መንገድ ማጽዳት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ማንሆል ክዳን ጥገና እና ፅዳት ፣ ህገወጥ እና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ተለጣፊ ግንባታዎች፣ ማስታወቂያዎችን እና ምልክቶችን ማስወገድ፣ በየቦታው ለረጅም ጊዜ የቆሙና የተጣሉ ተሽከርካሪዎችን፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን እና ሌሎች ቀሪ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን ከመንገድ ላይ በማስወገድ አዲስ አበባን ፅዱ፣ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተገልጿል።
መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የግንባታ ተረፈ ምርቶች የከተማችን ገፅታ በማስጠበቅ ረገድ አሉታዊ ተፅኗቸው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ 10 ቀናት ስታንዳርዳቸውን ያልጠበቁ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ተረፈ ምርቶችንና የመሳሰሉትን ከተማዋን የሚያቆሽሹ ተረፈምርቶችን በማንሳት እና በማስወገድ አዲስ አበባን እንደስሟ ውብና ፅዱ እናደርጋለን ብለዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም በከተማችን የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማዋን ፅዳትና ውበት ለመጠበቀ የተሰሩ ስራዎች የመዲናችንን መልካም ገፅታ ከመጠበቅ አንፃር ከፍተኛ ሚና ማበርከት መቻላቸውንም አብራርተዋል።
የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ባለፉት 5 ዓመታት ለከተማዋ ፅዳትና ውበት በትኩረት በመሰራቱ ከተማዋን ውብና ፅዱ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው በቀጣይም ይህንኑ አስቀጥለን ፅዱ ከተማ የማየት ህልማችንን እናሳካለን ብለዋል።
በፅዳት ንቅናቄ መርሀግብሩ ላይም የከተማችን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ፣ የካቢኔ አባላት ፣ በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል:: በዚህም መሰረት:-
1. አቶ ግርማ ሰይፉ - የከተማ ውበትና አረንጏዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. ወ/ሮ ቆንጂት ደበለ- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
3. ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ
5. አቶ ሙባረክ ከማል- የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ
6. አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
7. አቶ ታረቀኝ ገመቹ - የንግድ ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ
መልካም የስራ ዘመን
እንኳን ለ5ኛዉ ዓመት የብልጽግና ምስረታ አደረሰን!
“የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!”
"ብልጽግና የፓርቲያችን ስም አይደለም ለሀገራችን ያለን መሻትና ራዕይ እንጂ"
ብዙ ፈተናዎችን እና ተግዳሮቶችን አልፈን በበርካታ ድሎች ታጅበን 5ኛ ዓመት ላይ ያደረሰን ፈጣሪ ይመስገን።
ኢትዮጵያን ለማበልፀግ ያለረፋት እንተጋለን ፤ ፈጣሪ ያሳካልናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር ብልጽግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች የወል እውነት ነው። ብልጽግና ፓርቲም ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እንዲሁም እውነት፣ እውቀትና ጥበብን መለያው አድርጎ ባለፉት አምስት ዓመታት ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀየር በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል። በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችም የዜጎችን ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ ናቸው። በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ አዳዲስ ድሎችን በማስመዝገብ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍ ሀገር ለመገንባት እንሰራለን።
Kutannoo Itoophiyaan hiyyummaa keessaa bahuuf qabduun, badhaadhina mirkaneessuun galma waloo lammiilee hundaati. Paartiin badhaadhinaas obbolummaa sabdaneessa, dhugaa, beekumsaafi ogummaa irratti hundaa'uudhaan waggoota shanan darbanitti qorumsoota gara injifannootti jijjiiree bu'aawwan hedduu galmeessiseera. Bu'aawwan gama siyaasaa, dinagdeefi hawaasummaatiin galmaa'anis fayyadamtummaa lammiilee qabatamaan kan mirkaneessanidha. Waggoota shanan dhufanittis injifannoowwan haarawaa galmeessisuudhaan biyya ofirra darbitee kanbiroof qaqqabdu ijaaruuf ni hojjenna.
To align with Ethiopia’s determination to overcome poverty, ensuring prosperity remains a shared aspiration for all citizens. Over the past five years, the Prosperity Party has achieved significant successes, transforming challenges into victories through its foundation of fraternity, truth, knowledge, and wisdom. The accomplishments recorded in the political, economic, and social sectors have tangibly benefited the people. Looking ahead, our focus for the next five years is to continue building a resilient nation that not only thrives but also inspires others by achieving new milestones.
የስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የውይይት መድረክ በዛሬው እለትም እንደቀጠለ ነው።
በትናንትናው እለት ለጽ/ ቤቱ ተጠሪ ከሆኑት ተቋማት መካከል የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ለመዲናችን ነዋሪዎች እየሰጠ ያለውን አገልግሎት እንዲሁም በኮሚሽኑ በስራ ላይ ያሉ አዋጆች፣ መመሪያዎች፣ ደንቦች፣ማንዋሎችና አሰራሮችን የተመለከተ ሰነድ በኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ጥላሁን ቶላ ቀርቧል።
በተመሳሳይ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲም እንዲሁ የኤጀንሲው አገልግሎት ከተመሰረተበት ላለፉት 81 አመታት በላይ አገልግሎቱ ከየት ወዴት እንደደረሰ፣ አጠቃላይ አሁናዊ ሁኔታውንና በኤጀንሲው በስራ ያሉ አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎችን፣አሰራርና ማነዋሎችን በተመለከተ በኤጀንሲው ቡድን መሪ በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከፍተኛ አቅም የፈጠረው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ
ቋሚ ኮሚቴው ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ አቅም እየፈጠረ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ገለጹ፡፡
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
AMN - ህዳር 20/2017 ዓ.ም
See less
በአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለ19ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዮ ሁነቶች እየተከበረ የሚገኘውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን «ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሔራዊ አንድነት» በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ተከበረ::
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሰራተኞች የብሄር ብሔረሰቦችን ቀን ሲያከብሩ በፌደራሊዝም ሰርአት ምንነት እሴት እና ትግበራ ላይ በኮሙኒኬሸን ዘርፉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ በሰነድ የተደገፈ ሰፊ ማብራሪያ ቀርቦ እርስ በርስ መማመር የተቻለበት ውይይት ተድርጓል::
የተቋሙ ሰራተኞች በውይይታቸው የብሄር ማንነታቸውን አክብረው ለጋራ ሀገራዊ እሴት ግንባታ እና አብሮነት የበኩላቸውን የሚወጡበትን አሰተሳሰብ ለማዳበር በሚያስችሉ እሳቤዎች እና ተግባራት ላይ በማተኮር ለሀገራዊ መግባባት እና ለህብረብሄራዊ አንድነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበትን ግንዛቤ እንዳገኙ ገልፀዋል።
ህዳር 20 / 2017 አ.ም
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረሙስና ትግል፣የነገን ስብዕና ይገነባል‶ በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት ተከበረ::
እለቱ ለዚሁ በተዘጋጀ በቀረበ ሰነድ ሌይ የፓናል ውይይት በማካሄድ ተከብሯል።
በዚሁ ወቅት ሙስና ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም የዓለማችን ሀገራት የሚገኝና የሁሉም ሀገራት ተግዳሮት በመሆኑ ይህንኑ ለመፍታት የሚያስችል የተጠናከረ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ለሰራተኛው ግንዛቤ ተፈጥሯል::
የሰነምግባር መኮንን በሆኑት በአቶ አለማየሁ ሙላት በቀረበው ሰነድ በሀገር አቀፍ ደረጃና በከተማችን የፀረ ሙስና ትግል የእስካሁን እንቅስቃሴ የተመላከተ ሲሆን በተለይም አዲስ አበባ ከተማ የሙስና ወንጀልን ለመከላከል በሰጠችው ልዮ ትኩረት የሰነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በማቋቋም እና መዋቅሮችን በመዘርጋት ከፍተኛ የህዝብ እና የመንግስት ሀብትን በማዳን ተጠያቂነትን ማሰፈን መቻሉ ተገልፆል::
በተቋማችን በዓሉ ሲከበር ተገኝተው ለሰራተኞች ግንዛቤ የፈጠሩት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ የሰነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክተር አቶ ምህረቴ ሙሉ ሰው እንደ ከተማ ትውልድን በፀረ ሙስና ትግል ግንባታ ለመቅረጽ ሰፊ ሰራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በተቋማችን የስነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ትግል ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰራዎች በውጤት እንዲታጀቡ መላው ሰራተኛ እራሱን በሰነ-ምግባር በማነጽ እና መረጃ ላይ የተመሰረተ ትግል በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል::
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ተግባራት እና የህግ ማእቀፎች ዙሪያ እየተካሄደ ያለው የውይይት መድረክ በዛሬው የከስአት ውሎው "የለውጥ ትሩፋቶች፣ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችና የአመራር ዘይቤ" በሚል ርእስ በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል።
የውይይት መድረኩን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካና በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የከተማው ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እየመሩት ይገኛሉ።
የከተማው ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ስሉጥ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለማድረስ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ መጠናከር ይገባቸዋል ባሏቸው አሰራሮች ገንቢ የሆኑ ሐሳቦችንና አስተያዬቶችን እያነሱ በመወያየት ላይ ናቸው።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
