uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረሙስና ትግል፣የነገን ስብዕና ይገነባል‶ በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት ተከበረ:: እለቱ ለዚሁ በተዘጋጀ በቀረበ ሰነድ ሌይ የፓናል ውይይት በማካሄድ ተከብሯል። በዚሁ ወቅት ሙስና ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም የዓለማችን ሀገራት የሚገኝና የሁሉም ሀገራት ተግዳሮት በመሆኑ ይህንኑ ለመፍታት የሚያስችል የተጠናከረ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ለሰራተኛው ግንዛቤ ተፈጥሯል:: የሰነምግባር መኮንን በሆኑት በአቶ አለማየሁ ሙላት በቀረበው ሰነድ በሀገር አቀፍ ደረጃና በከተማችን የፀረ ሙስና ትግል የእስካሁን እንቅስቃሴ የተመላከተ ሲሆን በተለይም አዲስ አበባ ከተማ የሙስና ወንጀልን ለመከላከል በሰጠችው ልዮ ትኩረት የሰነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በማቋቋም እና መዋቅሮችን በመዘርጋት ከፍተኛ የህዝብ እና የመንግስት ሀብትን በማዳን ተጠያቂነትን ማሰፈን መቻሉ ተገልፆል:: በተቋማችን በዓሉ ሲከበር ተገኝተው ለሰራተኞች ግንዛቤ የፈጠሩት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ የሰነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክተር አቶ ምህረቴ ሙሉ ሰው እንደ ከተማ ትውልድን በፀረ ሙስና ትግል ግንባታ ለመቅረጽ ሰፊ ሰራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በተቋማችን የስነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ትግል ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰራዎች በውጤት እንዲታጀቡ መላው ሰራተኛ እራሱን በሰነ-ምግባር በማነጽ እና መረጃ ላይ የተመሰረተ ትግል በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል:: ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ በከተማ ስራ አስኪያጅና ተጠሪ ተቋማት ኃላፊነቶችና ተግባራት እንዲሁም የህግ ማእቀፎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል። የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ ር ግዛቸው አይካ በመክፈቻ ንግግር አስጀምረውታል። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ የለውጥ ትሩፋቶች፣ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችና የአመራር ዘይቤ በሚል ርእስ ሰነድ አቅርበዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የእሳትና ድጋተኛ አደጋ ስጋትን በጋራ ለመከላከል እንዲቻል ጥንቃቄ አይለየን" በሚል መሪ ሀሳብ በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ዙሪያ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ፡፡ ******************************* ህዳር 19-2017 ዓ.ም "የእሳትና ድጋተኛ አደጋ ስጋትን በጋራ ለመከላከል እንዲቻል ጥንቃቄ አይለየን" በሚል መሪ ሀሳብ በአሳትና ድጋተኛ አደጋዎች መከላከል ዙሪያ ለነዋሪ እና ለንግዱ ማህበረሰብ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና የኮሚሽኑ የአዲስ ከተማ ቅ/ቤት በጋራ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ይክፈላው ገ/መስቀል እንዳሉት በከተማችን እየደረሱ ያሉ የእሳትና ድገተኛ አደጋቀዎችን ቀድሞ ለመከላከል መደረግ ያለበት ዛሬ በዚህ መድረክ ላይ የተገኛችሁ በክ/ከተማው ወረዳዎች የብሎክ አመራር ትልቅ ስራ መስራት የምንችለው በቅንጅት ከህብረተስብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና የተለያዩ ተቋማት ጋር በመስራት ሊከሰት የሚችል ድገተኛ አደጋን መከላከል የሚቻል መሆኑን ተናግረዋል፡: የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ በበኩላቸው በክ/ከተማችን የሚከሰቱ የእሳትና ድገተኛ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል በየወረዳው የተደራጁ የብሎክ አመራሮችን በቂ የሆነ ግንዘቤ በመስጠት እና ለማህበረሰቡ ታች ወረደው ግንዘቤ እንዲስጡ በዚህ መድረክ የተገኛችሁ የብሎክ አመራሮች ለነዋሪው በቅርበት ልታገኟቸው የምትችሉት እናተ በመሆናችሁ ጠንከራች በመስራት የጋራ ስጋት የሆኑትን በእሳትና ድጋተኛ አደጋዎች የሚደረሱ ሰውና የንብረት ማዳን የሚቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ኮ/ል ብዙአየሁ ተስፋ በበኩላቸው የሚከሰቱ አደጋዎችና የሰላምና ፀጥታ ለመከላከል በየብሎኩ ያሉ የሠላም ሠራዊት በጠቀም ሊያጋትሙ የሚችሉ አደጋዎችን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል:: ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት በጋራ ለመስጠት ስምምነት ፈፀሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን የመመዝገብ አገልግሎት በአንድ ማዕከል ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት ዛሬ ህዳር 19/2017ዓ.ም በጋራ ፈፅመዋል። ተቋማቱ ስምምነቱ ከመደረሱ በፊት አሰራሩ በሃገሩቱ የመጀመርያ እንደመሆኑ መጠን የጋራ ጥናት ያከናወኑ ሲሆን አጠቃላይ ሁኔታዎች ዳሰሳ ተደርጓ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። የፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፎዓድ ኪያር እና የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ስምምነቱን የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱ በከተማው በሚገኙ 11ዱም የፍርድ ቤቱ ምድብ ችሎቶች አገልግሎቱ በቀጣይ ሳምንት በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል። አገልግሎቱ በኤጀንሲው የወረዳ ጽ/ቤት በሚሰጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በቴክኖሎጂ የሚሰጥ እንደሆነ ተጠቁሟል። የወቅታዊ ምዝገባ ሽፋንን ለማሳደግ እየሰራ ያለው ተቋሙ በሸሪዓ ፍርድ ቤት እና በ103 የጤና ተቋማት የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየሰጠ ያለ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ስምምነቱ ለክልሎች እና ከተማ አሰተዳደሮች ትልቅ ልምድ ሆኖ በተሞክሮነት እንደሚተገበር ይጠበቃል። ለበለጠ መረጃ በነፃ ስልክ መስመር 7533 ይደውሉ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በአዲስ አበባ ከተማ በስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ለመረጃ ሰብሳቢዎችና ለአስተባባሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። (ህዳር 18/2017):-የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የጥናት እና ልማት ትግበራ ዘርፍ የማዘጋጃ ቤታዊ የደረቅ ቆሻሻን የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በቀጣይ ለሚከናወነው ለመረጃ የማሰባሰብ ስራ ላይ ለሚሳተፋ መረጃ ሰብሳቢዎችና አስተባባሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። ጥናቱ በቀጣይ ለሚከናወኑ ስራዎች የማዘጋጃ ቤታዊ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ የመጠቀምና ኡደትን በተመለከተና በረጲ የሚገኙ መደበኛ ያልሆኑ ደረቅ ቆሻሻ የሚሰበስቡ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኖሚያዊ ሁኔታን የሚዳስስ መሆኑ ተገልጾ በዚሁ ጥናት የአገልግሎት አሰጣጡን ስርዓት ከማሻሻል፣አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ከማዘመንና፣ ስራዎችን በስታንዳርድ ከመስራት፣ አንፃር መፍትሄ አመላካች የሚሆን የጥናት ሪፖርት ለሰልጣኞች ቀርቦ የጋራ ዉይይት ተካሂዶበታል። በመድረኩም በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ም/ስራ አስኪያጅና የጥናት እና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የመረጃ መሰብሰቡ ስራ በቀጣይ የከተማችንን የአገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመንና ከተማዋን ገፅታ በይበልጥ አጉልተን የምናሳይበት እንደመሆኑ የመረጃ አሰባሰብ ስራዉ በጥራትና በጥንቃቄ መከወን እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። አክለዉም የሚከናወነው መረጃ የመሰብሰብ ስራ በቀጣይ የከተማዉን ነዋሪ ህብረተሰቡን የፅዳት እንቅስቃሴና ለከተማችን የእድገት ጉዞ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመዉ በስራዎች ላይ የሚስተዋሉ ክፍቶችን ከመቅረፍ አንፃር ከፍተኛ የሆነ ሚና እንደሚያመጣ ገልፀዋል:: በማጠቃለያቸዉ እንደገለፁት የሚወሰዱት መረጃዎች ከጥናትነት አልፈዉ መሬት ላይ ወርደዉ ችግር ፈቺ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር እዚህ ያለዉ ሁሉም ባለድርሻ አካል የተሰጠዉን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት በቀጣይም ወደ ተግባር በመግባት ተረባርቦ መስራት አስፈላጊ ነዉ ሲሉም አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመረዳት አደጋን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከሁሉም ክፍለ-ከተሞች ለተዉጣጡ ለ150 የህብረተሰብ ተወካዮች በአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ። በስልጠናዉ ህብረተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተረድቶ አደጋን አስቀድሞ በመከላከልና ሲያጋጥምም በፍጥነት መቆጣጠር የሚያስችል ስልጠና እንደተሰጠ የስልጠናዉ አስተባባሪዎች አስታዉቀዋል። የስልጠናዉ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ እንደተናገሩት አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ በቂ ግንዛቤ እንዳልነበራቸዉ ጠቅሰዉ በስልጠናዉ ያገኙትን ዕዉቀት በአካባቢያቸዉ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤዉ በማጨበጥ እራሳቸዉንና አካባቢያቸዉን ከአደጋ በመጠበቅ ኃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለበርካታ ጊዜ የነዋሪዎች የልማት ጥያቄ ሆኖ የቆየው የድጋፍ ግንብ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ማየታቸው እንዳስደሰታቸው የምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡ ******************* ህዳር 17-2017 ዓ.ም የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክፍለ ከተማው የተገነቡ ድጋፍ ግንቦችንና የቅድመ መከላከል ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ በቀለ ጉታ እንዳሉት አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት እየተሰሩ ያሉ የቅድመ መከላከል ስራዎች አበረታቸው መሆናቸውን ገልፀው የህዝባችንን ሁለንተናዊ ችግር ለማቃለል እየተሰራ መሆኑ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ በበኩላቸው ለበርካታ ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሆነው የቆዩ የስጋት አካባቢዎችን በመለየት ምላሽ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በወረዳ 6 የተገነባውን የድጋፍ ግንብ የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውብትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ባደረገው ከፍተኛ የፕሮጀክት ድጋፍ የተገነባ መሆኑንም አቶ ደረሰ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ የጉብኝቱ ተሳተፊ የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው የተመለከቱን ነገር የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን መገንዘባቸውን ገልፀው በተለይም ድንገተኛ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት እየተሰሩ ያሉ የቅድመ መከላከል ስራዎች መልካም ጅምር ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የዘንድሮውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሻለ ሁኔታ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን። በዚሁ መሰረት ዛሬ ከሆቴል ባለቤቶች እና ከዘርፉ አካላት ጋር ተወያይተናል። በውይይቱ እንደተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትንና እንግዳ ተቀባይነታችንን አጉልተን በማሳየት በላቀ አገልግሎት ሰጪነት እንድናስተናግድ እንዲሁም ከተማችንን የቱሪዝምና የኮንፍራንስ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስራ ይበልጥ በሚያጠናክር አግባብ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ትላልቅ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉባኤዎች ወደ ከተማችን እንዲመጡ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ተግባብተናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ