Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የኢሬቻ በዓልን በድምቀት አከበሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ከመጡ የክብር ተጋባዥ እንግዶች ጋር በጋራ በመሆን "ኢሬቻ ለሀገራዊ ማንሰራራት!" በሚል መሪ-ቃል በድምቀት አክብረዋል።
በዕለቱ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥናትና ትግበራ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሠ እንደተናገሩት የኢሬቻ በዓል ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማይዳሰስ ቅርስ መሆኑን ጠቁመው በዓሉ የአንድነት ፣የወንድማማችነትና የእህታማማችነት ምልክት መሆኑን አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅርና የምስጋና በዓል መሆኑን ገልፀው ለዚህ ታላቅ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ገዛኸኝ አክለውም ከተቋማችን ተልዕኮ አንፃር በዓሉ ፅዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ለማድረግ በተደረገው ርብርብ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ያበረከቱ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የፅዳት ስራችን በተያዘው ግለት ልክ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይም የኦሮሞ ባሕላዊ ምግቦችን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሞ ባህላዊ ሙዚቃዎች በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአብሮነትና የሠላም እንዲሁም በጋራ ሠርቶ የማደግ ተምሳሌት የሆነው የኢሬቻ በዓልን ላቆዩ አባቶች ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አስከያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ገለጹ ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም የኢሬቻን በዓል በደማቅ ሰነ-ስርዓተ አክበረዋል ።
በክብር በዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደተናገሩት የአሬቻ በዓል የአብሮነት ፣ የሠላምና የፍቅር፣ በጋራ ሠርቶ የማደግ ባህልን ያቀፈ መሆኑን አስታውሰው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆነው ይህን አኩሪ በዓል ላቆዩ አባቶች ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት መዋደድን መተሳሰብን እንዲሁም እርቅን መሠረት ባደረገው የኢሬቻ በዓል እሴትን መሠረት በማድረግ አንድ ሆነን ህዝባችንን በፍፁም ሰብአዊነት የማገልግል ተልዕኮችንን በላቀ ደረጃ የምንፈጽምበት ነው ብለዋል።
በስነ -ስርዓቱ ላይም የኢሬቻ በዓል ታሪካዊ ዳራን የተመለከተ ሰነድ በም/ኮሚሽነር ደሳለኝ ፉፋ ገለጻ የተደረገ ሲሆን
ኢሬቻ ላይ ያተኮረ ስነ-ግጥም ቀርቧል ።
በአባገዳዎች ምርቃት የተጀመረው በዓል በጎቤዎች ጨዋታ ደምቆ የዋለ ሲሆን የኦሮሞ ባህላዊ ምግቦችን የማስተዋወቅ መርሀ -ግብር ተካሂዷል ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ኢሬቻ ህብረ ብሄራዊነት የሚደምቅበት እና አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት ነው-ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ … See more
rreechaa ፥ Olkaiinsa Biyyaaf !
ኢሬቻ ለሃገር ማንሰራራት !
Erreecha ;For National Leap Up !
የ2018 ዓ.ም የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አየ ተከበረ ሲሆን በዓሉም በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ፣ በክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ እና በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች በተገኙበት በአባገዳዎችና በሃደስንቄዎች ምርቃት ተጀምሯል።
Kirkos Communication-ቂርቆስ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመዲናችን አዲስ አበባ የሆራ-ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራና አካባቢውን የምናፀዳበት ዋናው ምክንያት ስፍራውን ከማፅዳት ባለፈ የጋራ አብሮነታችን፣ ወንድማማችነታችንና አንድነታችን የምንረጋግጥበት በመሆኑ ነው ሲሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት በአዲስ አበባ የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት!" በሚል መሪ-ቃል የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ሃደ ስንቄዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበትን የፅዳት ንቅናቄ ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ነው።
በከተማችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ ጽዱ፣ ውብ፣ማራኪና አመቺ የማድረግ ስራዎች በተከታታይ መከናወኑን የጠቀሱት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በተጨማሪም በአሉ ከአደጋ ስጋት ነፃ ሆኖ፣ብርሃን በነገሰባት መዲናችን እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ በመጠናቀቁ የበአሉ ታዳሚዎች በሙሉ ያለምንም ስጋትና በአሉን በልዩና ሰላማዊ ድባብ በተሞላበተ ሁኔታ እንደሚያከብሩ ገልፀዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አክለውም የከተማችን ነዋሪዎች በዓሉን ለማክበር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገራት የሚመጡ እንግዶችና ቱሪስቶችን ለመቀበል አካባቢዎችን በማፅዳትና በማስዋብ እንዲሁም የደመቀ አቀባበል ለማድረግ ያሳዩትን ተሳትፎ አድንቀው ይኸው የአብሮነት የኢትዮጵያውያን ህብረትና ወንድማማችነት እስከ በአሉ ማጠናቀቂያ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው ኢሬቻ የተጣላን የምናስታርቅበት ዋቃ አምላካችንን የምናመሰግንበት በዓል ነው፤ በመሆኑም ይህ የሰላም የአንድነትና የወንድማማችነት ተምሳሌት የሆነው በዓል ፅዱና ውብ በሆነ ከተማ እንዲከበር የጽዳት ንቅናቄው መዘጋጀቱን ገልጸው በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የመጡ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው የዘንድሮ የኢሬቻ በአል ልዩ የሚያደርገው እንደ ሀገር ብሎም እንደ ከተማ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመሳተፍ ከፍተኛ ድል ያስመዘገብንበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ማግስት በመሆኑ በአሉ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በዓሉ ፅዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ለማድረግ ተከታታይ የሆነ የፅዳት ስራ መሰራቱን ጠቁመው በዓሉ ከተጠናቀቀም በኋላ ነዋሪ በጽዳቱ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የባለሞያዎች የእለት እቅድ ክንውን መመዝገቢያ ቅጽ
እፀገነት ተስፋሁን (ከ01/12/2017 ዓ.ም እስከ //2016 ዓ.ም/) ነሐሴ ወር
ቀን ዋና አገልግሎት ንኡስ አገልግሎት የንኡስ አገልግሎቶች ዋና ዋና ተግባራት ቀን የዋና ዋና ተግባራት ስታንዳርድ መለኪያ የተጀመረበት
ሰዓት የተጠናቀቀበት
ሰዓት የወሰደው ሰዓት የዋና ተግባር እቅድ (የBPR) የዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ስሌት ጥቅል የንኡስ አገልግሎት የዕቅድ አፈፃፀም ስሌት
የዋና ዋና ተግባራት የመጠን፣ የጊዜና የጥራት አፈፃፀም ስሌት የዋና ዋና ተግባራት ጥቅል አፈፃፀም ስሌት
1
በመዲናችን አዲስ አበባ የሆራ-ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራና አካባቢውን የምናፀዳበት ዋናው ምክንያት ስፍራውን ከማፅዳት ባለፈ የጋራ አብሮነታችን፣ ወንድማማችነታችንና አንድነታችን የምንረጋግጥበት በመሆኑ ነው ሲሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት በአዲስ አበባ የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት!" በሚል መሪ-ቃል የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ሃደ ስንቄዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበትን የፅዳት ንቅናቄ ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ነው።
በከተማችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ ጽዱ፣ ውብ፣ማራኪና አመቺ የማድረግ ስራዎች በተከታታይ መከናወኑን የጠቀሱት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በተጨማሪም በአሉ ከአደጋ ስጋት ነፃ ሆኖ፣ብርሃን በነገሰባት መዲናችን እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ በመጠናቀቁ የበአሉ ታዳሚዎች በሙሉ ያለምንም ስጋትና በአሉን በልዩና ሰላማዊ ድባብ በተሞላበተ ሁኔታ እንደሚያከብሩ ገልፀዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አክለውም የከተማችን ነዋሪዎች በዓሉን ለማክበር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገራት የሚመጡ እንግዶችና ቱሪስቶችን ለመቀበል አካባቢዎችን በማፅዳትና በማስዋብ እንዲሁም የደመቀ አቀባበል ለማድረግ ያሳዩትን ተሳትፎ አድንቀው ይኸው የአብሮነት የኢትዮጵያውያን ህብረትና ወንድማማችነት እስከ በአሉ ማጠናቀቂያ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው ኢሬቻ የተጣላን የምናስታርቅበት ዋቃ አምላካችንን የምናመሰግንበት በዓል ነው፤ በመሆኑም ይህ የሰላም የአንድነትና የወንድማማችነት ተምሳሌት የሆነው በዓል ፅዱና ውብ በሆነ ከተማ እንዲከበር የጽዳት ንቅናቄው መዘጋጀቱን ገልጸው በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የመጡ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው የዘንድሮ የኢሬቻ በአል ልዩ የሚያደርገው እንደ ሀገር ብሎም እንደ ከተማ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመሳተፍ ከፍተኛ ድል ያስመዘገብንበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ማግስት በመሆኑ በአሉ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በዓሉ ፅዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ለማድረግ ተከታታይ የሆነ የፅዳት ስራ መሰራቱን ጠቁመው በዓሉ ከተጠናቀቀም በኋላ ነዋሪ በጽዳቱ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ለሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጁ የሆነው
የኢሬቻ ፓርክ ከፊል ገፅታ ።
#Irreechaa
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመዲናዋ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን በድምቀት ለማክበር የተደረገው ዝግጅት…
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል አለ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት፡፡
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሆረ ፊንፊኔ ‘ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት’ በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል፡፡
በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነትና የአንድነት በዓል ነው፡፡
በዓሉ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት እንደሆነም አውስተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር ኮሚቴ ተዋቅሮ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው፤ በዓሉ የሚከበርበትን ሥፍራ መሰረተ ልማት የማሟላት ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡
በዓሉ የሚከበርበት ኢሬቻ ፓርክ ውብ፣ ጽዱ እና ለጉዳት ሊያጋልጡ ከሚችሉ ነገሮች ነጻ እንዲሆን ተደርጓል ነው ያሉት።
በተጨማሪም በማክበሪያ ሥፍራው አካባቢ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ እና የሌሎች አገልግሎቶች መቆራረጥ እንዳይፈጠር መሰራቱን ጠቅሰዋል።
በመዲናዋ ወደ ኢሬቻ ፓርክ የሚወስዱ መንገዶች በማታ ለእንግዶች እንቅስቃሴ አመቺ እንዲሆኑ የመንገድ ዳር መብራቶች እንዲሟሉ ተደርጓል ሲሉም ገልጸዋል።
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የፊታችን ቅዳሜ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የመሠረተ ልማት የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
