Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአልን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ቱሪስቶችና እንግዶች ያለምንም ስጋት በከተማዋ 24 ሰዓት የሚፈልጉትን አገልግሎቶች በቀላሉ እንዲያገኙ በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገልጸዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከጳጉሜ ቀናት እስከ መስከረም አጋማሽ ወር የተካሄዱ አበይት የስራ ክንውኖች በፎቶ ስላይድ ሲቃኝ:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የፊታችን ቅዳሜ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ በዓል የመሠረተ ልማት የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ …
See more
ሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ የሚከበርበትን ፓርክ የማፅዳት ስራ ተካሄደ
የሆራ ፊንፊኔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉ ጽዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ለማድረግ "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት!" በሚል መሪ-ቃል በዓሉ የሚከበርበትን ኢሬቻ ፓርክን፣ የወንዝ ዳርቻውን እና እንግዶች የሚገቡበትን መንገዶች አመራሮችን ጨምሮ፣ የፅዳት አምባሳደሮች ፣ አርቲስቶች ፣ ከሁሉም ክ/ከተማ የተውጣጡ የፅዳት አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል።
በዕለቱም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኢሬቻ በአል የአደባባይ በአል እንደመሆኑና በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ አገራት ቱሪስቶችና እንግዶች የሚታደሙበት እንደመሆኑ ባማረና ከአደጋ ስጋት ነፃ በሆነ መንገድ እንዲከበር የከተማ ፅዳት እና ውበት፣ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ ሁሉም የድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው በዓሉ የሚከበርበትን የኢሬቻ ፓርክ የማስዋብና ፅዳቱን የመጠበቅ ስራ በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
በፅዳት ንቅናቄው የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ ር ዘላለም ሙላትና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአ/ ከተማ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ይህም የፅዳት ንቅናቄ በዓሉ ከተጠናቀቀም በኋላ አካባቢውን ፅዱ የማድረግ ስራ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ በነገው ዕለት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የዕምነት አባቶች ፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች ፤ የፀጥታ አካላት፣ የፅዳት አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና የአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰብ የሚሳተፉበት በአይነቱ ልዩ የሆነ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በዓሉ የሚከበርበትን ቦታ እና አካባቢውን ከማለዳው ጀምሮ የፅዳት ንቅናቄ በድምቀት እንደሚከናወን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ አክለው ተናግረዋል።
በመዲናችን አዲስ አበባ የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለሰዎችና ተሽከርካሪዎች የምሽት እንቅስቃሴ መንገዶችን በበቂ ብርሀን ውብና ምቹ የማድረግ ስራ መከናወኑን በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት በትናንትናው እለት ምሽት የበአሉ ዋነኛ ማክበሪያ ስፍራ በሚገኝበት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተከናወኑ የመንገድ መብራት አዳዲስ መሰረተ-ልማቶችን የሟማላት፣ አገልግሎት የማይሰጡ የነበሩትን የመጠገን እና በሀይል ቆጣቢ መብራቶች የመተካት ስራዎችን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል በአደባባይ የሚከበር በአል እንደመሆኑ የመዲናችንን ድምቀትና ውበት የሚያጎላውን እና የማህበረሰቡን የምሽት እንቅስቃሴ ምቹ የሚያደርጉ የመንገድ መብራቶች መሠረተ ልማት ጥገና፣ አዳዲስ ተከላና የማሻሻል ስራዎች በመጠናቀቃቸው በሁሉም በአሉ በሚከበርበት ቦታ፣ የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች፣ አደባባዮችና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የበአሉ ታዳሚዎች ያለምንም ስጋት እጅግ ባማረ ሁኔታ ቆይታቸውን የሚያሳልፉበት ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል ።
ለሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በመዲናዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ባሉ አደባባዮችና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችም ተመሳሳይ የመንገድ መብራቶች መሠረተ ልማት ጥገና፣ ተከላና ማሻሻል ሲከናወን መቆየቱን አመልክተው በተለይም የመስከረም ወር በርካታ በዓላት የሚከበሩበት እንደመሆኑ በእነዚህ በዓላት ለመታደም ከአገር ውስጥም ከውጭም የሚመጡ ቱሪስቶችና እንግዶች በሰላም ወጥተው የሚገቡባት ውብ፣ ብርሐናማ ድምቀትን የተላበሰችና ሰላማዊ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ የማዘጋጃ ቤታዊ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡
ኢንጅነር ወንድሙ አያይዘውም የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር የመንገድ መብራት አገልግሎት የተሟላ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው በትናንትናው እለት ምሽት ጉብኝት የተደረገባቸው በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ ሶስትና አራት ከዋሺንግተን አደባባይ- ቡልጋሪያ፣ ከዋሺንግተን አደባባይ- ሀዲድ እንዲሁም ወደ መስቀል ፍላወር ባሉት መንገዶች ላይ የተከናወኑት ስራዎች ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል። በመስክ ምልከታ የተደረገባቸው መንገዶች የመንገድ ዳር መሰረተ ልማት በተሟላ መልኩ ሳይጠናቀቅና በተለያየ ምክንያት አገልግሎት ሳይሰጡ ረጅም ዓመት የቆዩትንም ማብራት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን በበኩላቸው ባለስልጣኑ በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ የመንገድ መብራት መሰረተ ልማት ሽፋን ለማሳደግ ለረጅም ጊዜ መንገዶቹ ተገንብተው አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩትንና በተለያዩ ምክንያቶች የተበላሹ መብራቶችን በመጠገን ወደአገልግሎት ማስገባታቸውን ተናግረዋል፡፡
የኢሬቻን በዓል በደመቀና ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ ጨለማ የነበሩ ቦታዎችን በከተማው ሁሉም አቅጣጫዎች አስፈላጊውን ጥገና በማድረግ ለአገልግሎት የማብቃት ስራ መከናወኑን ተናግረው ተጠግነው አገልግሎት የሚሰጡን ከተሽከርካሪ አደጋ፣ ስርቆትና ሌሎች ጉዳቶች እንዳይገለጡ እና አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ለሚመለከታቸው አካላት ርክክብ የተደረገ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡ መሰረተ-ልማቱን በመጠበቅ በኩል የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
መስከረም 21/2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም የኢሬቻ በዓል!
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት "ሙስናን በመከላከል ረገድ የመገናኛ ብዙሃን ሚና" በሚል ርእሰጉዳይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የፀረ ሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት ለፅ/ቤቱ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች በፀረ ሙስና ትግል ላይ መገናኛ ብዙሃን ባላቸው ፋይዳ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናዉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ቢሮ ሃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ ስልጠናው መገናኛ ብዙሃን ከተማችን ለተያያዘችው ፈጣን እድገትና ልማት ፀር የሆነውን ሙስናና ብልሹ አሰራሮችንና እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመከላከል ረገድ ያላቸውን ሚና የተቋሙ ባለሙያዎች በውል ተገንዝበው ባለድርሻ አካላትንና ማህበረሰቡን በማንቃት ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የአገርና ህዝብና ሃብትን በመመዝበር የሚፈጸሙ ውስብስብ የሙስና ወንጀሎች በአለምአቀፍም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ የምርመራ ጋዜጠኝነት ሙያን በማጠናከርና ሙሰኞችን በማጋለጥ ረገድ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ አስተዋፅኦ የማበርከት አቅም እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናም ሙስና የሚፈፀምባቸውን ውስብስብ መንገዶች በአግባቡ በመገንዘብና እንዲሁም በመሰረታዊ፣ተጨባጭና እውነተኛ መረጃዎች ላይ በመመስረት የፀረ ሙስና ትግልን ለማጠናከር የሚያስችል በቂ የሆነ ግንዛቤና አቅም ለመፍጠር ያስችላል ሲሉም ነው የገለጹት።
በዚሁ ስልጠና ላይ የሙስና ምንነትና መንስኤዎች፣መከላከያ መንገዶች፣የመረጃ መሰብሰብ ስነ ምግባር፣የመረጃና የዜና ምንነትና ልዩነት፣መረጃ የመሰብሰብ አላማና ከጊዜ ጋር የማጣጣም አስፈላጊነትና የመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን በመስጠት ሂደት የተሳተፉት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት የፀረ ሙስና የመከላከያ ዳይሬክተር አቶ ምህረቴ ሙሉሰዉ እንደተናገሩት ስልጠናዉ በሰራተኛዉ ዘንድ የሙስና መከላከል መንገዶች ላይ እዉቀት ከመጨመር አንፃር ግልፅነትን የሚፈጥር እና ለተቋሙ ሰራተኞችም በቂ የሆነ የሙስና ቀጣይ የመከላከያ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ለኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ክብረ በዓል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
*****************
ለኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ክብረ በዓል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከኢቢሲ ዶትስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ በያዝነው ሳምንት የሚከበረው ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ባማረ መልኩ በሰላም እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በመስከረም ወር በመዲናችን በርካታ እንግዶች እና ነዋሪዎች የሚታደሙባቸው ሁለት ታላላቅ ሃይማኖታዊ እና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት ባማረ መልኩ እንዲከበሩ ጽ/ቤቱ ከማዕከል እስከ ወረዳ በዘረጋው መዋቅሩ ላለፈው አንድ ወር በቅንጅት ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።
በደመራና መስቀል በዓልም አስቀድሞ በተከናወነ ተገቢ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በሁሉም አካባቢዎች በተከናወነው የደመራ ማብራት ሥርዓት ምንም ዓይነት አደጋ ሳያጋጥም ባማረና በደመቀ መልኩ መከበሩን ኢንጅነር ወንድሙ አስታውሰዋል።
የአደባባይ በዓል የሆነው ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች የሚታደሙበት በመሆኑ፤ ባማረ እና ከአደጋ ስጋት ነፃ በሆነ መልኩ እንዲከበር የከተማ ፅዳት እና ውበት፣ የቅድመ አደጋ መከላከል እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ሥራዎችን በተናበበ መልኩ ለማከናወን ጽ/ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገልጸዋል።
በሜሮን ንብረት
#EBCdotstream #Irreecha #HoraFinfine
አባገዳዎች ፣ ሃደስንቄዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር የኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ ለማክበር በተካሄዱ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ተወያዩ ።
የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ፤ የሰላም ፣ የእርቅ እና የወንድማማችነት የአደባባይ ክብረ-በዓል መሆኑን ገልጸው ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በርካታ ዝግጅት መደረጉን አባገዳዎች ገልፀዋል።
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸዉ የኢሬቻ በዓል ሲከበር በርካታ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገራት ዜጎች ጭምር የሚሳተፉበት ክብረ-በዓል በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀና ባማረ መልኩ እንዲከበር በማድረግ ለቱሪዝም ፍሰት የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ ይበልጥ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
ኢሬቻ ከፍተኛ የቱሪዝም ገቢ ማስገኛ በዓል ሆኗል ያሉት ተወያዮቹ በዓሉ ከፍተኛ የባህላዊ አልባሳት እና የሆቴሎች አገልግሎት ግብይት የሚካሄድበት በመሆኑ አግልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰፊ ዝግጅት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
አያይዘዉም በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ልማት እየተገነቡ ያሉ የልማት ስራዎች ለአደባባይ በዓላት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል ያሉት አባገዳዎች ፤ ከአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን የኢሬቻን ክብረ በዓል በደመቀ መልኩ እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል ።
የዘንድሮዉ አመት የኢሬቻ ክብረ በአል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት “ በሚል መሪ ቃል የሚከበር ይሆናል ።
#Irrecha
