uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሆራ ፊንፊኔ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጸዋል:: የሆረ ፊንፊኔ በዓል በስኬት መጠናቀቅ የአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች ላበረከቱት አስተዋጽዖ ከንቲባ አዳነች አመስግነዋል:: በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቀን እና ምሽት በቂ አቅርቦት እና አገልግሎት ለእንግዶቹ በመስጠት ለበአሉ በድምቀት መጠናቀቅ ትልቅ ድርሻ የተጫወቱ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች በ5ቱም በር ያለው የከተማችን ነዋሪ የወንድማማች እና እህትማማች መንፈስን ተላብሶ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት እንግዶቹን በፍቅር መቀበሉን ጨምረው ገልጸዋል:: ከንቲባ አዳነችች አቤቤ በዓሉ በድምቀቅ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅዖ ያበረከቱ የከተማችን ነዋሪዎችን፣ ወጣቶችን፣ የጸጥታ አካላትን እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩን አመራሮች አመስግነዋል::

ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ AMN-Addis Media Network ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

እንኳን ለኢሬቻ በአል በሰላም አደረስዎ! መልካም በአል! የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

በድምቀት እየተከበረ ያለው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል(በፎቶ)

የ2017 ዓ.ም ሆራ ፊንፊኔ የእሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በልዩ ልዩ ሁነቶች መከበር ጀምሯል። የበዓሉ ስነ ስርዓት የተጀመረው በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት ነው። የበዓሉ ተሳታፊዎች ከሌሊት ጀምሮ ወደ ስፍራው በማቅናት ነው በዓሉን እያከበሩ የሚገኙት። በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተሳታፊዎች ወደ ሆራ ፊንፊኔ በማቅናት በባህላዊ አልባሳትና ህብረ ዜማዎች ተውበው በባህሉ መሰረት ለፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ ላይም ይገኛሉ።

መልካ ፊንፊኔ! ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ - 2017 AMN-Addis Media Network

ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ የሚያከብሩት የወንድማማቾች በዓል ነው::

እንኳን ለ2017 አ.ም የኢሬቻ በአል በሰላም አደረሰን/ አደረሳችሁ! ኢሬቻ በለምለም ሳር ፣ በአደይ አበባ፣ በለመለመ ምድር የሚገለፅ የተስፋ ፤የወደፊት ብሩህ ዘመን መገለጫ እና የደስታ ጊዜ ነው፡፡ የኢሬቻ በአል የሰላም፣ የምስጋና፣ የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የመሻገር እና የመሰባሰብ የኦሮሞ ህዝብ መገለጫ፣ የሁሉም የኢትዮጵያውን የብዝሀነታችን ተምሳሌት ነው፡፡ ኢሬቻ ሰው ከሰው የሚታረቅበት፣ ፈጣሪውን የሚለምንበት፣ ሰላም የሚያወርድበት ፣ የእርቅ፣ የስምምነት፣ የህብረት እና አንድነት የሚጠናከርበት በአል ነው፡፡ ኢሬቻ ሰላምን፣ እርቅን፣ፍቅርን፣ መቻቻልን፣ አንድነትን፣ አብሮነትና የወንድማማችነት እሴት የሚያጎለብት የሁላችንም ኢትዮጵያውያን የጋራ በአላችንና የሁላችንም ሃብት ነው። መላው የከተማችን ነዋሪዎች :- ለአገራችን ኢትዮጵያ ጠንካራ ማንነት መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል የጋራ በአላችን እንደ መሆኑ በእውነተኛ የእህትማማችነትና የወንድማማችነት ስሜት ይህን መልካም እድል ለቀጣይ እድገትና ብልፅግናችን በአግባቡ ልንጠቀምበት እንደሚገባ በዚህ አጋጣሚ መልእክቴን አሰተላልፋለሁ። መልካም በዓል ለሁላችን! ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ

እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን! የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ጭጋግ አልፎ ብራ ሲሆን፣ ወንዞች ጎድለው ምድር አረንጓዴ ለብሳ በአበቦች ስትዋብ፣ ቡቃያው ደረስኩ ደረስኩ ሲል፣ ክረምቱ ወደ ጸደይ ሲሸጋገር ተለያይቶ የቆየው ሁሉ የሚገናኝበት የአንድነት እና የወንድማማችነት መገለጫ በዓል ነዉ። ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አንዱ ምሰሶ ሲሆን የምስጋና፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የእርቅ እና የይቅርታ ተምሳሌት፣ የተራራቀ የሚገናኝበት በዓል ነዉ ። በብዝሃነት አጊጣ፣ በበጎነት ተኩላ፣ በትጉህ እጆች ያበበችው የሁላችን ጎጆ አዲስ አበባ እንግዶቿን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተቀብላ እያስተናገደች የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ቱሪስቶችን የምትስብ የጋራ መድመቂያ ከተማችን ሆናለች። ዉድ የከተማችን ነዋሪዎች፤ ከተማችንን ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል፣ የቱሪስት መዳረሻ ካደረጓት የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የኢሬቻ በዓል በመሆኑ ለህዝብ ትስስር፣ አብሮነት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የላቀ ሚና እንዳለው በመረዳት እንግዶችን ተቀብላችሁ በማስተናገድ አብሮነትን እና ወንድማማችነትን ከፍ ስላደረጋችሁ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ! መልካም በዓል!! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኢሬቻ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበን በጋራ የምናከብረው የአንድነት ምልክታችን ነው” - የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ “ኢሬቻ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበን በጋራ የምናከብረው የአንድነት ምልክታችን ነው” ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። በ6ኛ የኢሬቻ ፎረም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት አቶ ሽመልስ፣ “ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እንዲሁም የጎረቤት ሀገራት በዓል እየሆነ መጥቷል” ብለዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ገንቢ የሆኑ የኦሮሞ ባህላዊ እሴቶችን የመንግሥት የአስተዳደር አካል እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል። ከእነዚሀ መካከል ባህላዊ ፍርድ ቤቶች እና የዜግነት ግዴታ የሆነውን የእርስ በርስ መተጋገዝ "ቡሳ ጎንፋን" ሥራ ላይ እያዋለ መሆኑን ነው የጠቆሙት። ሕፃናት ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ግብረ ገብነትን እንዲማሩ የገዳ ሥርዓትን የሥርዓተ-ትምህርት አካል ተደርጎ እየተሰጠ ይገኛልም ብለዋል። ኢሬቻ የመሻገር በዓል ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ፈጣሪው (ዋቃ) ስላደረገለት መልካም ነገር ሁሉ የሚያመሰግንበት እንዲሁም መጪው ጊዜ መልካም እንዲሆን ለፈጣሪው አደራ የሚሰጥበት ልዩ በዓል መሆኑን በንግግራቸው ጠቁመዋል።