Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
በነገዉ ዕለት በአዲስ አበባ የሚከበረዉ የኢሬቻ በዓል ከማናቸዉም አደጋ ክስተት ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች እንዲሁም የኮሚሽኑ የቅድመ ሆስፒታል ህክምናና አንቡላንስ አገልግሎት ባለሙያዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በዓሉ በሚከበርበት ቦታ በተለያዩ አቅጣጫዎች አስፈላጊዉን ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ።
በሌላ በኩልም እሁድ በቢሾፍቱ በሚከናወነዉ የኢሬቻ በዓል ላይም ተመሳሳይ ዝግጅት አድርገዉ ወደስፍራዉ ተጉዘዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የተከበርከው የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ
እንኳን አስቸጋሪውን የክረምት ወቅት አልፈህ ለብሩሁ ብራ ተሸጋገርክ!
ኢሬቻ ዕርቅ ነው፤ ፈጣሪ ደግሞ ዕርቅ ይወዳል። የተጣሉ ሰዎች ቂም ይዘው ለኢሬቻ ወደ መልካ አብረው አይወርዱም። ኢሬቻ መትረፍረፍ ነው! ኢሬቻ ምስጋና ነው! ኢሬቻ ልምላሜ ነው!
ለምለም ሣር ክብርን ፣ ፍቅርን እና መልካም ምኞትን ይወክላል። ብራ ሽግግር ነው፤ ያለፈውን ወደኋላ ትተን ወደ አዲስ ተስፋ በንጹሕ ኅሊና እንሻገራለን። ከሕዝቡ እሴት ውስጥ ጎልቶ የሚታየውም ይህ ነው። ኢሬቻ አንድነት ነው። ኢሬቻ ኅብረት ነው። ከኢሬቻው መልካ የሚቀርም ሆነ ወደ ኋላ የሚል የለም። አባቶችና እናቶቻችን አቆይተው ያወረሱን እሴት ማዳላት የለውም። ሰው ሁሉ እኩል ነው። “ሰብአዊነት ከሰው ውጪ ትርጉም የለውም” ብሎ ነው ኦሮሞ የሚያምነው። ኦሮሞ እና አብረውት የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦችም ፈጣሪ ባበጀው መልካና ወንዝ ላይ ይሰባሰባሉ። ይህ ደግሞ ወንድማማችነት ነው። ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ብዝኃነት በመልካ ኢሬቻ ላይ ይታያል። ይህ ደግሞ የሀገራችን ሕዝቦች እርስ በእርስ ያላቸውን መቀባበል እና መከባበር እንዲሁም መልካም ምኞት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያሳይ ነው። ወንድማማችነታችን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ነው። ከሌላ የወሰድነው ሳይሆን የተወለድንበት ነው ። ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያደግንበትና የኖርንበት ነው። ከውጭ እንደሚያዩን ሳይሆን በውስጣችን ከብረት የጠነከረ አንድነት አለ። አንድ ላይ ከቆምን፣ የእኛን መፍረስ ሲያሟርቱ የሚውሉትን ማሳፈር እናውቅበታለን።
ታሪካችንም ይህንኑ ያሳያል። ኦሮሞ ከሌሎች ፍጥረታት አንድነት ጋር እያነፃፀረ ፈጣሪውን ሲለምን ፦
“ ፈጣሪ ሆይ፣
ሠርተህ አታፍርሰን፣
ከለላ አታሳጣን፣
ልባችንን ከድንጋጤ ፣
ዓይናችንን ከዕንባ ታደግ ።
ከመለያየት ታደገን፣ እንደዛፍ አጽንተህ አቁመን!”
በማለት ፈጣሪውን ይለምናል። እንደዛፍ ተተክሎ የጠነከረና ሥር የሰደደ አንድነት ስጠኝ በማለት ወደ ፈጣሪው ይጸልያል። በዚህ ጸሎት ውስጥ ከሁሉም በላይ የሆነው ፈጣሪ አለ። ሰፍ (ሌላውን ማክበር) አለ። ፍጥረት አለ። የሰው ልጅ ከፈጣሪ ጋርና ከሌሎች ፍጥረታት ጋር ያለውን ግኑኝነት ከዚህ ወደ ፈጣሪ ከሚደረግ ጸሎት እንገነዘባለን።
ኦሮሞ የጊዜ ቀመርን/ዑደትን በራሱ ያውቃል። የከዋክብትንና የጨረቃን ዑደት በመቁጠር በዓላትን ያሰላል። ይህ ልዩ ስጦታ ነው። የክዋክብትን ዑደት ማወቅ መመራመርን ይጠይቃል፤ ሥልጣኔን ይጠይቃል። አርቆ በማሰላሰል ለሌላው አቅርቦ ማስገንዘብን ይጠይቃል። የክዋክብትን ዑደት ማወቅ ቀናትን ማወቅ ነው፤ ወራትን ማወቅ ነው፤ ዘመኑንና ገዳውን ማወቅ ነው፤ ታሪክንና ሁነትን ማወቅ ነው። በጋን እና ክረምትን ማወቅ ነው። የፈጣሪን ኃይልና የሚገባውን ምስጋናም ማወቅ ነው። ኦሮሞ ከልምድ ያካበተው ቱባ ዕውቀት እንደ አየር ሁኔታ ትንበያ ባለሞያ ወቅቶችን በመለየት እንደየባህሪያቸው አብሮ እንዲኖር ረድቶታል። ኦሮሞ የጨረቃና የክዋክብትን ግንኙነት የሚረዳበት ጥበብ አለው። ቅደም ተከተላቸውንና አሰላለፋቸውን በማየት ያለፈውን ነገር ይተነትናል፤ መጪውን ይተነብያል። የጊዜ ዑደት ይህን ዕውቀት ይጠይቃል። የገዳ ሥርዓት የዚህ የጊዜ ዑደት ውጤት ነው። የልቡና ዓይን ወይንም የአስተውሎት ውጤት ነው።
ስለመቸገር እና መትረፍረፍ፣ ስለ እንስሳትና ሀብት ማፍራት፣ ስለ ኑሮና ሕይወት፣ ከሌሎች ጋር ስለመኖር ግኑኝነትና ጉርብትና፣ ስለ አንድነትና ኅብረት፣ ስለ እውነትና ስለ ሰብአዊነት ሁሉ በወጉ ደንግጎ ያስቀመጠ ሥርዓት ነው። እንዲህ ያለው ሥርዓት ከራዕይ ውስጥ የሚቀዳ እንጂ በአንድ ጀምበር የሚረጋገጥ አይደለም።
የትናንቱ ሥልጣኔ መርሕ ዛሬም ያስፈልገናል። አሻግሮ የሚያይና ረጅሙን የምናሳጥርበት ሐሳብ ዛሬም እጅጉን ያስፈልገናል።
ገዳ የአስተውሎት ውጤት ነው። ኦሮሞ የቸገረውን ነገር የሚፈታበትና ዘመን የማይሽረውን ጠንካራ ሥርዓት በአስተውሎት በማበጀት ተጠቅሞበታል። ጎረቤቶቹ ሆነው የሚኖሩ ወንድሞቹ ከዚህ አስተዋይነቱ ተጠቅመዋል። ገዳ ምርጫን በስምንት ዓመት በማድረግና የሥልጣን ጊዜን በመገደብ በፈቃደኝነትና በሰላም ሥልጣንን መረካከብን አስተማረ።
ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ለመሻገር የዝግጅት ጊዜ እንደሚያስፈልግ አስቀመጠ። የኃላፊነትን ሥልጣን በየዘርፉ፣ በዕድሜና በጾታ በመከፋፈል፣ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሁሉንም በማሳተፍ ወደ ኅብረተሰቡ የመቅረብ መደበኛ አሠራርን በማስቀመጥ፣ ማኅበራዊ አንድነትንና ሰላምን በማስከበር ውስጥ ሁሉም ዜጋ ድርሻ እንዳለው ደነገገ። ይህ የአስተውሎት ውጤት ነው፤ የንቃት ውጤት ፤ የመገንዘብ ውጤት ነው፤ የመተንተን ውጤት ነው።
እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፋይዳ በሌላቸውና ማንም ተነሥቶ የግሉን እና የቡድን ፍላጎቱን ለማሳካት የሚያቀብለን አጀንዳ ላይ ጉልበታችንን ከመጨረስ ወጥተን፣ በዋናው ጎዳናችን ላይ እናተኩር። ክብርንና ፍቅርን ይዘን ድህነትና ችግር አውልቀን እንጣል። ወደ ብልጽግና መልካ እንገሥግሥ።
ያመለጠ ዕድል ድጋሚ አይገኝም። ለዚህ ትውልድ ያለን ዕድል አሁን ነው። በተገኘው ዕድል የሀገራችንን መጪ ጊዜ አሁኑኑ ማበጀት አለብን። እንደ አባቶቻችን ትልቅ የማስተዋል ጉልበት ያስፈልገናል። የወደቀ ሐሳብ ይዘን መደነቃቀፍ ለውድቀት ካልሆነ ወደፊት የምንወነጨፍበት ጉልበት አይሆነንም።
አባታቾቻን ከዚህም ከዚያም ጩኸትና ትችት ስለበረከተ የገነቡትን ሥርዓት አልጣሉትም። እኛም እንዲሁ ነን፤ ማንም በውሸት ከዚህም ከዚያም ተቀባብሎ በመጮህ በውሸት ጩኸት ቢረዳዳም የያዝነውን ነገር ከግብ ሳናድርስ አንቀርም። የተሰጠን አደራ አለ ። የተሰጠንን አደራ ይዘን የጀመርነውን በስኬት እናጠናቅቃለን። ብዙ ወጣቶችን አጥተንበት አደራ አንበላም። ሀገራችን ኢትዮጵያ እውነት አላት። ካለፈው መልካም ነገር እንወስዳለን፤ ያለፈው የሚወቀስበትን እያስተካከልን እንዳንወቀስ አድርገን እንሠራለን። የሰውን ልጆችን በእኩል ማየትን ከገዳ እንማራለን። አሁንም ትልቅ አስተውሎት ያለው ይህ ሕዝብ ለኢትዮጵያ የተሻለ ነገር በመፍጠር ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ታላቋን ኢትዮጵያ ይገነባል።
እንኳን ለ2017 የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ገዳው የበረከት ይሁንልን!
ዘመኑ የብልጽግና ይሁን!
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!
መስከረም 24፤ 2017
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
እሬቻ ለባህላችን ህዳሴ!
የኢሬቻ በዓልን በማስመልከት የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ
መስከረም 25 በአዲስ አበባ የሚከበረውን የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን በማስመልከት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት አስተባባሪነት በዓሉ በሚከበርባቸው አደባባዮች ፅዳት ዘመቻ ተካሄዷል።
“እሬቻ ለባህላችን ህዳሴ! ” በሚል መሪ ሀሳብ ዘንድሮ የሚከበረውን ኢሬቻ በአል በማስመልከት የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች፣ወጣቶች እንዲሁም አመራሮች በጋራ በመሆን የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።
በስፍራው ተገኝተዉ ንግግር ያረጉት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት የክፍለ ከተማው ወጣቶች እና ነዋሪዎች፣ የሰላም ሰራዊቱ እያከናወኑት ያሉት በጎ ተግባር የበዓሉን መንፈስ የሚያንፀባርቅና አገራዊ አንድነትን የሚያጎለብት ነው ብለዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ በበኩላቸዉ ነዋሪዎችና ወጣቶች ያሳዩት የአንድነት እንቅስቃሴ የሚያስመሰግንና የሚቀጥል መሆን እንዳለበት ተናግረው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጥሩ አካላት የጥፋት አላማ እንዳይሳካ የሚያደርግና የአገሪቱን ሰላምና አንድነት አጠናክሮ የሚያስቀጥል ነው ሲሉም ገልፀዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ በበኩላቸዉ የኢሬቻ በዓል ለማክበር በክ/ከተማችን ለሚያልፉ እንግዶች በፀዳ አካባቢ ለማስተናገድ ይረዳ ዘንድ ይሄ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል ያሉ ሲሆን በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ሁላችንም ርብርብ እናድርግ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ዛሬ የ2017 የኢሬቻ ፎረም አካሂደናል።
6ኛው ዙር የኢሬቻ ፎረም አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣ አምባሳደሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የፌደራል ክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ፎሌዎች፣ ዲያስፖራዎች እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት አካሂደናል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃ ማንነቶች ባለ ፀጋ እንደመሆኗ መጠን ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ በዓላት አንድነትን፣ ፍቅርንና የህዝቦች ትብብርን በማፅናት ረገድ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት በዓል ሆኖ በመከበር ላይ ይገኛል።
ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አንዱ ምሰሶ ሲሆን የምስጋና፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ሆኖ የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ከፈጣሪ፣ ከተፈጥሮ እና ከሰው ሁሉ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያድስበት ነው። በኢሬቻ የተራራቀ ይቀራረባል፤ የተቀያየመም ይታረቃል።
የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ለረጅም ዓመታት ተቋርጦ የቆየ ቢሆንም ለውጥን ተከትሎ ወደ ቀድሞ የማክበሪያ ስፍራው ተመልሶ በሁሉም ህዝቦች ወንድማማችነት ደምቆ መከበር ከጀመረ እነሆ ዘንድሮ 6ኛ ዓመቱን ይዟል።
ኢሬቻ አሁን ከባህላዊ ክንውንነቱ አልፎ የከተማችንና የሀገራችን የቱሪዝም መስህብ እና ሰፊ የገቢ ምንጭ ወደመሆን ተሸጋግሯል።
በዚሁ አጋጣሚ ለመላው ህዝባችን እንኳን ለ2017 የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ እያልኩ የሁሉም ቤት የሆነችው አዲስ አበባችን ለክብረበዓሉ ወደ ከተማችን የሚመጡ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት እንግዶቿን መቀበል ላይ የምትገኝ ሲሆን ውድ የከተማችን ነዋሪዎች እንግዶችን ለመቀበል እያደረጋችሁት ላለው መስተንግዶ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
በድጋሚ እንኳን አደረሰን!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ኢሬቻ ለህዝባችን ትስስርና ወንድማማችነት የሚኖረው አስተዋጽኦ የጎላ ነው!” ከንቲባ አዳነች አቤቤ
6ኛው የኢሬቻ ፎረም "ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ"በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በአድዋ ድል መታሰቢያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።
በፎረሙ ላይ የመከፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፡- የህዝባችን አብሮነት፣ አብሮ መኖርንና መተባበርን መሰረት ካስያዙ ባህሎች መካከል ኢሬቻ አንዱ ነው፡፡
ኢሬቻ ከባህላዊ ክንውን አልፎ ለከተማችን እና ለሃገራችን የቱሪዝም መስህብ እየሆነ መጥቷል፡፡ የበለጠ ካስተዋወቅነው እና ጎልቶ እንዲታይ ካደረግነው ከዚህ በላይ የቱሪዝም መስህብነቱ የሚጨምር እንደሚሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ኢሬቻ ፍቅር ነው፣ ኢሬቻ አብሮነት ነው፣ ኢሬቻ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ትስስርና ወንድማማችነት የሚኖረው አስተዋጽኦ የጎላ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
"እሬቻ ለባህላችን ህዳሴ" በሚል ከወረዳ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው 6ተኛው የእሬቻ ፎረም በከተማ ደረጃ ታሪክንና ቅርስን አጣምሮ በያዘው በግዙፉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል።
በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ አባገዳዎች፣ የድፕሎማሲ ማህበረሰቦች ፣ ሀደ ስንቄዎች ፣ ፎሌዎች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየታደሙ ይገኛሉ።
ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት የከተማ አቀፍ የገቢ ንቅናቄ መድረክ በማዘጋጅት ከግብር ከፋዮቻችን እና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገናል::
በውይይት መድረኩ ላይ ግብር ከፋዮቻችን በከፈሉት ግብር የተሰሩ ስራዎችን አድንቀው ቢስተካከሉ የሚሏቸው ክፍተቶችን ያስረዱን ሲሆን በግብር ከፋዩች በኩልም ሊስተካከል የሚገባውን ዘርዝረው አንስተዋል::
ግብር ከፋይና ግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቶች ቤተሰቦች በመሆናቸው በጋራ ፣ በትብብር መስራታችንን ይበልጥ በማጠናከር ሀገርን መገንባታችንን እንቀጥላለን:: ያለ ግብር ፍትሃዊነት እንዲሁም ያለ ግብር መሰረተ ልማት አይጠበቅምና ይህ የጋራ ጉዳያችን በመሆኑ ግብር ከፋዮቻችን ግብራቸውን በወቅቱ በፍቃደኝነት በመክፈል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እንዲሁም ጉቦ የሚቀበሉ አካላትን በማጋለጥ እና መብታቸውን አውቀው እንዲታገሉ ጥሪ አቀርባለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እናህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኢሬቻ በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም እንዲከበር ኮሚሽን መ/ቤቱ ዝግጁነቱን እንዲያጠናክር በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አሳሳቡ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች የኢሬቻን በዓል ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም በድምቀት አከብረዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት የኢሬቻ በዓል በርካታ እንግዶች የሚታደሙበት በመሆኑ በዓሉ ያለምንም አደጋ ክስተት ተከብሮ እንዲያልፍ በዓሉ በሚከበርበት አካባቢና እንግዶች በሚገቡበትና በሚወጡበት ስፍራ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመለየት የቅድመ መከላከል ስራ እንዲሰራ አሳስበዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት መገለጫ በመሆኑ ሰላም፣ አንድነት ፣ ፍቅር ፣ የሚሰበክበትና ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል እንደሆነ ጠቅሰዉ ኢሬቻ የሁላችንም የኢትዮጵያዊያን በዓል በመሆኑ እሴቱን ማስጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ጎቤዎች ፣የኮሚሽን መ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድነገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንሰ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
