cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ “ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።” — 2ኛ ቆሮ 11፥28

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
13 582
Obunachilar
+5824 soatlar
+3667 kunlar
+1 77930 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
The Theology of Illness
1 52522Loading...
02
https://youtu.be/rCv5y4PTbRM?si=GzdW4lf680jInTRR
3 02116Loading...
03
ቃና ዘገሊላ #ዲያቆን_ሄኖክ_ሀይሌ
3 43054Loading...
04
ቅድስት ሚስት #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
4 17167Loading...
05
Media files
3 9704Loading...
06
"በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ…" (ኤፌ. 3፥16) *** ወልደ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እስከ መስቀል በደረሰ የማዳን ግብሩ የገለጠው የሥላሴ ሰማያዊ ፍቅር በልቡናችን እስካልታተመ እና በፈቃዳችን ራሳችን ለወደደን ለእርሱ ትእዛዛት ተገዥዎች አድርገን እስካላቀረብን ድረስ ጌታችን ደጋግሞ የሚያወድሰው፣ ሐዋርያው ጳውሎስ ከአንደበቱ የማይለየው 'እምነት' ርቱዕ በሆነ መልኩ አለን ማለት አንችልም። እምነት ከተስፋ እና ፍቅር ያልተለየ ሕያው እና የሚለውጥ ነገር እንጂ ተራ እውቀት አይደለም። ስለ ክርስትና ብዙ እውቀት ስላለን እምነት አለን ማለት አይደለም። (እንዲያውም እውቀት ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆተ ከሆነ ትዕቢትን በማምጣት የእምነትን ብርሃን ሊያጨልም ይችላል!) እምነት ማለት ማንነትን የሚለውጥ ኃይል ነው። እምነት ጸሎተ-ሃይማኖትን መድገም ብቻ አይደለም፤ በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ መኖር እና ለጌትነቱ ራስን ማስገዛትም ነው እንጂ። ዲያቆኑ በቅዳሴ ሰዓት ጸሎተ ሃይማኖትን እንድንደግም ሲያዘን "በጥበበ እግዚአብሔር" ይሁን የሚለን ለዚህ ነው። እምነት በፍቅር ለፈጠረን፣ ላዳነን እና ልጆቹ ላደረገን አምላክ በፍቅር መታመንም ነው! ዛሬ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን መታሰቢያ አያደረግን ነው። እርሱ ከቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው። በዘመናት ሁሉ እንዲህ እንደ ጸሐይ እንዲያበራ ያደረገው ግን በዋናነት ሊቅነቱ ሳይሆን ቅድስናው ነው፤ ሊቅነቱ የቅድስና እንጂ የመራቀቅ ውጤት አይደለምና። Bereket Azmeraw
4 61228Loading...
07
https://youtu.be/hO6gduaui5E
4 64123Loading...
08
Repentance can comprise joy. The Holy Fathers have such a concept that encompasses both antipodes – sorrow and joy. It is when we cry over our sins, but in no way become desperate and discouraged, and our sorrow is dissolved by happiness, as we know that God loves us, no matter what and there is always hope and an opportunity, even for us the way we are… Our Church is full of such opportunities for a person to change and become a friend of God. #archpriestSergiyBaranov
5 2529Loading...
09
Repentance can comprise joy. The Holy Fathers have such a concept that encompasses both antipodes – sorrow and joy. It is when we cry over our sins, but in no way become desperate and discouraged, and our sorrow is dissolved by happiness, as we know that God loves us, no matter what and there is always hope and an opportunity, even for us the way we are… Our Church is full of such opportunities for a person to change and become a friend of God. #archpriestSergiyBaranov
160Loading...
10
Media files
7 409150Loading...
11
መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ከበርናባስ ሽፈራው ጋር ዳሰሳ አድርገናል። እንድትመለከቱት እንጋብዛለን። https://youtu.be/5vlFBkDnFFU?si=DTNwFOWwF1w4TZpy
5 9795Loading...
12
መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ከበርናባስ ሽፈራው ጋር ዳሰሳ አድርገናል። እንድትመለከቱት እንጋብዛለን። https://youtu.be/5vlFBkDnFFU?si=DTNwFOWwF1w4TZpy
10Loading...
13
#ግንቦት_11 #ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅድስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት። ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ። ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው። ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ። በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ። ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ። ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ። ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው። የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም። በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም። ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው። ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ። ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
6 29833Loading...
14
እስኪ ንገሩኝ! ከእናንተ መካከል ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ አንዲትዋን ምዕራፍ ወይም ከሌላው የቅዱሳት መጻህፍት ክፍል ውስጥ ጥቂት በቃልህ ድገም ቢባል ይህን ማድረግ የሚችል ማን ነው? አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም። የሚያሳዝነው ነገር ግን ይኼ ብቻ አይደለም። ከመንፈሳዊ ነገሮች አንፃር እንደዚህ አእምሮ የጎደላችሁ ኾናችሁ ሳለ ዲያቢሎሳዊ በኾኑ ነገሮች ላይ ግን ከእሳት በላይ ኀያላን ናችሁ። እንዲህም በመኾናችሁ አንድ ሰው መጥቶ ዲያቢሎሳዊ ዘፈኖችንና የዝሙት ዜማዎችን ንገሩኝ ቢላችሁ ከእናንተ መካከል እነዚህን የሚያውቁና ደስ ተሰኝተው የሚደግሟቸው ብዙ ሰዎችን ያገኛል። ነገር ግን"ለምንድን ነው እንደዚህ የምትኾኑት?" ተብላችሁ ስትጠየቁ የምትመልሱትስ መልስ ምን የሚል ነው? "እኔ ከመነኮሳት አንዱ አይደለሁም። ሚስት አለቺኝ፣ልጆችም አሉኝ፣የቤተሰብ መሪ ነኝ" የሚል ምክንያት ታቀርባላችሁ። ለምን እንደዚህ ትላላችሁ? ከመነኮሳቱ ይልቅ ይበልጥ ማንበብ ያለባችሁ እናንተ ኾናችሁ ሳለ ብዙዎች እንዲጠፉ ያደረገው "ቅዱሳት መፃህፍትን ማንበብ ለመነኮሳት ብቻ ነው" የሚለው አመለካከታችሁ ነው። ይበልጥ ብዙ መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው በማእከለ ዓለም የሚኖሩትና ዕለት ዕለትም መንፈሳዊ ቁስል የሚያገኛቸው ሰዎች ናቸውና። ስለዚህም ከለማንበባችሁም በላይ" የእኛ ማንበብ ትረፍ ነገር ነው" ብላችሁ ማሰባችሁ በራሱ የዲያብሎስ አሳብ ነው። ወይስ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ "ዝንቱ ኵሉ ተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ - ይህም ኹሉ እኛን ሊገስጸን ተፃፈ"(1ኛ ቆሮ 10:11) ያለውን አላዳመጣችሁምን? ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ
7 27387Loading...
15
https://youtu.be/2UKFfLFLUBg?si=-BJ0hCfY4uischBK
6 5943Loading...
16
https://youtu.be/kcTIPUPlmY4?si=IEAopD7PNSE-AI-S
6 7707Loading...
17
ብዙዎች በሰርጋቸው ቀን "የአገራችን ባሕል ነው" የዘፈን ድግስን ያዘጋጃሉ። ወይም ደግሞ "ቤተሰብ እሺ አይልም" በማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን የቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ቃል ማስታወስ ይገባል "ጋብቻ ዝሙትን የምናጠፋበት መድኃኒት ነው። ስለዚህ በዲያብሎስ ስራ (በዘፈን) ጋብቻን አናቃልል። ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያገቡ ሰዎች በቃና ዘገሊላ እንደ ኾነው ያድርጉ። በመካከላቸው ጌታችን ክርስቶስ እንዲኖር ያድርጉ። "እንዴት ይህን ማድረግ ይችላሉ? ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል። ካህናትን በመጥራት! 'እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል' ይላልና (ማቴ 10:40)። ስለዚህ ዲያብሎስን አርቁት። የሴሰኝነት ዘፈኖችን፣ የርኵሰት ዜማዎችን፣ ሥርዓት የለሽ ጭፈራዎችን፣ የሚያሳፍሩ ቃሎችን፣ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣ ሁከቶችን፣ቅጥ ያጡ ሳቆችን፣ ሌሎች እነዚህን የመሰሉ አግባብ ያይደሉ ነገሮችንም አስወግዱ። በእነዚህ ፈንታም የጌታችን ክርስቶስ ቅዱሳን አገልጋዮችን ጥሩ ፣ በእነርሱም በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋችሁ ላይ ይገኛል። " በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነው" ብሏልና (ማቴ 12:50)። አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ያሉ ተግሣጻትን ስለምናገርና የጥንት ባሕሎችን ስለማስቀር አሰልቺና አስቸጋሪ እንደ ኾንኩ አድርገው እንደሚያስቡ ዐውቃለው። ነገር ግን እነርሱ ስለ ተቃወሙኝ በፍጹም አልጨነቅም። እኔ የምፈልገው በእናንተ ዘንድ ተቀባይነትን ማግኝት ሳይኾን የእናንተን ጥቅም ነውና። ከዚህ ጥበብ ጥቅምን እንድታገኙ እንጂ እንድታመሰግኑኝ አልፈልግምና። ስለዚህ "ይህ ባሕል ነው" ብሎ አንድ ሰውስ እንኳ አይንገረኝ። ኀጢአት በድፍረት የሚፈፀምበት እስከ ኾነ ድረስ ባሕሉን እርሱት። ክፉ ሣራ የሚሰራባቸው እስከ ኾኑ ድረስ ባህሎቹ የቱንም ያህል ጥንታውያን ቢሆኑ ከእናንተ አስወግዷቸው። ክፉ ስራ የማይሰራባቸው ከኾኑ ግን ያልተለመዱ እንኳን ቢሆኑ ተቀበሏቸው።
9 663143Loading...
18
Media files
7 2335Loading...
19
https://youtu.be/UBOl18NwQP4?si=g9hXmpQxcXla3bK9
7 36820Loading...
20
Media files
6 9597Loading...
21
One of the main characteristics of love is self-sacrifice. If a person is ready to die for his beloved one, then he loves. If he is not ready to die, then this is something else. For a loving person, such sacrifice is not burdensome, but sweet. A loving person is ready to suffer voluntarily in order to please his beloved one and is even happy to suffer. After all, as far as gifts are concerned, it is more pleasant to give them then to receive. Thus, the point of human happiness is in love. However, people have committed some deeds that are contrary to love and let egotism into their hearts. I say it again, love is one's readiness to die for the beloved one, while egotism is readiness to kill the beloved one for one's own sake. This was the reason why paradise was lost. Egotism is the reason why we all suffer here on earth. God does not punish us. We ourselves came to this! #archpriestSergiyBaranov
8 11456Loading...
22
ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች 👉እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለ ሆነ 👉የቤተ ክርስቲያን ባሕርይዋና ማንነቷ የሚገለጥበት ስለሆነ 👉ከዕረፍታቸው በኋላም ሕያዋንና አዋቂዎች ስለ ሆኑ 👉አስተምህሯችን፣ እምነታችን፣ ተስፋችን፣ ... የሚገለጥበት ስለ ሆነ በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
7 957110Loading...
23
Media files
16 183157Loading...
24
https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ
8 0253Loading...
25
ወንድ ልጅ በገጽ፣ ሴት ልጅ በሕይወት ክርስቶስን ይመስሉታል። ወንድ በራስነቱ ሴት ልጅ ይክበር ይመስገንና ወልድ በፈቃዱ ለአብ እንደ ታዘዘ ለባሏ በመታዘዝ ክርስቶስን ትመስለዋለች። ወንድ እንደ ክርስቶስ ሕይወቱን እስከ መስጠት ደርሶ ሚስቱን እንደሚወዳት እርሷም ለእርሱ ለውዷ በሕይወትና በሞት መካከል ሆና ጽኑ ሕማምን ተቀብላ የፍቅራቸው ፍሬ የሆነውን ልጅ በእቅፉ ታኖርለታለች። እርሱ ጌታችን ጽኑ ሕማምን በመቀበል ሕያው በሆነ ሞቱ እኛን ልጆቹን እንደወለደን።(ዮሐ 16:21) Shimelis Mergia
10 123102Loading...
26
Media files
9 50467Loading...
27
ልደታ ለማርያም በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡ ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት
11 74183Loading...
28
https://youtu.be/t6cNxC1xFo8?si=_HYTllVZeXno-MRl
7 89824Loading...
29
በቅርብ ቀን በዐበይት ወቅታዊ ጉዳዮች ይጠብቁን! በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ብቻ! * ከግንቦት እስከ ግንቦት * የቅድስት ቤ/ክ ማእከላዊነት ላይ የተደቀኑ ፈተናዎች * የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና መጠበቅ * የመንግሥትና የሃይማኖት ድንበር * ኦርቶዶክሳዊ ኅብረት ለምን? * ዛሬ ምእመናን ከአባቶች ምን ይጠብቃሉ? * መልሶ ማልማትና የሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት
8 0789Loading...
30
ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤ ሰኞ የትንሣኤው ማግሥት ዕለተ ሰኞ ‹ፀአተ ሲኦል› ወይም ‹ማዕዶት› ትባላለች፡፡ ይህቺውም ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ናት (ዮሐ. ፲፱፥፲፰፤ ሮሜ. ፭፥፲-፲፯)፡፡ ማክሰኞ ይህቺ ዕለት፣ ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቶማስ› ተብላ ትጠራለች፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ በመጣ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት ‹‹ሳላይ አላምንም›› ብሎ ነበር፡፡ በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን በድጋሜ ለሐዋርያት ተገለጸ፡፡ ስለዚህም ይህቺ ዕለት በሐዋርያው ቶማስ ስም ተሰይማለች (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ረቡዕ ጌታችን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላስነሣው ለአልዓዛር መታሰቢያ ናት፡፡ በክርስቶስ ሥልጣን የአልዓዛርን ከሞት መነሣት አይተው ብዙ ሕዝብ በጌታችን ስለ አመኑ ዕለቲቱ (ረቡዕ) ‹አልዓዛር› ተብላ ትታሰባለች (ዮሐ. ፲፩፥፴፰-፵፮)፡፡
5 78547Loading...
31
ኀሙስ ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች (ሉቃ. ፳፬፥፳፭-፵፱)፡፡ ዐርብ የትንሣኤ እሑድ ስድስተኛዋ ዐርብ ደግሞ በክርስቶስ ደም ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቤተ ክርስቲያን› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ ሐዋ. ፳፥፳፰)፡፡ ቀዳሚት ሰንበት በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበያይባት ‹የቁራ ገበያ፣ የገበያ ጥፊያ› ተብላ ትጠራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጕልበታቸው ላገለገሉት፤ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት፤ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት፤ በትንሣኤውም ጌታችንን ከዅሉ ቀድሞ ለማየት ለበቁት ሴቶች መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቅዱሳት አንስት› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፭፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፫፥፳፯-፴፫፤ ፳፬፥፩-፲)፡፡ እሑድ ሰንበት በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
7 16650Loading...
32
ለምን አንጾምም? ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች? ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም? በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/። "የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ 15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው። በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።
7 27751Loading...
33
https://youtu.be/UN9VneMm4_Y?si=rEIAirNnqftzaCix
6 3590Loading...
34
https://youtu.be/lpkekZNczXQ
6 35224Loading...
35
https://youtu.be/X2Ii1bpj2-M?si=nxi-DiEljoafHJD-
5 81822Loading...
36
በዓለ ትንሣኤን በትንሣኤ ልቡና እናክብር! ፋሲካ ማለት መሻገር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ወልድ እኛን ከወደቅንበት አንሥቶና ተሸክሞ ከዚኽ ምድር ወደ ሰማያት ተሻግሯልና (ተነሥቶ ዐርጓልና)፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ፡- ‹‹እንግዲኽ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችኁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን ሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም፡፡ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችኁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሯልና፡፡ ሕይወታችኁ የኾነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችኁ፤›› እንዳለን /ቈላ.፫÷፩-፬/፣ በጥምቀት ውኃ ሞቱን በሚመስል ሞት ስንሞት፣ አሮጌው ሰውነታችን እንደ ግብጻውያን ተቀብሮ ቀርቷል፡፡ አዲሱ ሰውነታችን ግን እስራኤላውያን ባሕሩ ተከፍሎላቸው እንደ ተሻገሩ ተሻግሯል (ተነሥቷል)፡፡ ብልየት ያለበት የቀዳማዊ አዳም ሰውነታችን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተቀብሮ አዲሱ ሰውነታችን ሕይወትን አግኝቶ ተነሥቷል፡፡ መሬታዊው ሰውነታችን ሞቶ ሰማያዊው ሰውነታችንን ለብሰን መንፈሳውያን ኾነን ተነሥተናል፡፡ ወደ ጥንተ ተፈጥሯችን ተመልሰናል፡፡ አኹን ከእኛ የሚጠበቀው ይኽ ተፈጥሯችንን ሳናቆሽሽ መጠበቅ ነው፤ እንደ ተነሣን መዝለቅ፡፡ ይኽን ለማድረግም ተራራ መውጣት፣ ምድርን መቆፈር፣ የእሳት ባሕርን መሻገር አይጠበቅብንም፡፡ ይኽን ጠብቀን እንድንቈይ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ፈቃዳችንን፡፡ የሚሠራው እርሱ ራሱ ነውና /ዮሐ.፲፭÷፭/፡፡ መጽንዒ (የሚያጸና) መንፈስ ቅዱስን ያደለንም ስለዚኹ ነው፡፡ የምናመልከውን አምላክ መስለን በሕይወት ሳንሻገር የመሻገርን በዓል (ፋሲካን) የምናከብረው ምን ጥቅም እንዲሰጠን ነው? ከጨለማ ሥራ ወደ ብርሃን ሥራ፣ ከፍቅረ ዓለም ወደ ፍቅረ ክርስቶስ ሳንሻገር ፋሲካን የማክበራችን ትርጕሙ ምንድነው? እኛው ሳንነሣ የመነሣት በዓልን ማክበራችን በፍርድ ላይ ፍርድ በበደል ላይ በደል ከመጨመር ውጪ የሚሰጠን ጥቅም ምንድን ነው? የምንነሣውስ መቼ ነው? በዐይናችን ጉድፍ ብትገባ ስንት ደቂቃ እንታገሣታለን? ታድያ በነፍሳችን ላይ የተጫነውን የኃጢአት ግንድ መቼ ነው የምናስወግደው? መቼ ነው ወደ ላይኛው ቤታችን ቀና የምንለው? ብዙዎቻችን በሕይወታችን ሳንሻገር ነው በዓለ ፋሲካን የምናከብረው፡፡ ክርስቲያን ኾኖ በመብልና በመጠጥ ብቻ ፋሲካን ማክበር ኢ ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡ አዲሱን ሰውነታችን ለብሰን ከተነሣን በኋላ እንደ ቀድሞ ምልልስ የምንጓዝ ከኾነ ግን ተመልሰን ወድቀናል፤ አዲሱ ሰውነታችንን አውልቀን አሮጌውን ሰውነታችንን በድጋሜ ለብሰነዋል፡፡ በእኛነታችን ውስጥ ፍቅረ ንዋይ፣ ፍቅረ ሲመት፣ ፍትወት፣ ይኽንንም የመሰሉ ዅሉ ካለ አዲሱ ሰውነታችን ከእኛ ጋር የለም፤ ቢኖርም ታሟል፡፡ በኃጢአት የመቃጠል ስሜት፣ ርኵሰትና ክፉ ምኞት ከእኛ ዘንድ ካለ አሮጌ ሰው ኾነናል፤ ትንሣኤ ልቡናን ገንዘብ አላደረግንም፡፡ ስለዚኽ ከልቡና ሞት እንነሣና ፋሲካን እናክብር፡፡ እስከ አኹን በኃጢአት ውስጥ ካለን ወደ ብርሃን ክርስቶስ እንምጣ (እንሻገርና) የመሻገርን በዓል እናክብር፡፡ ከክፉ ሥራ ወደ ጽድቅ ሥራ እንሻገርና የእውነት ፋሲካን እናክብር፡፡ ከኃይል ወደ ኃይል እንሻገርና ፋሲካን እናክብር፡፡ ከሞት ሥራ ወደ ሕይወት ሥራ እንነሣና የመነሣትን በዓል እናክብር፡፡ እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ሆይ! እኛን የሚያሰነካክል ደግሞም የሚጥለን ፈርዖን (ዲያብሎስ) ተሰነካክሎ ወድቋልና ከግብጽ ሕይወታችን እንውጣ፡፡ ተነሥተንም እንሻገር፡፡ ተሻግረንም ሰማያዊውን ፋሲካ እናክብር፡፡ በግብጽ የነበሩት እስራኤላውያን የበጉን ደም በጉበኑና በኹለቱም መቃን ሲቀቡት አጥፊው ከቤታቸው እንዳለፈ አንብበናል /ዘፀ.፲፪÷፲፫/፡፡ ይኸውም በጉ በራሱ ያንን የማድረግ ኃይል ስለ ነበረው አይደለም፤ ደሙ የክርስቶስ ደም አምሳል ስለ ነበር ነው እንጂ፡፡ እኛ ግን የአማናዊውን በግ /ዮሐ.፩፡፳፱/ ደም በልቡናችን፣ በአስተሳሰባችንና በሰውነታችን ዅሉ እንቀባና (እንቀበልና) እንሻገር፡፡ ይኽን ስናደረግ በእባቡና በጊንጡ ይኸውም በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ ሥልጣን ይኖረናል /ሉቃ.፲÷፲፱/፡፡ የምንበላው በግ ራሱ ሕይወት ስለ ኾነ ሞት በእኛ ላይ አይነግሥም /ዮሐ.፲፬÷፮/፡፡ በዚኽ ዓለም ሳለን ከዚኽ ደስታ ተካፋዮች ከኾንን (የመዠመሪያውን ትንሣኤ ልቡና በንስሐ ከተነሣን) በሚመጣው ዓለምም በክብር ላይ ክብር፣ በሹመት ላይ ሹመት እንቀበላለን (ኹለተኛውን ትንሣኤ እንነሣለን) /ሉቃ.፳፪÷፲፭-፲፮/፡፡ ብንወድቅ እንኳን መልሰን በመነሣት ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር፣ የክብር ክብር፣ ጌትነት የባሕርዩ በሚኾን፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰጭነት በመንግሥተ ሰማያት ጸጋ ክብር እናገኛለንና የጭንቅ ቀን ሳይመጣ በዓለ ትንሣኤን እናክብር፡፡ ለዚህም ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የመከረንን የሚከተለውን ኃይለ ቃል በተግባር ላይ ብናውለው እንጠቀማለን፤ ‹‹በምነግራችኁ ነገር እያበሳጨኋችሁና እያሳመምችሁ እንደ ኾነ ይገባኛል? ግን ምን ላድርግ? እኔም እናንተም በምግባር በሃይማኖት የታነጽን እንኾን ዘንድ ብቻ ሳይኾን ከዚያም እናመልጥ ዘንድ ነው፡፡ ነገር ግን በኃጢአት ከመጨማለቃችን የተነሣ እንዴት አድርጌ ላሳምማችኁ እችላለኁ? ብትሰሙኝና ብትለወጡስ እኔም ማረፍ እንኳን በቻልኩ ነበር፡፡ ስለዚኽ እስካልተለወጣችሁ ድረስ እናንተን መገሠፄንና መምከሬን አላቆምም፡፡ ስለ ገሃነመ እሳት ተደጋግሞ ሲነገር የሚበሳጭ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔ ግን ‹ከዚኽ የበለጠ ያማረ የተወደደ አስደሳች ትምህርት የለም› እለዋለኁ፡፡ ‹እንዴት ይኽ አስደሳች ትምህርት ነው ትለናለህ?› ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔም ‹ወደዚያ መጣል ከደስታ ዅሉ የራቀ ነውና› ብዬ እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚኽ ነፍሳችን ከመታሠሯ በፊት የነቃን የተጋን እንኾን ዘንድ ይኽን ደጋግሜ እነግራችኋለሁ፡፡ ንስሐ ይግባ እንጂ ማንም እንደ ተወቀሰ አያስብ፤ በንግግሬም የሚቆጣ አይኑር፡፡ ዅላችንም ወደ ጠባቢቱ መንገድ እንግባ፡፡ እስከ መቼስ በስንፍና አልጋ እንተኛለን? ዛሬ ነገ ማለት አይበቃንም ወይ? ሰማያዊ ቪላችንን ቀና ብለን ብንመለከት እኮ በዚኽ ምድር ይኽንን ለመሥራት ባልደከምን ነበር፡፡ እስቲ ንገሩኝ! ሩጫችንን ስንጨርስ ከሬሳ ሳጥንና ከመግነዝ ጨርቅ ውጪ ይዘነው የምንሔድ ነገር ምን አለ? ታድያ ለምን እንከራከራለን?›› (ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች፣ ገጽ ፻፶፮ – ፻፶፯)፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
8 87279Loading...
37
ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) እንኳን አደረሰን! ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ ‹‹ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?›› ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡ ‹‹ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር›› በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ ‹‹እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤›› አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት ‹‹ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ ወኀጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንም ከፍርድአታድን፤›› ትላለችና ‹‹እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤›› ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ‹‹በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤›› ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድ ወደ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡ ጌታችን ሲሰቅልም የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤ ፩. ፀሐይ ጨለመ፤ ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤ ፫. ከዋክብት ረገፉ፤ ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤ ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤ ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
5 46430Loading...
38
፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤ ፩. ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)››፤ ፪. ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ››፤ ፫. ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››፤ ፬. እመቤታችንን ‹‹ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ››፤ ደቀ መዝሙሩንም ‹‹እናትህ እነኋት›› በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤ ፭. ‹‹አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ›› ፮. ‹‹ተጠማሁ››፤ ፯. ‹‹ዅሉ ተፈጸመ›› (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ኾኖአል፡፡ ‹‹ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነ ፀሐይ›› እንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡ በዘጠኝ ሰዓት ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ቅድስት ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር›› እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
5 61654Loading...
39
Media files
5 35118Loading...
40
Media files
5 14817Loading...
The Theology of Illness
Hammasini ko'rsatish...
12👍 11
Hammasini ko'rsatish...
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ / Yaregal Abegaz ዮጋ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት እይታ ኢትዮጵያ Ethiopian Orthodox sibket ስብከት

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በዮጋ ዙሪያ የተሰጠ ኦርቶዶክሳዊ ማብራሪያ።

29👍 2
ቃና ዘገሊላ #ዲያቆን_ሄኖክ_ሀይሌ
Hammasini ko'rsatish...
👍 31 18🙏 11
01:55
Video unavailableShow in Telegram
ቅድስት ሚስት #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Hammasini ko'rsatish...
55👍 20
"በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ…" (ኤፌ. 3፥16) *** ወልደ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እስከ መስቀል በደረሰ የማዳን ግብሩ የገለጠው የሥላሴ ሰማያዊ ፍቅር በልቡናችን እስካልታተመ እና በፈቃዳችን ራሳችን ለወደደን ለእርሱ ትእዛዛት ተገዥዎች አድርገን እስካላቀረብን ድረስ ጌታችን ደጋግሞ የሚያወድሰው፣ ሐዋርያው ጳውሎስ ከአንደበቱ የማይለየው 'እምነት' ርቱዕ በሆነ መልኩ አለን ማለት አንችልም። እምነት ከተስፋ እና ፍቅር ያልተለየ ሕያው እና የሚለውጥ ነገር እንጂ ተራ እውቀት አይደለም። ስለ ክርስትና ብዙ እውቀት ስላለን እምነት አለን ማለት አይደለም። (እንዲያውም እውቀት ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆተ ከሆነ ትዕቢትን በማምጣት የእምነትን ብርሃን ሊያጨልም ይችላል!) እምነት ማለት ማንነትን የሚለውጥ ኃይል ነው። እምነት ጸሎተ-ሃይማኖትን መድገም ብቻ አይደለም፤ በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ መኖር እና ለጌትነቱ ራስን ማስገዛትም ነው እንጂ። ዲያቆኑ በቅዳሴ ሰዓት ጸሎተ ሃይማኖትን እንድንደግም ሲያዘን "በጥበበ እግዚአብሔር" ይሁን የሚለን ለዚህ ነው። እምነት በፍቅር ለፈጠረን፣ ላዳነን እና ልጆቹ ላደረገን አምላክ በፍቅር መታመንም ነው! ዛሬ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን መታሰቢያ አያደረግን ነው። እርሱ ከቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው። በዘመናት ሁሉ እንዲህ እንደ ጸሐይ እንዲያበራ ያደረገው ግን በዋናነት ሊቅነቱ ሳይሆን ቅድስናው ነው፤ ሊቅነቱ የቅድስና እንጂ የመራቀቅ ውጤት አይደለምና። Bereket Azmeraw
Hammasini ko'rsatish...
77👍 25🙏 10
Repost from Mahibere Kidusan
Hammasini ko'rsatish...
MK TV || ከማኅደራችን || በ1991ዓ.ም መምህር ያረጋል አበጋዝ ያስተማረው ትምህርት

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

https://www.facebook.com/eotcmkidusan/

43🙏 18👍 1
Repentance can comprise joy. The Holy Fathers have such a concept that encompasses both antipodes – sorrow and joy. It is when we cry over our sins, but in no way become desperate and discouraged, and our sorrow is dissolved by happiness, as we know that God loves us, no matter what and there is always hope and an opportunity, even for us the way we are… Our Church is full of such opportunities for a person to change and become a friend of God. #archpriestSergiyBaranov
Hammasini ko'rsatish...
44👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
Repentance can comprise joy. The Holy Fathers have such a concept that encompasses both antipodes – sorrow and joy. It is when we cry over our sins, but in no way become desperate and discouraged, and our sorrow is dissolved by happiness, as we know that God loves us, no matter what and there is always hope and an opportunity, even for us the way we are… Our Church is full of such opportunities for a person to change and become a friend of God. #archpriestSergiyBaranov
Hammasini ko'rsatish...
106🙏 33👍 17👏 13🕊 7