uz
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Kanalga Telegram’da o‘tish

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias analitikasi

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 19 949 obunachidan iborat bo'lib, Tibbiyot toifasida 1 157-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 1 681-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 19 949 obunachiga ega bo‘ldi.

27 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -557 ga, so‘nggi 24 soatda esa -23 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 26.07% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 6.79% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 5 203 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 354 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 10 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 28 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Tibbiyot toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

19 949
Obunachilar
-2324 soatlar
-1257 kunlar
-55730 kunlar
Postlar arxiv
በክንድ ስር የሚቀበር የወሊድ መከላከያ (implanon) ውድ የዶክክተር ቤዛ ቤተሰቦች ሆርሞንን ከሚይዙ ወሊድ መከላከያዎች መሃከል በክንድ ስር የሚቀበር የወሊድ መከላከያ ዘዴን እነሆ ፦ Implanon ትንሽ መተጣጠፍ የሚችል ዘንግ ሲሆን በላይኛው የእጅ ክንድ ከቆዳ ስር ይቀበራል። ይህ መከላከያ በሴት ግራ ክንድ ቆዳን ባለ 2 ወይም ባለ 1 ቀጫጭን የክብሪት እንጨት መጠን ያላቸው ካፕሱሎችን በሰለጠኑ ባለሙያዎች በመቅበር የሚከናወን ዘዴ ነው፡፡ አንዴ ከተቀበረ በኃላ ፕሮጀስትሮን የተባለውን ሆርሞን በዝግታ ወደ ደም ስር እየለቀቀ እስከ 3 ዓመታት ያህል እርግዝናን ይከላከላል። Implanon የሚሰራው በሚከተለው መንገድ ነው፦ 1.እንቁላል ማኩረትን በማዘግየት (እንቁላሉ ከእንቁላል እጢ ሲወጣ) 2.የማህፀን በር (cervix) ውስጥ የሚገኘውን (የሚያጣብቅ ፈሳሽ) በማወፈር ነባዘር (የወንድ የዘር ፍሬ) ወደ ማሕፀን ውስጥ እንዳይገባ በመከልከል 3. የማሕፀን የውስጠኛው ሽፋን ላይ ለውጥ በማምጣት ፅንሱ እንዳይመቸው በማድረግ ነው። የጎንዮሽ ጉዳት፡- • የወር አበባ ዑደት መዛባት • የክብደት መጨመር • ራስ ምታት • የሆድ ህመም • ድብርት • መከላከያው የገባበት አካባቢ ላይ መቆጣት (infection) • የድካም ስሜት እና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላል፣ ለጤና ግን አያሰጋም በመጀመሪያው ወራቶች ውስጥ ሊጠፉ ይችላሉ፡፡ ጠቀሜታዎች፦ • ልክ እነደ ወሊድ መከላከያ እንክብሎች ሁሌ መውሰድን አይጠይቅም • Estrogen(ኢስትሮጂን) ያለበትን የእርግዝና መከላከያ እንክበል መውሰድ ለማይችሉ • ልጅ የሚወልዱም ሆነ ገና ያልተወለዱ ሴቶች ሊጠቀሙበት ይችላሉ • መከላከያው የግብረ ስጋ ግንኙነትን አያውክም • መከላከያውን በሰለጠነ ባለሙያ ከወጣ በኅላ ወዲያውኑ ፅንስ ሊፈጠር ይችላል፡፡ IMPLANO መጠቀም የሌለባቸው • ለ ፕሮጀስትሮን (allergy) ከሆኑ • የጡት ካንሰር ህመም ካለ • የጉበት በሽታ ካለ • ከመጠን በላይ ክብደት ካለዎት • የደም መርጋት ችግር • የስኳር ህመም • ከፍተኛ የደም ግፊት • ከፍተኛ የስብ ክምችት • ከፍተኛ የሆነ ድብርት ካለ ስለ ምትከታተሉን እናመሰግናለን............. please like share comment

ሳይነስን_ለማከም_8_ቀላል_መንገዶች ****************************** የሳይነስ ህመምን በህክምና ማስታገስ የሚቻል ሲሆን ቤት ውስጥ በሚያደርጓቸው መፍትሄዎችም ህመሙን በማስታገስ የሚድኑበትን ግዜ ማፋጠን ይችላሉ። ♥በእንፋሎት መታጠን የፈላ ውሃ ተለቅ ያለ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ካደረጉ በኋላ ጎንበስ ብለው ፊትዎን በእንፋሎቱ መታጠን እንፋሎቱ እንዳያመልጥ ጭንቅላትዎን በፎጣ ይከናነቡ እናም በአፍንጫዎ ብቻ ይተንፍሱ። ♥ብዙ ውሃ መጠጣት ለማንኛውም ህመም በቂ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል።ውሃ፣ የፍራፍሬ ጁስ፣ እና አረንጓዴ ሻይ መጠጣት ህመሙን ያስታግሳል። ♥ሙቅ ውሀ ሳይነስ አካባቢ ሙቀት ማድረግ ህመሙን ለማስታገስ ይረዳል። ይህንን ማድረግ ይሚችሉበት ቀላል መንገድ የእጅ ፎጣ ወስደው ሙቅ ውሃ ውስጥ ከነከሩ በኋላ ፎጣውን ጨምቀው አፍንጫዎ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በማድረግ። ♥ዕርድ ዕርድ በውስጡ ከርከሚን የሚባል እብጠትና የመለብለብ ስሜትን ሚከላከል ንጥረነገር አለው፡፡ ይህ ንጥረነገር ሳይነስን ከመከላከሉም በተጨማሪ የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ያደርጋል፡፡500mg የእርድ ዱቄትን በውሀ በማዋሀድ ወይም በእንክብል መልክ በቀን ሁለት ጊዜ መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡ ♥ነጭ ሽንኩርት ነጭሽንኩርትን በብዛት መመገብ እጅግ በርካታ የጤና ትሩፋቶችን ያስገኛል፡፡ በውስጡ አሊሲን የተሰኘ ንጥረነገር የያዘ ሲሆን፣ይህ ንጥረነገር ቫይረስ ፣ባክቴርያና ፈንገስን የሚከላከል በመሆኑ ለሳይነስ ኢንፌክሽን ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡ በቀን ውስጥ ከሁለት እስከ ሶስት ራስ ፍሬሽ ነጭ ሽንኩርትን በማንኛውም ዓይነት መመገብ ከፍተኛ ውጤት ያስገኛል፡፡ ♥ቀረፋ በውስጡ ጎጂ የሆኑ ሳይነስን የሚያስከትሉ ባክቴርያዎችን የሚገድል ኬሚካል ስላለው ከግማሽ የሻይ ማንኪያ እስከ አንድ የሻይ ማንኪያ ድረስ ከወለላ ማር በመቀላቀል ወይም ብቻውን በአንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሀ መጠጣት ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡ ♥ዝንጅብል ዝንጅብል በውስጡ ፀረ-የአፍንጫ ፈሳሽ እና ፀረ-መለብለብና እብጠት ኬሚካሎችን በውስጡ ስለያዘ እንዲሁም የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ስለሚጨምር ሳይነስን ለመከላከል ይረዳል፡፡ የዝንጅብል ሻይን ከሎሚ ጭማቂ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም ለሳይነስ ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡ ♥እረፍት ማድረግ ህመሙ በተሰማዎት ግዜ ስራ ወይም ጥናት ላይ ማተኮር ይከብዳል ግዜ ወስደው በማረፍ ሰውነትዎ እንዲያገግም ማድረግ ይችላሉ። እንዚህን የቤት ውስጥ መፍትሄዎች ሞክረው ህመሙ ከ2-3 ሳምንት ውስጥ ካልተሻለዎ ሃኪም ጋር ሂዶ ማማከር ተገቢ ነው።

የዲስክ መንሸራተት የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ። ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚቋቋሙ ክፍሎች ናቸው።ዲስክ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ አለው ። የዲስክ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውስጥ ፈሳሽ መውጣት ነው። ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው።ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ ግዜ በእጅ ላይ የመደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም ስሜት አይኖረውም። የተንሸራተተው ዲስክ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማንም። መንስኤዎች የዲስክ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከጊዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ዲስክ ከእድሜ ጋር ውሃማ ይዘቱን ያጣል። ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል:: የዲስክ መንሸራተት መቼ እንደተፈጠረ ማወቅ ያስቸግራል ነገር ግን የሚከተሉት እንደ መንስኤ ይገለጻሉ፡፡ ቁርጭምጭሚታችንን ሳናጥፍ ከባድ እቃ ለማንሳት ስንሞክር ከባድ እቃ ይዘን ከጀርባችን ስንታጠፍ ነው። ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች 🔺 ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት 🔺 እድሜ 🔺 ከባድ ስራ መስራት 🔺 በዘር ተመሳሳይ ችግር ካለ ምልክቶች 🔺 የታችኛው ጀርባ ህመም 🔺 በትከሻዎ ፤ በጀርባዎ ፣ በእጆችዎ ወይም በእግሮችዎ ላይ የመደንዘዝ ስሜት። 🔺 የአንገት ህመም 🔺 ጀርባዎን ማጠፍ ወይም ለማስተካከል ሲጥሩ ህመም 🔺 የጡንቻ ድክመት 🔺 ከወገብ በታች የዳሌ ህመም ውስብስብ ችግሮች 🔺 ህመም መደንዘዝ ወይም ድክመት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎን እስከሚያደናቅፉ ድረስ ሊጨምር ይችላል 🔺 የፊኛ ወይም የአንጀት ችግር መከላከያ መንገዶች 🔺 ትክክለኛ የሰዉነት አቋም እንዲኖር ማድረግ 🔺 ከባድ እቃ በሚያነሱበት ወቅት ጫናዉን/ክብደትዎን ከጀርባዎ ይልቅ በእግሮችዎ ላይ ማድረግ 🔺 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ 🔺 ለረጅም ጊዜ የሚቀመጡ ከሆነ ቀጥ ብለዉ ለመቀመጥ መሞከር 🔺 የሚተኙበትን ሁኔታ ምቹ ማድረግ 🔺 ክብደትዎን በትክከል መጠበቅ ህክምና 🔺 ሙቅ ነገር መያዝ ህመምን ለማስታገስ ይረዳል 🔺 ከመጠን ያለፈ እረፍት ማስወገድ/ መጠነኛ እንቃስቃሴ ማድረግ 🔺 የህመም ማስታገሻ መድሐኒቶች 🔺 ጡንቻን የሚያፍታቱ መድሐኒቶች መጠቀም 🔺 በባለሙያ የታገዘ የፊዚዮቴራፒ ህክምና 🔺 በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል የዲስክ መንሸራተት ችግር ሲከሰት ሕመሙ በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበት ወቅት፣ሰገራ ሲጠቀሙ በሚያምጡበት ወቅት ወይም ወደ ተወሰነ አቅጣጫ የጀርባ አጥንቶችን በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

✍ #ድብርት/ Depression! 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹?? ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ድብርት የሚባለው የባሕርይ መለወጥን የሚያስከትል የሕመም ዓይነት ሲሆን የመከፋት፤ደስተኛ ያለመሆን እና ፍላጎት የማጣት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ እነዚህ ስሜቶች የዕለት ተዕለት ኑሮአችንንና ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ሊጎዱ ወይንም ችግር ሲያስከትሉ የመደበት ሕመም / Depression ብለን እንጠራዋለን፡፡ድብርት በሁሉም ዕድሜ ፣ ዘር እና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ክፍሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ሁኔታው ከወንዶች በእጥፍ በሚበልጡ ሴቶች ውስጥ ይገኛል ፡፡ 👉👉 የድብርት አይነቶች ፡- 📌 ዋና የድብርት ዲስኦርደር (ኤም.ዲ.ዲ.) - ክሊኒካዊ ድብርት ተብሎም ይጠራል ፣ የሁለት ሳምንት ጊዜ ከፍተኛ የሃዘን ስሜት ወይም በሁሉም እንቅስቃሴዎች ላይ ፍላጎት ማጣት የሚጨምር የስሜት መቃወስ ነው ፡፡ የመንፈስ ጭንቀት ፣ ድካም ፣ የእንቅልፍ ለውጦች ፣ የክብደት ለውጦች ፣ ትኩረት የማድረግ ችግር ፣ ዋጋ ቢስነትና የጥፋተኝነት ስሜት ፣ በተለምዶ በሚደሰቱባቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ፍላጎት ማጣት ፣ የሞት እና ራስን የማጥፋት ሀሳብ ሊያስከትል ይችላል ። 📌 የማያቋርጥ የድብርት ጭንቀት። - እንዲሁም ‹dysthymia› በመባል የሚታወቀው ፣ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ያህል ሥር የሰደደ የመንፈስ ጭንቀት ዓይነት ነው ፡፡ መለስተኛ ፣ መካከለኛ ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል። 📌 ባይፖላር ዲስኦርደር - የማኒክ ድብርት በመባልም ይታወቃል ፣ የስሜት መቃወስ ተለይቶ የሚታወቅ ነው; ባልተለመደ ሁኔታ ከፍ ያለ የስሜት ሁኔታ። እሱ በድካም ፣ በእንቅልፍ ማጣት ፣ በቸልተኝነት ፣ ባልታወቁ ህመሞች ፣ ህመሞች ፣ የስነልቦና ስሜት ቀስቃሽነት ፣ ተስፋ ቢስነት ፣ ለድርጊቶች ፍላጎት መቀነስ ፣ በራስ መተማመን ማጣት ፣ ብስጭት ፣ ጭንቀት ፣ ውሳኔ መስጠት ፣ ራስን መግደል ሀሳቦች ሊያስከትል ይችላል ፡፡ እንዲሁም በጣም በሚከሰት ሁኔታ በሰው ሕይወት ውስጥ የአካል ጉዳትን ያስከትላል ፣ ሆስፒታል መተኛት ይጠይቃል ፣ ወይም የሰውን የእውነት ስሜት ይነካል። 📌 የድህረ ወሊድ ጭንቀት ፡፡ - በሴቶች ውስጥ በእርግዝና ወይም በልጅ መወለድ ምክንያት ይከሰታል ፣ በሆርሞኖች ከፍተኛ ለውጥ ምክንያት ፡፡ እስከ ወሊድ ሥነልቦና እስከሚደርስ ድረስ የሕክም ከሚጠይቅ የማያቋርጥ ግድየለሽነት እና ሀዘን ሊሆን ይችላል ፣ ይህ ሁኔታ የስሜት ትዕይንት ግራ መጋባት ፣ ቅዥቶች ወይም ማጭበርበሮች የታጀቡበት ሁኔታ ነው ፡፡ 📌 የቅድመ ወሊድ የደም ሥር ነቀርሳ በሽታ (PMDD) - በአብዛኛዎቹ የወር አበባ ዑደቶች ውስጥ የወር አበባ መከሰት ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ የሚጀምሩ የተስፋ መቁረጥ ምልክቶችን ያካትታል ፡፡ ተለይቶ የሚታወቅ ነው; ብስጭት ፣ ከፍተኛ ድካም ፣ ጭንቀት ፣ ስሜታዊነት ፣ የሆድ መነፋት ፣ የምግብ ፍላጎት መጨመር ፣ የምግብ ፍላጎት ፣ ህመም ፣ የጡት ርህራሄ ፣ ሀዘን ፣ ተስፋ መቁረጥ ፣ ራስን መተቸት ፣ ከፍተኛ የጭንቀት ስሜቶች ፣ የስሜት መለዋወጥ ፣ ትኩረት መስጠት አለመቻል ፣ የምግብ ፍላጎት እና ቂጣ 📌 ያልተለመደ ጭንቀት - የማይመቹ ገፅታዎች ያሉት ዲፕሬሲቭ ዲስኦርደር ነው) የበሽታው “ዓይነተኛ” ነው ተብሎ የታሰበውን የማይከተል የድብርት ዓይነት። ተለይቶ የሚታወቅ ነው; ከመጠን በላይ መብላት ፣ ክብደት መጨመር ፣ ከመጠን በላይ መተኛት ፣ ድካም ፣ ድክመት ፣ “ክብደት ያለው” ስሜት ፣ ውድቅ የመሆን ስሜታዊነት እና አጸፋዊ ስሜታዊ ስሜቶች 📌 ረብሻ የስሜት መታወክ በሽታ። - በልጆች ላይ የሚመረመር ሲሆን የቁጣ ቁጣ ፣ ቁጣ እና ብስጭት ያካትታል 👉👉 የድብርት መንስኤዎች። 📌 ሐዘንና ማጣት 📌 ደካማ የአመጋገብ ስርዓት 📌 ህመም 📌 የሕይወት ላይ የተለየ ክስተቶች መፈጠር ። 📌 የተወሰኑ የህክምና መድኃኒቶች። 📌 የጄኔቲክ (ተፈጥሮ) 📌 ብቸኝነት 📌 የገንዘብ ማጣት 📌 ጉርምስና 📌 ልጅ መውለድ ፡፡ 👉👉 ጭንቀትን እንዴት መቋቋም ይቻላል 📌 መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ 📌 አመጋገብን ማስተካከል 📌 የትርፍ ጊዜዎትን በአግባቡ ማሳለፍ 📌 አስጨናቂ ነገሮችን ለመውጣት በራስ የመተማመን ስሜት ማዳበር 📌 የቤተሰብ አባልን ወይንም የቅርብ ጓደኛን ማማከር 📌 የመደበር ስሜት ሲሰማዎ በአፋጣኝ ወደ ሐኪም በመሄድ ሁኔታው እንዳይባባስ ማድረግ 📌 ሕመሙ ተመልሶ እንዳያገረሽ ከሐኪምዎ ጋር ዘላቂ መፍትሔ ላይ መወያየት ⏩ #ከስነልቦና ጋር የተያያቱ ችግሮ እና በሌላ ጤና ጉዳይ መወያየት ካሻዎ 8809 ላይ በመደወል ከባለሙያ ጋር ይማከሩ!!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!

የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን >>>>>>>>>>>>>>>>>>>(Vulvovaginal yeast infection) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምንድን ነው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ላይ የመቆጣት እና የማሳከክ ስሜት የሚያስከትል ኢንፌክሽን ነው። ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዳ(candida) በመባል በሚጠራው የፈንገስ ዝርያ ነው። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶችና የህመም ስሜቶች ምንድን ናቸዉ? ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ ● የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማሳከክ ● የሽንት ማቃጠል ● የሴት ብልት እና የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማቃጠል፣ መቅላት ወይም መቆጣት ● በወሲብ ወቅት ህመም ● የሴት ብልት ፈሳሽ አንዳንድ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ያላቸው ሴቶች ከሴት ብልት ውስጥ ትንሽ ፈሳሽ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ ፈሳሽ በአብዛኛው ነጭና እንደ አይብ የሚበጣጠስ ነው። ነገር ግን ቀጭን እና እንደ ውሃም ሊሆን ይችላል። ምልክቶቼ በፈንገ ኢንፌክሽን ምክንያት መሆኑን እንዴት አውቃለሁ? አብዛኛዎቹ ሴቶች የምልክታቸው መንስኤ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ይሁን ወይም ሌላ ነገር ይሁን ሊያውቁ አይችሉም ። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶች ከሌሎች የሴት ብልት ኢንፌክሽን ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ፤ ስለዚህ ምርመራ ሳያደርጉ በዚህ ምክንያት ነው ብሎ ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ነው። እርግጠኛ ለመሆን ሃኪም ወይም ነርስጋ ቀርቦ መታየት እና ከማህጸን ፈሳሽ ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ነው የሚከሰተው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያመጣው ፈንገስ አብዛኛውን ጊዜ በአንጀት ውስጥ እና በሴት ብልት ውስጥ ይኖራል። ይሁንና የፈንገሱ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የበሽታ ምልክቶች አይኖርም። የተወሰኑ መድሃኒቶች (በተለይም አንቲባዮቲክስ) ፣ ጭንቀትና ሌሎች ምክንያቶች ፈንገሶቹ እንዲባዙ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የማህጸን የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክት መታየት ይጀምራ። ከስር የተዘረዘሩት ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ናቸዉ ●የአንቲባዮቲክስን መጠቀም ●የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠቀም ●የስኳር በሽታ ●እርግዝና ●የተዳከመ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ስርዓት (የኬሞቴራፒ ሕክምና፣ኤች አይ ቪ) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል? ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚሆኑ መድኃኒቶች ​​ሊወስዱ ይችላሉ። መድኃኒቶች የሚዋጡ ወይም በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡት መድሃኒቶች በክኒን ወይም በክሬም መልክ ሊመጡ ይችላሉ። ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚወሰዱ ሁሉም መድሃኒቶች ኢንፌክሽኑን የሚያስከትሉ ፈንገሶችን በመግደል ይሰራሉ። ጥሩ ስሜት የሚሰማኝ መቼ ነው? ሕክምና እንደጀመሩ በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ጥሩ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። ህክምናን ካጠናቀቁ በኋላ ካልተሻለዎት ​​ዶክተርዎን ወይም ነርስዎን እንደገና ማየት አለብዎት ፤ ተጨማሪ መድሃኒት መውሰድ ወይም ሌላ መድሃኒት መውሰድ ይኖርብዎት ይሆናል። ባለቤቴስ ህክምና ማድረግ ይጠበቅበታል? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ አይደለም ። አልፎ አልፎ ከአንዱ ወደ አንዱ የመጋባት ሁኔታ ቢስተዋልም ፤ ባለሙያዎች የወሲብ ጓደኛ ህክምና እንዲያደርግ አይመክሩም። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

በእርግዝና ወቅት ሊስተዋሉ የሚገቡ አድገኛ ምልክቶች 👉ከባድ የሆነ እራስ ምታት 👉ከፍተኛ ትኩሳት/ብርድ ብድር ማለት/ማንቀጥቀጥ 👉ብዥ ማለት 👉ራስን ስቶ መውደቅ 👉ከማህጸን ደም መፍሰስ 👉የጽ
በእርግዝና ወቅት ሊስተዋሉ የሚገቡ አድገኛ ምልክቶች 👉ከባድ የሆነ እራስ ምታት 👉ከፍተኛ ትኩሳት/ብርድ ብድር ማለት/ማንቀጥቀጥ 👉ብዥ ማለት 👉ራስን ስቶ መውደቅ 👉ከማህጸን ደም መፍሰስ 👉የጽንስ እክንቅስቃሴ መቀነስ ወይም ሙሉ በሙሉ መቆም 👉ፊት ወይም እጅ ማበጥዝ 👉ከፍተኛ የሆነ ሆድ ህመም 👉ከአልጋ ለመነሳት መክበድ 👉ለመተንፈስ መቸገር እንዚህን ምልክቶች በራሶ ላይ ወይም በእርጉዝ እናት ላይ ካስተዋሉ ወደ ጤና ተቋም ያድርሱዋቸው

ድንግልና- ምንድነው? እንዴትስ -ይገለጻል? 👉👉ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የዶክተር ቤዛ ተከታታዮች በዚህ ጽሁፋችን ብዙዎቻችን ላይ ጥያቄ ስለሚፈጥረው ድንግልና እና ተያያዥ ሃሳቦች ላይ አተኩረናል አንበበው ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩት! ከዶክተር ቤዛ ጋር በመወዳጀት አስፈላጊ ሆኑ የጤና መረጃዎችን ያግኙ!!!! ✅ #ድንግልና #ሳይንሳዊ #ፍቺው #ትክክለኛ #ግንኙነትን #አድርጎ #አለማወቅ (የማያውቅ ) ማለት ነው፡፡ ድንግልና እንደ ባህላችን ፣ሃይማኖት የተለያየ ፍቺ የሚሰጡት ቢሆንም ድንግልና ሃሳባዊ ነገር ነው፡፡ አንዳንዶች ድንግልናን ከክብረ ንጽህና ጋር (hymen) በማገናኘት አንዳንዴ ከላይ ከጠቀስነው ፍቺ በተለየ ይተረጉሙታል፡፡ ✅ክብረንጽህና የምንለው የብልት ቀዳዳን በደም ህዋስ ሸፍኖ የሚገኝ ነው፡፡ ክብረንጽህና (hymen) አብዛኛውን ጊዜ በተፈጥሮ ጠቦ የሚፈጠር ቢሆንም አንዳንዴ ሰፍቶ የሚፈጠርበትም ሁኔታ አለ፡፡ 👉👉 #ጠቦ #የተፈጠረ #ከሆነ #ድንግል #የሆነ #ሰው #ግንኙነት #ሲያደርግ #ሊታዩ #የሚችሉ #ምልከቶች #መሃከል ፡- • በግንኙነት ወቅት ህመም መሰማት፤ • ደም መታየት፤ • የወንድ ብልትን ለማስገባት መጥበብ የመሳሰሉት ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ✅ሰፍቶ የተፈጠረ ክብረ ንጽህና (hymen) ያላቸው ድንግል ቢሆኑም ( ግንኙነት አድርገው ባያውቁም) ለመጀመሪያ ግንኙነት ሲያደርጉ ከላይ የተጠቀሱ የተለመዱ ምልክቶች #ላይስተዋሉ ይችላል፤ ይህም በአብዛኛውን ጥንድ ግርታን ይፈጥራል፡፡ 👉👉 #ከትክክለኛ #ግንኙነት #ውጪ #ክብረንጽህና #በምን #ሊጠፋ #ይችላል? • እራስን በራስ ማርካት ( በተለይ ባዕድ ነገር መጠቀም)፤ • እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያዘወትሩ ሰዎች( በተለይ ለረጅም ጊዜ ሳይክል የሚነዱ፣ ኳስ የሚጫወቱ እና ሌሎች ጫና ያላቸው እስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ )፤ • ከባድ ስራዎችን የሚሰሩ በተለየይ ብልት አካባቢ ተጽዕኖ የሚሳድሩ ከሆነ፤ 👉👉 #አንድን #ሴት #ድንግል# እንደሆነች #በምርመራ #ማወቅ #ይቻላል? • ሙሉ ለሙሉ ማወቅ አይቻልም ነገር ግን መገመት ቻለላል ፡፡ ለመገመትም ቢሆን ክብረንጽህናቸው ክፍት ሆነው የተፈጠሩት ላይ አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህም ከሚጠቀሟቸው መንገዶች መሃከል አንደኛው ክፍተቱ በክብረ ንጽህና የተሸፈነ መሆኑን መለየት ሲሆን ሌላው ደግሞ ሁለት ጣቶችን በመጠቀም የብልት ጡንቻ የመለጠጥ አቅሙን(ጥበቱነን ) ቼክ ማድረግ ነው፡፡ 👉👉 #በግንኙነት #ጊዜ #ድንግል #የሆኑ #ሰዎች #ላይ #የሚፈጠሩትን #የህመም #ስሜቶች #ለመቀነስ #ምን #ማድረግ #አለብን? • ወደግንኙነት ከመገባቱ በፊት ሰውነትን ዘና ማድረግ፤ • ለግንኙነቱ በአካልም ሆነ በስነ ልቦናም ዝግጁ መሆን፤ • ቀድመን ስለህመሙ የሚወሩትን ነገሮች በመስማት የሚፈጠሩ ፍርሃትና ጭንቀትን ማስወገድ፤

(ጠቃሚ ጤና መረጃ) መቸም አያድርስብዎትና በቤትዎ ዉስጥ የፈላ ነገር ቢፈስብዎ ወደ ጤና ድርጅት ከመሄድዎ በፊት ሊያደርጉት የሚገባ የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ • ህመሙን ለመቀነስ የተቃጠለዉን ቦታ ማቀዝቀዝ፡- የተቃጠለዉን ቦታ በጣም ቀዝቃዛ ባልሆነ ቧንቧ ዉሃ ለ10 እስከ 15 ደቂቃዎች ወይም ህመሙ እስኪቀንስልዎ ድረስ እንዲፈስበት ማድረግ • በጣም ጥብቅ ያሉ አልባሳት ወይም ጌጦች በተቃጠለዉ አካባቢ ካሉ ማዉለቅ፡- ይህ ቦታዉ ከማበጡ በፊት ፈጠን ብለዉ በቀስታና በቶሎ ማዉለቅ • ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ ቦታዎችን ያለማፍረጥ፡- ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ ቦታዎች ካሉና ከፈነዱ ቀስ ብላዉ በዉሃና ሳሙና ማፅዳት፣ ፀረባክቴሪያ ቅባቶችንን መቀባት፣ በጎዝ ቦታዉን መሸፈን • ካስፈለገዎ ያለሀኪም ትእዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንደ አይቡፕሮፌን/ አድቪል፣ፓራሲታሞል የመሳሰሉትን መዉሰድ በጣም ትላልቅ ዉሃ የቋጠሩ ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር፡፡ የተቃጠለዉ ቦታ ሰፊ ቦታ የሸፈነ ከሆነ፣ የኢንፌክሽን ምልክቶች (የሚያዥ ነገር ካለ) ፣ ህመሙ ከጨመረ፣ መቅላትና ማበጥ ካለ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ይጠበቅብዎታል፡፡

ያፈነገጠ የሴክስ ድርጊት 1- ፍሮቴሪዝም ========================= የአውቶብስ ትኬት ቆራጭ የሆነችው ነፃነት ...ለወሲባዊ መተሻሸት ሆነ ብለው የሚገቡ ተሳፋሪዎችን ለይታ እስከማወቅ እንደደረሰች ትናገራለች። "አውቶቢሱ በሚጨናነቅበት ሰአት ካልሆነ አይሳፈሩም።" ትላለች የእነዚህን ተንኳሾች መገለጫ ስታወራ። "ትኬት ለመቁረጥ የሚሰለፉትም የሚፈቅዷትን ሴት ተከትለው ነው። አውቶቢሱ ከልክ በላይ ሲሞላ ሴት ተሳፋሪዎችን መተሻሸት ይጀምራሉ.... ...አንድ ቀን ረጅም ጃኬት የለበሰ ሰው አውቶቢስ ውስጥ ገብቶ እኔ ቁጭ ከምልበት ፊትለፊት 'ሚኒ ስከርት' ካደረገች ልጅ ጋር ሲደርስ ቆመ። "ልጅቷን ሲተሻሻት ሌባ መስሎኝ ነበር። እሱ ለካ ሌላ ጉዳይ ላይ ነው። ልጅቷ ጫማውን አውጥታ ጠፈጠፈችው። አውቶቢሱ ሲቆም ዘሎ ወረደ...." መሀመድ ሰልማን ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝ። ገፅ 56 ፍሮቴሪዝም (Frotteurism) ካፈነገጡ የሴክስ ፍላጎትና ድርጊቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ይህ ህመም ያለባቸው ሰዎች ከሴክስ እርካታ የሚያገኙት ያልተጠበቀ ሁኔታ ውስጥ ሴቶችን በመነካካትና ቀመተሻሸት ነው። የዚህ ችግር ተጠቂዎች በብዛት አንናፋርና ከሰው ጋር ለመቀላቀል የማይደፍሩ ናቸው። አንዳንዶቹ በተፈጥሮ ከፍተኛ የሆነ የሴክስ ፍላጎት ያላቸው ናቸው። ፍሮተሪዝም የመድሀኒት እንዲሁም የስነ ልቦና ህክምና ቢኖረውም የችግሩ ተጠቂዎች በፖሊስ ተይዘው ካልቀረቡ በስተቀር ወደ ህክምና አይሄዱም።

✍️ ሴክስ ማድረግ ለሴቶች የሚሰጠው 10 አስደናቂ ጠቀሜታዎች 👉 ወሲብ መፈጸም ተፈጥሯዊ ስለሆነ ጥሩ ስሜት ሊሰማው ይገባል ፤ ግን ወሲብ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ያውቃሉ? 👉 ወሲብ ለጤንነታችን እጅግ ጠቃሚ ነው። ወሲብ በአዕምሮአችን ላይ ብቻ ሳይሆን በሰውነታችን ውስጥ ባሉ ሌሎች በርካታ የአካል ክፍሎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ የነርቭ አስተላላፊዎችን ያነቃቃል። 👉 ወሲብ ለሴቶች በርካታ ጥቅሞች አሉት። 1. በሽታ የመከላከል ሥርዓትዎን ይቆጣጠራል። 👉 ወሲብ የሚፈጽሙ ሴቶች ሰውነታቸው ከቫይረሶች ፣ ከባክቴሪያዎች ፣ ከጀርሞች እና ከሌሎች ሊታመሙ ከሚችሉ ነገሮች የሚጠብቀውን እና የሚከላከለውን ከፍ ያለ ደረጃ ያሳያሉ። 2. ሊቢዶአችሁን ከፍ ያደርገዋል። 👉 ወሲብ መፈጸም ብዙ ወሲብ የመፈጸም ፍላጎትዎን ያጠናክራል። በሴቶች ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም የሴት ብልትን ቅባትን ፣ የደም ፍሰትን እና መለጠጥን ያበረታታል ፣ ይህም ወሲብን የበለጠ አስደሳች እና ተፈላጊ ያደርገዋል። 3. የሴቶችን ፊኛ መቆጣጠር ያሻሽላል። 👉 አለመቻቻል በተወሰነ የሕይወት ዘመናቸው 30% የሚሆኑ ሴቶችን የሚጎዳ ችግር ነው። የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚፈጽሙበት ጊዜ የሚከሰቱት የማሕፀን ዓይነቶች እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን ለመከላከል የሚረዳውን ጡንቻ ያጠናክራሉ። 4. የደም ግፊትን ይቀንሳል። 5. እንደ ልምምድ ይቆጠራል። 👉 ወሲብ በሚፈጽሙበት ጊዜ ብዙ የጡንቻ ቡድኖችን ይጠቀማሉ ፣ የልብ ምትዎን ይጨምሩ እና በደቂቃ እስከ 5 ካሎሪዎችን ማቃጠል ይችላሉ። 6. ዝቅተኛ የልብ ድካም አደጋ። 👉 ኢስትሮጅንና ቴስቶስትሮን መጠን ውስጥ ሚዛን ለመጠበቅ ወሲባዊ ግንኙነት ጠቃሚ ነው። እንዲሁም ለልብ ጥሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሆነውን የልብ ምትዎን ከፍ ያደርገዋል። ይህ ሁሉ በሴቶች ውስጥ የልብ ድካም አደጋን ለመቀነስ አስተዋፅኦ ያደርጋል። 7. ህመምን ይቀንሳል። 👉 በተወሰኑ የሰውነት ክፍሎችዎ ውስጥ ለራስ ምታት ወይም ለሥቃይ ወሲብ መፈጸም መድኃኒት ሊሆን ይችላል። ኦርጋዜዎች ህመምን የሚቀንስ ሆርሞን ከመልቀቅ ጋር የተቆራኙ ናቸው። 8. የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትዎን ሊቀንስ ይችላል። 👉 ሴክስ የፕሮስቴት ካንሰርን አደጋ ከመቀነስ ጋር የተቆራኙ ናቸው። ሌላው ቀርቶ ማስተርቤሽን ወይም ሌላ ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሴቶች እንኳ የካንሰር ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ይረዳሉ። 9. እንቅልፍን ያሻሽላል። 👉 የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከተፈጸመ በኋላ ፕሮላክቲን በመባል የሚታወቀው የእፎይታ ሆርሞን ይለቀቃል። ይህ ሰውነትዎ ዘና እንዲል ይረዳል እና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከተፈጸመ በኋላ እንደ ሕፃን እንዲተኙ ይረዳዎታል። 10. ውጥረትን ያቃልላል። 👉 ውጥረት ሲሰማዎት ከባልደረባዎ ጋር መቀራረብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል። እርስ በርሳችሁ ስትተቃቀፉ ፣ ስትሳሳሙ ፣ እና ከምትወዱት ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ስትፈጽሙ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎት የሚያደርግ ሆርሞን ይለቀቃል።

እንቦክስ ላይ በብዝዎች ጥያቄ መሰረት በድጋሚ የተፖሰተ ዶክተር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ነኝ ቪማክስ የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው vimax ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ትንሽ ነገር ልበል እንደምታውቁት በማህበራዊ ሚድያ ብስፋት የሚያስተዋዉቁት ነገር ነው። ከማህበራዊ ሚድያ ደሞ እውነተኛ ነገር ማግኘት አዳጋች ነገር ነው እናም ዝም ብላቹ ከፊስቡክ ወይም ከቴሌግራም የሚለቀቁትን ማስታወቅያዎች አምናቹ ምንም አይነት መዳኒት ባትገዙ ጥሩ ነው በጣም አደገኛ ሊሆንባቹ ይችላል በተለይ የዉስጥ ደዌ ችግሮች ያሉባቹ በጣም መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል የህክምና ባለሞያዎን ማመከር አለባቹ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች የብልት አልቆም ማለት የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የቁመት ማጠር እና/ የመቀጠን ችግር ቶሎ የመጨረስ ችግር በአጠቃላይ ከለይ የጠቀስኳቸው የስንፍፈተ ወሲብ ችግሮች እንዳለባቹ ካረጋገጣቹ ችግሩን በህክምና ሞክራቹ ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች አሉ ግን ኬት ማግኘት እንዳለባቹና የትኞቹ ናቸው ትክክለኛና ፈዋሽ የሆኑትን ማወቅ ይኖርባቹኃል ቢያንስ ቢያንስ ስለ መዳኒቶቹ Google ላይ ማጣራት እና Original ምን አይነት እንደሆነ መለየት ትችላላቹ የጎንዮሽ ጉዳቱቹ ምንምን እንደሆኑ Google ይነግራቹኃል በህክምና ሞክራቹ ወይም ሀኪም ማማከር ፈርታቹ መዳኒት ለመጠቀም የምትፈልጉ በጥያቅያቹ መሰረት ስለ Vimax የተወሰነ ነገር ልበላቹ እና ኬት እንደምታገኙ አድራሻ ለምትጠይቁኝ ሰጣቹኃለው Vimax Originally የካናዳ ምርት ሲሆን ጥቅሞቹ 1 የብልት አልቆም ማለት ቆሞ ያለመቆየት ቶሎ መልፈስፈስ ችር ላለበት 2 የቁመት እና የዉፍርት ችግር 3 ቶሎ የመጨርስ ችገር/የዘር ፈሳሽ የማምለጥ vimax አወሳሰድ/አጠቃቀም እንዷ ብልቃጥ 60capsule/60እንክብል ነው ምቲዘው ባለ 30capsule የምቲዝም አለች ግን እኔ የማወራው ስለ original ነው አወሳሰዱ በቀን አንድ አንድ ቢሆን ይመከራል በቀን ሁለት ሁለትም መውስድ ይቻላል። Side Effect/የጎንዮሽ ጉዳት እነሱ እንደሚሉት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያመጣም ይበሉ እንጅ እኔ ከማቃቸው ተጠቃሚዎች እንደተረዳሁት የጨጓራ በሽታ ያለባቸው ላይ ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው ነግር ግን ጎን ለጎን የጨጓራ መዳኒት እየወሰዱ የሚጨርሱም አሉ ከዚ ዉጪ ሌላ ምንም አይነት ጎዳት የለዉም አንድ አንዶች ላይ አላርጂክ ከሞሆን በስተቀር። የሚከለክላቸው ነገሮች መዳኒቱን መጠቀም ከጀመራቹ መዉሰድ/መጠቀም የሌለባቹህ ነገሮች .አልኮል/አረቄ ነገሮች ናቸው። መዳኒቶቹን መግዛት የምትፈልጉ እኔ ትክክለኛው Original Vimax አስመጪዎችን ስልካቸውን ልሰጣቹህ እችላለው መዳኒቱ ሀገር ዉስጥ እንዲሸጥ ገና ፍቃድ ስላላገኘ በዚም ምክንያት ዋጋው በጣም የተጋነነ ነው በዛ ላይ አስመጪዎቹ እየሸጡ ከተያዙ ወይም እጃቸው ላይ ከተገኘ የሚቀጡ ነው የሚሆኑት እናም ብዙ ጊዜ እራሳቸውን ደብቀው ነው የሚሸጡት ነገር ግን እኔ በትክክል ስለማዉቃቸው ችግር አይኖርም መዳኒቱም ፍቃድ ሊያገኝ በሂደት ላይም ስለሆን ብዙም አያሳስብም። በተጨማሪም የኔ ምክር ነው ጫት እየቃማቹ መዳኒቱን ባትወስዱ/ባትጠቀሙ ጥሩ ነው ቢያንስ መዳኒቱን እስክጨርሱ ጫቱን ብተዉት እላለው ስለ ጫት የጎንዮሽ ጉዳቶች በቅርቡ ፅፍላቹኃለው የአስመጪዎችን ስልክ እና አድራሻ በብዛት inbox ላይ ስትጠይቁኝ የነበራቹ ስልካቸው 0992484672 በ inbox ለማግኘት https://t.me/Sellerman12 አመሰግናለው እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias