Dire Soccer
Kanalga Telegram’da o‘tish
The Voice of Ethiopian Football Telegram : https://t.me/DireSoccer Facebook : https://m.facebook.com/diresoccer
Ko'proq ko'rsatish1 607
Obunachilar
+124 soatlar
+27 kun
-630 kun
Postlar arxiv
1 607
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ10 ጨዋታዎች ታገዱ
የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የአስር ጨዋታዎች ዕግድ እንደተላለፈባቸው ተገለጸ።
አሰልጣኙ ወላይታ ድቻ ከባህርዳር ከተማ ባደረገው ጨዋታ ላይ የጨዋታውን ዋና ዳኛ መሳደባቸው እና ለፀብ መጋበዛቸው ተገልጿል።
በዚህም ምክንያት በድምሩ የአስር ጨዋታዎች ዕግድ የተላለፈባቸው መሆኑም አወዳዳሪው አካል አሳውቋል።
በተያያዘም በጨዋታው ላይ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ረዳት ዳኛ በድንጋይ በመማታታቸው ክለቡ የ50 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል።
@DireSoccer
1 607
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2019 ውድድር ዘመን እሁድ ጥቅምት 15 ጅማሮውን ያደርጋል !
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ጥቅምት 15 እና ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን በተለያዩ ስታዲየሞች ይካሄዳሉ።
በመክፈቻው ዕለት እሁድ ጥቅምት 15 ቀን የባለፈው የውድድር ዓመት ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከይርጋጨፌ ቡና ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ በተመሳሳይ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ቀጥሎም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል ከሻሸመኔ ከተማ በጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ሜዳ፣ አዳማ ከተማ ደግሞ ከልደታ ክፍለ ከተማ በወንጂ ስታዲየም ይፋለማሉ። ቀን 10፡00 ሰዓት ላይ መከላከያ ከቦሌ ክፍለ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም፤ ሲዳማ ቡና ከጉለሌ ክፍለ ከተማ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ በሚደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የድሬዳዋ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ የመጀመሪያ ሳምንት መርኃ ግብር ይጠናቀቃል።
©EBC SPORT
@DireSoccer
1 607
ሊዮነል ሜሲ ስፔን ገባ!
አርጀንቲናዊው ተጫዋች ሊዮነል ሜሲ የ2026 ' Princess of Asturias' ሽልማትን ለመቀበል ስፔን ገብቷል። ይህ ሽልማት በስፖርት፣ በኪነ-ጥበብ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በማህበራዊ ሳይንስ፣ በግንኙነት እና ሰብአዊነት፣ ቴክኒካል እና ሳይንሳዊ ምርምር፣ አለም አቀፍ ትብብር እንዲሁም ሰላም ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች የሚሸጥ በስፔን ትልቅ ክብር ያለው ሽልማት ነው። እ.ኤ.አ ከ1980 አንስቶም ታላላቅ ሰዎችን ሲሸልም ቆይቷል። በ2026 የሽልማት ስነ-ስርአትም ታዲያ ሊዮነል ሜሲ በስፖርቱ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኖ ተመርጧል።
ሊዮነል ሜሲ ከሽልማት ስነ-ስርአቱ በኋላም ልክ በየአመቱ ተሸላሚዎች እንደሚያደርጉት ከንጉስ ፌሊፔ 6ኛ፣ ከስፔን ንጉሳዊ ቤተሰብ እና ከሌሎች ተሸላሚዎች ጋር በይፋዊ እራት ፕሮግራም ላይ ይታደማል።
ከእግር ኳስ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ሽልማቱን የወሰዱት ዣቪ እና ኢኔሽታ ናቸው። በወቅቱ ዣቪ እና ኢኔሽታ ሽልማቱን በጣምራ ያገኙ ሲሆን ሜሲ ይህን ሽልማት ዘርፍ በብቸኝነት የተሸለመ የመጀመሪያው እግር ኳስ ተጫዋች ይሆናል። ከዚህ በፊት በዚህ ዘርፍ ከተሸለሙ ስፖርተኞች መሀከል ሴሪና ዊሊያም፣ ራፍየል ናዳል እና ኤሉድ ኪፕቾጌ ይገኙበታል።
ሸላሚው ተቋም እንዳሳወቀው ከሆነ ሊዮነል ሜሲ ለዚህ ሽልማት የተመረጠው በስፖርታዊ ስኬቶቹ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ተፅእኖውን በመጠቀም ለሰራቸው የሰብአዊነት ስራዎች ነው። ሜሲ በራሱ ፋውንዴሽን ስር እንዲሁም ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በተለያዩ የሰብአዊነት ስራዎች ላይ እንደሚሳተፍ ይታወቃል።
©Sheger Sport Arena
@DireSoccer
1 607
የፈርናንዴዝ መኖሪያ ቤት መዘረፉ ተነገረ !
የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ መኖሪያ ቤት ትላንት ምሽት በዘራፊዎች መዘረፉ ተገልጿል።
የተጨዋቹ መኖሪያ ቤት ትላንት የኮሞ ጨዋታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ጭምብል በለበሱ ሶስት ሰዎች ተዘርፏል።
በዝርፊያው ወቅት የብሩኖ ፈርናንዴዝ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት ውስጥ እንዳልነበሩ ማንችስተር ዩናይትድ አረጋግጧል።
ዘራፊዎቹ ውድ እቃዎችን እና ጌጣጌጦችን መዝረፋቸው ሲነገር ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ክለቡ አሳውቋል።
@DireSoccer
1 607
አርዳ ጉለር :-
ጎል ካስቆጠረ በኋላ የሚያሳየው ለየት ያለ የጎል አከባበር ስነ-ስርዓት (Goal Celebration) ትልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን በዓለም ዙሪያ ባሉ እግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ ትኩረትን ስቧል።
ጎል ሲያስቆጥር ቀኝ እጁን በደረቱ (በልቡ) ላይ በማድረግ የግራ እጁን አመልካች ጣት ወደ ሰማይ የመቀሰር ልማድ አለው።
ይህንን ምልክት የሚያደርግበት ዋና ምስጢር እና ትርጉም የሚከተለው ነው፦
እምነት እና ሁሉንም ነገር ለአምላክ መስጠት፦ አርዳ ጉለር ይህንን አከባበር በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ፣ "የእኔ የጎል አከባበር ትርጉም በተውሂድ (በአላህ አንድነት) ላይ የተመሰረተ ነው። ሁሉንም ነገር የሚያደርገው አምላክ እንደሆነ አምናለሁ። እኔ ዝም ብዬ እሰራለሁ፣ የቀረው ግን የአምላክ ፍቃድ ነው" ብሏል።
ትሕትናን ማሳየት፦ ቀኝ እጁን ደረቱ ላይ ማድረጉ በልቡ ውስጥ ያለውን ትሕትና እና ለደጋፊዎቹ ያለውን ክብር ሲገልጽ፣ ጣቱን ወደ ሰማይ ማድረጉ ደግሞ ለፈጣሪው ያለውን ምስጋና እና እውቅና የሚያሳይ ነው።
ይህ አከባበር አሁን ላይ የእሱ መለያ ምልክት (Signature Move) ሆኗል፤ በሪያል ማድሪድም ሆነ በቱርክ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ ጎል ባስቆጠረ ቁጥር ይህንን ድርጊት ይደግመዋል።
@DireSoccer
1 607
የኢትዮጵያ ከ15ዓመት በታች ቡድኗ ከ189 ተሳታፊ ሃገራት አንዱ ነው!
የፊታችን ቅዳሜ፣ 189 ብሔራዊ ቡድኖችን እና 32 ምድቦችን ያካተተው የመጀመሪያው የዕድሜ ክልል ከ15 ዓመት በታች (U-15) የዓለም ዋንጫ በአዘርባጃን ባኩ ይጀምራል!!
ውድድሩ በ8 ተጫዋቾች የሚካሄድ አዲስ አሠራርን የሚከተል ሲሆን፣ ጨዋታዎቹም እያንዳንዳቸው 20 ደቂቃ በሆኑ ሁለት ክፍሎች ይከፈላል።
የመጫወቻ ሜዳዎቹ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም፣ የግብ መረቦቹ (ጎሎቹ) ግን በመደበኛ መለኪያ መጠን ይቆማሉ።
ውድድሩ የሚቆየው ለስድስት ቀናት ብቻ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ወደ 1,000 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
የኢትዮጵያ ከ15 ዓመት በታች አዛርባጃን ባኩ ከገባ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ሲሆን በምድብ ኤች ተደልድሏል!
©Arada Sport
@DireSoccer
1 607
የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ ያደርጋል
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ በዛሬው ዕለት በግብፅ ካይሮ በዙም በሚያደርገው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት የቀረበውን የሀገራት ጥያቄ ሂደት እና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ታውቋል።
ከአንድ ወር በኋላ በናይጄሪያ የሚካሄደውን የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ አካሄድ፣ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የሱፑር ካፕ ዋንጫ፣ በሴኔጋል የሚደረገውን የአሸዋ እግር ኳስ ውድድር እንዲሁም በናይጄሪያ የሚደረገውን የካፍ ሽልማትን በተመለከተ የካፍ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፓትሪስ ሙትሴፔ በሚመሩት ስብሰባ የሚነሱ አጀንዳዎች መሆናቸው ተገልጿል።
@DireSoccer
1 607
የማይክል ካሪክ ተተኪ ማን ይሆን ?
በዘንድሮ የውድድር አመት በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እንዲሁም በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ደካማ ጅማሮን እያደረጉ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች አሰልጣኝ ማይክል ካሪክን ለማሰናበት እያሰቡ እንደሆነ ቴሌግራፍን ጨምሮ በርካታ የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ይገኛሉ ።
ማንችስተር ዩናይትዶች አሰልጣኝ ማይክል ካርኪን ለመተካት አራት አሰልጣኞችን እየተመለከቱ ሲሆን አንቶኒዮ ኮንቴ ፣ ጁሊያን ናግልስማን ፣ ፋቢያን ሀልዝለር እና ኤዲ ሀው ናቸው ።
@DireSoccer
1 607
የ2019 የኦሮሚያ ዋንጫ ጥቅምት 17/2019 ይጀመራል !
በኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በባቱ ከተማ አስተናጋጅነት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች መካከል የሚሄደው የኦሮሚያ ዋንጫ ቀደም ተብሎ በ7 ቡድኖች መካከል እንደሚካሄደ የተገለፀ ቢሆንም አሁን ተጨማሪ ተጋባዥ ቡድን ድሬዳዋ ከተማን በማካተት በ8 ቡድኖች መካከል ጥቅምት 17/2019 በባቱ ከተማ ይካሄዳል
በ2019 የኦሮሚያ ዋንጫ ተሳታፊ ክለቦች
.ባቱ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
.መልካ ኖኖ ክ/ከተማ እግር ኳስ ክለብ
.ቢሾፍቱ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
.ሻሸመኔ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
.ቤንች ማጂ ቡና እግር ኳስ ክለብ
.መንጌ ቤላሻንጉል እግር ኳስ ክለብ
.አርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
.ድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
©Dagu_Sport
@DireSoccer
1 607
“ ግንቦት ላይ የምታዩት ቼልሲ ሌላ ነው “ ዣቢ አሎንሶ
የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ቼልሲ በቀጣይ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ከጄሚ ካራገር ጋር ቆይታ ያደረጉት ዣቢ አሎንሶ “ አሁን ከምናየው ቼልሲ ግንቦት ላይ የምናየው ቼልሲ የተለየ ይሆናል በዚህ እርግጠኛ ነኝ “ ብለዋል።
“ ቼልሲ ፕሪሚየር ሊግ እና ሻምፒየንስ ሊግ ካሸነፈ ብዙ አልቆየም “ ያሉት ዣቢ አሎንሶ “ ክለቡን ወደዛ ደረጃ ለመመለስ እና ለዋንጫ ለመፎካከር ጓጉተናል “ሲሉ ገልጸዋል።
“ ነገርግን ሁሉም ነገር በአንዴ መሆን አለበት ብለን የምናምን የዋህ አይደለንም “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
@DireSoccer
1 607
ሙስጠፋ መሐመድ የሆሞሻ ሸንጋ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተሹሟል !
የቀድሞው የሆሞሻ ሸንጋ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ የነበረው ሙስጠፋ መሐመድ በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ ሊግ አንድ በሆሞሻ ሸንጋ እግር ኳስ ክለብ በተለያዩ ኃላፊነቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን ከጥቅምት 6/2019 ጀምሮ የሆሞሻ ሸንጋ እግር ኳስ ክለብ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተሹሟል።
ሆሞሻ ሸንጋ የ2018 የኢትዮጵያ ሊግ አንድ አሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን ወደ 2019 የኢትጵያ ከፍተኛ ሊግ ማደጉ የሚታወስ ነው።
©Dagu_Sport
Telegram :
https://t.me/DireSoccer
1 607
ሴስክ ፋብሬጋስ ወደ ጨዋታው መጨረሻ በወሰነው ውሳኔ መፀፀቱን ተናግሯል!
"ጨዋታው ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃዎች ሲቀሩት በወሰንኩት ውሳኔ አዝኛለሁ ። ምክንያቱም 4-0 እየመራን እያለ ቀጣይ ጨዋታዎችን በማሰብ ፍጥነት እንዲቀንሱ ለተጫዋቾቹ የነገርኩት እኔ ነበርኩ።
ሩጫቸውን እንዲያቆሙ እና በመሀል እንዲቆዩ ነግሬያቸዋለሁ፤ ይህ ደግሞ የምጸጸትበት ነገር ነው ምክንያቱም ሁልጊዜ እስከመጨረሻው እንዲታገሉ የምገፋፋቸው እኔ ነበርኩ።
በኋላ ግን ግብ ተቆጠረብን። ያቺ ግብ የገባችውና የመከላከያ ክልላችን ኃይሉን ስላሳጣን ጎድቶኛል፤ ግን ሁሉም የእኔ ጥፋት ነበር።" ብሏል
@DireSoccer
1 607
የ2019 ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚጀመርበት ቀን ተራዝሟል !
የ2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ጥቅምት 21 እንደሚጀምር ይፋ ተደርጎ የነበር ቢሆንም የተወሰኑ ክለቦች ምዝገባቸውን በጊዜ ባለመጨረሳቸው ምክንያት የሚጀመርበት ቀን መራዘሙን ፌዴሬሽኑ ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።
በዚህም ውድድሩ ሕዳር 5 እንደሚጀመር እና ጥቅምት 26 ደግሞ በጁፒተር ሆቴል የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ታውቋል።
@DireSoccer
1 607
ነጌሌ አርሲ የአመቱን የጀመሪያ ድል አስመዝግበዋል !
በሶስተኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ቡናማዎቹን የገጠሙት ነጌሌ አርሲዎች በገብረ መስቀል ዱባለ ግብ እንዲሁም በዳዊት ተፈራ እና በኮሊንስ ኮፊ የፍፁም ቅጣት ምት ግቦች 3ለ0 በማሸነፍ የአመቱን የመጀመሪያ ድል ማስመዝገብ ችለዋል ።
@DireSoccer
1 607
ሊግ ካምፓኒው እየዋሸ ይሆን ?
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሊግ ካምፓኒ የዘንድሮ አመት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጫወቻ ቀናቶችን በተመለከተ ተመልካቾች ወደ ሜዳ በመምጣት ጨዋታዎች ላይ እንዲታደሙ በማሰብ የጨዋታ መርሀ ግብሮቹ አርብ ፣ ቅዳሜ ፣ እሁድ እና ሰኞ ብቻ እንደሚደረጉ እና የእኩለ ቀን ጨዋታዎች እንደማይኖሩ ማሳወቁ ይታወሳል ።
ሆኖም የሊግ ካምፓኒው ቃል ከሁለተኛ ሳምንት መሻገር ተስኖታል ለዚህም ማሳያው ከማክሰኞ እስከ ሀሙስ እንዲከናወን መርሀ ግብር ወቶለት እየተከናወነ የሚገኘው የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ናቸው ።
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አ.ማ በስራ ቀናት የሚደረጉ ጨዋታዎችን ወደ ምሽት የሚቀይርበትን አማራጭ ቢፈልግ የተሻለ ነው ።
@DireSoccer
1 607
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ ጋር ለሚያደርጋቸው ከ23 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዛሬ 12፡00 ላይ በደብረ ዳሞ ሆቴል ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።
©EFF
1 607
147 የክለብ አመራሮች ከህገወጥ ውርርድ ጋር በተያያዘ ታገዱ
የቱርክ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከህገወጥ ውርርድ ጋር በተያያዘ በ147 የክለብ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተሰምቷል።
ከነዚህ ግለሰቦች መካከል ከቱርክ ትላልቅ ክለቦች አንዱ የሆነው ትራብዞንስፖር ፕሬዚዳንት ኤርቱግሩል ዶጋንን ይገኙበታል።
ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ 147 የሚሆኑት የክለብ አመራሮች ለ45 ቀናት ጊዜያዊ ዕግድ ተጥሎባቸዋል።
የቱርክ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አጠቃላይ 448 አመራሮች ላይ ማጣራት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን 301 በሚሆኑት ላይ በቂ ማስረጃ አላገኘም።
ከአንድ ዓመት በፊትም 149 ዳኞች እና 1,204 ተጫዋቾች ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዕግድ ተላልፎባቸው ነበር።
©ARADA SPORT
@DireSoccer
1 607
+1
ቡናማዎቹ ወይስ ሰጎኖቹ !
ሶስተኛ ሳምንቱን በያዘው የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ቡናማዎቹን ከሰጎኖቹ ያገናኛል ።
በሁለተኛ ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር በሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሸነፍ የአመቱን የመጀመሪ ድል ያገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ከሶስት ነጥብ ጋር መገናኘት የተሰናቸው እና ሽንፈትንም ያላስተናገዱት ነጌሌ አርሲዎችን የሚያገናኘው ጨዋታ ብቸኛው የእለቱ መርሀ ግብር ነው ።
አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌን ካስፈረሙ በውሀላ የሜዳ ላይ የጨዋታ አቀራረባቸውን የቀየሩት ቡናማዎቹ የሊጉን ተከታታይ ድል ለማስመዝገብ ወደ ሜዳ ሲገቡ በአንፃሩ ባሳለፍነው የውድድር አመት በሊጉ ጠንካራ ፉክክር ሲያደርጉ የነበሩት ነጌሌ አርሲዎች የአመቱን የመጁመሪያ ሶስት ነጥብ ለማሳካት ወደ ወደ ሜዳ ይገባሉ ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል ።
ቡናማዎቹ ወይስ ሰጎኖቹ ? በጨዋታው ዙሪያ ግምቶን እና ያላቹን ሀሳብ አጋሩን !
@DireSoccer
1 607
ኢትዮ ኤሌክትሪክ የዓመቱን የመጀመሪያ ድል ሲያስመዘግብ ፋሲል ነማ ነጥብ ተጋርቷል !
የሲቢኢ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት መደረግ ጀምረዋል። አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ከ9:00 ጀምሮ በተደረገው የሳምንቱ ቀዳሚ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
የኢትዮ ኤሌክትሪክን የማሸነፊያ ግብ ካሌብሴትሜልቪነ በሶስተኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ሀላባ ስታድየም ላይ የተደረገው የሀላባ ከተማ እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ 1 ለ 1 ተጠናቋል።
ካሌብ አማንክዋህ ለሀላባ ከተማ ሮማረክ ዲንሆ ደግሞ ለፋሲል ከነማ ግቦቹነ ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
የሊጉ መርሐግብር በነገው ዕለትም ሲቀጥል ኢትዮጵያ ቡና ከነገሌ አርሲ በአዲስ አበባ ስታድየም ከ9:00 ጀምሮ ይጫወታሉ።
@DireSoccer
1 607
የሲቢኢ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀምራል
የሲቢኢ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መደረግ ሲጀምር አዲሰ አበባ ስታድየም ላይ በሚደረገው ቀዳሚ የሳምንቱ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሸገር ከተማ ከ9:00 ጀምሮ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሁለቱ ጨዋታዎች አንድ ነጥብ የያዘ ሲሆን ሸገር ከተማ በበኩሉ አራት ነጥቦች ስብስቧል።
በሀላባ ስታድየም ደግሞ ሀላባ ከተማ እና ፋሲል ከነማ 10:00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሀላባ ከተማ ከሁለቱ ጨዋታዎች አራት ነጥቦችን ያሳካ ሲሆን አንድ ጨዋታ ብቻ ያደረገው ፋሲል ከነማ አንድ ነጥብ ይዞ የዛሬውን ጨዋታ ይጀምራል።
@DireSoccer
