uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Admas

Admas

Kanalga Telegram’da o‘tish

......@@በየቀኑ አስገራሚ እና የተለየያዩ(social Media) ፅሁፎች የምታገኙበት channel ነው.....@@

Ko'proq ko'rsatish
473
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+27 kun
+130 kun
Postlar arxiv
የሃይማኖት ሰዎች «ጨዋ» እና «ቆንጆ» ሴት በማግባታቸው ለምን ኩራት ይሰማቸዋል? (አሌክስ አብርሃም) መቸስ የአንድ ሃይማኖት አባት ዋና ሥራ ሰዎችን «ከክፉ» ወደ «ደጉ» መንገድ መመለስ፣ ከነፍስና ሥጋ ጉስቁልና ወደ እረፍትና ሰላም መጥራት ነው፤ የተጣሉትን ማንሳት፣ ሕይወት የገፋቻቸውን መደገፍ ነው፤ ዓለም የናቀችና ያቆሸሻቸውን በላይኛው አምላካቸው ፊት ነፍሳቸው የከበረች መሆኗን ማሳየት፣ ወደ ሳቱበት መንገድ መልሶ ማስገባት ነው። በሌላ አባባል የነፍስ ድንግልናቸውን ላጡ የዘላለም ድንግል ይሆኑ ዘንድ ወደሚቀድሰው ዙፋን ማስጠጋት ነው! ሁሉም በከፍታም በዝቅታም እኩል የአምላክ ፍጥረት መሆኑን ተቀብሎ ሌሎች እንዲቀበሉት ማድረግ ነው! ቆንጆ ትሁን ፉንጋ፤ ድንግል ትሁን አመንዝራ. . . ወላድ ትሁን መካን. . . ጨዋ ቤተሰብ ያሳድጋት ወይም ጎዳና ተጥላ ትደግ፣ ይህ ነገር የሃይማኖት አባቶችንም እንደ ሌላው ተራ ሕዝብ ተሰልፈው ምርጫ ይገቡ ዘንድና መልኳንና ጨዋነቷን እያዳነቁ ያሳዩ ዘንድ ተገቢ ነው? ወይንስ በስብከት ብቻ ነው ዓርአያ መሆን ያለባቸው? አውቃለሁ፣ ሰው ናቸው፤ የሰውን ልጅ ተፈጥሮአዊ ነፃነትና የስሜት መብትን ማቅለል አልሻም! ጋብቻ ከመንፈሳዊ ተልዕኮና ከሞራል ግዴታ ባሻገር የሁለት ሰዎች የግል ስሜት፣ የጋራ መግባባትና የስነ ልቦና ስምምነት ውጤት ነው። የሃይማኖት አባትም ቢሆን ሰው እንደመሆኑ መጠን በፍቅርና በግል ምርጫው የመመራት መብቱን ሙሉ በሙሉ ወደ "ሃይማኖታዊ ተልዕኮ" ብቻ ማጥበብ «አጉል ማካበድ» እና ከእውነታው መራቅ ሊመስል ይችላል። እኒህ ሰዎች የወደዱትን የማግባትና የመምረጥ መብትም አላቸው፤ ግን «ጨዋ ሴት አገባሁ» ተብሎ እልል ማለት ልክ አይመስለኝም! «የተከበረ ቤተሰብ ልጅ አገባሁ»፣ «ቆንጆ አገባሁ» ብሎ የአንድ ሃይማኖት አባት አደባባይ ላይ የሚያስመካው ነገር ሊሆን ይገባል ወይ? ብዙ «ጨዋ አይደሉም» የተባሉትን በትምህርቱ የመለሰ አባት ሴተኛ አዳሪ ከመንገዷ መልሶ ቢያገባ የበለጠ የሚያስመሰግነው ይመስለኛል! ዓለም «አትረባም» ብሎ ያሽቀነጠራትን ሴት ከወደቀችበት አንስቶ ሚስት ቢያደርግ የእምነቱ ጽናት በገረመን ነበር! መውለድ አትችይም ተብላ ከሞቀ ትዳሯ የተሽቀነጠረች ሴት ቢያገባ . . .እድሜዋ አለፈ ቁማ ቀረች የተባለችን ሴት ቢያገባ... የዘላለም ህይዎት የሚጠብቅ ሰው ለዚች ሰባ ዓመት ያውም ከአስርና አስራ አምስት ዓመት በላይ ለማይዘልቅ መልክ ምን አስጨነቀው? ነገሩ ከጋብቻ ጋር አይያያዝም፤ ግን «የተጣሉትን ማንሳት» የሚለውን መንፈስ ያዙትና ወንጌል የሚያስተምረውን አስታውሱ ኢየሱስ ማርያም መግደላዊትንና ሌሎችንም የተናቁ ሴቶች እንዴት እንዳነሳቸውና ከሚገፋቸው ማኅበረሰብ በተለየ ከፍ ያለ ቦታ እንደሰጣቸው ተመልከቱ! እንግዲህ ለታላቁ ተልዕኮ እንዲህ ዓይነት ሴቶች ከተመረጡ ለትዳር ምን ያንሳቸዋል ነው ጥያቄው? «ጨዋ ለጨዋ»፣ «ታዋቂ ለታዋቂ»፣ «ቆንጆ ለቆንጆ»፣ «ሃብታም ለሃብታም». . . "የተማረ ከተማረ" ...ዓለማዊውስ ከዚህ የተለየ ምን አደረገ? «አሳየው የደሙን ሻሽ. . . እኛ ያሳደግናት በማር በወተት. . .».... «ምን በልተው ወለዷት እናትና አባቷ» ...የሚሉ መታበይ እስከ አፍንጫቸው የሞላቸው የሠርግ ዘፈኖች በመዝሙር ስለተተኩ ከዚያ መታበይ ነፃ ያደርገናል? በነገራችን ላይ፣ ይህን እንኳን የድሆችን አምላክ የሚሰብክ የሃይማኖት ሰው፣ ታላላቅ ስኬት ላይ የደረሱ ዓለማዊ ሰዎች ያደርጉታል! ምሳሌ እንጥቀስ? ወይስ ጊዜ የላችሁም? እሺ፣ ሴተኛ አዳሪ ከቡና ቤት አንስቶ ያገባ ታላቅ ንጉሥ ነበር፤ «አብዳለች» ተብላ መንገድ ላይ እርቃኗን የተጣለች ሴት አንስቶ ያገባ ታዋቂ አርቲስት ነበር፤ የአልጋ ቁራኛ የሆነች ሴት አንስቶ ያገባ ገጣሚ ነበር (በኋላ ድና ታዋቂ ገጣሚ ሆናለች)፤ ባሪያዎቻቸውን ነፃ አውጥተው ያገቡ ጌቶች ነበሩ! የተገፉ ሚሊዮኖችን አንሥተው ሚስቶቻቸው ያደረጉ ሚሊዮን የሞራል ሰዎች ነበሩ! ስነፅሁፍ የአንድ ማህበረሰብ ነፀብራቅ ነውና ፍቅር እስከመቃብር ላይ የምናገኘው ጉዱ ካሳ ለስንት «ጨዋ» ሲታሰብ ባሪያዋን ፣ ገረዷን እንቆጳን ማግባቱ፣ «ጨዋዋ» ሰብለ እድሜዋ 26 ደረሰ ተብሎ ቁማ መቅረቷን ፣ አንድ ዲያቆን በመውደዷ የደረሰባትን እስከሞት የደረሰ መከራ አይተናል! ነበር አለ ችግሩ! መቸስ ልብ ወለድስ ቢሆን የሌለ አይፃፍ! ምን ለማለት ነው. . . የትዳር ምርጫ ግላዊ ቢሆንም፣ መስፈርቱን መልክ ይሁን ጨዋነት፣ ጥሩ ቤተሰብ ይሁን መማር እንደ ትልቅ ብቃት ማየት በሕይወት ውጣ ውረድም ይሁን በተፈጥሮ ዕድሉን ያጡ ሚሊዮኖችን በጣም ጥልቅ በሆነ የሕይወት ቅኔ መዝለፍ ነው! በተለይ አሁን አሁን የሚታየው በቅንጦት የፋፋ ሐይማኖተኝነት ዓለማዊን አሸሸና ታይታ የሚያስከነዳ በሽታ መሆኑ ያሳዝናል። እንደው ከሆነስ ሆነና በዚህ በሶሻል ሚዲያ ዘመን «መልከ-ጥፉ» የምትባል ሴት ያገባ የሃይማኖት አባትም ይሁን ሃብታም አይታችሁ ታውቃላችሁ? ማለቴ ዲያስፖራ ያልሆነች መልከጥፉ😀

ኢትዮጵያ ሄጀ ነበር! (አሌክስ አብርሃም) እንዴት ከረማችሁ? ከዚህ ሰፈር ዞር ብየ ቆየሁ። እንኳን ሌላ ሰው የራሳችሁ አንገት ተጠምዝዞ ቢዞር የማታስታውሱበት ፋታ የማይሰጥ ትርምስ ፣ እና ሰበር ዜና ውስጥ ናችሁና መጥፋቴ ብዙም እንዳልተሰማችሁ አውቃለሁ። እንደውም "መጣ ደሞ ሊጨቀጭቀን" ባትሉ ነው! ተሰምቷችሁ ለጠየቃችሁኝ ግን ምንድነው የምትነዘንዙኝ ሰው ማረፊያ ያጣል እንዴ የምል ነጭናጫ አይደለሁም 😀 አመሠግናለሁ🙏 ለማንኛውም የኖርኩ ኑሬ ድንገት በዚህ ሰዓት ተነስቸ ኢትዮጵያ መሄድ የጤና ነውን? ምን ይደረግ ሰው ማለት አገሩን በሰላም ጊዜ ብቻ የሚወድ አይደለም ዘራፍ! ከረዢም ጊዜ በኋላ ነው የሄድኩት! መቸስ ያየሁ የሰማሁትን አካፍል ዘንድ ወዳጃዊ ግዴታ አለብኝና እንደሚከተለው በክፍል በክፍል አቀርባለሁ። ክፍል አንድ የተሳፈርኩበት ግዙፍ ኤርባስ አውሮፕላን ኢራን ከተኮሰቻቸው ሰላሳ ሮኬትና 25 ድሮኖች መካከል አልፎ የምትቀጠቅጣቸውን ሶስት የአረብ አገራትን አቋርጦ እኩለ ሌሊት ላይ አዲስ አበባ ደረሰ። ወቅቱ የኢራን ሮኬቶች እንደአገራችን ሴቶችና ወንዶች ወደሁሉም አረብ አገራት በህገወጥ መንገድ የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር። አንድ ድሮን ከተሳፈርኩበት አውሮፕላን ጎን እየተምዘገዘገ መጣና ካሜራውን ዞር አድርጎ በመስኮት አየኝ ፣ ዓይን ለዓይን ተገጣጠምን ፤ አመጣጡ የሰላም አልነበረም...ግን ፍጥነቱን ቀነስ አድርጎ "ውይ በሞትኩት፤ አንተ አሌክስ አይደለህም እንዴ? በዚህ ክፉ ቀን ምን ክንፍ ጣለህ? የሳዲቅ ሂዳያት ፣የነፊርዶውሲ የነ ሳዲ ሺራዚ የአገሬ ፀሐፍት መንፈስ አንተ ላይ ታየኝ፣ እኔማ አንተን ...አድርጌ ድል ራቱ ከምባል በቃ በሰላም ግባ እዚህ ውቂያኖሱ ላይ እፈጠፈጣለሁ" አለና ለሚከተሉት የሚሳኤልና ድሮን መንጋ "አቅጣጫ ቀይሩ" ብሎ አዞ ቁልቁል ወረደ ....አንዳንዶቹ ኳታር፣ አንዳንዶቹ ሳኡዲ፣ አንዳንዶቹ ኩዌየት ብዙወቹ ኢስራኤል ካለፕሮግራማቸው አረፉ። ያው ጉራ እንዳይመስል ለማንም አልተናገርኩም። ዓለም እንደፈለገ ይተንትን። ቆንጆ ቆንጆ ዘጠኝ ሆስተሶች በየተራ እየመጡ ስላተረፍከን እናመሰግናለን እያሉ በሽሚያ እያቀፉ ሲስሙኝና "የቀረውን ስንደርስ እናወራርዳለን" ሲሉኝ "የቀረው ምንድነው?" ልል ስል ከእንቅልፌ ነቃሁ። አፍንጫቸው ላይ መተንፈሻ የተገጠመላቸው ወፍራም ሰውየ እያንኮራፉ በክንዳቸው ወድቀውብኛል። ሳልተኛ በፊት ለህክምና የሆነ አገር ቆይተው እየተመለሱ መሆናቸውን ነግረውኝ ነበር። ኤዲያ! አዲስ አበባ መድረሳችን በፓይለቱ ሲታወጅ በናፍቆት ሰፍ ብየ በመስኮት በኩል ወደታች ተመለከትኩ ፤ ምን አየሁ? ምንም አላየሁም! ምክንያቱም ኳስ ሜዳ የሚያክለው የአውሮፕላኑ ክንፍ ከልሎኝ ነበር። በክንፍ በኩል ያውም ተጨማሪ ሒሳብ ከፍየ መሳፈሬ ቆጨኝ። አዲስ አበባን ከሰማይ ላይ በምሽት የማየት ፍላጎት ነበረኝ። ድሮም ኳስ ስጨዋት በክንፍ በኩል ነበር አሰላለፌ። መንግስት ልማቱ መብራቱ የማይታያቸውን ሰወች ሁሉ ፀረ ልማትና ምቀኛ አድርጎ ማየት የለበትም የምለው ለዚህ ነው¡ ብዙ ምክንያት ይኖራል። ይልቅ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ክንፍ አልባ አውሮፕላኖችን ቢጠቀም፣ አልያም ክንፎቹ ልማቱን እንዳይከልሉ ከመስተዋት የተሰሩ ኤር ባስ በትዕዛዝ ቢያሰራ የሚል ቅን ሐሳብ አለኝ¡ እንደሀሳብ! አብራሪው አውሮፕላኑን ቦሌ ላይ አሳረፈው ከማለት አነቦጨው ቢባል ልክ ይመጣል። እንዴ ፓይለት ከመሆኑ በፊት አጥፍቶ ጠፊ ድሮን አብራሪ ነበር እንዴ? አስተራረፍማ የኢትዮጵያ ፓይለቶች ይምጡብኝ። ዞሮ ዞሮ ያው በሰላም ቦሌ አረፍን። ... ሻንጣየን ተቀብየ ዲያስፖራ እንዳልመስል የተቻለኝን መጎሳቆል ከከወንኩ በኋላ ከቦሌ ወጣሁ። አሁን ኢትዮጵያን በግላጭ የማየት ጊዜው ሆነ...

በክፍሉ ውስጥ ያለው እውነተኛው ብልህ ሰው ማን ነው? 🧠💡 በአንድ ክፍል ውስጥ ያለ እውነተኛው ብልህ ሰው «ብዙ የሚያውቀው» ሰው አይደለም፤ ይልቁንም «ምን እንደሚያስፈልግና ዋናው ነገር ምን እንደሆነ የሚረዳው» ሰው ነው! እውቀት (Knowledge) ማለት ዝም ብሎ መረጃዎችንና እውነታዎችን መሰብሰብ ነው—ልክ የምግብ አሰራር መመሪያን በቃል እንደመሸምደድ። ጥበብ (Wisdom) ማለት ግን «ጨው መቼ መጨመር እንዳለብህ» ማወቅ ነው! እውቀት አእምሮህን በዝርዝር መረጃዎች ሲሞላው፣ ጥበብ ግን ህይወትህንና አኗኗርህን ይቀርጻል፤ የትኞቹ ጥያቄዎች መጠየቅ እንዳለባቸው የሚያሳይህም እሱ ነው። ስለዚህ መረጃዎችን በከንቱ መሰብሰብ አቁም! በምትወስዳቸው ውሳኔዎችና ምርጫዎች ህይወትህን መፍጠር ጀምር። 🧠 የስነ-ልቦና እውነታው፡ በስነ-ልቦና ትምህርት ውስጥ ሜታኮግኒሽን (Metacognition፡ ስለ አስተሳሰብ ማሰብና መረዳት) የሚባል ከፍተኛ የእውቀት ደረጃ አለ። በአሁኑ የቴክኖሎጂ ዘመን መረጃ በየቦታው ይገኛል። አእምሮን ባልተፈለገ መረጃ መሙላት (Information Overload) ለጭንቀትና ለውሳኔ ማጣት (Decision Fatigue) ይዳርጋል። እውነተኛ ብልህነት መረጃን ማከማቸት ሳይሆን፣ አላስፈላጊውን አስወግዶ ጠቃሚውን መለየት (Filter ማድረግ) እና በጥቅም ላይ ማዋል ነው! ዋናው መልእክት፡ የእውቀትህ ልክ በሚያውቁት መረጃ ብዛት ሳይሆን በህይወትህ በምታሳየው ጥበብና ውሳኔ ይመዘናል.

💡የፊፋ (FIFA) የማርኬቲንግ ስትራቴጂ እግር ኳስን ከተራ ስፖርትነት ባለፈ "የዓለም አቀፍ ስሜት እና የቢሊዮን ዶላር ንግድ" ያደረገ እጅግ ግዙፍ ስትራቴጂ ነው። 🛡ፊፋ ራሱን የሚያስተዋውቀውና ገቢ የሚያመነጨው በእነዚህ 5 ዋና ዋና ስልቶች ነው፦ ⚽️ 1. ስሜትንና ብሔራዊ ኩራትን መሸጥ (Selling National Pride) ፊፋ የሚሸጠው 90 ደቂቃ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን የአገራትን ኩራትና ፍቅር ነው። የዓለም ዋንጫን በየአራት ዓመቱ በማድረግ የጉጉት ስሜት ይፈጥራል። የስፖርቱን ስሜታዊነት በመጠቀም ዓለም አቀፍ ትኩረትን ሙሉ በሙሉ ወደራሱ ይስባል። ⚽️ 2. ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖንሰርሺፕ ጥቅሎች (Tiered Sponsorship) ፊፋ የስፖንሰርሺፕ መብቶችን በደረጃ ከፋፍሎ በውድ ዋጋ ይሸጣል፦ ⛳️ የፊፋ አጋሮች (FIFA Partners)፦ እንደ ኮካ ኮላ እና አዲዳስ ያሉ ዓመቱን ሙሉ ከፊፋ ጋር የሚሰሩና ሁሉንም መብቶች የሚቆጣጠሩ ግዙፍ ኩባንያዎች ናቸው። ⛳️ የዓለም ዋንጫ ስፖንሰሮች (World Cup Sponsors)፦ ለዋንጫው ውድድር ብቻ ከፍተኛ ክፍያ የሚከፍሉ ናቸው። ⛳️ የቀጣናው ደጋፊዎች (Regional Supporters)፦ በተወሰኑ አህጉራት ብቻ የማስተዋወቅ መብት የሚሰጣቸው ናቸው። ⚽️ 3. የብሮድካስት መብት የበላይነት (Broadcasting Monopoly) የፊፋ ትልቁ የገቢ ምንጭ (ከ45% በላይ) የጨዋታዎችን በቀጥታ የማስተላለፍ መብት ለቴሌቪዥንና ለዲጂታል ሚዲያዎች መሸጥ ነው። ይህንን መብት ለማግኘት የዓለም ትላልቅ የሚዲያ ተቋማት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ። ⚽️ 4. ጥብቅ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ (Ambush Marketing Protection) ፊፋ የእሱን ስም፣ አርማ፣ አልፎ ተርፎም "World Cup" የሚሉ ቃላትን ያለፈቃድ መጠቀምን በጥብቅ ይከለክላል። ይህ ጥበቃ ስፖንሰር ላደረጉት ኩባንያዎች ብቻ ልዩ የበላይነት (Exclusivity) ስለሚሰጥ፣ ኩባንያዎቹ ለስፖንሰርሺፕ የሚያወጡትን ዋጋ እጅግ ከፍ ያደርገዋል። ⚽️ 5. አሳታፊ የደጋፊዎች ቀጠና (Fan Zones & Experiential Marketing) በአካል ወደ ስታዲየም መግባት ለማይችሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊዎች "Fan Festival" የተባሉ ትላልቅ የስክሪን መመልከቻ ቦታዎችን ከተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ጋር ያዘጋጃል። ይህም ደጋፊዎች ከብራንዶቹ ጋር በቀጥታ እንዲገናኙና የውድድሩ አካል እንዲሆኑ ያደርጋል። #FIFA © ሳይንስኛ

ከራሴ የማልወደው አንድ ነገር ቢኖር አስራ ስድስት አመት ዘግይቼ መፈጠሬን ነው። በቻልኩት አቅም ላስተካክለው እሞክራለሁ። ጂንስ አልለብስም። ካኪ ሱሪ በወፍራም ሹራብ ለብሼ ጥግ ላይ እቀመጣለሁ። የዘወትር ፀሎቴ ሌላ አይደለም። "እባክህ ጌታዬ እኩያዋ አርገኝና አግብቻት ከዚህ መርዛማ ህዝብ ነጥቄ ወደ ሸዋ ልውሰዳት!!" ነው። በዚህ አመት ነው ከባለቤቷ እና ከሁለት ልጆቿ ጋር እኛ ወደምንኖርበት አከባቢ የመጡት። መልኳ፣ ፀባዩዋ እና አለባበሷ አንድ አይነት የሆነላት ሴት የማውቀው እሷን ነው። እንዲሁ ቀልብን የሚሰልብ ርግት ያለ ድባብ አላት። መንገድ ላይ ስታልፍ አባውራው ሁላ ምናምኑን በጋቢው እየሸፈነ ነው የሚያያት። ራሷን ልታጠፋ ሞክራ ከተረፈች ቡኃላ ግን ሁሉም አገለላት። እነማዬም እሷን ቡና መጥራት አቆሙ። ባሏም "ራሷን ብታጠፋ የለሁበትም" ለማለት ነው መሰል እየዞረ ስላለባት ችግር ሲያወራ ነው የሚውለው። «ምንድን ነው እንዲህ አይነት ቅብጠት? ማንም ሴት ትዳሯ በምትፈልገው መንገድ ላይሔድላት ይችላል! ራስን ለማጥፋት መሞከር ግን ትኩረት ፈላጊነት ነው።» ትላለች እማዬ ስለሷ ሲነሳ። እንዳለ ቡና ጠጭው በስምምነት ራሱን ይነቀንቃል። እኔጋ ስለምንቀራረብ እንድታብራራልኝ የማላደርገው ጥረት የለም። «ለምንድን ነው ግን ሁሉም የሚጠሉሽ?» «ምንድን ነው እንዲህ ያስከፋሽ?» እላታለሁ። የሷ መልስ ሁሌም አንድ ነው። «ወፍ ረግማኝ!» ትለኛለች እየሳቀች። መመለስ እንዳልፈለገች ይገባኝና እተወዋለሁ። የመጣች ሰሞን ከሷ የያዘኝ የአይን ፍቅር በሽተኛ አድርጎኝ ነበር። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ትክክለኛ የዘፈን ግጥሞች ላይ ያለው ፍቅር ነበር የያዘኝ። ፍቅር አያስበላ አያስጠጣ የሚለው ያፈቀርከውን ሰው ማግኘት እንደማትችል እያወቅክ ስታፈቅረው ሳይሆን አይቀርም። በመጨረሻ ግን ተሸነፍኩ። ቀጥ ብዬ ቤቷ ገባሁ። በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ለወፎች ጥሬ እየመገበች ነበር። ደንግጣ ዙራ አየችኝ። ተጠግቼ ሰላም እንኳን ሳልላት «ዘርዬ እወድሻለሁ» አልኳት። ቀልዴን መስሏት ነበር። እንባዬን ስታይ ከሳቋ ላይ ግርምት ጨመረችበት። «ና እስኪ ተቀመጥ የኔ ቆንጆ!» አለችኝ! እንባዬን እየጠረግኩ ተቀመጥኩ። «ስንት አመትህ ነው?» «አስራ ስድስት» «ታውቃለሀ? እኔ ራሱኮ በጣም ነው የምወድህ!» «እውነት?» «የምሬን ነው። ይሔ ልጅ ልጄ በሆነ ብዬ እመኝ ነበር።» ኧረ ቅስሜን! «ትምህርት እንደወጣህ የቤት ስራ ምናምን ካለብህ እኔጋ እየመጣህ ስራ እሺ! ጓደኛ ትሆነኛለህ።» ከዛ ጊዜ ጀምሮ ጓደኞቼን ዞር ብዬ አይቻቸው አላውቅም። የነሱ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደወንድሜ ነው የማይህ" አለችኝ ነው። የኔ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደልጄ ነው የማይህ" አለችኝ...እኩያቸውን ይፈልጉ። ትምህርት ቤት ራሱ የምሔደው የቤት ስራ ለመቀበል ነው። እንደመጣሁ እነማዬ ሳያዩኝ ተደብቄ ዘሪቱጋ እሔዳለሁ። ስራ ጨርሳ ወደ በረንዳው ስትመጣ ከአጠገቧ ሂጄ እቀመጣለሁ። ባሏ እንደልጅ ነው የሚያዬኝ መሰለኝ ሲያዘኝ ራሱ ሰላም ሳይለኝ ነው። እኔም ለነገሩ ለሱ ሰላምታ ግድ ኑሮኝ አያውቅም። «እንዴት ግን ይሔን ሰው አገባሽው?» አልኳት የሆነ ቀን። ምንም ብጠይቃት አትደነግጥም። ርጋታዋ ሳይናድ ትመልስልኛለች። «የህልም ሽንት ታውቃለህ?» አለችኝ። በቃ እኔ ለሷ ሁሌም ህፃን ነኝ። «ኧረ አላውቅም» አልኩ አልጋ ላይ ሸንቼ ማወቄን እንዳታውቅብኝ። «ሽንት ቤት ሂደህ በስነስርዓት ልብስህን አውልቀህ ትሸናለህ...ስትነቃ ግን አልጋህ ላይ ነው የሸናኸው።» «እእእእ» አልኩ! «እንደዛ ነው የኔ ፍቅር። በኔ ቤት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ መርጨ ጨርሻለሁ። ስባንን ያልሆነ ቦታ ላይ ነው ልቤን የጣልኩት» አሁን አሁን በአጠገቤ ሲያልፍ በሆዴ "አንተ የህልም ሽንት" እለውና ለራሴ እስቃለሁ። ዘርዬ እንደነገረችኝ ከሆነ አዲሳባ እያሉ ለመፅሔቶች አንዳንድ ፅሁፎችን ትሰራ ነበር። ሰው መስሏት ይሔን የባንክ ሰራተኛ አገባችው። ከተራ የደንበኛ አስተናጋጅነት አንስተው ማናጀር አደረጉትና ወደዚህ አዛወሩት። የሱ ኑሮ ቀጠለ። የሷ እንደነገሩ ሁኖ ቀረ። እናት መሆን አቃታት። ሚስት መሆን አጎበጣት። እነማዬ ሌላ ህልም ኑሯቸው አያውቅምና ፍላጎቷን እንደቅንጦት ቢያዩት አይገርመኝም። አንድ ቀን ማታ ዘርዬ ባልተዘጋጀሁበት ስለዛች ወፍ ታወራኝ ጀመር። «ከአስራ ስድስት አመት በፊት ባንተ እድሜ እያለሁ ይመስለኛል።» አለች በድንገት። ነቃ አልኩ። «እንዲሁ በጨዋታ ዲንጋይ ስወረውር ያንደኛዋን ወፍ ክንፍ ሰበርኩት። በኢላማዬ ደስ ብሎኝ የወደቀችውን ሒጄ ሳያት መብረር አትችልም። አሳዘነችኝ። ቤት ወሰድኳት። ዶሮዎቼ ጋር ቀላቅዬ ጥሬ እያበላሁ እስክትሞት ድረስ አኖርኳት።» «ታዲያ ምን አጠፋሽና ትረግምሻለች? የተሳሳትሽውን አስተካክለሻልኮ!» አልኩ በጭንቀት። «ሁለት ጊዜ ነው የገደልኳት። ክንፏን መስበሬ ሳያንስ የክንፏን መሰበር እንደ ችግር በማያዩ ዶሮዎች መሀል እንድትኖር አደረኳት። ሲመስለኝ እሷ ወፍ ረግማኛለች።» ከጃኬቷ ኪስ ወረቀት አውጥታ ሰጠችኝ። ላነበው ስል «ነገ ማታ እንድታነበው ነው የምፈልገው» አለችኝ። ነገ ተነስታ ልትሰወር ነው ብዬ አልጠረጠርኩም። እኔ በተኛሁበት የኔ ወፍ ዘርዬ ሰባራ ክንፏን እየጎተተች ርቃ ሔደች። ጧት ወደ ትምህርት ቤት ስሔድ የግቢያቸው በር ተከፍቶ ፊትለፊት ባዶ ቤታቸው ከመንገድ ላይ ይታያል። ተንደርድሬ ስገባ ሁለት ሰዎች እየዞሩ እያዩ ነው። ለቀው መሔዳቸውን አረዱኝ። መከዳት ተሰማኝ። ትምህርት ቀርቼ ሳለቅስ ዋልኩ። በሶስት ቀን ውስጥ አንድ ሰሞን ወደነበርኩበት በሽታ ተመለስኩ። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ከመሔዷ በፊት ወረቀት ሰጥታኝ እንደነበር ያስታወስኩት ራሱ መምሬ ሶስት ቀን በፀበል ካጠመቁኝ ቡኃላ ነው። መሔዷን እያሰብኩ ያልረሳሁት ምን አለ? አልጠበኩም ነበር! ገልጨ ሳነበው ከህመሜ ተፈወስኩ። መምሬ በመዳኔ እማዬ ስታመሰግናቸው «ሶስት ቀን መቆዬቱ ራሱ ገርሞኛል» ሲሉ ጉራቸውን ነፉ። ዛሬ በዘሪቱ እድሜ ሁኜም ያ ደብዳቤ ከኪሴ አይጠፋም። የስሜት መዋዠቅ ሲገጥመኝ አውጥቼ አነበዋለሁ። «ቻው ያላልኩህ አንተን ቻው ማለት ስለከበደኝ ነው። ደስ ትለኛለህኮ። በአንተ ውስጥ ራሴን አያለሁ። አስራ አምስት አመት ፈጥኜ ባልወለድ የማገባው አንተን ነበር። አምላኬን የምጠይቀው አንድ ነገር እኔ ያጣሁትን ሁሉ ላንተ እንዲሰጥህ ነው። ያልኖርኩትን ኑርልኝ። ስለሁሉም አመሰግንሀለሁ። ያላንተ አላልፈውም ነበር ይሔን ጊዜ።» ይላል። ዛሬ ላይ የመፅሔት አዘጋጅ ነኝ። ደስተኛ ሰው ነኝ። ጓደኞቼ «ለምንድን ነው ሰው ሁሉ ያለ ምክኒያት የሚወድህ?» «ለምንድን ነው የነካኸው ሁሉ የሚሳካልህ?» ይሉኛል። የኔ መልስ ሁሌም አንድ ነው። «ወፍ መርቃኝ!» እላቸዋለሁ እየሳቅኩ። ማብራራት እንዳልፈለኩ ይሰማቸውና ይተውኛል። ፨፨፨ (March 2022) Mickel azmeraw

ጭንቀት እነዚህን ነገሮች በ አንድ ላይ ማድረግ ነው               ®አሁን መደረግ ያለበት               ®መዘግየት የሚችል                ®ለሌላ ሰው መስጠት የሚቻል               ®ከነ መተው

photo content

የሆነው ሁሉ ሁኖ መጨረሻ ላይ ሕሊና አዕምሮን ፈልጋ ስትሔድ በሩን ዘግተው ሊያስቆሟት የሚሞክሩት እኒያው ደባል ሱሶቹ ነበሩ። የዚያኔ ግን ድክመቷን ብቻ ሳይሆን ድክመቶቹንም ጠንቅቃ ስለተረዳች ማናቸውም ሊያስቆሟት አልቻሉም። የወይን አበባዬ 📯 የወይን 🎶 Mickel Azmeraw

የወንዶች ጉዳይን ከሳቅ በዘለለ መረዳት የሚፈልግ አንድም ጤነኛ ሰው ያለ አይመስለኝም። እኔ ግን ጤና ስለሚጎለኝ የወደድኩትን ነገር እስክጠላው ድረስ መጎርጎሬን አላቆምም። የመጀመሪያው ጥያቄዬ "ደራሲው የዋና ገፀባሕሪዎቹን ስም አዕምሮ እና ሕሊና ያለው ባጋጣሚ ነው?" የሚለው ነበር። በርግጥ ይሕ ጥያቄ ብቻውን ወደ ሌላ አለም ይወስደኛል ብዬ አላሰብኩትም። ምክኒያቱም ሌሎች ደራሲዎች እንዲህ አይነት ነገር የሚያደርጉት ከላይ ሲታይ ደስ ስላላቸው ብቻ ነው የሚሆነው። አድማሱ ግን የደበቀውን ታሪክ እንድናገኝበት ያስቀመጠልን ካርታ ነበር። ፊትለፊታችን ሁኖ የተሰወረው ስቶሪ ባጭሩ ይሕ ነው። አዕምሮ ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ሲል ሕሊናውን እየዋሻት ነው። እንዲዋሻት የሚተባበሩት ደግሞ ስድስት ደባል ሱሶች አሉበት😃 ላይሆን ይችላል...ይሕ ቲዎሪ ብቻ ነው። እስከሚያስኬደን ድረስ እንሒድበት🙂 ወዳጆቹ...እስከጥግ የሚገዙለት አንድ ነገር አላቸው። አንደኛው ያገኘውን የሚያገበሰብስ ሆዳም ነው። አንደኛው አላፊ አግዳሚውን የሚያስረግዝ ዘማዊ ነው። አንደኛው ሰርግ ቤት ሳይቀር ከመለኮስ የማይመለስ አጫሽ ነው። አንደኛው ከሰከንድ በፊት ያገኛትን ሴት ቂጧን ካልጨበጥኩ የሚል ሴሰኛ ነው። አንደኛው እቁብ ሲወጣለት ልብስ ልግዛ ሶፋ ልቀይር ሳይሆን "ዛሬ ይጠጣል!" የሚል ጠጃም ነው። አንዳቸውም በሰውነታቸው ላይ ሀይል የላቸውም። ህይወታቸው በሱሳቸው ዙሪያ ነው የሚያጠነጥነው። ሱሰኛ ብቻ ሳይሆን ሱስ ራሱ ናቸው። ግን አትጠሏቸውም። በጣም ነው የሚያዝናኑት። ሲጫወቱ ለምናያቸው ለኛ "ጓደኞቼ በሆኑ!" የሚያስብሉ ናቸው። ያው ሱስ ሱስን ይወዳልና አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው የመሰረቱት ማሕበርም አላቸው። የዚህ ማሕበር አስተባባሪ እና ዋና ፀሀፊ ቀጮ ነች። ቀጮ እንደሌሎቹ ሱስን አትወክልም። "ታዲያ ሱስ ካልሆነች ሱሶችን የምትሰበስባቸው እሷ ማነች?" ልትሉ ትችላላችሁ። ቀጮ ማለት ሴት ሁና ሳለ ራሷን እንደ ሴት የማታይ ሰው ነች። "ሴቶች" እየተባለ ሲወራ እንኳን እኔን ይመለከተኛል ብላ አትሰማም። ለዛም ነው ወንዶች ሴቶች ላይ ለሚፈፅሙት ተንኮል ተባባሪ ሁና የምትገኘው። ያ ማለት ግን ሴቶችን ትንቃለች ማለት አይደለም። የምትንቀው ራሷን ነው። አዕምሮን ስትመርቅ እንኳን "ቀጠን ያለችዋን፤ እንደ እንዝርት ተሽከርካሪዋን፤ እንደ ዳር ተወርዋሪዋን ያጋጥምህ!" ነው የምትለው። የሷ ምርጥ ሴት...እሷን የማትመስል ነች። ስለዚህ የነዚህ ሱሶች ሰብሳቢ የወረደ በራስ መተማመን ያላት እና ከተቃራኒ ወገን ተሰልፋ የምትዋጋ ፍጡር መሆኗ ስሜት ይሰጣል። ሱሶችን የሚጠራቸው ይሔ አይነቱ ራስ ጠልነት ነው'ና! (ቀጮ Insecurity ነች እያልኩ ነው ምዕመናን😭) አዕምሮም ወደነሱ የተሳበው በዚችው ጎኑ ነው። ማሕበራቸውን እንዲቀላቀል ያላደርጉት ጥረት አልነበረም። አንዱም አልሰራም። የሚወዳት ፍቅረኛው ከውጭ ለመጣ ሰው ጥላው መሔዷም ለሽንፈት አላበቃውም። ከዛ በፊትም ብዙ ሴት ጋ ተለያይቷል። ብርቁ አይደለም ፍቅሩን ማጣት። ለሽንፈት ያጋለጠው ከመሔዷ በፊት የጣለችበት ንግግር ነው። "አንተን ብዬ መቼም ከምመኛት አሜሪካ መቅረት አልችልም!!!" 😃 ይሕ ንግግር ጥላቻም የለውም። ርሕራሔም የለውም። ምርር ያለ እውነት ብቻ ነው። ይሔንን እውነት ለመዋጥ አዕምሮን Pride ያንቀዋል። ያጥወለውለዋል። ስራ ትቶ መኝታ ላይ ይውላል። የዚያኔ ማሕበርተኞቹ ደም እንዳሸተተ ሻርክ ተቀላቀለንና ከሀዘንህ እናድንህ እያሉ ይዞሩታል። የደረሰበትን ሽንፈት እምደሚያስረሱት ደጋግመው ቃል ይገቡለታል። መፍትሔው ያለው በነሱ እጅ እንደሆነ ጨቅጭቀው ያሳምኑታል ልክ ሁነውም ይገኛሉ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወደቀበት ተነስቶ መሳቅ መጫወት ይጀምራል። ሕሊናውን ከመዋሸት ቢሆንም ደስታው የተገኘው ከነበረበት መጥፎ ስሜት አንፃር ይሔ አስር እጥፍ የሚሻል መንገድ ይሆንለታል። "አሁንማ እንከባከብሀለን ቅድም እኮ ቅጥል ነው ስታደርገን የነበረው!" እያሉ የበለጠ ሰምጦ እንዲገባ ያበረታቱታል። ውሸቱ እንዲሰራ መንገዱን ያሳልጡለታል። ፅዋ ያነሱለታል። እጃቸውን ጭነው ይመርቁታል። ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ይሆናል። ችግሩ ይሔንን ስሜት ለማስቀጠል ሁሌም ጧት ተነስቶ አንድ አዲስ ውሸት መዋሸት አለበት። ዛሬ አለቃውን አታልሎ ከስራ የቀረ እንደሆነ ነገ ደግሞ የእህቱን ሽቶ ሰርቆ ቤቱን መበጥበጥ ይኖርበታል። ደባል ሱሶቹ ለሚሰጡት ደስታ በምላሹ ከሱ የሚጠይቁት ሕሊናን እንዲተኛት፤ በውሸት አለም ውስጥ እንዲያባክናት...ባጭሩ Corrupt እንዲያደርጋት ነው። እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያትም ቶሎ ቶሎ አይስቁለትም። በሆነ ባልሆነው ነው የሚነጫነጩበት። "ታዲያ አዕምሮ ይሔ ሁሉ ውሸት ውስጥ ሲዋኝ ሕሊና እንዴት መጠርጠር ይሳናታል?" የሚለው ሁለተኛው ጥያቄዬ ነበር። እንግዲህ አዕምሮ የምናዬው የምንዳስሰው የማሰቢያ ማሽን ነው። ይሕን ማሽን የሚጠልፉትም የምናያቸው የምንዳስሳቸው አደንዛዥ ዕፆች ናቸው። ሕሊና ግን የማናያት፤ 'ማንዳስሳት...አዕምሯችንን እየወቀሰች በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድ የምታስገድደው ስውር አለቃችን ነች። ህሊናን ሱስ አያሸንፋትም። እሷን ሚጠልፋት እንደሷ ለማዬት ለመዳሰስ የሚከብደው ዲያቢሎስ አልያም እርኩስ መንፈስ ነው። ሸዊት የምትጫወታት ገፀባህርይ (ማርታ) የምትወክለው ይቺን ከሕሊናችን ጆሮ ላይ የማትጠፋውን አንሾካሿኪ ድምፅ ነው🙂 ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአዕምሮ ውሸቶች የምትማልለው እሷ ነች እንጂ ሕሊና አልነበረችም። በፍቅሩ ተይዛለች። "ሶፋ ብናስቀይረው፤ ወርቅ ብናስገዛው" እያለቻት ነው ጆሮዋ ላይ ቁማ። ሐሳቧን ውድቅ እንዳታደርግባት ደግሞ ለቤተሰባችን ስንል ነው እያለች ታግባባታለች። ቤት የጋበዘችው ቀን ሶፋቸው መበላሸቱን ነግራ ልታስገዛው ስትሞክር አዕምሮ "እሰራዋለሁ!" ብሎ መዶሻ ነገር ፍለጋ ይገባል። ማርቲ አመዷ ቡን ብሎ "ምንም ነገር የለንም...ጎረቤትም የላቸውም!" ስትለው ሕሊና ተነስታ ከጠረንጴዛው ስር የተቀመጠውን ዘነዘና ትሰጠዋለች። የአዕምሮ እውነተኛ ማንነነቶች ፈንቅለውት በሚወጡበት ቅፅበቶች ሁሉ ሕሊናን ይማርካታል። በተቃራኒው ማርታን ያቅለሸልሻታል። ሁለቱ ያለ ሶስተኛ ወገን ብቻቸውን ሲገናኙ የሆነ ደስ የሚል ነገር አላቸው። አንዳቸው ላንዳቸው ነው የተፈጠሩት ያስብላሉ። መዋደዳቸውም ያስቀናል። ነገር ግን መሰረቱ ወሸት ላይ ነው'ና ሒሳቡ ሳይወራረድ ግኑኝነቱ ሊፀና አይችልም። አዕምሮ መቼም መቼም መቼም ቢሆን ከገባበት ክብ መውጣት አይችልም። ከገባበት ክብ ልታወጣው የምትችለው ሕሊናው ብቻ ነች። እሷ ደግሞ እሱን ማውጣት እንድትችል በቅድሚያ ጆሮዋ ላይ ያለችውን መንፈስ ጠንቅቃ መረዳት ይኖርባታል። መረዳት ብቻ ሳይሆን ንቃ መተው መቻልም አለባት። ያን ማድረግ እንድትችል መንፈሳዊ እገዛ ትፈልጋለች። ለዛ ነው የቤተክርስቲያኑ ትዕይንት ትክክለኛ ቦታ ላይ ገብቷል የምለው። አዕምሮ እንደልማዱ "ጌታዬ ውሸቴን የማስቀጥልበት ገንዘብ ስጠኝ!" አይነት ፀሎት ይፀልያል። እሷ ግን እውነቱን መኖር እንዲጀምሩ ነው የምትማፀነው። ጌታም የሕሊናን ልመና ሰምቶ የጠዬቀችውን ብርታት ይሰጣታል። ማርታ ያስጀመረቻትን ድራማ ትታ ሀቁን በማፍረጥረጥ አዕምሮን ከገባበት ስካር ታባንነዋለች። ነፍሱ ስትያዝ ይናዘዛል። መክፈል ያለበትን የንስሀ ዋጋ ይከፍላል። እውነቱን ማውራት ሲጀምር እሷም እንዳዲስ እየወደደችው ትመጣለች።

ደላላነት ስራ ብቻ አይመስለኝም የሆነ ሱስ ነገር ነው። አንድ እሳት የላሰ የሰፈራችን ደላላ ጌታን ተቀብሎ ከድለላው ጎን ለጎን ሰባኪ ሆነ። እና የዛን ሰሞን ቤት ያገኘላት አንዲት የክለብ ዘፋኝ አምሽታ ስለምትገባ ቤት ፈልጊ ተብላ አዝና እየነገረችው ነው። "ስራየ ከሰው አላኗኗረኝም ፣ ዘፈን መረረኝ ከአሁን በኋላ የሆነ ሐይማኖት ተከታይ ሆኘ ማረፍ ነው የምፈልገው" ትላለች በምሬት። ደላላው ፈጠን ብሎ "አታስቢ እጀ ላይ ምን የመሰለ ጌታ አለ" 😁

የሆነ ጊዜ ጧት የስራ ባልደረባየ ጋር ታክሲ ውስጥ በአጋጣሚ ተገናኝተን ወደቢሯችን አብረን እየሄድን ነበር። ልክ ስንደርስ ክንዴን ያዝ አድርጎኝ ሰዓቱን ተመለከተና... "ልክ በሰዓቱ ደረስን፣ ትንሽ እናርፍድ" አለኝ። "እ? ለምን?" "በሰዓቱ ከገባን አለቃችን ይለምዳል"😁 ትቸው ገባሁ እርሱ አርፍዶ መጣ። ሌላ ቀን አርፍጀ ስገባ አለቃየ ተነጫነጨ፣ በማርፈዴ ድርጅቱ ሊደርስበት የሚችለውን የመሬት መንቀጥቀጥ አስረዳኝ። ይቅርታ ጠይቄ ገባሁ። ከእኔ በኋላ ብዙ ቆይቶ ያ እናርፍድ ያለኝ ጓድ ሲደርስ "በቃ አይሞላልህም አንተ " ምናምን ብሎ በሞቀ ሰላምታ ተላለፉ። በየቢሮው ስንት ስትራቴጂስት አለ እናንተ?

photo content

የRed Car Theory ወይም «የቀይ መኪና ቲዎሪ» በህይወታችን ውስጥ ስለሚኖሩ ዕድሎች እና በትኩረታችን (Focus) ኃይል ላይ የሚያጠነጥን በጣም ድንቅ የስነ-ልቦናዊ ምሳሌ (Metaphor) ነው። ይህንን ሜታፎር በቀላሉ ለመረዳት የሚከተለውን ጥያቄ እናስብ፡ “ዛሬ ወደ ስራ ወይም ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ስንት ቀይ መኪናዎችን አየህ?” አብዛኛውን ጊዜ መልሱ “አላውቅም” ወይም “ትኩረት አልሰጠሁትም” የሚል ነው። ቀይ መኪናዎች በየመንገዱ ነበሩ፤ ነገር ግን አንተ እነሱን ለመፈለግ ስላልተዘጋጀህ አእምሮህ እንደ አላስፈላጊ መረጃ (Noise) ቆጥሮ አሳለፋቸው። አሁን ግን እራስህን እንዲህ ብለህ እዘዘው፡ “ነገ መንገድ ላይ ለሚያጋጥመኝ ለእያንዳንዱ ቀይ መኪና 1,000 ብር እሸለማለሁ።” በማግስቱ ወደ ውጭ ስትወጣ ምን የሚፈጠር ይመስልሃል? በየደቂቃው ቀይ መኪናዎችን ማየት ትጀምራለህ። እንዲያውም «በየመንገዱ ይሄን ያህል ቀይ መኪና የት ነበረ?» ብለህ ትገረማለህ። መኪናዎቹ በድንገት ከሰማይ አልረገፉም፤ ሁልጊዜም እዚያው ነበሩ። ልዩነቱ አንተ እነሱን መፈለግ መጀመርህ ብቻ ነው። የሬድ ካር ቴዎሪ ዋና መልዕክቶች (The Core Lessons) ይህ ሜታፎር በዕለት ተዕለት ህይወታችን፣ በንግድም ሆነ በግል ስኬታችን ላይ ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል፦ ዕድሎች ሁልጊዜም አጠገባችን አሉ። ልክ እንደ ቀይ መኪናዎቹ ሁሉ፣ አዳዲስ የንግድ ሀሳቦች፣ የስራ ዕድሎች፣ ጠቃሚ ግንኙነቶች እና መፍትሄዎች ሁልጊዜም በዙሪያችን አሉ። ነገር ግን ዝግጁ ካልሆንንና ትኩረታችንን ካላስተካከልን ልናያቸው አንችልም። የአእምሮአችን ማጣሪያ (The RAS Filter)፤ በስነ-ልቦና ውስጥ Reticular Activating System (RAS) የሚባል የአእምሮአችን ክፍል አለ። ይህ ክፍል በየቀኑ ከሚመጡብን በቢሊዮን የሚቆጠሩ መረጃዎች መካከል እኛ «ትኩረት የሰጠናቸውን» ብቻ አጥሮ ያሳየናል። ስለ ውድቀት የምታስብ ከሆነ አእምሮህ የውድቀት ምክንያቶችን ብቻ ያሳየሃል። ስለ ስኬትና ዕድሎች የምታስብ ከሆነ ደግሞ መፍትሄዎችን ማሳየት ይጀምራል። ዕድል የዕድለኛነት ጉዳይ አይደለም፣ የዝግጁነት ነው። ብዙ ሰዎች «እሱ እኮ ዕድለኛ ነው» ይላሉ። ነገር ግን ስኬታማ ሰዎች ዕድለኛ የሆኑት በዙሪያቸው ያሉትን «ቀይ መኪናዎች» (ዕድሎች) ነቅተው ለመመልከት እራሳቸውን ስላዘጋጁ ነው። ይህንን በህይወትህ እንዴት ትተገብረዋለህ? የምትፈልገውን ነገር በግልፅ እወቅ፦ ምን ማሳካት ትፈልጋለህ? ምን ዓይነት ዕድል ነው የምትፈልገው? ይህንን በግልፅ ስታውቅ አእምሮህ ያንን ነገር «መፈለጊያ ራዳር» ያበራል። አእምሮህን አሰልጥን፦ በየቀኑ ጠዋት ስትነሳ «ዛሬ አዳዲስ ዕድሎችን አገኛለሁ» ብለህ እራስህን አሳምን። በንቃት ተከታተል፦ በአካባቢህ የሚፈጠሩ ችግሮችን ተመልከት፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ችግር ጀርባውን የዞረ «ቀይ መኪና» (ትልቅ የንግድ ወይም የስኬት ዕድል) ሊሆን ይችላል። ባጭሩ፦ ዓለም በዕድሎች የተሞላች ናት። ጥያቄው “ዕድሎች አሉ ወይ?” ሳይሆን “የአንተ አእምሮ ቀይ መኪናዎችን ለመፈለግ ዝግጁ ነው ወይ?” የሚለው ነው። Psych addis

photo content
+1

አሜሪካ ሄጀ ወያላ ልሁን የሚል ኮሜንት እንዳትሰጡ! (አሌክስ አብርሃም) ባለፈው አንድ መኪና ከፊቴ ቆመና የ "STOP" ምልክቱን ዘረጋ። ሁላችንም ከኋላ ተደርድረን ቆምን። ልክ እንደስኩል ባስ አይነት ግን ትንሽ ቫን ነገር ነው። እና በሩ ተከፍቶ አንድ ውሻ ሮጦ ወጣና ቁማ ወደምትጠብቀው ሴት ጋር ሄዶ በደስታ ይቦርቅ ጀመር። አቅፋ ሳመችው። ውሾች ልክ እንደትምህርት ቤት ውለው ሲመለሱ የሚመላለሱበት የውሻ ሰርቪስ ነው። Doggy Daycare Bus” ወይም “Puppy School Bus” እየተባለ ይጠራል። ​ ውሾቹ የት ነው የሚውሉት? ብየ ጎግል ሳደርግ ​እነዚህ ውሾች የሚሄዱት ባለቤቶቻቸው ስራ ሲሄዱ "Doggy Daycare" ወደሚባሉ ቦታዎች ነው። ​እዚያ ቀኑን ሙሉ ብቻቸውን ቤት ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ እንደልጆች ጧት ከየቤታቸው በሰርቪስ ሄደው ከሌሎች ውሾች ጋር ይጫወታሉ፣ ዋና ይዋኛሉ፣ እንቅልፍ ይተኛሉ፣ እንዲሁም አንዳንድ የስነ ምግባር ስልጠናዎችን ያገኛሉ። ​ ባለቤቶች ጠዋት ወደ ስራ ከመሄዳቸው በፊት ውሻቸውን ማቆያ ቦታ ድረስ መውሰድ ስለሚደክማቸው፣ ይህ የባስ አገልግሎት ትልቅ እፎይታ ሆኖላቸዋል። አስባችሁታል "ውሻሽ የት ነው የሚማረው?" ምናምን ሲባባሉ! ወደቲክቶክ ስመለስ አንዲት መንግስት ቤት 20 ዓመት የሰራች ሴትዮ ከኮየ ፈጨ በሰልፊ ቪዲዮ ቅሬታዋን እያቀረበች ነው። "ለሚመለከተው አድርሱልኝ... 56 ቁጥር ባስ ቀረችብኝ ይሄው ሕዝቡ ተሰልፎ እየጠበቀ ... ከስራ አረፈድን " እያለች።

Alex abrham ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካልደረሰ መውጣቷ አይቀርም" ብሎ ችላ ይላታል። ወዲያው ግን አንድ በጣም አስደንጋጭ ነገር ትዝ ይለውና፣ በአስደናቂ ጀግንነት ድጋሚ ዘሎ ወደሚቃጠለው ቤት ይገባል። ሚስቱንም አንከብክቦ ይዟት ይወጣል። ​በኋላ ላይ ጋዜጠኞች ተሰብስበው፦ "እንዴት በዚህ ድፍረት ወደሚቃጠለው ቤት ገብተህ ሚስትህን ልታተርፋት ቻልክ? ስታገኛትስ በምን ሁኔታ ላይ ነበረች?" ብለው ጠየቁት። ​ስሜቱን በራሱ ቋንቋ እንስማው... ​我不能把手机和妻子单独留在家里。我一直担心她会拿起我的手机偷看信息。当我急匆匆地冲进家门时,果然不出所料,她正一边被浓烟包围着剧烈咳嗽,一边在翻看我的手机。最终,我把她和手机一起救了出来。 ​አቻ ትርጉም ከትንሽ ቅመም ጋር ​"ስልኬንና ሚስቴን ብቻቸውን እቤት ውስጥ መተው ፈጽሞ አልችልም! 'የተላላኩትን መልዕክት እያነበበች ይሆን?' የሚለው ስጋት እረፍት ነሳኝ። ​ዘልዬ እቤት ውስጥ ስገባ ልክ እንደፈራሁት፤ በጭስ ተከባ የቀሚሷ ጫፍ በእሳት እየተቀጣጠለና እያሳለች ስልኬን ስትፈትሽ አገኘኋት! በጨዋነት ስልኬን ተቀብየ ልወጣ ስሞክር 'ዢዋን ማናት? ለምንስ የልብ ኢሞጂ ላክህላት?' እያለች በዚያ ጭስ ውስጥ መጨቃጨቅ ጀመረች። ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ፣ ከነስልኩ አንጠልጥዬ ይዣት ወጣሁ።" ​ክፉ ጊዜ ላይ ነን እ? 😁

ነገሩ እንደአደንዛዢ እፅ ነው...ልጆች ወይም ወጣቶች ተደብቀው የወደቀች ሲጋራ ጫት ወይም ቤት ውስጥ ጠላ መቀማመስ ይጀምራሉ...ተደብቀው "ይሳሳሙ "ይሆናል። መደበቅ የይሉኝታና የአክብሮት ስሜት አለው። የምሰራው ልክ አይደለም ሌሎች አይዮብኝ የሚል ፀፀት አለው። ከፍ ሲሉ ሲጋራው ተራ ይሆንባቸዋል ፤ ወደመጠጥና ሽሻ ቤት ይሄዳሉ፣ መደበቁን ይተውታል። ያም አያረካቸውም ወደከባድ መጠጦች፣ ወደአደንዛዢ እፅ ይሄዳሉ፣ ሴተኛ አዳሪወች ጋር ባለጌ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ፣ ወሲብ ፣ማርገዝ ፣ወልዶ መጣል፣ ማስወረድ ወዘተ ተራ ነገር ይሆንባቸዋል። ጥርሳቸው መልካቸው ሰውነታቸው በቁማቸው መፈራረስ ይጀምራል ...እንኳን ምክርና ይሉኝታ ሞት ከሱሳቸው በላይ አያስፈራቸውም። ቤተሰብ ፣ ዕምነት ሕዝብ ተራ ይሆንባቸዋል። ከሞት አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው ወደሞት ያዘግማሉ። እንደውም "ኖርማል ሰው" ሲመለከቱ ጤነኛ አይመስላቸውም። ለሱሳቸው ይዋሻሉ፣ ማንንም አሳልፈው ይሰጣሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይገድላሉ። አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ሱስ በዚያ ደረጃ ላይ ነው። ጥበብ፣ ውይይት አሽሙር፣ ቅኔ ፣ የሰከነ ሐሳብ ፣ ይሉኝታ ሞራል፣ ትምህርት የሚባለውን ጉዳይ አልፏል። ተራ ስድድቦችንም ዘሏል። ወሲብ ነክ ጉዳዮች፣ አደባባይ ላይ የማይታዮ ገመናወችን መዘርገፍ ተራ ነገር ሁኗል። ራስን ማ*ፋት የሚያስቅ ቀልድ ሁኗል፣ ስለመገዳደል ካልተወራ ሬሳ ካላየ፣ ያዛጋዋል። የለየለት ፖርኖግራፊ እና የቆሸሸ የግል ገመና ገበያ ሆኗል። በየሚሴንጀርና ቴሌግራም እንደቆሸሸ የከተማ ወንዝ ዝሙት ሲፈስ ውሎ ያድራል፣ ገምቷል ሸቷል። በውስጥ የተራቆተው ከላይ ተከናንቦ እየተስለመለመ ብቅ ይላል። ከፈጣሪ እስከነብያት ከአገር እስከህዝብ ከማንነት እስከተፈጥሮ ስብዕና የማይዘለፍ የማይንቋሸሽ የለም። ብዙ ሺወች ከየመንደሩ የከረፋ ባህሪያቸውን ተሸክመው አደባባይ ወጥተዋል። የመላ ከተማው ቆሻሻ ተሰብስቦ እንደሚጣልበት ቆሸ ቆሻሻ መጣያ ሆኗል። ቤተሰብ እንኳን የሚፀየፋቸው ሰወች ሺህ ሚሊየን ሰው አስከትለው አደባባይ ውለዋል። የታዳሚው አእምሮ የቆሻሻ ሱስ ይዞት ቆሻሻ ያነፈንፋል። ቆሻሻው ላይ ሚሊየን ዝንቦች ያርፋሉ። "ማን ብዙ ዝንብ አለው " የሚለው ሐሳብ ኩራት ሆኗል። ድግሪ ያለው ዝንብ፣ ማስተርስ ያለው ዝንብ፣ ፒኤች ዲ የተሸከመ ዝንብ፣ ሐብት ያለው ዝንብ፣ ስልጣን ያለው ዝንብ፣ ሐይማኖተኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ዲያስፖራ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ቆንጆ ነኝ የምትል ዝንብ... ዝንባዊ ማንነት የሚኮራበት ሆኗል። "ለመኖር ስል ዝንብ ሆንኩ" ይልሃል። ንቦች ቆሻሻ ላይ ያበቀለ አበባ ፍለጋ አፍንጫቸውን ይዘው በቆሻሻ ክምር ላይ ክንፋቸው እስኪዝል ይበራሉ! የጨነቀው አየሩ ያፈነው ጨዋ ትውልድ በዚህ ቆሻሻ ታፍኖ እየተጨነቀ ነው። አየሩ ቆሽሿል... የሰው አዕምሮ ቆሽሿል፣ ቃላት ቆሽሸዋል። ንቦች የሚሰሩት ጥቂት ማርም ቢሆን ዝንብ ይሰፍርበታል። ዝንብ በቆሻሻና በማር መካከል ያለው ልዮነት አይገባውም። ሱሱ ግን አሁንም አልቆመም ነገ የከፋ ቆሻሻ ሊያዋልድ እያማጠ ነው።

photo content

የሚገርመኝ ነገር ነበር ኢትዮጵያ ውስጥ በአንዳንድ የገጠር አካባቢወች ይደረጋል...ስም ሁሉ አለው ጠፋኝ እንጅ! ጭራሽ ዛሬ ህንድ አካባቢ ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርጉ አየሁ። አንዲት ላም ከወለደች በኋላ ጥጃዋ በሆነ ምክንያት ከሞተች ወተቷ ይደርቃል። ጠባችም አልጠባችም ጥጃዋ በአካባቢው ካለች ግን ሰውነቷ ወተት ማምረት ይቀጥላል። (የተፈጥሮ ተዓምር፣ የእናትና ልጅ ትስስር) ስለዚህ ባለቤቶቹ የሞተችዋን ጥጃ ቆዳዋን በሳር(ጭድ) ይሞሉና እንዲህ ጥጃ አስመስለው እናቷ አጠገብ ያቆሟታል። ሚስኪን ላም ገና ለገና ልጀ ታድጋለች ብላ በሰው ስትታለብ ትኖራለች። ትልሳታለች ታሸታታለች...ምን ልላችሁ ነው? ለመሆኑ ዋጋ እየከፈላችሁለት ያለው ነገር በህይወት አለ? ፍቅራችሁ አለ? እምነታችሁ አለ? ህልማችሁ አለ? ወይስ አለ እያሉ ባቆሙላችሁ የሞተ ነገር ለሌሎች ዕድሚያችሁ፣ ገንዘባችሁ፣ ጤናችሁ እየታለበ ነው?

ስምንተኛ ክፍል እያለን የሳይንስ ትምህርቶች በራሳችን ቋንቋ ይሰጡ ተባለ! እና ባዮሎጅ አስተማሪያችን ስለተክሎች ሲያስተምረን ዝንቡጤ፣ አምቡጤ ፣ ጉንቁሌ፣ ዘርጉጤ ጎጥጉጤ ምናምን ሲል ....እንዴ ይሄ ሰውየማ ድግምት ነው የሚያስተምረን አልን😀 ሰሞኑን አንዳንድ የኢኮኖሚክስ ቃላትን አማርኛ ትርጉም ሰጠን ብለው ግራ የሚያጋቡን ባለሙያዎችና ጋዜጠኞችን ሳይ ተመሳሳይ ስሜት ነው የፈጠረብኝ!ዛሬ ረፍት ነኝ የሰሞኑን ብዢታ፣ ኑሮየንም ያስረዳኛል ብየ አንዱን ዮቲዮብ ላይ ብሰማው "ለስነ ምጣኒያዊ ብያኔ አስኳለ መርህ መሠረት የሆኑት መሻትና ችረት ሲወሳሰኩ...." አለ! እ? ተወው በቃ! ዘይት ቢወደድ ይሻለኛል! እንዴ በዚህ ኑሮ ላይ...