cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Seid Mussa (ሰዒድ ሙሳ)

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
3 765
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-97 kunlar
-5130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 4 ~ ያያያዝኩት የባህሩ ተካ ንግግር ነው። የውሸት እርከኑን በዚህ መጠን ከፍ አድርጎታል። ውሸቱን ሲለማመደው ጊዜ "አንባቢ ይታዘበኛል" የሚለውንም ትቶታል። እንዲያው አንድ ሰው መስሎት ተሳስቶ ቢናገር ይሁን። ይሄ ሐያእ የቀለለው ፍጡር ግን በምን መልኩ ሰው ላይ እንደሚዋሽ ተመልከቱ። ሳዳት ነው ወደነዚህ አካላት የሚጣራው? በሐዲሥ እንደመጣው ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ ሁለቱ ሲያወሩ መዋሸት እና በሙግት ላይ አመፀኝነት ወይም ገልብጦ መወንጀል ነው። በነዚህ አጥፊዎች ላይ ረድ መስጠት ነው ወደነሱ መጣራት ተብሎ የሚገለፀው? ጥላቻ አናቱ ላይ ወጥቶ በትክክል ማየት እንዳይችል ጋርዶታል። በረድ ስም እየዋሸ መለጠፍ ጣፋጭ ምግብ ሆኖለታል። እጅ እጅ የሚል ፅሁፉን ውሸት ጣል ሲያደርግበት ውበትና ጥንካሬ የሚጨምር ይመስለው እንደሁ አላውቅም። "የሰካራም ግጥም ሁሌ ቅዳ ቅዳ" እንዲሉ ወጥሮ የውሸት አውቶማቲክ መተኮሱን ተያይዞታል። ረድ ማለት የጠሉት ሰው ላይ የፈለጉትን መለጠፍ ሆኗል ባህሩ ዘንድ። ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ውሸትን ስራዬ ብሎ አጥብቆ ይይዛል? ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ وإِيَّاكُمْ والْكَذِبَ، فَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، ومَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَكْذِبُ ويَتَحَرَّى الْكَذِبَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللَّهِ كَذَّابًا “አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል፤ ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡ አንድ ሰው ሲዋሽና ውሸትም ላይ ሲያተኩር አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይመዘገባል።” [ቡኻሪይ እና ሙስሊም] ሳዳትን በማጠልሸት ላይ እንቅልፍ ከምታጡ ራሳችሁን ከዚህ የውሸት ሱስ አውጡ። ሳዳት እናንተን ከነ ንዝንዛችሁ እርግፍ አድርጎ ትቶ አነሰም በዛም የራሱ ስራ ላይ ነው ያለው። ደግሞም በተለይ ተራውን ህዝብ በማንቃት ላይ ባለው አስተዋፅኦ አንዳችሁ እንኳ የሚስተካከል ቀርቶ የሚቀርብ ነገር የለውም። የራሳችሁን ድርሻ ባግባቡ እንደመወጣት ሰዎች የሱን ትምህርት እንዳይከታተሉ ጥላሸት መቀባትን ጂሃድ አድርጋችሁታል። ይሄ ነው የናንተ ስኬት። ባህሩ ተካ እንደምታዩት ወንድማችን ሳዳትን ወደ "ቲክ – ቶክ መንደር ወርዶ ወጣቱን ወደ ዮኒ ማኛና ኢክራም አውቶሞቲቭ" ይጣራል እያለ ነው። * ሳዳት ከአጥፊዎች ነው ያስጠነቀቀው። ባህሩ ደግሞ አጥፊዎቹን ጥሎ ሳዳትን መዝለፍ ላይ ነው የተጠመደው። ከአጥፊዎች ማስጠንቀቅ ወደነሱ መጣራት ከሆነ እንዳበደ ውሻ ሁሉን የምትናከሱት እናንተ አጥፊዎች ወደምትሏቸው እየተጣራችሁ ኖሯል ለካ? መቼም በራሳችሁ ጩኸት ስለደነቆራችሁ ሂሳባችሁ ምን እንደሚሰጥ አይገባችሁም። * ምናልባት አጥፊዎቹን ፊት ለፊት ተገኝቶ መምከሩን ከሆነ ወደነሱ መጣራት የምትለው ይሄ ምን ያህል በልብህ ያረገዝከው ጥላቻ ነገሮችን የመረዳት አቅምህንም እንዳሽመደመደው ነው የሚያሳየው። እንዲያው አቀራረቡ ላይ ሂስ አለኝ ብትል እንኳ እንዳንተ አይነቱ በቆሻሻ የብሄር ካባ ተጀቡኖ የጉራጌ ካፊ'ሮች ጋር አንድነት ስለማድረግ የሚሰብክ ሰው ሂስ የመሰንዘሩን ድፍረት እንዴት ነው የሚያገኘው? የጥላቻ ብቅል ይህን ያክል ያሰክራል ለካ! የሚገርመው በዚህ መልኩ አይኑን በጨው አጥቦ እየዋሸ "ውሸታም" ተባልኩ ብሎ ሲብሰው ማየት ነው። የእውነት ህሊና ካለህ ከመባልህ ይልቅ መሆንህ ያስጨንቅህ። ያለበለዚያ ነገሮችን እየገለበጥክ ማየትህን ትቀጥላለህ። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁላህ ምን እንደሚሉ ተመልከት:- إياك وَالْكذب فَإِنَّهُ يفْسد عَلَيْك تصور المعلومات على مَا هِيَ عَلَيْهِ وَيفْسد عَلَيْك تصورها وَتَعْلِيمهَا للنَّاس فَإِن الْكَاذِب يصور الْمَعْدُوم مَوْجُودا وَالْمَوْجُود مَعْدُوما وَالْحق بَاطِلا وَالْبَاطِل حَقًا وَالْخَيْر شرا وَالشَّر خيرا فَيفْسد عَلَيْهِ تصَوره وَعلمه عُقُوبَة لَهُ. "ውሸትን ተጠንቀቅ። እሱ መረጃዎችን ባሉበት ሁኔታ (በትክክለኛ ቅርፃቸው) የመረዳት አቅምህን ይበክልብሃል። በተጨባጭ መሳልና ማሳወቅንም እንዲሁ ያበላሽብሃል። ውሸታም የሌለውን እንዳለ፣ ያለውን እንደሌለ፣ እውነቱን ሃሰት፣ ሃሰቱን እውነት፣ ኸይሩን ሸር፣ ሸሩን ደግሞ ኸይር አድርጎ ገልብጦ ያቀርባል። በውሸቱ ይቅቀጣ ዘንድ የመረዳት አቅሙም እውቀቱም ይበላሽበታል።" [አልፈዋኢድ፡ 135] ውሸትን እንደ ፅድቅ ማየት የመጣው በዚህ ምክንያት ነው። "የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይ የሰው ማገዶ ያስጨርሳል።" = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 3 ~ ከሶስት አመት በፊት ኮምቦልቻ ላይ በተካሄደ ደውራ ላይ ከወንድሞች ጋር ተካፍዬ ነበር። በጊዜው አንድ ሸይኽ ከሳዑዲ በስልክ እንዲያስተምር ይደረጋል። በእለቱ እኔ የተሰጠኝን ላስተምር የተገኘሁ ተጋባዥ እንግዳ እንጂ የፕሮግራም አስተባባሪ አልነበርኩም። የሰውየውን ትምህርትም አልተከታተልኩም። እነዚህ ውሸት የቀለላቸው ፍጡሮች ግን ልክ ሰውየውን እኔ እንደጋበዝኩ አድረገው ደጋግመው መክሰሳቸውን ቀጥለዋል። እኔ ስለ ሰውየው አላውቅም ብልም እምቢ ብለው እየተቀባበሉት ነው። "ሞኝ እምቢ ብሎ ይረታል" ይባላል። አይናቸውን በጨው አጥበው ቀጥለዋል። የዚህ ቅጥፈት መነሻ የሆነው ፀሐፊ ያኔውኑ መጥቶ አናግሮኝ ስለ ሸይኹ የማውቀው ነገር እንደሌለ፣ እንዲቀርብ ያደረግሁትም እኔ እንዳልሆንሁ ተናግሬ ነበር። ይህንን ከማውራታችን ጋር ነው እንግዲህ እኔ እንደጋበዝኩ አድርጎ የፃፈው። የዚህን ቀጣፊ ወሬ ነው እነ በህሩ ተካ የሚቀባበሉት። ሰውየው ማነው? ማንስ ጋበዘው? ስሙ ዓዲል ብኑ ሙሐመድ አሱበይዒይ ይባላል። ይህንን ሸይኽ የጋበዘው ደግሞ ጠሀ ኸዲር ነው። ጠሀ ማለት የዚህ ሰካራም አንጃ አካል እንደሆ ያዙ። ስለዚህ የጠሀ ቻናል ላይ ፍንጭ እንደማገኝ በማሰብ ገባሁ። ግምቴ ልክ ነበር። 1ኛ፦ ሸይኹን የጋበዝነው እኛ ከሆንን ከባድ ወንጀል ነው አይደል? እናንተስ ከሆናችሁ? ይሄው ሸይኹን የጋበዘው ጠሀ ኸዲር ነው። ራሱ በጊዜው የፃፈውን አያይዤላችኋለሁ። አሁንስ ክሱን ወደሱ ታዞራላችሁ? 2ኛ፦ ሸይኽየው እናንተ ዘንድ የጋበዘው ሳይቀር የሚወነጀልበት ከባድ የመንሀጅ ችግር ያለበት ነው ኣ? ይሄው ጠሀ ኸዲር ዘንድ ደግሞ ሰውየው ሌላ ነው። "ፈዲለቱ ሸይኽ"፣ "ሸይኻችን"፣ "አልሙጃሂድ"፣ "አልሙረቢ"፣ "አልዋሊድ"፣ "ፈዲለቱ ሸይኽ አልኡስታዝ አልሙሐዲሥ"፣ "ሸይኹነል ከሪም" እያለ በመግለፅ ደጋግሞ ያሰራጭለታል። በነገራችን ላይ ስለ ሸይኹ ዛሬም ድረስ ክፉም ደግም አላውቅም። እንደሚሉት ችግር ያለበት ከሆነ ግን እነ ጠሀ ስንት ፊት እንዳላቸው ተመልከቱ። ሳዑዲ ሌላ፣ ኢትዮጵያ ሌላ። ሌላው ቀርቶ ሳዑዲ ኤምባሲ ወይም የሳዑዲ የባህል ማዕከል ዘንድ ራሱ ሌላ ፊት ነው ያላቸው። እዚያ የሚያልሙት መስለሐ ስላለ የሚቀርቡበት ሌላ ጭምብል አላቸው። ከኢኽዋን ቁንጮዎች ጋር አግድም ተሰልፎ ፎቶ መነሳትም ችግር የለውም። በፊጥራ ጥሪ ላይ ድንገተኛ መገጣጠም ብቻ እንደተከሰተ አድርጎ ባህሩ ተካ ፅፎ አይቻለሁ። ከዚያ እንዳይወጡ በጥበቃ ተከልከለው ነው ኣ? ከዚያም አፈሙዝ ደቅነው አንድ ላይ ተሰልፈው ፎቶ እንዲነሱ አደረጓቸው አይደል? የፊጥራውን እንለፈው። በቅርቡ የተካሄደው ኮንፈረንስ ፊጥራ አልነበረም። የዚህ ቡድን አባል የሆነው ኡስታዝ (ነዚፍ) ራሱ ድግሱ ላይ ፕሮግራም አቅራቢ ነበር። በህሩ እንደለመደው ነው እየዋሸ ያለው። እኔ እነዚህን ነጥቦች የማነሳው ለተብዲዕ አይደለም። ጩኸታቸውና ግብራቸው የማይገናኝ እንደሆነ ለመጠቆም ያህል ብቻ ነው። ወደ ተነሳሁበት ስመለስ ሰዎቹ ራሳቸው ባቀረቡት ሰው ሰበብ ዞረው የሚናደፉ እባቦች ናቸው። ከላይ የተጠቀሰው ሸይኽ እንደሚሉት ችግር ያለበት ከሆነ ተጠያቂው ጦሀ ኸዲር ነበር። ሰውየው ችግር ያለበት ከመሆኑ ጋር "ሸይኻችን" እያለ የሚገልፀው፣ የቴሌግራም ቻናሉን የሚያስተዋውቅለት እሱ እንጂ እኛ አይደለንም። ከሰውየው ላይ ቁጭ ብሎ የሚማረው ራሱ ነው። ቢሆንም ቡድናዊ ያለመከሰስ መብት ስላለው አይነኩትም። አንዱ ይህንን ቅጥፈት እያሰራጨ ያለው በህሩ ተካ ነው። በህሩ ሲበዛ ውሸት የቀለለው ፍጡር ነው። እነዚህ ሰዎች ላይ እንዳጠቃላይ የማየው ችግር ስለ 'ረድ' ያላቸው ግንዛቤ በጣም የተንሻፈፈ መሆኑ ነው። የሚናገሩበትን ሰው ያጠልሽላቸው እንጂ እውነት ይናገሩ ውሸት አያስጨንቃቸውም። ችግራቸው በሚጠሉት አካል ላይ ሆነ ብለው የሚያሳድሩት ክፉ ቀስዳቸው ብቻ አይደለም። ንግግሮችን የሚረዱበት አቅምም ሲበዛ የወረደ ነው። ክፉ እሳቤ እና እጅግ የወረደ የመረዳት አቅም ከቅጥፈት ጋር ሲጣመር ውጤቱ አሁን እነሱ የሚያሳይቱን ይሰጣል። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ - ረሒመሁላህ - ሲሞቱ ጊዜ ታስረውበት በነበረው ወህኒ ቤት ውስጥ በሳቸው የእጅ ፅሑፍ የተፃፉ እንዲህ የሚሉ አሳዛኝ የግጥም ስንኞች ተገኝተዋል። በግርድፉ ተርጉሜዋለሁ። “እኔ ነኝ ደካማው ከጃይ … ከሰማያቱ ባለቤት በሁለመናዬ ስንኩል … እኔው ነኝ ምስኪኑ ማለት። እኔው ነኝ የራሴ ጠላት … ነፍሴ እራሷ ነች በዳዬ ኸይር ሁሉ የሚገኘው … ከሱ ብቻ ነው ጌታዬ። ለራሴ እንኳን የማልሆን … የማላቀርብ አንዳች ፋይዳ መከላከል አይሆንልኝ … በክፉ እንዳልጎዳ። ሌላ ፈጣሪም የለኝ … ከሱ ውጭ ‘ሚያስተናብር አማላጅም አይኖረኝ … ወደ ጌታ የሚያሻግር በሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ … በፈጠረኝ በረሕማኑ የሰማያቱ ባለቤት … እንዳወሳው በቁርኣኑ ቅንጣት የሌለኝ ከንቱ … ያለ ጌታዬ ይሁንታ አንዳች ተጋሪም የለው … በየትኛውም ሁኔታ አጋዥ አይፈልግ ደጋፊ … ረዳት አይሻ የኔ ጌታ ልክ እንደሚያስፈልጋቸው … ለወልዮቹ አይነታ። ችግር ድህነት አርማዬ … የኔ ቋሚ መገለጫ መብቃቃቱ የጌታ ነው … የሁልጊዜ ባለብልጫ አንጋጣጭ ነው ወደ ጌታ … ፍጡር ሲባል ጠቅላላ ሁሉም ተዋርዶ ይቀርባል … ቢሻው ጠላ ቢሻው ደላ። ከፈጠረው ጌታ ውጭ … ምኞት ፍላጎት የሚሻ ቂል፣ በዳይ፣ አረመኔ … አጋሪ ነው መጨረሻ። ይመስገነው ፈጣሪዬ … አለሙን በፀጋው የሞላ ላለፈውም ለመጪውም … ላደረገልን በመላ። ከዚያም ሶላቱ ይትረፍረፍ … በምርጡ ነቢያችን ላይ የፍጡራን ቁንጮ አይነታ … የሁሉ ላይ የላይ በላይ።” [አልዑቁድ፡ 391] = * ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor * ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL * ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M * ኡማ ላይፍ፦ https://ummalife.com/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ያ ጀማዓ እንዴት ናቹህ በመቀጠል ይህ ግሩፕ የተከፈተዉ  የእህታችን ነፊሳ አህመድን  ህይወት ለመታደግ ነዉ  እህታችን ለረዥም ጌዜ  በልብ ህመም ምክንያት ስትሰቃይ  የቆየች ሲሆን  ከዛሬ ነገ ይሻላታል በሚል ተስፋ   ለአራት አመታት ህክምናዋ የቡታጀራ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል  ስትከታተል ቆይታለች ። ሆኖም ግን ህመምዋ ከጌዜ ወደጌዜእየተባባሰ  በመሂዱ ምክንያት የህመምዋ  ሁኔታ በጣም አስጊ ሆናል። እህታችን በከፍተኛ ህመም ውስጥ ነው ምትገኘው በዶክተሮች መረጃ መሰረት ልቧ በጣም እንደተጎዳና  አንዱ ጎን እንደሌለ እንዲሁም  አርቴፊሻል የደም መረጫ በአፋጣኝ እንዲገባላት አያይዘው ገልፀዋል አርቴፊሻል የደም መረጫው ለመግዛትና ሌሎች ፕሮሰሶችም ጭምር ለ ሙሉ ህክምናዋ ለመሸፈን 1.1 ሚሊን ብር እንደሚያስፈልጋት ገልፀዋል ። ቤተሰቦቿ ደግሞ ይህንን ወጪ የመሸፈን አቅም የላቸውም ። እስካሁንም ለ4 አመታት አቅማቸው በቻለው ሲያሳክሟት  ቆይተዋል አሁን ግን ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ ከአላህ በታች የእኛን እርዳታ ፈልገው ፊታችን ቆመዋል ። እህታችን ነፊሳ አህመድ ገና ለጋ ወጣትና የ 10ኛ ክፍል ተማሪ ናት አሁን ላይ ግን በህመሟ ምክንያት የምትወደው ትምህርቷ አቋርጣ ለህይወቷ አስጊ በሆነ ከፍተኛ ህመም ውስጥ ትገኛለች። ያጀማዓ  5    10  ሳንል  ያለንን አቅማችን በቻለው እንተባበራት ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልኮች ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ:- የአባቷ ስልክ :- 0916698816 የወንድሟ ስልክ :- 0926612043 ለእህታችን ነፊሳ የእርዳታ ገቢ ማሰባሰቢያ አካዎንት :- 👇👇 ((1000585445952))  ንግድ ባንክ ተጨማሪ:-(( 7000050832347 )) ንብ ባንክ አካዎንቶቹ የተከፈተባቸው ስም ዝርዝሮች:- 👇 አህመድ ኢድሪስ , ሉባባ አህመድ & አንዋር አህመድ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ¶https://t.me/ehtachin_nefisan_enrdahttps://t.me/ehtachin_nefisan_enrda
Hammasini ko'rsatish...
"እኛ ለአላህ ነን። እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን!" {إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ } የወንድማችን ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ልጅ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሞቷል። ቀብር ላይ መገኘት ለምትፈልጉ ቦታው የት እንደሚሆን ሲወሰን እናሳውቃለን፣ ኢንሻአላህ።
Hammasini ko'rsatish...
Repost from Fuad Mohammed
فائدة: قال الشيخ صالح الفوزان -متعه الله بالصحة والعافية، آمين-: نحنُ لا نهملُ قضايا المسلمين؛ بل نهتم بها، ونناصرهم ونحاول كف الأذى عنهم بكل وسيلة، وليس من السهل علينا أن المسلمين يقتَّلون ويشردون. ولكن ليس الاهتمام بقضايا المسلمين أننا نبكي ونتباكى، ونملأ الدنيا بالكلام والكتابة، والصياح والعويل؛ فإن هذا لا يجدي شيئا. لكن العلاج الصحيح لقضايا المسلمين: أن نبحث أولا عن الأسباب التي أوجبت هذه العقوبات التي حلَّت بالمسلمين، وسلطت عليهم عدوهم... وأهم هذه الأسباب... هو إهمالهم للتوحيد). انتهى باختصار من ((دروس من القرآن الكريم)).
Hammasini ko'rsatish...
አንድ የኛን ነባራዊ ሁኔታ ገላጭ የሆነ እንዲህ የሚል ግጥም አለ:- "ዝም ያለው ዘመዴ - እኔ ሳጣጥር፣ ሞተ ቢሉት መጣ - አልቅሶ ሊቀብር።" . በቅርቡ አንድ ዳዒያ ለህክምና ወደ ቱርክ በሄደበት የሞቱ ዜና ሲዘዋወር ነበር፣ አላህ ይማረውና። በርግጥ ይህንን ወንድም ቀድሜ ከነ ጭራሹ አላውቀውም። ግን ረዘም ላለ ጊዜ በህመም ላይ እንደቆየና ማንም ከጎኑ እንዳልነበረ አሁን ከሞተ በኋላ ሲወራ ሰማሁ። በጣም የሚያሳዝን ነው። ለምንድነው ግን በዚህ መጠን ሰው በቁሙ እያለ ከመጠየቅ ይልቅ ሩጫችን ብዙም በማይጠቅምበት ባለቀ ሰዓት መዋከብ ወይም ሞቱ ሲሰማ ጊዜ መጯጯህ የሚቀናን? ያሳዝናል። ለማንኛውም አሁንም ከምናውቃቸው መሻይኾችና ኡስታዞች ውስጥ ጤናቸውና ኑሯቸው ፈተና ውስጥ የሆኑ ይኖራሉና ቀረብ ብሎ መጠየቅ ይልመድብን። በርግጥ እንዲሁ ሰሞንኛ ስሜቴን ለመግለፅ ያህል እንጂ ዞረን እዚያው እንደሆንን ይገባኛል። ብቻ ባለቀ ሰዓት መሯሯጥ ወይም ሞታቸውን ጠብቆ ከንፈር መምጠጥ ትርጉም የለውምና ሊበቃን ይገባል። ይሄ አካሄድ ከሞቱት ባልተናነሰ ያሉትንም ጭምር ሞራላቸውን በመጉዳት፣ ተስፋቸውን በማደብዘዝ፣ ልባቸውን በሃዘን በመስበር የሚገድል ነው። አላህ ልብ ይስጠን! Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

01:20
Video unavailableShow in Telegram
فضيلة الشيخ سليمان الرحيلي - حفظه الله - عن شبهة أن بعض المحدثين رووا عن أهل البدع في الحديث، فما المانع أنْ نتعلم على يد المبتدع ؟ https://t.me/Abulbuhari
Hammasini ko'rsatish...
7.19 MB