cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

🍃بالقرآن نحي {በቁርአን እንኖራለን

የተለያዩ ቁርኣናዊ አስተምህሮ’ዎች፣ ጣፋጭ ቲላዋዎች፣ ቁርኣንን የሚመለከቱና በቁርኣን ዙሪያ የሚሽከረከሩ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ቻናል join ይበሉ ! ቁርኣን የወረደው ለሰው ልጅ መመሪያ፣ እንድናስተነትነውና እንድንገሰፅበት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦ (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ {Q 38:29}

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
972
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kunlar
-1230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Repost from Tofik Bahiru
ኑ እንሰደድ! (ክፍል ሁለት) ** …ከክፉ ንግግር ወደ መልካም ቃል! ** ንግግራችን፣ ቃላቶቻችን፣ ፅሁፎቻችን… የአላህ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ራሳችንን እንድንገልፅባቸው፣ እንድንማማርባቸው፣ ህይወታችንን እንድናቀናባቸው የተሰጡን ስጦታዎች ናቸው፡፡ አላህ ህግ አለው። ስጦታ ከሰጠ እንዲመሰገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሰጠን ፀጋዎች ላይ ትዕዛዛትና ክልክሎችን ደንግጓል፡፡ ልሳንና ብዕር ሰጥቶን ሐቅን እንድንበይንበት ስህተትን እንድናጋልጥበት አዞናል፡፡ ፀያፍ ቃላት፣ ሃሜት፣ ስድብ እና ሌሎችንም እንድንርቅ አስጠንቅቆናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- وَقُل لِّعِبَادِي يَقُولُوا الَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِنَّ الشَّيْطَانَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلْإِنسَانِ عَدُوًّا مُّبِينًا ‹‹ለባሮቼም በላቸው፡- ያችን እርሷ እጅግ መልካም የኾነችውን (ቃል) ይናገሩ፡፡ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና፡፡›› መልካም ንግግር እንድንናገርና ክፉን እንድንርቅ የታዘዝነው ሰይጣን በመሀላችን ያለውን ግንኙነት እንዳያበላሽ ነው እየተባልን ነው፡፡ በክፉ ቃል ውስጥ ሰይጣን ብዙ እድሎች ይከፈቱለታል፡፡ ልቦችን ማሻከር እና ማጋጨት የሚችልበት አጋጣሚ ያገኛል፡፡ ንግግሮቻችን ጥሩ ወይም በጣም ጥሩ ይሆናሉ፡፡ ወይም መጥፎና እጅግ በጣም መጥፎ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወይም በመካከል ያሉ የሚፈቀዱ -ጥሩም መጥፎም የማይባሉ- ንግግሮችም አሉ፡፡ አላህ በዚህች አንቀፅ ያዘዘን እጅግ መልካም የሆነችዋን ንግግር ነው፡፡ ጥሩውን ሳይሆን እጅግ በጣም ጥሩ የሆነውን ቃል እንድንናገር መከረን፡፡… ** ይህንን ያዙልኝና ወደ ተጨባጫችን ተመልሰን ራሳችንን እንገምግም፡፡ ብዙዎቻችን የምንናገረውም ሆነ የምንፅፈው ፀያፍ ወይም እጅግ በጣም ፀያፍ ንግግር ነው፡፡… አንዳንዴም የሚፈቀዱ -ጥሩም መጥፎም የማይባሉ ንግግሮች አሉን፡፡ እጅግ በጣም ጥቂት ንግግሮቻችን እርከናቸው ከፍ ብሎ መልካም ንግግሮች ይሆናሉ፡፡ ነገርግን… መልካም ንግግሮች ብቻቸውን የሰይጣንን ተንኮል አይከላከሉም፡፡ እኛ የታዘዝነው እጅግ መልካም የሆነውን እንድንናገር ነው፡፡ እጅግ በጣም መልካም ቃል ብቻ ነው ከሰይጣን ማበላሸትና ክፋት የሚጠብቀን! ** የኔ አጀንዳ… ** ሶሺያል ሚዲያ ፀጋ ነው፡፡ ታላቅ የአላህ ስጦታ፡፡ ይኸውም ይህንን ስጦታ በአግባቡ ለሚጠቀሙበት ሰዎች ነው፡፡ ነገርግን በላእ ነው ፈተና፤ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት፡፡ አላህ በምላሳችንም ሆነ መረጃን ወደ ሁለተኛ ወገን ማስተላለፍ በምንችልባቸው ማናቸውም ሚዲያዎች ላይ ያዘዘን ታላቅ ነገር አለ፡፡ ወደርሱ ሰዎችን መጣራት፣ በበጎ ነገሮች ማዘዝና ከክፉ ነገሮች መከልከል፡፡ ሰዎችን ማስታረቅና ማቀራረብ፡፡ በተቅዋና በመልካም ነገሮች ዙርያ መወያየት፡፡… አላህ በሱረቱል—ዒምራን ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡›› ሱረቱን—ኒሳእ ላይም እንዲህ ብሏል:— ‹‹ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡›› ሱረቱል—ሙጃደላ ላይም:— ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተንሾካሾካችሁ ጊዜ በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ፣ መልክተኛውንም በመቃወም አትንሾካሾኩ፡፡ ግን በበጎ ሥራና አላህን በመፍራት ተወያዩ፡፡ ያንንም ወደእርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ፡፡›› ይላል። እነዚህ አንቀጾች በድምራቸው ሰዎች ሲናገሩ እጅግ መልካም የሆነውን ብቻ እንዲናገሩ ሌላውን ንግግር እንዲተዉ ያዝዛሉ፡፡… ** ልሳንና መሰሎቹ አደገኛ ጣጣ ያመጣሉ፡፡ በዝምታ እንጂ ከነዚህ አደጋዎች አንድንም፡፡ ለዚህ ነው ሐዲሶቹ ዝምታን የሚያበረታቱት፡፡ ‹‹መን ሶመተ ነጃ፡፡›› (ዝም ያለ ዳነ) ፣ ‹‹ዝምታ ጥበብ ነው፤ ሰሪዎቹ ግን ጥቂት ናቸው፡፡››… ሶሐቢዩ ከሰለመ በኋላ ‹‹ምንን ልጠንቀቅ?›› ሲላቸው -የአላህ መልእክተኛ [ﷺ]- ‹‹የተከበረው ምላሳቸውን እየጠቆሙ "ይህንን!"›› አሉት፡፡…፣ ‹‹መዳን እንዴት ይገኛል?›› ያላቸውን ሶሐባ ‹‹ምላስህን ያዝ፣ ቤትህ ይስፋህ (ከፍጡር አትከጅል)፣ ለኃጢኣትህ አልቅስ፡፡›› ብለው መለሱለት፡፡…፣ እሳት የሚያስገቡ ዋና ነገሮች ምንድን እንደሆኑ ሲጠየቁ ‹‹አፍና ብልት፡፡›› ብለውም መልሰዋል፡፡… አዎን! ዝሙትና የምላስ ጣጣ ሰዎችን በብዛት ጀሀነም የሚያስወረውሩ ኃጢያቶች ናቸው! ‹‹አብዝሃኛው የሰው ልጅ ኃጢኣት በምላሱ የመጣ ነው፡፡›› ይሉናል የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)፡፡ በሌላ ሐዲስ ‹‹ምላሱን የጠበቀ ነውሩን አላህ ይደብቅለታል፡፡ ቁጣውን የተቆጣጠረ አላህ ከቅጣቱ ይጠብቀዋል፡፡ አላህን ምህረት የጠየቀ አላህ ምህረቱን ይቀበለዋል፡፡›› ብለዋል። ** ከሀሜትና ሒጃብን ከመጣል ወይም ወንድ የወርቅ ጌጥ ከመጠቀሙ አላህ ዘንድ የትኛው ከባድ ኃጢያት ነው?!... ሀሜትን ስለለመድነው ቀሎናልና ሁለተኛውንና ሦስተኛውን እንደምንጠየፍ አውቃለሁ፡፡ ነገርግን ሐቁ ሀሜት ከብዙ ከምንጠየፋቸው ኃጢያቶች በላይ አላህ ዘንድ የተጠላ ነው፡፡… ስድብ ፋሲቅ ያደርጋል፡፡ ተሳዳቢ ለምስክርነት ብቁ አይሆንም፡፡ "ሙስሊም ተራጋሚም ተሳዳቢም አይደለም!"፣ ‹‹ሙስሊምን መስደብ ፍስቀት ነው፡፡ እርሱን መጋደል ደግሞ ኩፍር ነው፡፡›› ይላሉ ታላቁ ሰው (ﷺ)፡፡ ነገርግን ሙስሊምን መሳደብ አሁን አሁን ዝንብን እሽ ብሎ ከአፍንጫ ላይ ከማባረር በላይ የቀለለ ተግባር ሆኗል፡፡ ነገር ማሳበቅ/ነሚማ ከባድ ኃጢኣት ነው። እዚህ ማህበራዊው ሚዲያ ላይ በስፋት የማየው ችግር ነው፤ ነሚማ። እንዴት መሰላችሁ!?… ሰዎች የሃሳብ ፀብ ይኖራቸውና ይጣላሉ። ያኔም ነገሩ እንዳይበርድ የሚያፋፍሙ ሰዎች ታውቃላችሁ!?… የሰዎች ፀብ የሚማርካቸው?!… ለስድድባቸው ላይክና ሼር በማድረግ የሚያጋግሉ!?… እነዚህ ነማሞች ናቸው። ሙስሊሞች ሲጣሉ ደስ የሚላቸው። እንደኔ ትዝብት ከሆነ በብዛት ሙስሊሞች የሚመሰጡበት አጀንዳ ፀብና ጥል ነው። በዳዒዎች ዙርያ የሚሰበሰቡ ሰዎችን ስብሰባቸው አለቃቸውን አግዝፈው ተቃራኒውን ለማራከስ ነው። በንግግር ራስን ማዳነቅ/ ማሞካሸት በፌስቡክ ቢሆንም አይፈቀድም። "ነፍሳችሁን አታወድሱ፤ እርሱ የተጠነቀቀውን ይበልጥ ያውቃል።" ይለናል፤ ረቡል—ዐለሚን። ፎቶን ለጥፎ ለአላፊ አግዳሚው "ቴንኪው!" እያሉ መኖር እንዴት ያስጠላል። በተለይ ሴቶች እናንተን ነው!… እንደኔ ሴትነት ትጋት፣ ጥረት፣ እዝነት፣ ፍቅር፣ ሰላም… እንጂ ቅርፅ ወይም ሥጋ አይደለም። ፍላጎታችሁን ከፍ ባለ ነገር ላይ አንጠልጥሉት። የእውቀትና የስብዕና ግንባታ ላይ አስተዋፅኦ አበርክቱ። -ማንበብ እንደማንወድ አውቃለሁና- እንዳላረዝምባችሁ ፌስቡክም ሆነ ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ኦፖርቹኒቲ ይዘው እንደመጡ ሁሉ ማንነታችንን፣ የደረስንበትን የስነምግባር ዝቅጠት… አጋልጠዋል፡፡ እናም እባካችን… እባካችን… እባካችን… እጅግ በጣም መልካም ንግግሮች ሞልተው እያለ ለምን በሰፋሲፍ/ቂላቂል ነገር ጊዜ እናቃጥላለን!... መስጂድ ያለው አላህ እዚህም አለና ንግግራችንን እንመርምረው! ኑ ከክፉ ንግግር እጅግ በጣም መልካም ወደ ሆኑ ንግግሮች እንሰደድ! https://t.me/fiqshafiyamh
Hammasini ko'rsatish...
Repost from Tofik Bahiru
በዐሹራ ቀን ራስን እና ቤተሰብን ማስፋፋት ሱና ነው። ይህ አራቱ መዝሀቦች የተስማሙበት ሃሳብ ነው። ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «በዐሹራ ቀን ለራሱ እና ለቤተሰቡ ያስፋፋ ሰው አላህ በቀረው አመቱ ያስፋፋለታል።» ኢብኑ ዐብዲል‐በር 'አል‐ኢስቲዝካር' ላይ ሰይዲና ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህን [ረዲየላሁ ዐንሁ] በመጥቀስ ዘግበውታል። ጦበራኒይ፣ በይሀቂይ፣ ኢብኑ አቢድ‐ዱንያ ከአቡ ሰዒድ አል‐ኹድሪይ ዘግበውታል። ሰይዲና ጃቢር [ረዲየላሁ ዐንሁ] «ዐርባ አመታት ሞክሬዋለሁ።» ብለዋል። ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና [ረዲየላሁ ዐንሁ] በበኩላቸው: ‐ «ሃምሳ ወይም ስድሳ አመታት ሞክረነው መልካምን ነገር እንጂ አላየንም።» በማለት በሐዲሱ መልእክት እንደተጠቀሙ ይናገራሉ። ከሻፊዒዮቹ ሱለይማን አል‐ጀመል "ፈትሑል‐ወሃብ" በተሰኘው የሸይኹል‐ኢስላም ዘከሪያ አል‐አንሷሪይ መፅሀፍ ላይ በሰሩት ማብራሪያቸው (ሓሺያ) ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በእለተ ዐሹራ ለቤተሰብ እና ለዘመድ ማስፋት ለድኾችና ምስኪኖች ሶደቃ ማድረግ ይወደዳል። ነገርግን ራስን ከአቅም በላይ ማስጨነቅ አያስፈልግም። የሚያስፋፋበት ነገር ካጣ ጠባዩን ያስፋላቸው። ከበደልም ይታቀብ።» 🔺 ማስፋፋት: ‐ በሚበሉ እና በሚጠጡ ነገሮች ላይ ከሌላው ጊዜ የተሻለ ነገር ማድረግ ማለት ነው። አላህ ያግራልን! http://t.me/fiqshafiyamh
Hammasini ko'rsatish...
لَقَدْ مَنَّ اللَّهُ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا مِن قَبْلُ لَفِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣ የሚጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡ (አል- ኢምራን 164) አላህ ሀቢቡና ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ልኮ ከፅልመት ወደ ብርሃን አመጣን ካለመኖር ወደ መኖር አሸጋገረን። اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد.
Hammasini ko'rsatish...
❤ 1
የሒጅራው ጉዞ የሚገርም ነው! የእምነት መንገድ እንዲህ ነው። አላህ የባረከው መንገድ ሁሉ የተቀደሰ ነው! ሒጅራ ቢነገር የማይጠገብ ድንቅ ጉዞ ነው! በቦታው የነበርኩ እስኪመስለኝ ድረስ ባነበብኩትና በሰማሁት ቁጥር ይነዝረኛል። ከዚህ ሁሉ ክስተት በኃላ የአላህ መልዕክተኛ እሳቸውን በመናፈቅ ቁባ ላይ ሆነው የሚጠብቋቸውን ሙሐጂሮችና አንሳሮች ተቀላቀሉ። አዲስ ማህበረሰብ! አዲስ ሐይል! ውብ ታሪክ'ን ሊፅፉ ወደ መዲና ዘለቁ! 🥰 የዛሒድ ኢቅባል'ን ግጥም እዚህ ጋር ልዋስ 😊 ሰይዲ ﷺ ሲያሰሙ ዳዕዋቸው ልዝብ ነው ጣፋጩ ቃላቸው እንደ ማር ወለላ ይፈልቃል፤ ሰውታቸው በድን ቀልብ ያነቃል። ምክራቸው ጥሜትን ይነጥቃል፤ ዋዕዛቸው ለሹመት ያበቃል። ምክራቸው ፅልመትን አበራው። ሰምቶ ነው ምዕመኑ የተግራራው፤ ምግባሩን በአደብ የገራው። የትውልድ ክፋት የነበረ፤ ጭቆና ቀንበር ተሰበረ። ባሪያውም ከሰው ተቆጠረ፣ ወንድሜ መባል ተጀመረ፣ የፍቅር መሰረት ተኖረ። የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ መልዕክተኛችንﷺ ላይ ይውረድ! ♥️🥰 #هجرة_النبي_الى_المدينة Nadia
Hammasini ko'rsatish...
#ታላቁ_የኢማን_መንገድ ♥️ #ከኡሙ_ማዕበድ_ጋር ✨ ...፮ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከሳሂባቸው አባበክር እና ከሁለቱ መንገድ ጠቋሚያቸው ጋር ሆነው ወደ ቤቱ ዘልቀው የሚበላ ካለ ጠየቁ። ኡሙ ማዕበድ ያሉበትን ከባድ ሁኔታ አስረዳቻቸው! በጣም ከሲታ፤ ወተት የማታወጣ ፍየል ብቻ እንዳለቻቸው ነገረቻቸው። ውዱ ነብያችን ﷺ አምጪያት ብለው ቢስሚላህ ብለው አለብዋት። ወዲያውም ብዛት ያለው ወተትን ሰጠች። የወተት ማጠራቀሚያውን ይሞላ ጀመር! ሁሉም እስኪጠግቡ ጠጡ! የዚህን ጊዜ ኡሙ ማዕበድ "እናንተ ግን ማናችሁ? ስማችሁ ማነው" ብላ ጠየቀች! ረሱለላህ'ም ﷺ "አብዱላህ: የአላህ ባሪያ" አልዋት። ከዛም አመስግነዋት ከድንኳኗ ወጥተው ጉዟቸውን ቀጠሉ! ከዚህ ሁሉ አስደናቂ ክስተት በኃላ ባልዋ አቡ ማዕበድ መጣ! ቤቱ ውስጥ የሞላውን ወተት ሲመለከት በአግራሞት ጠየቀ። ምን ተፈጥሮ ነው ሲላት እንዲህ አለች: አንድ የተባረከ መልካም ሰው በድንኳናችን አልፎ ነበር ብላ ሁኔታውን ተናገረች! ባልዋም እስኪ ስለሱ ግለጪልኝ አላት። ኡሙ ማዕበድ'ም በሲራ ውስጥ ልናገኝ ከምንችለው ሁሉ የበለጠ እጅግ ውብ የሆነ ገለፃዋን ጀመረች! ♥️ አለችም: رأيت رجلا ظاهر الوضاءة, حسن الخلق, مليح الوجه .... «ንፅሕናው እና ጥራቱ ጉልህ የሆነ ሰው ተመለከትኩ! ፊቱ ያበራል። ከፍጥረቱ ሁሉ ውብ ነው። ወደፊት ወጣ ያለ ሆድ የለውም፤ አነስ ያለ ጭንቅላትም አልነበረውም። ቆንጆ ነበር! የተሟላ የተስተካከለ ፊት አለው። አይኖቹ በጣም ጥልቅ እና ሰፊ ናቸው! ሽፋሽፍቶቹ ረጅም ናቸው! ድምፁ የተረጋጋ እና ጥርት ያለ ነበር። የአይኖቹ ነጮች በጣም የነጡ፤ ጥቁሩም በጣም ጥቁር ነበር ። ቅንድቦቹ ጥቅጥቅ ያሉ፤ ሊጋጠሙ የደረሱ ግን ያልተጋጠሙ ነበሩ። አንገታቸው ረጅም፤ ፀጉራቸውም በጣም ጥቁር ነበር! إذا صمت فعليه الوقار, وإذا تكلم سما وعلاه البهاء. .... ዝም ሲል የክብር መንፈስ ይከበዋል፤ ሲናገር ደግሞ ብርሃን ከውስጡ የሚወጣ ይመስላል። ንግግሩ ቆንጆ እና ጣፋጭ ነው። አጭር አልነበረም፤ ረጅምም አልነበረም! ይልቁኑ ንግግሩ ልክ ሀብል ላይ እንዳለ ጨሌ የተደረደረ ነበር ። 🥰 أجمل الناس وأبهاهم من بعيد, وأحسنه وأحلاه من قريب. .... ከሩቅ ሲመለከቱት በጣም ውብ እና የሚማርክ ሰው ነው። ሲቀርቡት የበለጠ ውብ እና የሚማርክ ነው። ቁመቱ ለአይን አያስቸግርም። ከሁሉም(ከሶስቱ ሰዎች) የሚያበራው እና ላቅ ያለ ክብር የሚሰጠው እሱ ነው! ባልደረቦቹ ከበውት ይቀመጣሉ! إن قال استمعوا لقوله, وإن أمر تبادروا إلى أمره .... ሲናገር ሁሉም በትኩረት ያዳምጣሉ፤ ሲያዛቸው ደግሞ ትዕዛዙን ለመቀበል ፈጣን ናቸው። ከሱ በፊትም ሆነ በኃላ እንደሱ አይነት ሰው አላየሁም!» ... በማለት ውብ የሆነውን ገለፃዋን አሰፈረች! 🥹♥️♥️ አጂብብብብ... ከውዱ መልዕክተኛ ﷺ ጋር የነበራት የትንሽ ጊዜ ቆይታ ይህንን አስባላት! ከቶ እንዴት አድርጎ ቢኸልቃቸው ነው? 🥹 ባልዋ'ም : "ወላሂ ይህ ሰው የቁረይሽ ህዝብ እያወራለት ያለው ሰው ነው! እኔም ብቀላቀለው ደስ ይለኛል!" አለ ረሱሊ ﷺ ከኡሙ ማዕበድ ቤት ወጥተው ወደ መዲና ጉዟቸውን በመቀጠል ላይ እያሉ መካ ላይ ከየት እና ማን እንዳለው የማይታወቅ አንድ ድምፅ ይሰማል! በግጥም መልክ ነበር የተወራው። የመካ ሰዎች ከውስጣቸው ባወጡት ትልቅ ሰው ማዘን እንዳለባቸው የሚያሳይ እና ለማረጋገጥ ኡሙ ማዕበድ'ን እና ከሳሳው ፍየልዋን ቢጠይቁ ለሙሐመድ ﷺ እንደሚመሰክሩ የሚያሳይ ውብ ግጥም ነበር የተሰማው! **** جزى الله رب الناس خير جزائه * رفيقين حلا خيمتي أم معبد هما نزلا بالبر وارتحلا به * فأفلح من أمسى رفيق محمد فيال قصي ما زوى الله عنكم * به من فعال لا تجازى وسؤدد سلوا أختكم عن شاتها وإنائها * فإنكموا إن تسألوا الشاة تشهد دعاها بشاة حائل فتحلبت * له بصريح ضرة الشاة مزبد فغادره رهنا لديها لحالب * يدر لها في مصدر ثم مورد **** ከቆይታ በኃላ ኡሙ ማዕበድ እና ባልዋ ረሱለላህ'ን ﷺ መዲና ላይ ሄደው እንደተቀበሉ ይነገራል። ኢብኑ ሐጀር አንድ ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: "ረሱለላህ ﷺ ቢስሚላህ ብለው ወተቱን ያወጡላት ፍየል ምን ተፈጠረባት ልትሉ ትችላላችሁ! በሐቢቢ ﷺ እጅ የተባረከችው ፍየል የራማዳ አመት ላይ ማለትም (ሂጅራ ካደረጉ ከአስራ ስምንት አመት በኃላ) እስክትደርስ እና እስክትሞት ድረስ ወተት እየሰጠች ነበር በማለት ይናገራሉ! ሱብሃነላህ! ♥️... ረሱሊ'ኮ ﷺ እርሶ የነኩት ነገር ሁሉ እኮ መድሐኒት ነው። በረካ ነው! አልሃምዱሊላህ ያንቱ ላደረገን! 🥰 የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በሒጅራ ጉዟቸው ላይ ብዙ የሚገርሙ ክስተቶችን አይተዋል፤ አስተናግደዋል። ከኡሙ ማዕበድ ቤት ከወጡ በኃላ ወደ መዲና መቅረብ ጀመሩ! መሽቷል፤ ደክሟቸዋል። በዚህም ወቅት 70 ሰዎችን የያዘ ጎሳ ያረፈበትን ድንኳን ይመለከታሉ። የጎሳው መሪ የሆነው ቡረይዳ ኢብን አል ሁሰይብ በዛ ማታ ወደ ድንኳናቸው የሚመጡትን ሰዎች ማንነታቸው ለማረጋገጥ ወደ ረሱለላህ ﷺ መጓዝ ጀመረ! ሸፊዒ ﷺ ጋር ሲደርስ ግን እሱ ሳይጠይቃቸው አስቀድመው "ማን ነህ አንተ?" ብለው ጠየቁት! እሱም "ቡረይዳ" እባላለሁ አላቸው። ረሱሉ'ም ﷺ ወደ አባበክር ዞረው እንዲህ አሉ: "ያ አባበክር! በረደ አምሩና: አባበክር ሆይ! አሁን ጉዳያችን ቀዘቀዘ!" አሉት። ቡረይዳ የሚለውን ስም በመጠቀም በሁኔታው የተፈጠረውን ግራ የመጋባት ስሜት ለማብረድ ተጠቀሙት። ያ ረሱለላህ! ከቶ እንዴት አድርጎ ቢኸልቆት ነው ወዱዱ?! 🥹♥️ የዚህን ጊዜ ተራው የቡረይዳ ነበርና ማንነታቸውን ይጠይቃቸዋል። ... የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የመካ ስደተኛ እንደመሆናቸው እና ሙሽሪኮች እየፈለግዋቸው እንደመሆኑ እራሳቸውን ለመግለፅ ቅንጣት አልፈሩም፤ አላንገራገሩም'ም! "ሙሐመድ ኢብኑ አብዱላህ አላህ የላከኝ መልዕክተኛ ነኝ!" አሉት። ለኡሙ ማዕበድ ማንነታቸውን ሳይገልፁ የወጡት ነብይ ለቡረይዳ ገለፁለት። ስለ እስልምናም ሰበኩት! በእንደዚህ ሁኔታ ላይ ሆነውም ዳዕዋ ከማድረግ ወደኃላ አላሉም። የኔ ነብይ ﷺ 😍♥️ ቡረይዳ ወዲያውኑ እስልምናን ተቀበለ። ሰባ የሚሆኑት ተከታዬቹም አብረውት ሰለሙ። በቅፅበቶች ውስጥ ሰሐባዎች ሆኑ። በሒጅራው ጉዞ ላይ ጓደኛቸው አባበክር እና ሁለቱ መንገድ ጠቋሚያቸውን በሚገርም ክስተት ቡረይዳ እና ሰዎቹ ተቀላቀልዋቸው። መዲና መግቢያ ላይ እስኪደርሱ ከበረካቸው እየተቋደሱ አብረዋቸው ተጓዙ። ቡረይዳ እና ሰዎቹ በሰአቱ መዲና መግባት ስለማይችሉ ቡረይዳ ጥምጣሙን አውልቆ ለሸፊዒ ﷺ ሰጣቸው! በቅርቡ እንደሚቀላቀልዋቸው ቃል ገብተውላቸው ተለያዩ። ♥️ ከዛም ከኡሁድ በኃላ እንደተቀላቀልዋቸው ይነገራል። የረሱለላህ ﷺ ታማኝ ሰላይ እንደሆነ እና የፈትህ መካ ጊዜ እንደ ጦልሓ ጦሩን ፊት ለፊት በመምራት ባንዲራዎቹን ይዘው ወደ መካ ከገቡት መካከል እንደሆነም ይነገራል። ሱብሃነላህ
Hammasini ko'rsatish...
በኢስላማዊው አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ይባላል ። ወሩ ሙሐረም መሆኑን እንኳን ሳላስተውል 3ኛው ቀን ላይ ደረስን። ከረመዷን ቀጥሎ ምርጡ ወር ሙሐረም መሆኑን እንተዋወስ። ሙሐረም ከአራቱ የተከበሩ ወራት ከሚባሉት መካከል አንዱ ነው። አላህ ክብርና ልቅና በሠጣቸው ወራትም ሆነ ጊዜያት ውስጥ መልካም መሥራት አላህ ዘንድ የሚወደድ ነው። የሙሐረምን ዘጠነኛዉን እና አሥረኛውን ቀን መፆምን ዛሬውኑ እንተዋወስ። አሥረኛው ቀን ዓሹራእ ይባላል ። አላህ ሱ. ወ ነቢዩ ሙሳን ዐ.ሰ. ከአምባገነኑ ፊርዐውን ያዳነበት ቀን። Abx
Hammasini ko'rsatish...
Repost from ABX
ዕውቀት ዲን ነው፣ ዐቂዳ ነው፣ አቋም ነው፣ አመለካከት ነው፣ ሕይወትም ሞትም ነው ። ስለዚህ ዕውቀትን ከማን እንደምትወስዱ ምረጡ። https://t.me/MuhammedSeidAbx
Hammasini ko'rsatish...
ABX

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

የነብያችን ሙሃመድ (ሰዐወ) የሂወት ታሪክ አጠር ብሎ ተሰናድቶላችኋል ገብታችሁ ከክፍል አንድ ጀምራችሁ ማዳመጥ ትችላላችሁ።
Hammasini ko'rsatish...
Repost from Fuad kheyredin
የተሸፈነ ነገር አይገለጥም። በተለይ አንድ ባርያ በርሱና በጌታው መካከል ስላጠፋው ጥፋት ለሰዎች እንዲታያቸው የምንገልጠው መጋረጃ አይኖርም። ደብቀንለት ለመምከር ካልሆነ በቀር ጌታው ጋር ይጨርስ ዘንድ መተው የደጋጎች መገለጫ ነው። ሁሉም ሰው ከራሱ ጋር እንኳን የሚተፋፈርበት መጥፎ ጎን ይኖረዋል። ለራሳችን እንኳን ደግመን ለመንገር የሚቀፈን ስንት ኃጥያት አለን? በቃ ሰዎች አክብረውን እንኳ ጥሩ ጎናቸውን ካሳዩን ይበቃናል። የጥፋት መዝገባቸውን ሙሉ ለሙሉ ብናውቅ እንኳን ከጌታቸው ዘንድ ያወሩ ዘንድ እድል እንሰጣለን እንጂ ለሰው ምላስ አሳልፈን አንሰጥም። እየተሸፋፈንን የምንመካከርበት ሜዳ ናት… ዱንያ። @fuadkheyr @fuadkheyr
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.