cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ko'proq ko'rsatish
Advertising posts
130 132Obunachilar
-71724 soatlar
+987 kunlar
+95030 kunlar
Postni joylashtirish vaqti tarqalishi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrlar tahlili
PostlarKo'rishlarUlashishlarKo'rishlar dinamikasi
01
የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53 በመቶ ድርሻ መያዙ ጥናት አመላከተ! የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ" እንዲሆን እያደረገው እንደሚገኝ ገልጿል።ማህበሩ በዚሁ ጥናቱ በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉን አስታዉቀዋል። እነዚሁ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸዉ በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።እንደ ጥናቱ ከሆነ በአለም አቀፍ ደረዳ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው እና እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ ርካሽ ልብሶች መሞላታቸዉን በጥናቱ ተመላክቷል።የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገብ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንግድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል። @YeneTube @FikerAssefa
7 84531Loading...
02
አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች! የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
10 81215Loading...
03
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
9 7242Loading...
04

10Loading...
05
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia! Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter. #EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia #DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia #EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
10 2902Loading...
06
የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተነገረ! የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነ ተሰምቷል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦን ላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ብለዋል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኛች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል። @YeneTube @FikerAssefa
12 21441Loading...
07

12 6749Loading...
08
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር። የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል። @YeneTube @FikerAssefa
15 25910Loading...
09
በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ! የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል።ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል።ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው። [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
14 5553Loading...
10
ዐቃቤ ሕግ የሽብር ተከሳሾችን ክስ እንዲያሻሽል በተሰጠው ብይን ላይ አቤቱታ አቀረበ! ዐቃቤ ሕግ፣ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን የእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ዛሬ ኀሙስ በሰጠው ብይን ላይ፣ “ምስክሮቼን ያጋልጥብኛል” በማለት አቤቱታ አቅርቧል፤ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ክሱ ካልተሸሻለ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡በተከሳሶቹ የወንጀል ድርጊት “ተገድለዋል” የተባሉ ሰዎች፣ በክሱ ላይ በስም እንዲጠቀሱ ብይን ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፣ በዛሬው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ በእነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐቃቤ ሕግ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ዛሬ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ችሎት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት የተቀጠረው፣ ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት በታዘዘው መሠረት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ለመመልከት ነበር፡፡ የዐቃቤ ሕግ ክስ፣ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት የሽብር ወንጀል፣ የ217 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መጎዳታቸውንና ከፍተኛ ንብረትም መውደሙን ሲያስረዳ፣ በተከሳሽ ጠበቆች ጥያቄ መሠረት፣ ሟቾቹ በስም ተጠቅሰው፣ ሌሎች ጉዳቶችም በዝርዝር ተገልጸው ክሱ እንዲሻሻል፣ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ኅዳር 12 ቀን በይኖ ነበር፡፡ ኾኖም፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ክሱ እንዲሻሻል የተሰጠው ብይን እንዲሻር በደብዳቤ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ለዚኽም በምክንያትነት ያቀረበው፣ እንደ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሟቾቹን ስም መጥቀስ “ምስክሮቹን ለጉዳት የሚዳርግ ነው፤” የሚል እንደኾነ፣ ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡ጠበቆች በበኩላቸው፣ ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ቤቱን ብያኔ አክብሮ ክሱን የማያሻሽል ከኾነ ክሱ እንዲነሣ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ፣ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለግንቦት 12 ቀን መቅጠሩን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ አመልክተዋል፡፡ በክስ መዝገቡ ላይ ከተጠቀሱ 51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎችን ጨምሮ 23ቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ለሕክምና እንደወጡ ማምለጣቸውን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ተወካዮች ከዚኽ ቀደም ለፍርድ ቤት ማሳወቃቸውን ጠበቆቹ ገልጸዋል፡፡ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾችን፣ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ውጤቱ ለቀጣዩ ችሎት እንዲቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ Via VoA @YeneTube @FikerAssefa
14 0526Loading...
11
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
13 5205Loading...
12
ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ለ 122 ሺህ አርሶአደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድህን ካሳ ሊከፍል መሆኑ ተገለፀ! በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ፣ በአለም ምግብ ፕሮግራም እና በፑላ አድቫይዘር ጥምረት ተጀምሯል የተባለውና በሀገሪቱ ትልቁ ነዉ የተባለው የሰብል መድህን ፕሮግራም የክፍ ስርአት መተግበር መጀመሩ ተነግሯል። በኢትዮጵያ የሰብል መድህን ታሪክ ዉስጥ ትልቁ መሆኑ በተነገረለት ፕሮግራም የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የመድህን ሰጪ እና የካሳ ከፋይ ተቋም በመሆን ለትግበራዉ 39 ሚሊዮን ብር መመደብ ካፒታል ሰምቷል። የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ በተገለጸው ቢዚህ ስርዓት በአማራ ክልል የሚገኙ አነስተኛ አርሶአደሮች ተጠቃሚ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ለ 7.5 ሚሊዮን አርሶአደሮች ተደራሽ ይደረጋል ተብሏል። [Capital] @YeneTube @FikerAssefa
14 9073Loading...
13
አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው! በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡ አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። @YeneTube @FikerAssefa
14 3512Loading...
14
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። Via Addis Maleda #ዳጉ_ጆርናል
10Loading...
15
የሰሊጥ ግብይት በሱዳንና በኢትዮጵያ የግጭት መነሻ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ! የሰሊጥ ምርት እና ግብይት፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል፣ እንዲሁም በሁለቱም አገሮች የውስጥ አወዛጋቢ ጉዳዮች ዙሪያ የግጭት መንሥኤ እየሆነ እንደሚገኝ፣ አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ አመለከተ፡፡ “The ‘conflict economy’ of sesame in Ethiopia and the Sudan” በሚል ርእስ የወጣውን ጥናት ከአዘጋጁት ሁለት ምሁራን አንዱ ዶ/ር አቤል አባተ ደምሴ፣ “የሰሊጥ ግብይት በሱዳንና በኢትዮጵያ የውስጥ እና የውጭ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል፤” ይላሉ፡፡ ዶ/ር አቤል፣ ላለፉት አራት ዓመታት፣ በለንደን በሚገኘው ዓለም አቀፍ የፖሊሲ ተቋም(ቻተም ሃውስ) የሮያል ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም የምርምር ባልደረባ ሆነው በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ምሁሩ በጥናታቸው ላይ እንዳመለከቱት፥ የመንግሥት ኀይሎች፣ የአካባቢ ልሂቃንና ሚሊሻዎች በሰሊጥ ምርት እና ንግድ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እየተፎካከሩ ናቸው፡፡ ፖሊሲ አውጪዎች፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ትስስር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የግብርና ለውጦችን በማስተካከል ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት፣ መሠረታዊ እና ተለዋዋጭ ፖሊሲዎችን መቅረጽ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ ፖሊሲ አውጭዎቹ መደበኛ ያልሆነ የንግድ ልውውጥን እንዲደግፉና ከታች ወደ ላይ ለአካባቢያዊ አብሮ መኖርና ትብብር ኹኔታዎችን እንዲያመቻቹ ጥናቱ ምክረ ሐሳብ ማቅረቡን ከአዘጋጆቹ አንዱ ዶ/ር አቤል አባተ ተናግረዋል፡፡ https://www.chathamhouse.org/2024/04/conflict-economy-sesame-ethiopia-and-sudan [VoA] @YeneTube @FikerAssefa
15 2428Loading...
16
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተገለጸ! ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል። እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። [Addis Maleda] @YeneTube @FikerAssefa
13 85112Loading...
17
በ59 ሃገራት የሚገኙ ከ282 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን የመንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመለከተ። የዓለማቀፉ ድርጅት ሪፖርት እንዳለው በአስከፊ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የጋዛ ሰርጥ በርካታ ቁጥር ያለው ተጋላጮችን በመያዝ ትመራለች። ከጎርጎርሳውያኑ 2022 ወዲህ 24 ሚሊዮን ተጨማሪ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት እና ለረሃብ መጋለጣቸውን ያመለከተው መረጃው ከጋዛ ጦርነት በተጨማሪ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ሚሊዮኖች እርዳታ ጠባቂ አልያም በረሃብ አፋፍ ላይ ያሉ ናቸው ብሏል። በየዓለም የምግብ እርሻ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሳየው በአምስት ሃገራት ውስጥ የሚገኙ እና ቁጥራቸው ከ705 ሺ በላይ የሆኑ ሰዎች ደረጃ አምስት ወይም ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶውን ቁጥር የሚሸፍነው በጋዛው ጦርነት አስከፊውን ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ፍልስጥኤማውያን ናቸው።ደቡብ ሱዳን ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሶማሊያ እና ማሊ እያንዳንዳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች እና ስደተኞች በመያዝ ይከተላሉ።በሀገራቱ እና በአካባቢያቸው እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች እስካልቆሙ ድረስ ችግሩ እየከፋ ሊሄድ እንደሚችል ዓለማቀፉ ድርጅት አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ በያዝነው የጎርጎርሳውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ኤል ኒኖ ያስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ወቅት እንደነበር ያስታወሰው ድርጅቱ የጎርፍ መጥለቅለቅን ጨምሮ በአንዳንድ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የዝናብ እጥረትን በማስከተል ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ እንዳያደርገው ያሰጋኛል ብሏል።መንግስታት እና ለጋሾች በረሃብ ምክንያት «የጅምላ የሰውን ልጅ ውድቀት ለመታደግ» ርብርብ እንዲደረግ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ጥሪ አቅርበዋል። [DW] @YeneTube @FikerAssefa
14 9771Loading...
18
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
10 8677Loading...
19
ኢትዮ ቴሌኮም የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ! ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በዛሬው ዕለት አስጀመረ፡፡በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት መታቀዱ ተመላክቷል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ተዓማኒነት ያለው የማንነት መለያ ዲጂታል መታወቂያ ነው ብለዋል።ዲጂታል መታወቂያ አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ዜጎች በኢኮኖሚው ዕኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባው አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች ዛሬ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፥ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ ይችላሉ መባሉን ፋና ዘግቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
16 63625Loading...
20
“በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰብአዊ መብት አያያዙ እንደከፋ ነው” - ዩኤስ የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተመለከተ የሚያወጣውን ዓመታዊ ሪፖርት በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ትላንት ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም ባወጣው የሃገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በሚተነትነው ሰፊ የአውሮፓያኑ የ2023 ዓመታዊ ሪፖርቱ፤ ፣የኢትዮጵያ መንግሥት ወይም የመንግሥት ወኪሎች፣ ከሕግ ውጪ የዘፈቀደ ግድያ መፈፀማቸውን፣ በርካታ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገራት የሰብአዊ መብት ቡድኖች ሪፖርት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።ግድያዎቹ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች እንዲሁም ትግራይን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ እንደሆነ አስታውቋል። የክልል ፖሊስ አባላትም ፣ ከመጠን ያለፈ እና ሕይወት የቀጠፈ ኃይል መጠቀማቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ለማሳያም፣ “በየካቲት ወር በወልቂጤ ከተማ የውሃ አገልግሎት እንዲመለስ በሰልፍ ለመጠየቅ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በተወሰደው ርምጃ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ 30 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ብሏል። በሌሎችም አካባባዎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ያካተተው ሪፖርት፣ የፌዴራሉ ፖሊስ ምርመራ ቢሮ በፖሊስ ኃይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ የሚያደርጋቸው ምርመራዎች ውስን መሆናቸውን እና የሚሰጠውን ቅጣት በተመለከተም በሚስጥር እንደሚይዝ ጠቁሟል።በግዳጅ መሰወርን አስመልክቶም፣ መንግሥትን የሚነቅፉ የፖለቲካ አስተያየት የሚሰጡ ግለሰቦች፣ የቀድሞ ጦር አባላት፣ የምርመራ ጋዜጠኞች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች መሰወራቸውን አትቷል። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://amharic.voanews.com/a/7582081.html @YeneTube @FikerAssefa
17 0206Loading...
21
"የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተላለፈ ያለው መልዕክት ሀሰተኛ ነው" :- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት አወጣ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲተላለፍ የነበረው "የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" የተመለከተ ደብዳቤ በሐሰት የተቀናበረ መሆኑን የአማራ ክልል አስታውቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ ከመስሪያ ቤታቸው የወጣ አለመሆኑን እና የተቀነባበረ መሆኑን ገልጸዋል። ክልሉ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሚሊሻ ኃይሉን የማጠናከር ስራን እየሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊው፤ የርዕሰ መስተዳድሩን ጽ/ቤት የደብዳቤው ይዘትም ሆነ ቅርጽ ሀሰተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
16 2055Loading...
22
የአሜሪካ ሴኔት ቲክቶክን በአገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ! የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በአገሪቱ ቲክቶክን ሊያግድ የሚችል አወዛጋቢ አዋጅን አጽደቀ።አዋጁ የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ የማህበራዊ ትስስር ገጹን ድርሻ በ9 ወር ውስጥ የማይሸጥ ከሆነ ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ ያግዳል።አዋጁ ወደ ፕሬዝዳንት ባይደን የተመራ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አዋጁ ኋይት ሃውስ እንደደረሰ ፊርማቸውን አኑረውበት ሕግ እንደሚያደርጉት ተናግረው ነበር። ባይትዳንስ ለዚህ ውሳኔ ፈጣን መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ለቢቢሲ ተናግሯል።ቀደም ብሎ ግን ቲክቶክ በጫና ለማሸጥ የሚደረግ ሙከራን አጥብቆ እንደሚቃወም ተቋሙ ገልጿል።አሜሪካ ቲክቶክን እንዲሸጥ ባይትዳንሳ ላይ ጫና አድረጋ ቢሳከላት እንኳን ለሽያጩ ሂደት የቤጂንግ ባለስልጣናት ይሁንታ ያስፈልጋል።ሆኖም ቻይና ይህንን አይነቱን ውሳኔ እንደምትቃወም ገልጻለች። ተንታኞች ይህ ሂደት ዓመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ይገልጻሉ።ይህን አዋጅ ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት አብለጫዎቹ ደግፈውታል።79 የምክር ቤት አባላት ሲደግፉት 18 የሚሆኑት ደግሞ ተቃውመውታል። የምክር ቤት እውቅ የሪፐብሊካን እና የደህንነት ኮሚቴ አባል የሆኑት ማርኮ ሩቢዮ “ለአመታት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በአሜሪካ ዝነኛ የሆነውን መተግበሪያ እንዲቆጣጠረው ፈቅደናል። ይህ ሁኔታ በአደገኛ ሁኔታ የቅርቡን ብቻ የተመለከተ ነው” ብለዋል።ጨምረውም አዲሱ አዋጅ ቻይናውያን ባለቤቶቹ መተግበሪያውን እንዲሸጡ የሚጠይቅ እንደሆነ ጠቅሰው ለአሜሪካ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
14 6154Loading...
23
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
15 57410Loading...
24
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በፀጥታ ሀይሎች ተያዘ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በዛሬው እለት አመሻሹን ሚያዚያ 15ቀን 2016ዓ.ም ወደ እስራኤል ሊያቀና በነበረበት ወቅት ላይ በፀጥታ ሀይሎች መያዙን የአርቲስቱ የቅርብ ምንጮች ገልፀዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጅ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ያያ ዘልደታ" ጉዳዩን አስመልክቶ ተከታዩን አስፍሯል። " ዛሬ ከመሽ ዕብደት በሕብረት የተሰኘውን አዲሱን ትያትር ለማሳየት ወደ ሃገረ እስራኤል ለመሄድ ዝግጅቱን ጨርሶ እነሆ አሁን ከመሸ ከኤርፖርት ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዷል::" ሲል አስታውቋል። እስከ አሁን ባለው ሂደት ከመንግስት አካላት ስለ ጉዳዩ የተሰጠ ምላሽም ሆነ ማብራሪያ የለም። ዳጉ_ጆርናል @Yenetube @Fikerassefa
8 4110Loading...
25
⚽️ እድል SPORT 🎮 በጽሑፍ ቀጥታ የጨዋታ ስርጭት 🚨 የዝውውር ዜናዎች 📊 ስታትሰቲክስ 🧐 ትንተና 🔍 የእግር ኳሱ ዓለም እንዴት ሰነበተ? ማን ምርጥ ጨዋታን አሳለፈ? የላቀ የጨዋታ እቅድ ማን ይዞ ገባ? 📌 ለመሳሰሉ ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት ቻናል https://t.me/edilsport
16 1761Loading...
26
ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል። አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል። ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል። "ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።
16 7947Loading...
27
🇪🇹 ውድ ኢትዮጲያውያን አሜሪካ ሀገር የሚገኝ ዪኒቨርስቲ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ነፃ የትምህርት እድል ለአፍሪካውያን አቅርቧል፣ የዚህ እድል ተካፋይ ሁኑ ወይም ለእህት/ወንድም/ጓደኛ ላኩላቸው እና እድላቸውን ይሞክሩ፣ Application የሚያበቃው ሚያዚያ 28 ነው ፈጥነው ይመዝገቡ __________ 🇺🇸 Are you passionate about Artificial Intelligence and Business? Do you want to become an Al leader and tackle global challenges? Arizona State University , in partnership with the Mastercard Foundation, is offering 5 scholarships for the 2024/2025 academic year! These scholarships will cover: - Full tuition fees - Accommodation expenses - Comprehensive support - Visa application costs - English language test costs - Airfare to and from Phoenix, Arizona - Participation in Scholarship programming To be eligible, you must: - Be a citizen of an African country - Be between 18 and 33 years old -Demonstrate leadership, academic excellence, and community engagement - Have earned an undergraduate degree with a minimum 4 years of study - Not have started or completed another graduate or master's degree before August 2024 - Be able to live in Phoenix, Arizona for the duration of the program Apply here: https://lnkd.in/eFbEMfQt Official Link: https://asu.co1.qualtrics.com/jfe/form/SV_07WFFri1Y0P5LWm Women, refugees, displaced persons, and people with disabilities are strongly encouraged to apply! #scholarship #africa #ethiopia #free #ethiopia
15 724325Loading...
28
Media files
13 23240Loading...
29
በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ በአማራ ክልል ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ። ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ ም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መንስኤው እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በፓርኩ የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ነው የተገለጸው። እሳቱ በአካባቢው ሕዝብ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሣ በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች መያዛቸውን አመልክተዋል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሕግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ጉዳዩ የሚጣራ መሆኑን፤ ቃጠሎው ያደረሰው የጉዳት መጠንም ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግም ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኝበት አካባቢ ሦስት ዓይነት የአየር ጠባይ እንዳለና በየዓመቱም ተመሳሳይ የእሳት አደጋ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንደሚከሰት ነው ባለሥልጣኑ የገለጹት። ከቀናት በፊት የተነሳው እሳት በፓርኩ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደነበር በማመልከትም ፓርኩ ጓሳ እንደመሆኑ የተዳፈነ እሳት ንፋስ አቀጣጥሎት እንዳይነሳ ክትትል የማድረግ ጥረት መኖሩንም ተናግረዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር በ1978 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል። Via:- ዳጉ ጆርናል @Yenetube @Fikerassefa
14 7832Loading...
30
Media files
12 7463Loading...
31
ከጅቡቲ የባሕር ወደብ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ሰጥማ በደረሰው አደጋ 16 ተሰዳጆች መሞታቸው ተገለጸ። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት IOM ዛሬ እንዳስታወቀው 28ቱ የጀልባዋ ተሳፋሪዎች እስካሁን አልተገኙም። ጀልባዋ 77 ተሰዳጆችን አሳፍራ እንደነበር ነው IOM በኤክስ ገጹ ይፋ ባደረገው አጭር መረጃ ያመለከተው።ከተሳፋሪዎቹ ውስጥም ልጆች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። የጅቡቲ መንግሥት የአደጋ ጊዜ ሕይወት አድን ሠራተኞች ባሕር ላይ በደረሰው አደጋ የተጎዱትን ለማዳን ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል። እንዲህ ያለ አደጋ በተሰዳጆች ላይ በተጠቀሰው አካባቢ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሲደርስ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የዛሬ ሁለት ሳምንት በጅቡቲ የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ በደረሰው ተመሳሳይ የጀልባ አደጋ ልጆች ጨምሮ 38 ስተደኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በተያያዘ ዜና ከፈረንሳይዋ ካሌ ደሴት ወደ ብሪታንያ ለመሻገር ሲሞክሩ አምስት ስደተኞች ባሕር ላይ በደረሰ አደጋ መሞታቸው ተሰምቷል። ሟቾቹን ጨምሮ ከመቶ በላይ ስደተኞችን ጭና የነበረች መርከብ የገጠማትን አደጋ ተከትሎ የፈረንሳይ የባሕር ኃይል መርከቦች በስፍራው ደርሰው ተሳፋሪዎቹን ለማውጣት መቻላቸው ነው የተገለጸው። ተሰዳጆቹ ወደ ብሪታንያ ለመሻገር በሞከሩበት ምሽቱን የብሪታኒያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ሕገወጥ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማሻገር የሚያስችለውን ሕግ አጽድቋል። [DW] @YeneTube @FikerAssefa
13 0542Loading...
32
በኢትዮጵያ በግማሽ አመት ብቻ 1ሺህ 358 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው እንዳለፈ ተነገረ። በ2016 አመት በባለፊት ስድስት ወራቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት 1ሺህ 358 ዜጎች ለሞት መዳረጋቸው ተነግሯል።በደረሱ አደጋዎች ምክንያትም ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ንብረት እንደወደመ ነው የተገለጸው። ባለፉት 6 ወራት ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ህግ የተላለፉ ተሽከርካሪዎችን በመቅጣት ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡የመንገድ ደህንነትና መድህን ፍንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አባሶ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከልና ሕግ ተላልፈው የሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን የቅጣት ዕርምት ለመውስድ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሃላፊው አክለው እንደተናገሩት ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የመንገድ ደኀንነት ትምህርቶች በካሪኩለም ውስጥ ለማካተት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ እና የተሽከርካሪዎች ቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ተቋማት ያልተገቡ ማስረጃዎችን እንደሚሰጡ የገለፁት ሥራ አስፈጻሚው ተገቢውን ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለ ብለዋል። ለአደጋ አጋልጭ የሆኑ መንገዶች ተለይተው የማሻሻያ ሥራዎች መከናወናቸውና የሞተር አልባ ትራንስፖርትንም ለማስፋፋት በ13 ከተሞች የመንገድና መሰል መሰረተ ልማቶችን የማልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።ተደጋጋሚ ጥፋት የሚያጠፉ አሽከርካሪዎች ላይ መንጃ ፈቃድ እስከመንጠቅ የሚያደርስ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የገለጹት ሃላፊው አገልግሎቱ በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
14 1846Loading...
33
በኮሬ ዞን በቀጠለው ጥቃት አራት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ! በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ፣ አራት ወጣት አርሶ አደሮች፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በተነሱ ታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።በእርሻ ሥራ ላይ እንደነበሩ የተገለጹት አርሶ አደሮች የተገደሉት፣ “ኦነግ ሸኔ” ባሏቸው ታጣቂዎች እንደኾነ፣ የኮሬ ዞን የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆቦ ቀበሌ ትላንት ሚያዚያ 13 ተገደሉ ከተባሉ አራት ወጣት አርሶ አደሮች ውስጥ ሁለቱ የወንድማቸው ልጆች እንደኾኑ አቶ ምትኩ ሽብሩ በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ገልፀዋል። አራቱም የሁለት ቤተሰብ አባላት መኾናቸውን፣ የሟቾቹን ስም በመዘርዘር የገለፁት አቶ ምትኩ እርስ በርሳቸውም ዘመዳማቾች መኾናቸውን አክለዋል። ለጥቃቱ ጉጂ ዞን ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸውን ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደረጉት አቶ ምትኩ፣ ይህን የሚያስቆም ኃይል ባለመኖሩ ሕዝቡ ስጋት ላይ መውደቁን ገልፀዋል። አቶ አጋፋሪ መንገሻ የተባሉ የቆቦ ቀበሌ ነዋሪ የእርሻ ማሳቸውን አረም በሚያርሙበት እና ከብቶቻቸውን በሚጠብቁበት ወቅት እንደተገደሉ ተናግረዋል። አቶ አጋፋሪ ተዘርፈዋል የተባሉ ከብቶች እና ሌሎች ንብረቶች ወደ ገላን ወረዳ እንደተወሰዱባቸው ገልፀው ክስ አሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት የ13 ዓመት አዳጊ እና ሌላ አርሶ ከቆቦ ቀበሌ መገደላቸውን አቶ አጋፋሪ አስታውሰዋል። የኮሬ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ በግብርና ሥራቸው ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች የተገደሉት ሸኔ ሲሉ በጠሯቸው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መኾኑን ተናግረዋል።አቶ ተፈራ አክለው ካለፈው ሚያዚያ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሰባት አርሶ አደሮች ዳኖ ፣ መቅሬዲ እና ቆቦ ከተሰኙ ቀበሌዎች ያልታጠቁ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን አክለው ገልጸዋል:: ስለ ጉዳዩ ከአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረባ ነሞ ዳንዲ የተጠየቁት፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም፣ በዓለም አቀፍ ቃል አቀባዩ አቶ ኦዳ ተርቢ ክሱን አስተባብለዋል። ከምዕራብ ጉጂ ዞን ባለሥልጣናት አስተያየትና ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም::ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ የተጠየቁት የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ቀበሌዎቹ በሸማቂዎች በሚደርሰው ጥቃት የተነሳ ከቁጥጥር ውጭ መኾኑና ለኅብረተሰቡ መግሥታዊ አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ መናገራቸው ይታወሳል። Via VoA @YeneTube @FikerAssefa
15 2572Loading...
34
መልዕክት ወደ ክልል ከተሞች ይላኩ ይቀበሉ። #ፈጥን #ቀላል እና #አስተማማኝ ቁ.1 አዲስ አበባ ከጎላጎል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ኳሊቲ ህንፃ 0962627762 -ሀዋሳ 0988627762 - አርባምንጭ 0925636333 - ቦረና 0980526262 - አዳማ
15 6966Loading...
35
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከሦስት ቀናት በፊት የተነሳው እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል። ሚያዚያ 10፣ 2016 ዓ.ም. በስፍራው የተነሳው እሳት በቁጥጥር ሥር አለማዋሉን የክልሉ ባለሥልጣን ገለጹ።የክልሉ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አባይ መንግሥቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እሳቱ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና አመራሮች ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም። “የቦታው አቀማመጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ጠፋ ሲባል እንደገና እየተነሳ በቁጥጥር ሥር ማዋል አልተቻለም” ብለዋል።ሆኖም እሳቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ የአሰሳ እና የጥበቃ ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት ኃላፊው፣ እሳቱ ከቁጥጥር ውጪ አለመውጣቱን ተናግረዋል። በፓርኩ የእሳት አደጋ ሲከሰት ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ከአምስት ዓመታት በፊት በፓርኩ ከፍተኛ እሳት ተነስቶ ከክልሉ እና ከፌደራል አቅም በላይ ሆኖ የእስራኤል እና የኬንያ እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተርን ድጋፍ እስከ መጠየቅ ተደርሶ ነበር። @YeneTube @FikerAssefa
17 1576Loading...
36
በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት በሚል የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ዋዜማ ከተመለከተችው የጨረታው ሰነድ ተረድታለች። የሊዝ ጨረታው ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውጭ በተቀሩት የከተማው አስር ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ላይ ወጥቷል። የሊዝ ጨረታው ለአመታት ከተቋረጠ በኋላ ሲወጣ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።የጨረታው ሰነድም ከረቡዕ ሚያዝያ 9 2016 አ.ም ጀምሮ መሸጥ የተጀመረ ሲሆን ፣ የሰነድ ሽያጩ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ተነግሯል። Via Wazema @YeneTube @FikerAssefa
17 06947Loading...
37
የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ። የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በወረራ ይዟል:: ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደትላንቱ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ከሰርጎ ገቦች ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል:: ሕዝቡ ከክልሉ መንግሥት እና በየአካባቢው ከሚገኙ አስተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቹ የከፈቱበትን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ጥሪ ያደረገው:: የክልሉ መንግሥት ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ ለፌደራል መንግሥት እና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ አቅርቧል፤ ለፌደራል መንግሥት ባስተላለፈው ጥሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን በወረራ ከያዛቸው ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንዲወጣ እና ሕዝቡን ከጥፋት መታደግ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መታደግ እንደሚገባ ጠቁሟል:: ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ሕወሓት በክልሉ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝ እና ከክልሉ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል:: ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም @Yenetube @Fikerassefa
16 3708Loading...
38
የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ፡፡ በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአንዳንድ ሆቴሎች የሴት መስተንግዶ ሠራተኞች አለባበስ ከሀገሪቱ ባሕል ወጣ ያለ ነው። ይህን ለማስተካከል የሚረዳ የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲፀድቅ በመላኩ መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል ብለዋል። ለቱሪስቶች መስተንግዶ ሲሰጥ የሀገራችንን ባሕልና እሴት በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ያሉት ኃላፊዋ፤ በሆቴሎች ያለው የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ ሥነ-ሥርዓቱን የጠበቀ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። ሂሩት (ዶ/ር)እንዳመላከቱት፤ አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ። ድርጊቱ ከሴት ልጅ መብት አኳያ ክብርን ያልጠበቀ እና አሳፋሪ ነው ብለዋል። መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ያሉት ኃላፊዋ፤ ይህም የኢትዮጵያን ባሕልና ወግ ያልጠበቀ የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን ለመቆጣጠር እንደሚያስችል አስረድተዋል። አሁን ላይ በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታየውን ከባሕል ያፈነገጠ የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ መስተካከል እንዳለበት የከተማው ነዋሪዎች ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልጸው፤ መመሪያው ሲፀድቅ የሁሉንም ጥያቄ እንደሚመልስ አብራርተዋል። ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል ጠቁመዋል። የአለባበስ መመሪያውን ለማውጣት ቢሮው ሁለት ዓመት ሲሠራ መቆየቱን ተናግረው፤ ሕጉ ከፀደቀ በኋላ ወደ ርምጃ እንደሚገባ አመላክተዋል። ሕጉ እስኪፀድቅ የቁጥጥር ሥራ የሚሠራ ሲሆን በሚደረገው ክትትልና ድጋፍም አሁን ላይ ለውጦች መኖራቸውን ተናግረዋል። በቱሪዝም ዘርፉ ውድድር በዓለም አቀፍ ይዘት ያለው በመሆኑ ደረጃውን ያልጠበቀ መስተንግዶ የሚሰጥ ከሆነ ቱሪስቶች ተመልሰው እንደማይመጡ የሚገልጹት ሂሩት (ዶ/ር)፤ በሆቴሎች መልካም መስተንግዶ እንዲሰጥ ለማስቻል ቢሮው በየዓመቱ ሁለት ሺህ ለሚደርሱ በሥራ ላይ ላሉ መስተንግዶ ሰጪ ባለሙያዎች ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። በከተማዋ ያሉ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች የመስተንግዶ ባለሙያዎቻቸው አለባበስ ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመጠኑ ከሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች የፀጉር አያያዝ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የማይፈቀዱ ነገሮች በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታዩ በመሆኑ እንዲሻሻሉ ክትትል ይደረጋል ብለዋል። Via EPA @YeneTube @FikerAssefa
15 61010Loading...
39
የአሜሪካው ም/ቤት የ95 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ዕርዳታ አጸደቀ! በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት ለዩክሬን እና ለእስራኤል የሚሰጥን የ95 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ጥቅል ሕግ ከወራት ሙግት በኋላ ትናንት ቅዳሜ አጽድቋል።በኮንግረስ ያሉ መሪዎች ከቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂዎች የደረሰባቸውን ተቃውሞ ወደ ጎን በማለት፣ ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ቅዳሜ ዕለት በተገናኘው ም/ቤት ሕጉን እንዲጸድቅ አድርገዋል። አሁን የቀረው ሕጉን ወደ ሕግ አውጪው ሸንጎ ወይም ሴኔቱ መላክ ሲሆን፣ በዲሞክራቶቹ ቁጥጥር ስር ያለው ሴኔት እስከ ማክሰኞ ድረስ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል። ከፓርቲያቸው ከፍተኛ ግፊት ያላባቸው ሪፐብሊካኑ የም/ቤቱ አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን፣ ወንበራቸውን እንደሚያጡ በፓርቲያቸው አባላት ዛቻ እየደረሰባቸው ሲሆን፣ ሕጉን ለማጽደቅ በተደረገው እያንዳንዱ እርምጃ የዲሞክራቶቹን ዕገዛ አግኝተዋል ተብሏል። አራት ክፍሎች ያሉት ሕግ፣ ለዩክሬን፣ እስራኤል እና በኢንዶ ፓሲፊክ ለሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች ገንዘብ የሚመድብ ሲሆን፣ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ማኅበረሰብ ዘንድ ፈጥሯል የሚባለውንም ችግር የሚመለከት ነው።ሕጉ በም/ቤቱ የሚጸድቅ ከሆነ፣ በፊርማቸው እንደሚያጸኑት ፕሬዝደንት ባይደን ሲያስታውቁ ቆይተዋል። [VoA] @YeneTube @FikerAssefa
18 2360Loading...
የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53 በመቶ ድርሻ መያዙ ጥናት አመላከተ! የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ" እንዲሆን እያደረገው እንደሚገኝ ገልጿል።ማህበሩ በዚሁ ጥናቱ በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉን አስታዉቀዋል። እነዚሁ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸዉ በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።እንደ ጥናቱ ከሆነ በአለም አቀፍ ደረዳ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው እና እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ ርካሽ ልብሶች መሞላታቸዉን በጥናቱ ተመላክቷል።የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገብ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንግድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 38😁 37 3
አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች! የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 29😭 12 4😁 4
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች! የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia! Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter. #EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia #DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia #EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
Hammasini ko'rsatish...
👍 6 2
የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተነገረ! የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነ ተሰምቷል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦን ላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ብለዋል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኛች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 24 3
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia! Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter. #EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia #DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia #EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
Hammasini ko'rsatish...
👍 14👀 1
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር። የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 49 5🔥 4
በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ! የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል።ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል።ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው። [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 22 2👏 1

👍 16 4