cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
127 902
Obunachilar
-22424 soatlar
-2 5347 kunlar
-1 73230 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
በየአካባቢው የቁም እንስሳት ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉ ተገለጸ! በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ለትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል። በየአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማውን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም ቢሮው ባወጣው መረጃ አመላክቷል። የከተማው ነዋሪ በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገው ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን አሳስቧል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 52😁 29 5
ትላንት ማታ በአቃቂ የገበያ ማዕከል በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ 16 ሱቆች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል። ሚያዚያ 24 ቀን2016 ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 ንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጥለዋል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ ቦቴ ከ44 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፍቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷአል። በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ አንዱ ሲሆን በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል። ኮሚሽን መ/ቤቱ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ ዕርምጃዎች አልተወሰዱም።በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ እንዲሰጥ ኮሚሽኑ ያሳስባል። Via Ethio FM @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 15 4
Photo unavailableShow in Telegram
የ ‘ገበታ ለሀገር’ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ለስካላይት ኢትዮጵያ ሆቴል ተሰጠ! በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተከናወኑት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶች ከዛሬ ጀምሮ ለክልል መንግስታት ተላልፈው መሰጠታቸው ተገለጸ።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ ካደረገው መረጃ አዲስ ማለዳ እንደተመለከተችው ፕሮጀክቶቹ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ተሰጥተዋል። እንዲሁም በ'ገበታ ለሀገር' የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ኃላፊነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስር ለሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል እንዲወስድ ስምምነት መፈረሙ ተመላክቷል። በዚህም እስካሁን የተጠናቀቁት ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ በስካይላይት ሆቴል የሚተዳደሩ ይሆናል። የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል።ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠው ኃላፊነት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እና ለዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ስለሚፈጥር እንደሆነ ተመላክቷል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
26👍 22😁 9👎 1
‘’ የፕሬስ ነጻነት ቀን ስናከበር ጋዜጠኞች ለአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል‘’ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት የ2016 የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል፡፡ምክር ቤቱ በላከው መግለጫ የዘንድሮው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ‘’ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ” ወይም “Journalism in the face of the Environmental Crisis” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገፃል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ አማካይነት በየዓመቱ ሚያዝያ 25 ወይም ሜይ 3 የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም ዙሪያ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ሁኔታ ለመገምገም፣ መገናኛ ብዙሃን በነጻነታቸው ላይ ከሚሰነዘረው ጥቃት ለመከላከል እና ህይወታቸውን ላጡ ጋዜጠኞች ክብር ለመስጠት የሚከበር በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃንና የፕሬስ ነፃነት አቀንቃኞች ዕለቱን በተለየ ሁኔታ ይመለከቱታል ተብሏል፡፡ የአየር ንብረት እና የብዝሃ ህይወት ቀውስ በአካባቢ እና ስነ–ምህዳር ላይ ብቻ ሳይሆን በአለም ዙሪያ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየጎዳ ነው፤ በዚህም በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ ሃገራችን የጉዳቱ ገፈት ቀማሽ ከመሆንዋም ሌላ ችግሩን ለመቅረፍ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ትገኛለች የሚለው መግለጫው፡፡ በዚህ ረገድ ባለፉት በርካታ አመታት በሃገራችን ቀላል የማይባሉ ጥረቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን በተለይ ባለፉት 5 አመታት የተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃ ጥረቶች ቀላል አይደሉም፡፡በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች የሚተከሉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርና በየአካባቢው የሚካሄደው የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ በሀገራችን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት መካከል ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ የሃገራችን መገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ቀላል የማይባል ሚና ተጫውተዋል፡፡የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ የመጡ አካባቢያዊ ለውጦችን በማጠናከር፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ህጐች፣ አሰራሮችና ለአካባቢ ደህንነት ጠንቅ የሆኑ አመለካከቶች ላይ በመወያየት ትኩረት እንዲያገኙ ሲጥሩ ጋዜጠኞች ሥራቸውን ከስጋትና ፍርሃት ነፃ ሆነው በኃላፊነት ስሜት የሚሰሩበት ሁኔታ ትኩረት ሊስጠው እንደሚገባ ምክር ቤታችን ያምናል ሲል በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ Via Ethio FM @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 14😁 11
Photo unavailableShow in Telegram
የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ ተላለፈ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፥ የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት ወደነበረው ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል። @Yenetube @Fikerassefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 39 11😁 7👎 2
የአውሮፓ ህብረት የጣለውን ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ውሳኔ እንዲያጤነው ኢትዮጵያ ጠየቀች! የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት በህገወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታወቀች።የአውሮፓ ህብረት ይህንን አቋሙን እንዲያጤነው በቤልጂየም፣ ብራስልስ ተቀማጭነቱን ያደረገው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት ሚያዝያ 22/ 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት (ካውንስል) ያስተላለፈው የእግድ ውሳኔ በህብረቱ አባል አገራት ለመኖር ህጋዊ ፍቃድ የተነፈጋቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በክብር፣ በስርዓት እና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ እንዲመለሱ ለማድረግ ሁለቱ ወገኖች በቅርበት እየሰሩ ባለበት ወቅት ነው ሲልም መግለጫው አስፍሯል።የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ከሰሞኑ በኅብረቱ ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ መደረጉን አስታውቋል። በዚህ ዕገዳ መሠረት፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም።ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉየዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።ለዚህም ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ገልጾ “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ ለመውሰድ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም” ብሏል።ኢትዮጵያ በበኩሏ በሰጠችው ምላሽ ጊዜያዊ የቪዛ እግዱ ዜጎቿን ወደ አገራቸው ለመመለስ እና ከማህበረሰቡም ጋር መልሶ ለማዋሃድ በኢትዮጵያ እና በህብረቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር ያላገናዘበ ነው ብላለች። በተጨማሪም ውሳኔው ማንነትን ለማረጋጋጥ የሚደረገውን አድካሚ ሂደት ከግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም ሲል ኤምባሲው ተችቶታል።የምክር ቤቱ እርምጃ "ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከህብረቱ አባላት አገራት ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን የቅበላ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ላይ እንቅፋት የሚፈጥር ነው ብሏል ከቤልጂየም በተጨማሪ ለሉክሰምበርግ ፣ ኔዘርላንድስ እና የአውሮፓ ህብረት የሚያገለግለው ኤምባሲው። የአውሮፓ ህብረት አቋሙን እንደገና እንዲያጤን የጠየቀው ኤምባሲው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከአውሮፓ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን አሰራር በተመለከተ ከተሰጠው ውሳኔ ጋር በሚጣጣሙ እርምጃዎች ላይ ይመክራል ብሏል።ህብረቱ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ የጉዞ ሰነዶች በመስጠት እንዲሁም በፍቃድ እና ያለ ፈቃድም የሚደረግ ስደተኞችን የመመለስ ሂደትን በተመለከተም ኢትዮጵያ “በቂ ትብብር አላደረገችም” ብሎ ነበር። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 23😁 13 4 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
Hammasini ko'rsatish...
👍 8 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንግሊዝ በዚህ ዓመት በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ልታሸጋግር ነው! የእንግሊዝ መንግስት በያዝነው የአውሮፓውኑ 2024 ቁጥራቸው 6,000 የሚሆን ስደተኞችን ‘ወደ ሩዋንዳ ያሸጋግራል’ ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ።እንግሊዝ ወደ ሩዋንዳ የምትልካቸውን ስደተኞች የሚመለከተው ይህ አሃዝ ይፋ የተደረገው ሰሜናዊ አውሮፓን በአነስተኛ ጀልባዎች አቋርጠው የሚመጡትን ስደተኞች ሙከራ ለማስቆም የተያዘው ውጥን ለወራት ከዘለቀ የፓርላማ ውዝግብ በኋላ ጽድቆ የሃገሪቱ ሕግ በሆነ ቀናት ዕድሜ ውስጥ ነው። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ሩዋንዳ በአሁኑ ወቅት እንግሊዝ ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 5,700 የሚደርሱ ስደተኞችን ለመቀበል “በመርህ ደረጃ” ተስማምታለች ሲል የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ከእነኚም መካከል 2,143 የሚሆኑት ወደሩዋንዳ ከመላካቸው አስቀድሞ "እስር ላይ ሊቆዩ መቻላቸውን" የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ አክሎ አመልክቷል። የእንግሊዝ የጤና ሚንስትር ቪክቶሪያ አትኪንስ በበኩላቸው የሕግ አስፈጻሚ አካላት ቀሪውን ካሉበት ፈልገው ያመጣሉ ብለዋል አያይዘውም ማንኛውም ስደተኛ በደንቡ መሰረት መጥቶ ካልተመዘገበ ካለበት ተይዞ ይቀርባል’ ብለዋል።ባለስልጣናቱ የመንግስት አኃዛዊ መረጃዎችን ጠቅሰው እንዳመለከቱት ባለፉት 18 ወራት ጊዜ ውስጥ በትናንሽ ጀልባዎች ተሳፍረው የእንግሊዝ ቻናልን ለማቋረጥ የሞከሩ ቁጥራቸው ከ57, 000 በላይ ፍልሰተኞች ከዚያች አገር ዘልቀዋል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 32 6😭 6👏 3👎 2👀 2😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአብን አባሉ አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከአማራ ክልል የመንግሥት ኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡ ላለፈው ሁለት ዓመት ከስምንት ወር ገደማ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን (አባሉ) አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ካባለፉት “ሶስት፣ አራት ወራት” ወዲህ አንስቶ ከኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር “በዝርዝር” ንግግር ማድረጋቸውን ያስታወሱት አቶ ጣሂር፤ የክልሉ መንግሥት ጥያቄውን እንደተቀበለው ገልጸዋል።የቀድሞው የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ፤ “ትንሽ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረብኝ በቤተሰብ እና በራሴ ጉዳይ ነው የለቀቅሁት” ሲሉ ከኃላፊነት የለቀቁበትን ምክንያት አስረድተዋል። አቶ ጣሂር፤ “[ከክልሉ አመራሮች ጋር[ በመነጋገር ከፓርቲያችን ሰው ተክተን ነው የወጣሁት” ሲሉም ከኃላፊነት ሲለቅቁ በእሳቸው ቦታ የሚሾም ሌላ የፓርቲው አባል እንዲተካ መደረጉን ገልጸዋል።በአቶ ጣሂር ቦታ ሌላኛው የአብን አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሾማቸውን የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል። [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 37😁 15 9
ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው ስደተኛ በአሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆነ! ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ።የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል።ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር።ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 ሚሊዮን ዶላር ያህል የሚደርሰው ሲሆን ይህንንም ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ አስታውቋል። “አሁን ቤተሰቤን አንበሻብሻለሁ። ለራሴም ጥሩ ዶክተር መቅጠር እችላለሁ” ሲል አስረድቷል።“ህይወቴ ተቀይሯል” ሲል ለሲቢኤስ አጋር የሆነው ኮይን የተናረው ቼንግ አምላኩ እንዲረዳው በጸሎት መማጸኑን አስረድቷል።ቼንግ አክሎም ለቤተሰቡ ሲያልሙት የነበረውን ቤት መግዛት እንደሚፈልግ እና ፓወርቦል የሎተሪ ጃክፖት መጫወቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል።“እንደገና እድለኛ ልሆን እችላለሁ” ሲል ተስፋውን አስረድቷል። ሲቢሲኤስ በአሜሪካ ውስጥ የቢቢሲ የሚዲያ አጋር ነው።ላለፉት ስምንት ዓመታት በኬሞቴራፒ ህክምና ውስጥ ያለው ቼንግ ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር በመተባበር ከ20 በላይ የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶችን መግዛታቸውን ተናግሯል።የሎተሪ ቲኬቶቹ አሸናፊ ቁጥሮች 22፣ 27፣ 44፣ 52፣ 69 እና ቀይ ፓወርቦል 9 ነበሩ ተብሏል። በፓወርቦል ታሪክ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የገንዘብ ሽልማት መሆኑ የተነገረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የተቀመጠው በ2022 አሸናፊ የነበረው የ2.04 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት ነው።የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶች በ45 አሜሪካ ግዛቶች፣ በኮሎምቢያ እንዲሁም በፖርቶ ሪኮ እና በአሜሪካ የቨርጂን ደሴቶች እያንዳንዳቸው በ2 ዶላር ነው የሚሸጡት።የሎተሪ ቲኬቶች ዋጋ መጨመሩ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የቢሊዮን ዶላር ሽልማቶች በጣም የተለመዱ ሆነዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 72 13 4👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
😁 3👍 1👏 1
ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በሁለት ወራት ገደማ የመጨረሻውን ሥምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል! ለሶማሌላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ሥምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለባሕር ኃይል የጦር ሠፈር ልትከራይ የምትችላቸው ሦስት አማራጭ ቦታዎች መለየታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ዲፕሎማቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሙሴ ቢአብዲ የተፈራረሙት “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” በመጪዎቹ ወራት ወደ ተግባር ይሸጋገራል ብለው እየጠበቁ ነው። የመግባቢያ ሥምምነቱ ከአራት ወራት በፊት ታህሳስ 22 ቀን 2016 ሲፈረም ድርድሩ በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ አስታውቆ ነበር። የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ የመግባቢያ ሥምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን እና የቴክኒክ ኮሚቴዎች መታጨታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። “ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ነበር” ያሉት ዶክተር ኢሳ ካይድ በረመዳን የጾም ወር ወቅት ሒደቱ ቢቀዛቀዝም በመጪዎቹ ወራት ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሥምምነቱን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር የመጨረሻውን ሥምምነት ሊፈራረሙ እንደሚችሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። “ሁሉም ነገር ሁለቱ ቡድኖች በሥምምነቱ ላይ ለመደራደር ሲገናኙ ይወሰናል” ያሉት ዶክተር ኢሳ “የሕግ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች አሉ። በመጪዎቹ ወራት ምን አልባትም በሁለት ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሳዓድ አሊ ሽሬ ሥምምነቱ ተፈርሞ “ዕውቅና ስናገኝ በዓለም አቀፍ መድረክ ድምጽ ስለሚኖረን በፖለቲካ ረገድ ጠቃሚ ነው” ሲሉ ተስፋቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። ሶማሌላንድ የምታገኘው ዕውቅና “ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድ፣ ለጉዞ እና በዕድገት በር ስለሚከፍት በኤኮኖሚ ረገድ ጠቃሚ ይሆናል” የሚሉት የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሶማሌላንድ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት እንድትተሳሰር ይረዳታል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል። “ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ መበደር እንችላለን” ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሳዓድ አሊ “በዕውቅናው ምክንያት እጅግ በርካታ በሮች” ለሶማሌላንድ እንደሚከፈቱ ይጠብቃሉ። ሥምምነቱ ከተፈረመ ሶማሌላንድ ዕውቅና ስታገኝ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር የምታቋቁምበትን ወደብ በኪራይ ታገኛለች። ሶማሌላንድ 850 ኪሎ ሜትር ገደማ በሚረዝመው የባሕር ዳርቻ ኢትዮጵያ ልትከራይ የምትችልባቸውን ሦስት ቦታዎች በአማራጭነት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ አረጋግጠዋል። “የለየናቸው የተወሰኑ ቦታዎች አሉ። ከኢትዮጵያ አቻዎቻችን ጋር ከተገናኘን በኋላ አንዱ ይመረጣል” ያሉት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተለዩትን ሦስት ቦታዎች ስሞች ከመናገር ተቆጥበዋል። ኢትዮጵያ የደርግ ሥርዓተ መንግሥት ወድቆ ኤርትራ ነጻነቷን ስታውጅ የፈረሰውን የባሕር ኃይል መልሳ ያቋቋመችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በፈረንሳይ እና የቀድሞ የባሕር ኃይል መኮንኖች ድጋፍ የባሕር ኃይሉን በአዋጅ መልሶ ያቋቋመው በ2011 ነበር። Via DW @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 59😁 17🔥 14 6 1
የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ! የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት (ካውንስል) ኢትዮጵያውያን ላይ በጊዜያዊነት የቪዛ ገደብ ማሳለፉን አስታወቀ።በአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ድረ ገጽ ላይ ዛሬ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ. ም. በወጣው መግለጫ መሠረት፣ በአውሮፓ ኅብረት ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ ተደርጓል። በዚህ ዕገዳ መሠረት፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም።ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉም። የዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም።በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።መግለጫው እንደሚለው፣ ይህ ውሳኔ በኮሚሽኑ የተላለፈው “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ካውንስሉ ባደረገው ግምገማ ስለተገነዘበ” ነው። አክሎም “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ ለመውሰድ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም” በማለት መግለጫው ያብራራል።የአስቸኳይ ጊዜ የጉዞ ሰነዶች በመስጠት እንዲሁም በፍቃድ እና ያለ ፈቃድም የሚደረግ ስደተኞችን የመመለስ ሂደትን በተመለከተም ኢትዮጵያ “በቂ ትብብር አላደረገችም” ሲልም መግለጫው የውሳኔውን ምክንያት ያስረዳል።ስደተኞችን በመቀበል ረገድ በኢትዮጵያ በኩል ያለውን “ትብብር” በድጋሚ እንደሚቃኝም ኮሚሽኑ አክሏል። በአውሮፓ ኅብረት የቪዛ ሕግ መሠረት፣ ኮሚሽኑ አገራት ስደተኞችን መልሶ በመቀበል ረገድ ያላቸውን ተባባሪነት እንደሚገመግም በድረ ገጹ የወጣው መግለጫ ይገልጻል።በኢትዮጵያ በኩል ስደተኞችን የመቀበል መጠኑ “አናሳ” እንደሆነ ጠቅሶ፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ለኢትዮጵያ ያቀረቡት ስደተኞችን የመመለስ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ “እምብዛም አለመሆኑ” ያለውን ትብብር “ትንሽ” ነው ብሎ እንዲደመድም ምክንያት እንደሆነው ማብራሪያ ሰጥቷል።ውሳኔው ጊዜያዊ ቢሆንም ቀነ ገደብ እንደሌለው የኮሚሽኑ መግለጫ ይጠቅሳል። [BBC] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 45👎 4 4😁 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
Hammasini ko'rsatish...
👍 10
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል! በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል። የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 27😭 25 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
50 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዉያን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ባለመሆናቸው በጨለማ ዉስጥን እንደሚገኙ የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ገልጿል! ሚኒስትሩ እንዳለዉ በሀገሪቷ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት 50 በመቶ ማድረስ መቻሉንና ነገር ግን የተቀረው የማህበረሰብ ክፍል በጨለማ ዉስጥ እየኖሩ ይገኛሉ ብሏል። በኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍ አደረጃጀቱን ለመቀየር ከዓለም ባንክ 552.6 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የገለፀው ሚኒስትሩ አሁን ላይ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት የማዘመን፣ ማደስ፣ ተጨማሪ የማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ማዕከላትን የመገንባት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 18 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በአለም አቀፉ የልማት ማኅበር(አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ግባኤ ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል። ጉባኤው ማኅበሩ ደጋፊዎች እና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ አቅራቢዎች በ21ኛው የማኅበሩ ዘመን ድጋፋቸውን ለመጨመር በፅኑ እንዲያጤኑ የማሳሰብ አላማ ያነገበም ነው። [PM Office] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
😁 25👍 19 9👎 7👏 1
አሜሪካ የራፋህን ጥቃት እንድታስቆም የፍልስጤሙ መሪ ተማጸኑ! የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እስራኤል ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በተጠለሉባት ደቡባዊ የጋዛ ከተማ ራፋህ ላይ ጥቃት ከማድረስ የምታስቆማት ብቸኛዋ አገር አሜሪካ ናት ብለዋል።ከፊል ዌስት ባንክን የሚያስተዳድሩት አባስ ማንኛውም የእስራኤል ጥቃት ፍልስጤማውያን ከጋዛ እንዲሸሹ ሊያደርግ ይችላል ብለዋል።እስራኤል በራፋህ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ደጋግማ እየዛተች ትገኛለች። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እሑድ ዕለት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት “በራፋህ ላይ ያላቸውን ግልፅ አቋም” በድጋሚ አስታውቀዋል።ሰላማዊ ዜጎችን ከጉዳት ለማዳን የሚያስችል አስተማማኝ ዕቅድ ካላየች በስተቀር አሜሪካ በራፋህ የሚካሄድን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ መደገፍ እንደማትችል ደጋግማ ተናግራለች።በሳዑዲ ርዕሰ መዲና ሪያድ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ጉባዔ (ደብሊውኢኤፍ) ላይ ንግግር ያደረጉት አባስ አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ አሳስበዋል። "እስራኤል ይህን ወንጀል እንዳትፈጽም ማድረግ የምትችለው አሜሪካ ብቻ ስለሆነች እስራኤል የራፋህ ዘመቻዋን እንድታቆም እንድትጠይቅ አሜሪካን እንማጸናለን። ራፋህ ላይ የሚደረግ "ትንሽ የሚባል ጥቃት" ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለመሸሽ እንደሚያስገድድ ተናግረዋል።"በፍልስጤም ህዝብ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ጥፋትም ያኔ ይከሰታል።" ብለዋል።ከግማሽ በላይ የሚሆነው የጋዛ ህዝብ በራፋ የሚገኝ ሲሆን በከተማዋ ያለው ሁኔታም የከፋ የሚባል ነው። የተፈናቀሉ ሰዎች የምግብ፣ የውሃ እና የመድሃኒት እጥረት እንዳለባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዋይት ሃውስ በራፋህ የሚካሄደውን ዘመቻ በተመለከተ ባይደን ለኔታንያሁ የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ በዝርዝር አልገለጸም። የብሔራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ለኤቢሲ እንደተናገሩት እስራኤል ወደ አካባቢው ከመግባቷ በፊት የአሜሪካን ስጋቶች እና ሃሳቦችን ለማዳመጥ ተስማምታለች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ሪያድ አቅንተው ከአባስ ጋር ሊነጋገሩ መሆኑም ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ ተስፋ እየፈነጠቀ የመጣው በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የሚደረገው ቀጥተኛ ያልሆነ የተኩስ አቁም ድርድር እና በጋዛ የቀሩትን ታጋቾች የማስለቀቅ ሂደት በእስራኤል ጥምር መንግሥት ውስጥ ያለውን መከፋፈል ይበልጥ እያጋለጠው ነው። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 29 5😁 4
Photo unavailableShow in Telegram
የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53 በመቶ ድርሻ መያዙ ጥናት አመላከተ! የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ" እንዲሆን እያደረገው እንደሚገኝ ገልጿል።ማህበሩ በዚሁ ጥናቱ በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉን አስታዉቀዋል። እነዚሁ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸዉ በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።እንደ ጥናቱ ከሆነ በአለም አቀፍ ደረዳ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው እና እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ ርካሽ ልብሶች መሞላታቸዉን በጥናቱ ተመላክቷል።የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገብ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንግድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
😁 59👍 46 4👎 1
አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች! የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 36😭 14 4😁 4
Photo unavailableShow in Telegram
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
Hammasini ko'rsatish...
👍 8
አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች! የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia! Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter. #EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia #DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia #EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
Hammasini ko'rsatish...
👍 6 2
Photo unavailableShow in Telegram
የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተነገረ! የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነ ተሰምቷል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦን ላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ብለዋል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኛች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 26 5
Photo unavailableShow in Telegram
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia! Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter. #EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia #DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia #EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
Hammasini ko'rsatish...
👍 15👀 1
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር። የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 50 5🔥 4
Photo unavailableShow in Telegram
በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ! የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል።ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል።ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው። [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 23 2👏 1
ዐቃቤ ሕግ የሽብር ተከሳሾችን ክስ እንዲያሻሽል በተሰጠው ብይን ላይ አቤቱታ አቀረበ! ዐቃቤ ሕግ፣ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን የእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ዛሬ ኀሙስ በሰጠው ብይን ላይ፣ “ምስክሮቼን ያጋልጥብኛል” በማለት አቤቱታ አቅርቧል፤ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ክሱ ካልተሸሻለ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡በተከሳሶቹ የወንጀል ድርጊት “ተገድለዋል” የተባሉ ሰዎች፣ በክሱ ላይ በስም እንዲጠቀሱ ብይን ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፣ በዛሬው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ በእነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐቃቤ ሕግ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ዛሬ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ችሎት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት የተቀጠረው፣ ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት በታዘዘው መሠረት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ለመመልከት ነበር፡፡ የዐቃቤ ሕግ ክስ፣ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት የሽብር ወንጀል፣ የ217 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መጎዳታቸውንና ከፍተኛ ንብረትም መውደሙን ሲያስረዳ፣ በተከሳሽ ጠበቆች ጥያቄ መሠረት፣ ሟቾቹ በስም ተጠቅሰው፣ ሌሎች ጉዳቶችም በዝርዝር ተገልጸው ክሱ እንዲሻሻል፣ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ኅዳር 12 ቀን በይኖ ነበር፡፡ ኾኖም፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ክሱ እንዲሻሻል የተሰጠው ብይን እንዲሻር በደብዳቤ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ለዚኽም በምክንያትነት ያቀረበው፣ እንደ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሟቾቹን ስም መጥቀስ “ምስክሮቹን ለጉዳት የሚዳርግ ነው፤” የሚል እንደኾነ፣ ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡ጠበቆች በበኩላቸው፣ ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ቤቱን ብያኔ አክብሮ ክሱን የማያሻሽል ከኾነ ክሱ እንዲነሣ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ፣ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለግንቦት 12 ቀን መቅጠሩን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ አመልክተዋል፡፡ በክስ መዝገቡ ላይ ከተጠቀሱ 51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎችን ጨምሮ 23ቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ለሕክምና እንደወጡ ማምለጣቸውን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ተወካዮች ከዚኽ ቀደም ለፍርድ ቤት ማሳወቃቸውን ጠበቆቹ ገልጸዋል፡፡ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾችን፣ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ውጤቱ ለቀጣዩ ችሎት እንዲቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ Via VoA @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 19 5
Photo unavailableShow in Telegram
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ለ 122 ሺህ አርሶአደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድህን ካሳ ሊከፍል መሆኑ ተገለፀ! በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ፣ በአለም ምግብ ፕሮግራም እና በፑላ አድቫይዘር ጥምረት ተጀምሯል የተባለውና በሀገሪቱ ትልቁ ነዉ የተባለው የሰብል መድህን ፕሮግራም የክፍ ስርአት መተግበር መጀመሩ ተነግሯል። በኢትዮጵያ የሰብል መድህን ታሪክ ዉስጥ ትልቁ መሆኑ በተነገረለት ፕሮግራም የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የመድህን ሰጪ እና የካሳ ከፋይ ተቋም በመሆን ለትግበራዉ 39 ሚሊዮን ብር መመደብ ካፒታል ሰምቷል። የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ በተገለጸው ቢዚህ ስርዓት በአማራ ክልል የሚገኙ አነስተኛ አርሶአደሮች ተጠቃሚ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ለ 7.5 ሚሊዮን አርሶአደሮች ተደራሽ ይደረጋል ተብሏል። [Capital] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 39😁 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው! በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡ አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
😁 29👍 17👎 7👏 2 1👀 1
Photo unavailableShow in Telegram
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። Via Addis Maleda #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የሰሊጥ ግብይት በሱዳንና በኢትዮጵያ የግጭት መነሻ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ! የሰሊጥ ምርት እና ግብይት፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል፣ እንዲሁም በሁለቱም አገሮች የውስጥ አወዛጋቢ ጉዳዮች ዙሪያ የግጭት መንሥኤ እየሆነ እንደሚገኝ፣ አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ አመለከተ፡፡ “The ‘conflict economy’ of sesame in Ethiopia and the Sudan” በሚል ርእስ የወጣውን ጥናት ከአዘጋጁት ሁለት ምሁራን አንዱ ዶ/ር አቤል አባተ ደምሴ፣ “የሰሊጥ ግብይት በሱዳንና በኢትዮጵያ የውስጥ እና የውጭ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል፤” ይላሉ፡፡ ዶ/ር አቤል፣ ላለፉት አራት ዓመታት፣ በለንደን በሚገኘው ዓለም አቀፍ የፖሊሲ ተቋም(ቻተም ሃውስ) የሮያል ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም የምርምር ባልደረባ ሆነው በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ምሁሩ በጥናታቸው ላይ እንዳመለከቱት፥ የመንግሥት ኀይሎች፣ የአካባቢ ልሂቃንና ሚሊሻዎች በሰሊጥ ምርት እና ንግድ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እየተፎካከሩ ናቸው፡፡ ፖሊሲ አውጪዎች፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ትስስር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የግብርና ለውጦችን በማስተካከል ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት፣ መሠረታዊ እና ተለዋዋጭ ፖሊሲዎችን መቅረጽ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ ፖሊሲ አውጭዎቹ መደበኛ ያልሆነ የንግድ ልውውጥን እንዲደግፉና ከታች ወደ ላይ ለአካባቢያዊ አብሮ መኖርና ትብብር ኹኔታዎችን እንዲያመቻቹ ጥናቱ ምክረ ሐሳብ ማቅረቡን ከአዘጋጆቹ አንዱ ዶ/ር አቤል አባተ ተናግረዋል፡፡ https://www.chathamhouse.org/2024/04/conflict-economy-sesame-ethiopia-and-sudan [VoA] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 20😁 3 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተገለጸ! ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል። እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። [Addis Maleda] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 33😭 8 2
Photo unavailableShow in Telegram
በ59 ሃገራት የሚገኙ ከ282 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን የመንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመለከተ። የዓለማቀፉ ድርጅት ሪፖርት እንዳለው በአስከፊ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የጋዛ ሰርጥ በርካታ ቁጥር ያለው ተጋላጮችን በመያዝ ትመራለች። ከጎርጎርሳውያኑ 2022 ወዲህ 24 ሚሊዮን ተጨማሪ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት እና ለረሃብ መጋለጣቸውን ያመለከተው መረጃው ከጋዛ ጦርነት በተጨማሪ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ሚሊዮኖች እርዳታ ጠባቂ አልያም በረሃብ አፋፍ ላይ ያሉ ናቸው ብሏል። በየዓለም የምግብ እርሻ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሳየው በአምስት ሃገራት ውስጥ የሚገኙ እና ቁጥራቸው ከ705 ሺ በላይ የሆኑ ሰዎች ደረጃ አምስት ወይም ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶውን ቁጥር የሚሸፍነው በጋዛው ጦርነት አስከፊውን ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ፍልስጥኤማውያን ናቸው።ደቡብ ሱዳን ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሶማሊያ እና ማሊ እያንዳንዳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች እና ስደተኞች በመያዝ ይከተላሉ።በሀገራቱ እና በአካባቢያቸው እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች እስካልቆሙ ድረስ ችግሩ እየከፋ ሊሄድ እንደሚችል ዓለማቀፉ ድርጅት አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ በያዝነው የጎርጎርሳውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ኤል ኒኖ ያስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ወቅት እንደነበር ያስታወሰው ድርጅቱ የጎርፍ መጥለቅለቅን ጨምሮ በአንዳንድ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የዝናብ እጥረትን በማስከተል ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ እንዳያደርገው ያሰጋኛል ብሏል።መንግስታት እና ለጋሾች በረሃብ ምክንያት «የጅምላ የሰውን ልጅ ውድቀት ለመታደግ» ርብርብ እንዲደረግ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ጥሪ አቅርበዋል። [DW] @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 22😭 7 4
Photo unavailableShow in Telegram
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
Hammasini ko'rsatish...
👍 10👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ! ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በዛሬው ዕለት አስጀመረ፡፡በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት መታቀዱ ተመላክቷል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ተዓማኒነት ያለው የማንነት መለያ ዲጂታል መታወቂያ ነው ብለዋል።ዲጂታል መታወቂያ አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ዜጎች በኢኮኖሚው ዕኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባው አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች ዛሬ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፥ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ ይችላሉ መባሉን ፋና ዘግቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 57👎 12 7👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
“በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰብአዊ መብት አያያዙ እንደከፋ ነው” - ዩኤስ የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተመለከተ የሚያወጣውን ዓመታዊ ሪፖርት በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ትላንት ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም ባወጣው የሃገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በሚተነትነው ሰፊ የአውሮፓያኑ የ2023 ዓመታዊ ሪፖርቱ፤ ፣የኢትዮጵያ መንግሥት ወይም የመንግሥት ወኪሎች፣ ከሕግ ውጪ የዘፈቀደ ግድያ መፈፀማቸውን፣ በርካታ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገራት የሰብአዊ መብት ቡድኖች ሪፖርት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።ግድያዎቹ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች እንዲሁም ትግራይን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ እንደሆነ አስታውቋል። የክልል ፖሊስ አባላትም ፣ ከመጠን ያለፈ እና ሕይወት የቀጠፈ ኃይል መጠቀማቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ለማሳያም፣ “በየካቲት ወር በወልቂጤ ከተማ የውሃ አገልግሎት እንዲመለስ በሰልፍ ለመጠየቅ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በተወሰደው ርምጃ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ 30 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ብሏል። በሌሎችም አካባባዎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ያካተተው ሪፖርት፣ የፌዴራሉ ፖሊስ ምርመራ ቢሮ በፖሊስ ኃይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ የሚያደርጋቸው ምርመራዎች ውስን መሆናቸውን እና የሚሰጠውን ቅጣት በተመለከተም በሚስጥር እንደሚይዝ ጠቁሟል።በግዳጅ መሰወርን አስመልክቶም፣ መንግሥትን የሚነቅፉ የፖለቲካ አስተያየት የሚሰጡ ግለሰቦች፣ የቀድሞ ጦር አባላት፣ የምርመራ ጋዜጠኞች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች መሰወራቸውን አትቷል። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://amharic.voanews.com/a/7582081.html @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 25😁 7 2
Photo unavailableShow in Telegram
"የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተላለፈ ያለው መልዕክት ሀሰተኛ ነው" :- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት አወጣ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲተላለፍ የነበረው "የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" የተመለከተ ደብዳቤ በሐሰት የተቀናበረ መሆኑን የአማራ ክልል አስታውቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ ከመስሪያ ቤታቸው የወጣ አለመሆኑን እና የተቀነባበረ መሆኑን ገልጸዋል። ክልሉ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሚሊሻ ኃይሉን የማጠናከር ስራን እየሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊው፤ የርዕሰ መስተዳድሩን ጽ/ቤት የደብዳቤው ይዘትም ሆነ ቅርጽ ሀሰተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 30😁 14👎 3 3🔥 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአሜሪካ ሴኔት ቲክቶክን በአገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ! የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በአገሪቱ ቲክቶክን ሊያግድ የሚችል አወዛጋቢ አዋጅን አጽደቀ።አዋጁ የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ የማህበራዊ ትስስር ገጹን ድርሻ በ9 ወር ውስጥ የማይሸጥ ከሆነ ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ ያግዳል።አዋጁ ወደ ፕሬዝዳንት ባይደን የተመራ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አዋጁ ኋይት ሃውስ እንደደረሰ ፊርማቸውን አኑረውበት ሕግ እንደሚያደርጉት ተናግረው ነበር። ባይትዳንስ ለዚህ ውሳኔ ፈጣን መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ለቢቢሲ ተናግሯል።ቀደም ብሎ ግን ቲክቶክ በጫና ለማሸጥ የሚደረግ ሙከራን አጥብቆ እንደሚቃወም ተቋሙ ገልጿል።አሜሪካ ቲክቶክን እንዲሸጥ ባይትዳንሳ ላይ ጫና አድረጋ ቢሳከላት እንኳን ለሽያጩ ሂደት የቤጂንግ ባለስልጣናት ይሁንታ ያስፈልጋል።ሆኖም ቻይና ይህንን አይነቱን ውሳኔ እንደምትቃወም ገልጻለች። ተንታኞች ይህ ሂደት ዓመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ይገልጻሉ።ይህን አዋጅ ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት አብለጫዎቹ ደግፈውታል።79 የምክር ቤት አባላት ሲደግፉት 18 የሚሆኑት ደግሞ ተቃውመውታል። የምክር ቤት እውቅ የሪፐብሊካን እና የደህንነት ኮሚቴ አባል የሆኑት ማርኮ ሩቢዮ “ለአመታት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በአሜሪካ ዝነኛ የሆነውን መተግበሪያ እንዲቆጣጠረው ፈቅደናል። ይህ ሁኔታ በአደገኛ ሁኔታ የቅርቡን ብቻ የተመለከተ ነው” ብለዋል።ጨምረውም አዲሱ አዋጅ ቻይናውያን ባለቤቶቹ መተግበሪያውን እንዲሸጡ የሚጠይቅ እንደሆነ ጠቅሰው ለአሜሪካ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Hammasini ko'rsatish...
👍 23 7👏 4👎 2