cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ «በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ» ሀሳብ አሰተያየት ካለዎት ⇙ @AlJUDDAEWA_bot

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 057
Obunachilar
-224 soatlar
-127 kunlar
-3430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ሙፍቲ ዳውድና አረፋ /ዒደል አድሃ/ … አረፋን ከየቲሞች ጋር 1 በ2013 ዓ/ል ለ110 አይታሞች አረፋን ከየቲሞች ጋር 2 በ2014 ዓ/ል ለ200 አይተሞች አረፋን ከየቲሞች ጋር 3 በ2015 ዓ/ል ለ300 አይተሞች ከሁሉ በፊት የአዛኞች ሁሉ አዛኝ በሆነው አል ረህማን ችሮታ በእናንተ ደጋግ ባሮች ርብርብ የቲምነት ያጎደለባቸውን በተቻለን ከጓደኞቻቸው እኩል ሆነው ዒዱን በደሰታ ያሳልፉ አንድ ዝንጥ አድርገን አልብሰናል። በዓሉ በዓል ሆኖላቸዋል። አልሃምዱ ሊላህ ዘንድሮም በጀሊሉ ፍቃድ "አረፋን ከየቲሞች ጋር 4" ለ300 አይታሞች በዓሉን ልናደምቅላቸው የጎደላቸውን ለሞምላት ነይተን ተነሰተናል። እናንተ ቅንና ደጋግ የአላህ ባሮች ዝግጁ ናቹህ! #አረፋን_ከየቲሞች_ጋር_4 #ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም #አረፋ #አይታሞች
Hammasini ko'rsatish...
የሴትልጅ አለባበሰ (ሒጃቧ) የአባቷን ተርቢያ ፤የእናቷን ክትትል፤የወንድሟን ተቆጪነት (ጊራ) ፤የባሏን ወንዳ ወንድነት፤ ከነዚህም በላይ የጌታዋን ሙራቀባ ፤ የሚገልፅ ነው። 🙏 © ustaz mohammed Abduikadir oumer
Hammasini ko'rsatish...
የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ? ቢስሚላህ ! ቁጥር 2 በቁጥር አንድ እንደ ጀመርኩላችሁ የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ቤተሰቦቹ የጁ ዉስጥ እንደ ሆኑ ያወራል ( በርግጥ አንዳቸዉም ቤተሰቡ ነኝ ብሎ የመጣ አላዉቅም ) ሰዉየዉ በአንድ ወቅት መርሳ ከተማ ላይ ለትልቅ እስላማዊ ዝግጅት ስንጓዝ ከፊት ወንበር ጋቢና ላይ ተቀምጧል ታላላቅ ዓሊሞችና ጎደኞቼ ከሓላ ተቀምጠን ከካራቲስትነት ከፍ ብሎ በሆነ ጦርነት ( ስሙን ረሳሁት ሀገር ዉስጥ በተደረገ ) ላይ ከሄሊኮብተር ሲወርድ እንደተጎዳ አገግሞ እንደ ዳነ ያወራል ። ይህ ሰዉ በማበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ የቁርአን ሂፍዝ ማእከሉ አድራጊ ፈጣሪ ሆነ ሚስትም አገባ ትንሽ ቆይቶ ሀኪም ነኝ የህክምና ት/ት መማር አለባችሁ ብሎ ከመርከዝ ልጆች አምስት ሰዉ መርጦ በጊዜዉ እኔ አብዱራህማን ሱልጧን ዶ/ር አህመድ ኑርየ ኢንጂነር ሙሀመድ ጀዉሀር ( አሏህ ይማረዉ ሁላችሁም ዱዓ አድርጉለት ) ሌሎች ሁለት ወንድሞቼ ረሳሃቸዉ ሁነን ለአንድ ሳምንት መርፌ እንዴት እንሚሰጥ አስተማረን እኔም በሳምንት የመርከዙ ሀኪም ሆኜ እርፍ !። በጊዜዉ ለህክምና ብዙ ትልልቅ ሰዎች ይመጡ ነበር ቪ B2 ወግቶ በጊዜዉ የማይታመን ብር ነበር የሚጠይቀዉ ለምን የሚለዉም አልነበረም ። ሚስት የሓላ ሓላ ስቃዪ በዛ ከአንድ የዲን መምህር ነኝ ከሚል ሰዉ የማይጠበቁ ነገሮችን ስታይ ለማን ትናገር ማንስ ያምናታል ። የመርከዝ ልጆችም ለሁለት መከፈል ጀመሩ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅም ያዮትንና የጠረጠሩትን ልጆች የኢማን ድክመት አለባቸዉ ፡ ጅሀድ ይጠላሉ የተለያዮ ስም እየለጠፈ የመርከዙ ልጆችን ከፋፈላቸዉ በመሀባ እንባ ይራጩ የነበሩ ወንድማማቾች ተኮራረፉ ። ባጭሩ የወልዲያ ሰዉ ዳዒ አለመሆኑን እየተረዳ ይመስላል ስለዚህ ክትትል ጀምሯል ። የሚገርሙ ታሪኮች ይቀጥላሉ ወልዲያ የጀመዓዉና የሚስቱ ታሪክ ከቆቦ እስከ ኮምቦልቻ …..። © ustaz Abdurahman Sultan
Hammasini ko'rsatish...
የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ?!! ቢስሚላህ ! ከ 25 አመት በሗላ የጠፋኝን ሰዉ ወንድሜ የህያ ኢብኑ ኑህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፎት ባይ ገረመኝ !! የዛን ዘመን አፍላ የቁርአንና የዳዕዋ ንቅናቄን ከየት እንደመጣ ሳናዉቅ ነበር የተቀላቀለን ። ፂሙ ያደገ የፓኪስታን ልብስ የለበሰ በቀኝ እጁ ሲዋክ በግራ እጁ ሙስበሃ ይዞ የፈጅርን ሰላት ለመስገድ የሂፍዝ ተማሪዎች ዉዱእ ማድረጊያ ላይ በዛ ብርድ ወቅት እንጣደፋለን ። ከመሀላችን ሞቅ ባለ ከፍ ባለ ድምፅ “ እናንተ ወጣቶች በናንተ ጊዜ ዲን ሲደፈር ነብያችን ሰ.ዐ.ወ ክብራቸዉ ሲነካ እናንተ እያላችሁ እንዴት ይሆን ለጅሀድ ተነስ እኔ አሰለጥንሀለሁ !” የሚል የወጣቱን ስሜት በሚቀሰቅስ መልኩ በቁጣ ንግግር አደረገ ። ብዙዎቻችን ሙሀመድ ሱሩር በሚል የቀረበንን ሰዉ ያኔ ተዋወቅነዉ ከፈጅር ሰላት በሓላ የቁርአን ሀለቃ ላይ አብሮን ተቀመጠ ። መስጅድ ላይ በተበላሸ ምላስ የቁርአን አያቶችን እየሰባበረ ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ የዋሁ ማህበረሰባችን እና ወጣቱ ተከተለዉ ። በጣም የሚገርሙ ሊታመኑ የማይችሉ ለሀገር ሲል ከኤርትራ ጋር በተደረገ ጦርነት መሳተፉንና ለኢስላም ሲል አፍጋኒስታን ድረስ ዘልቆ የተዋጋበትን ባዶ ታሪክ ለወጣቱ ይግተዉ ጀመር አንዳንዱ በየት ብለን ጅሀድ በወጣን እስኪል ድረስ ፣ የማልረሳዉ ሁሌ ግን ጥያቄ የሚሆንብኝ የነበረዉ ጠዋት ከሀለቃ በሗላ ከቁርስ በፊት ወደ ዉጭ እንዳንወጣ እንከለከል ነበር ። ለምን አትሉም ? ሙሀመድ ሱሩር ካራቴ እየሰራ ጩሀቱን እንጅ ስራዉን ማየት እንዳንችል ምክኒያቱም በጩሀቱ ብቻ ካራቲስት እንደሆነ እንድንመሰክር ። ማህበረሰባችን በዚህ ብቻ አልቆመም በዲኗ ጠንካራ የሆነች ልጅ ተፈልጋ ተዳረ ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የሙሀመድ ሱሩር ማንነት ይጋለጥ ጀመረ ። ይቀጥላል !! © ustaz Abdurahman Sultan
Hammasini ko'rsatish...
አላህ አያረፍድም። ዩሱፍ ላይ እንዳላረፈደው፣ የዕቁብን እንዲሁ እንዳልተወው፣ ዩኑስ ላይ እንዳልጨከነው። እኛ ላይም አያረፍድም፣ አይጨክንም። ✧ https://t.me/ALJUEDDAAWA
Hammasini ko'rsatish...
👍 8
በጀናዛ በማጠብ ላይ የተሰማራ አንድ ወንድም የሆነን አጋጣሚ እንዲህ ይተርክልናል.. ከእለታት አንድ ቀን አርባወቹ ያልደረሰ ወጣት ሙቶ ከጓደኞቹና ከቤተሰብ ጋር ታጥቦ እንዲሰገድበት ወደ መስጅድ መጣ.. ከመጡት ሰወቹ መሀል አንድ ወጣት በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሳበኝ ወጣቱ የሞቹ አይነት እድሜ ውስጥ ያለ ወጣት ነው ። በጣም ያለቅሳል በየመሀሉ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ቃልን ይደጋግማል ራሱን ለመቆጣጠር ድምፁን ዝቅ ለማድረግ ቢሞክረም አልቻለም በጣም እያለቀሰ ነበር። ከኔ ጋር ወደ ማጠቢያ ክፍል ገባ ወጣቱ በየመሀሉ በጣም ሲያለቅስ አብሽር ታገስ ትግስት ማድረግ እንዳለበት እነግረዋለሁ ። ምላሱ ይህን ቃል ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ደጋግሞ ይል ነበር ። ይህንን ቃል ስሰማ እኔ እርጋታ ይሰማኛል ለቅሶው በጣም ስራውን እንዳልሰራ እያደረገኝ ስለነበር ። ለወጣቱም ወንድምህን አላህ ይማረው ካንተ በላይ አላህ ለሱ አዛኝ ነው ። ትግስት ማድረግ አለብህ አልኩት.... ወጣቱም ወደኔ እየተመለከተ ወንድሜ አይደለም አለኝ ! በጣም ተገረምኩ ይህ ሁሉ ለቅሶ ይህ ሁሉ እዝነት እንዴት አልኩ በውስጤ ... ወጣቱም ከወንድሜ በላይ የሆነ ውድ የሆነ ጓደኛየ ነው ። የልጅነት ጓደኛየ..የትምህርት ቤት ጓደኛየ ክፍል ውስጥ አብረን ተቀምጠን በረፍት ሰዓትም አብረን አሳልፈን ...በሰፈር ውስጥ አብረን ተጫውተን...አብረን አድገን ግንኙነታችንም አብሮ አድጎ አብረን ዩኒቨርስቲ ገብተን አብረን ተመርቀን አንድ አይነት ስራ ይዘን እህትማማቾች አግብተን ወንድና ሴት ወልጄ እሱም በተመሳሳይ ወንድና ሴት ወልዶ በአንድ አከባቢ ቤት ተከራይተን እየኖርን ደስታችንንም ሀዘናችንንም አብረን እያሳለፍን አብረን ደስታ ሲኖር ደስታው እየጨመረ ስንገናኝ ሀዘኑ እየቀነሰ በሁሉም ነገር አብረን ነበር የምንኖረው ... ታሪካቸውን ሲነግረኝ አልቻልኩም በጣም አለቀስኩ... ያሸይኽ ምድር ላይ እንደኛ አይነት ግን አለ...⁉ ይች ንግግር ልቤን ነካው.. ሩቅ ያለውን ወንድሜን አስታወስኩና የለም አልኩት.... ሱብሐነላህ የሚለውን ቃል እየደጋገምኩ አጥቤው ጨረስኩ ወጣቱም የጓደኛውን ግንባር ሳመና በጣም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ.. ሰወች ይዘውት ወጡ ሶላቱል ጀናዛ እንድንሰግድበት .... ሰግደን እንደ ጨረስን ጀናዛውን ተሸክመን ወደ ቀብር ቦታ ሄድን ... ጥግ ላይ ቁሞ ወዳጅ ዘመድ እያፅናናው ቀብረን ጨረስን ሰወች ሲሄዱ ለጓደኛው ዱዓ አርጎ ተመለስን .... በሚቀጥለው ቀን አሱር አከባቢ መስጂድ ትናንት የተመለከትኮቸው ሰወች አንድ ጀናዛ ይዘው መጡ.... ትናንት የተመለከትኩትን ወጣት መልክ ያለው አንድ አባት እያለቀሱ ተመለከትኩ ያ ሸይኽ ትናንት እኮ ጓደኛው ጋር ነበር ጓደኛውን ሸኝቶ ዛሬ ተከትሎ ሄደ ትናንት ለጓደኛው ከፈንና መቀስ ሲያቃብል ጓደኛውን እየገለባበጠ ሲነካ ነበር ትናንት በጓደኛው ሞት ልብ ተነክቶ ሲያለቅስ ነበር እያለ አባቱ ስቅስቅ ብሎ አለቀ.. የተሸፈነበትን ስገልጠው ትናንት በጓደኛው ሞት እያለቀሰ የነበረው ወጣት እንደሆነ አወኩ በጣም ደንግጫ እንዴት ሞተ አልኮቸው ሚስቱ የሚበላ ብታቀርብለት አልበላ አለው መተኛት ፈልጎ ተኛ አሱር ላይ ሚስቱ ስቀሰቅሰው ሙቶ ተገኘ ... በጓደኛው ሞት ድንጋጤ አልቻለም ነበር ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን የሚለውን ደጋግሞ ይል ነበር.... ጀናዛውን አጥበን ሰግደንበት ወደ ቀብር ቦታ ስንሄድ ሌላ አስገራሚ ነገር አገኘን ከትናንት ሞች ብኋላ ሌላ የሞተ ሰው አልነበረም ይህ ብዙ ጊዜ አያጋጥምም ነበር ከጓደኛው ቀብር ጎን ቀብረነው ተመለስን ✧ https://t.me/ALJUEDDAAWA
Hammasini ko'rsatish...
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ «በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ» ሀሳብ አሰተያየት ካለዎት ⇙ @AlJUDDAEWA_bot

👍 3
አንድ ወንድም አጋጣሚውን እንዲህ ይተርክልናል ። የሆነ ጊዜ ወንድሜ አዲስ ቤት ሰራና ለመዘየር ሄኩኝ በአዲሱ ቤቱ ወንድሜም በጥሩ መስተንግዶ ተቀበለኝና ጥሩ ጊዜ አሳለፍኩ ወደ ሰዓቱ ስመለከት ለኢሻ ሶላት ግማሽ ሰዓት ይቀር ነበር ...! ለወንድሜ ወደ መስጂድ መሄድ እንደምፈልግ ስነግረው ገና ነው አዛን አልተባለም አለ...? ሶላት እስኪደርስ ድረስ ቁርዓን እየቀራሁ እጠብቃለሁ ልሂድ ብየ ሄኩኝ ... ወደ መስጂድ ስደርስ መስጂዱ ባዶ ሁኖ አገኘሁት ቁርዓን አንስቼ መቅራት ጀመርኩ..! ከትንሽ ደቂቃ ብኋላ አንድ ልጅ ወደ መስጅድ በመግባት ሰላምታ አቀረበልኝና ሶላት ቆመ ሁለት ረከዓ ሰገደ አሰላመተ በድጋሜ ሶላት ቆመ ሱጁድ ላይ በጣም ይቆይ ነበር .... በሶላቱ በጣም ተገረምኩ በዚህ እድሜው በዚህ ልክ ኹሹእ ሲያደርግ አላህ ጋር ያለው ግንኙነት አስቀናኝ ። ሱጅድ ላይ ሲቆይ ምን እያለ ነው ብየ ጠጋ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ... ወደ ልጁ ተጠግቼ ሳዳምጠው ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ማልቀስ ጀመርኩ ጌታውን እንዲህ እያለ ሲጣራ ነበር... ያረቢ አባቴ የሆነ ነገር ሲቸግረን ወደዚህ እንድመጣ አደራ ብሎኛል.. እኔም ኢሄው እጅህ ላይ የተናነሰ ደካማ ራሀብተኛ የተቸገረ ሁኜ ቀርቤለሁ.... ያረቢ ትናንት ጀምሮ ምንም እንዳልበላን አንተም ታቃለህ .. ያረቢ ትናንሽ ወንድሞቼና እህቶቼ ረሀብን መቋቋም አይችሉም .. እኔና እናቴ ግን መቋቋም እንችላለን ... ነገር ግን ታናናሾቼ በረሀብ ምክንያት ሲያለቅሱ ሳይ ወደ አላህ ሂጄ የሚበላ እንዲሰጠን እጠይቀዋለሁ አልኮቸው! አባቴ እንዳስተማረኝ ያረቢ እባክህን እናቴና ታናናሾቼ ዘንድ አታሳዝነኝ እባክህን አንተ እኮ አሸናፊ ሀብታም አዛኝ በጣም ሩህሩህ መልካም ነገሮች በሙሉ በእጅህ ነው አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ ያረቢ የዱዓ አደራረጉ በጅጉ ልብ ይነካል እድሜው ገና አስር ቤት ቢሆንም ሁኔታው ልብ ይነካል አላህን ደጋግሞ ይለምናል ሱጁድ ላይ እያለ ታናናሾቹን አላህ ምግብ እንዲሰጣቸው እያለቀሰ ይማፀናል ። ሰወች መተው ኢሻን እስክንሰግድ ድረስ ተከታተልኩት ። ኢሻን ሰግደን ስንጨርስ ወንድሜን አገኘሁትና ይህ ልጅ ማነው ታቀዋለህ ወይ ስል ጠየኩት...? ወንድሜም አዎ አቀዋለሁ የመስጅዳችን ኢማም ልጅ ነው አባቱ ሙቷል አላህ ይዘንለት አለኝ ። የት እንደሚኖር ልጠቁመኝ ትችላለህ አልኩት ወንድሜም ታሪኩ ምንድን ነው አለኝ..? ምንም የለም ዝም ብለህ ቤቱን አሳየኝ ....! ከመስጅድ ወተን የልጁን ቤት አሳየኝ ወደ ሱቅ ሂጄ በርካታ የሚበላ ምግብና በርከት ያለ ገንዘብ በውስጡ አስቀምጫ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ቆሮቁሬ ቶሎ ተደበኩኝ! ልጁም ወደ ውጭ ወጣና ቀይና ግራውን ሲመለከት ማንም የለም ወደ ታች ሲመለከት ምግቡን አየው የተቆጠሩትን ምግቦች እየነካካ እንዲህ ሲል ጮሀ እናቴ ሆይ በርካታ ምግብ አገኘሁ አላህ አመጣልን .... በጣም ደስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ለአላህ ሱጁድ አደረገ ..... ✧ https://t.me/ALJUEDDAAWA
Hammasini ko'rsatish...
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ «በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ» ሀሳብ አሰተያየት ካለዎት ⇙ @AlJUDDAEWA_bot