የጥበብ እመቤት 📜
Kanalga Telegram’da o‘tish
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
272
Obunachilar
-124 soatlar
+77 kunlar
+15230 kunlar
Postlar arxiv
272
📚 አሁን መመልከትህ ብቻ ትርጉም የለውም
ዋናው በደምብ አትኩረህ ማየት መቻልህ ነው። ህይወት እንደዚ ነች።
ልፋትህ እና የዛሬው ስቃይህ ቀሪ ህይወትህን
በአሸናፊነት እንድትኖር ያደርጋል።
📚📚
✨✨🍿☕️🫖✨🍿☕️🫖✨
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 𝚒𝚜 𝚗𝚘𝚝 𝚐𝚒𝚟𝚎𝚗,
𝚋𝚞𝚝 𝚑𝚊𝚛𝚍 𝚠𝚘𝚛𝚔, 𝚍𝚎𝚝𝚎𝚛𝚖𝚒𝚗𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗,
𝚊𝚗𝚍 𝚊 𝚛𝚎𝚕𝚎𝚗𝚝𝚕𝚎𝚜𝚜 𝚜𝚙𝚒𝚛𝚒𝚝,
✨🍿☕️🫖✨🍿☕️🫖✨🍿☕️🫖
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
𝚝𝚑𝚎𝚛𝚎 𝚊𝚛𝚎 𝚗𝚘 𝚜𝚎𝚌𝚛𝚎𝚝𝚜 𝚝𝚘 𝚙𝚛𝚎𝚙𝚊𝚛𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗, 𝚑𝚊𝚛𝚍 𝚠𝚘𝚛𝚔,
𝚙𝚛𝚎𝚙𝚊𝚛𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗, 𝚑𝚊𝚛𝚍 𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚊𝚗𝚍 𝚕𝚎𝚊𝚛𝚗𝚒𝚗𝚐 𝚏𝚛𝚘𝚖
𝚏𝚊𝚒𝚕𝚞𝚛𝚎.
✨🍿☕️🫖✨🍿☕️🫖✨
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
የቃላት ወሳኝነት መረዳት
ሰዎች እውነተኛ አስተሳሰባችንን ልባችን፣ አዕምሯችን ውስጥ ገብተው ማየት አይችሉም፤ ከምንናገረው ከአፋችን ከሚወጣው ቃላት ተነስተው የራሳቸውን ድምዳሜ ይወስዳሉ። ለቃላቸው ዋጋ የማይሰጡ፣ ቃላቸውን የማያከብሩ ሰዎችን ማመን የለብንም፤ ሰው በቃሉ በንግግሩ ይመዘናል። ስለዚህ ከአፋችን ለሚወጡት ቃላት ዋጋ እንስጣቸው። ከመናገራችን በፊት በደንብ ማስብ ይኖርብናል።
ሰዎችን ለማስደሰት ማድረግ የማንችለውን ነገር ቃል አንግባ። ሁሌም እውነቱን እና እውነቱን ብቻ መናገር አለብን። የማይሆን ነገር ላይ ቃል መግባት አላስፈላጊ ችግር ውስጥ ሊከተን ይችላል። ሰዎች ከአፋችን በሚወጣው ቃል ይገመግሙናል እና ቃላትን እንምረጥ። የምንናገረው ሲኖረን እንናገር። ቃላት አጠቃቀማችንን የእኛነታችን መገለጫ ናቸው እና በጥንቃቄ እንምረጣቸው።
✨🍿☕️🫖✨🍿☕️🫖✨🍿☕️🫖
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
እራስን ከመውቀስ መታቀብ
እራስን አዘውትሮ መውቀስ እጅግ አደገኛ ነው። ይህን ክፍ ልማድ ከህይወታችን ፈንቅለን መጣል አለብን። ራስን መውቀስ እራሳችንን ከመጉዳት አልፎ በዙሪያችን ያሉ የቤተሰብ አባላት እና ወዳጆቻችንን ሊጎዳ ይችላል። ይህ ልምድ ካለብን በተደጋጋሚ እራሳችንን እንድንወቅስና ለራሳችን ያለን ክብር እንዲያሽቆለቁል ያደርጋል። ያለፈው አልፏል፣ ከስህተታችን ተምረን ወደፊት መጓዝ አለብን። ካለፈ በኋላ እራስን መውቀስ ጉዳት እንጂ ትርፍ የለውም። ስለዚህ እራስን ከመውቀስ መውጣት እና በህይወታችን ያሳካናቸውን ነገሮች እያሰብን እራሳችንን ማበረታታት ወደ በለጠ ስኬት ይመራናል።
🍿☕️🫖
272
ዓላማን አለመሳትና አለመዘንጋት
በዚህ አለም ከትኩረታችን የሚያዘናጉን ነገሮች ብዙ ናቸው። መዘናጋት ደግሞ የአንተ፣ የአንቺ ችግር ብቻ ሳይሆን የብዙዎች መሠረታዊ ችግር ነው። ስኬታማ ሰዎች ግን ከግባቸው ለሴኮንድ እንኳን አይዘናጉም። ከላይ እንደተጠቀሰው ቀናችንን በዕቅድ መጀመር እንዳንዘናጋ ያደርገናል። ያቀድነውን ነገር በሰዓቱ መከወን ይገባል። በተቻለንም መጠን በዕቅዳችን ላይ ባስቀመጥነው የጊዜ ማእቀፍ ስራችን መስራት አለብን። የሚያዘናጉንን ነገሮች መለየት እና ከእነርሱ መራቅ።
ለምሳሌ አዝናኝ የሆኑ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብለን በማየት መዝናናት እንችላለን። መዝናናት አስፈላጊ ነው፤ ሆኖም በስራ ሰዓት አልያም የሆነ የምንሰራው ነገር እያለ ጉዳያችንን ሳንፈፁም ቴሌቭዥን እያዩ መዋል ለኑሯችን ፋይዳ የለውም። ሰለዚህ ይህን የመሰሉ በሚያዘናጉ ነገሮች ውስጥ ከመዘፈቃችን በፊት ቆም ብለን ዓላማችንን ለማሳካት ምን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ መመዘን ይገባል።
🍎🍎🍎
272
እራስን ማወቅ
ስኬታማ ሰዎች እራሳቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ማን እንደሆኑ፣ ምን እንዳላቸውና ምን እደሚጎድላቸው በደንብ ይገነዘባሉ። ግባቸውን በጥንካሬያቸው፣ በችሎታቸው ዙሪያ ይቀርጻሉ። አለመቻላቸውን አምነው ይቀበላሉ። ከእነርሱ ለተሻሉት ዕድል በመስጠት ካሰቡበት ይደርሳሉ። ስኬታማ ሰዎች የማይችሉትን እችላለሁ ብለው ከመገበዝ ይልቅ ሁል ጊዜም ከሌሎች ለመማር ይጥራሉ። ድክመታቸውን ማወቃቸው እንዲሻሻሉ ያደርጋቸዋል። ድክመታቸውን አምነው ሰለሚቀበሉ ከሌሎች ጋር ተግባብተው መስራት ይችላሉ። እራስን ማወቅ ከስኬታማ ሰዎች ልንማረው የሚገባ ዓብይና ወሳኝ ባህሪ ነው። በሌሎች ምዕራፎች የበለጠ ትንታኔ ያገኛሉ።
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ህልሞቻችን ከፍርሀቶቻችን በላይ ግዙፍ ይሁኑ፤
ተግባራችን ከቃላቶቻችን በላይ ይናገሩ፤
ህይወታችን ካተናገርነው በላይ ስለኛ ይስበክ…
ስኬታችን ጫጫታችን ይሁን!
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ዝም!!! ያለ ዝምታ!!!
ከግርግር ዓለም ከብዙ ጫጫታ፣
ግርማ ሞገስ አለው ያስፈራል ዝምታ፣
ውል ከሌለው ጩኸት ከውሸት ፈግግታ፣
ልብን ይማርካል ጀግና ነው ዝምታ!!!
ከወሽካች ግርግር ከምላስ ጋጋታ፣
እኔን የሚያስፈራኝ ፀጥ ያለ ዘምታ!
ሳይደማመጡ በጋራ ከሚያብዱ፣
ዝም! ያለ ዝምታ! ቅኔ ነው ከባዱ!!
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
እናቴ ጨው ለመነች...
አጭር እና አስተማሪ ታሪክ።
እናቴ ግረቤታችን ጨው እንዲያበድሯት ስጠይቅ ሰማኋት። እኔም ተገርሜ ""እማየ በቤታችን እኮ በቂ ጨው አለ። ታድያ ለምን ጠየቅሻቸው"" አልኳት ?
#እናቴም እንዲህ አለቺኝ እነሱ ሁሌም የተለያዩ ነገሮች ❝እኛን ይጠይቁናል እንደምታውቀውም ድሀ ናቸው። ስለዚ እኔም እነሱ ብዙ የማይጎዳ ነገር ለመጠየቅ አስቤ የመጣልኝ ነገር ጨው ነው።የህን ያደረኩት እነሱ ላይ ጫና ለመፍጠር ሳይሆን እኛም እንደምንፈልጋቸው እንዲሰማቸው ብዬ ነው።
በዚ የፈለጉት ነገርን ያለ ህፍረት በቀላሉ መጠየቅ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ብዬ በማሰብ ነው ❞ አለቺኝ።እኔም በውስጤ ተገርሜ ለካ እንደዚህም ይደረጋል አልኩኝ።
አንዳንድ ጊዜ ደሞ ወደ ህይወታችን የሆኑ ሰዎች ይመጡና የሌለ ሁሉ ነገራችን ሳንጠየቅ እናወራችዋለን ለምሳሌ ስለባህርያችን ስለ ፍላጎታችን ምን አይነት ሰው እንደምንፈልግ በቃ ባጭሩ ምን ለማለት ፈልጌ ነው እኛ ላይ ሀላፊነት እንዲሰማቸው እና እንዲያዝዙን መንገድ እንከፍታለን ከዛ ያ ሰው በኛ ህይወት በነፃነት እንዲኖር ናደርጋለን ። እንደዛ ካላደረግን መጠየቅ ማውራት ማጋራት የሚፈልገው ነገሮች ቢኖርም ደብቆት በይሉኝታ ይኖራል ።ከዛ በማሀል አለማወቅ የመጋጨት ያለመግባባት የመሸሽ የመራቅ ይፈጠራል ።
በተቻለህ አቅም ለሰዎች በቀና መንገድ ምራቸው መንገድ አሳያቸው አንተ ላይ ነፃነት እንዲሰማቸው አድርግ።
🥀🥀🍿☕️🫖🥀🥀
272
አይናማው አይነ ስውር ..
ሁለት ሰዎች ብአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል ።ሁለቱም በጠና ታመሙ በአምላክ እጅ ተይዘዋል።
◍ አንደኛው ሳምባው የቋጠረው ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለስአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል። ከመስኮት አጠገብ ነው።
◎ሌላኛው ህመምተኛ ደሞ በተቃራኒ ለስአታት በጀርባው እኝዲተኛ ይደረጋል። እነዚ ሁሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጫውተዋል። ስለቤተሰብ ,ስለ ኑሮአቸው ,,በወታደር ቤት ለሰጡት አገልግሎት ,, የእረፍት ጊዝያቸው,,የት እንደሚያሳልፉ ወዘተ አውርተዋል።
◍ከመስኮቱ አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ስአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉም ነገር በጀርባ ለተኛ ሰው ይገልፅለታል።
በሚያማምሩ ፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል።በሀይቁ ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ ። ህፃናት ደሞ ከወረቀት የሰሩት መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ። ፍቅረኛሞች በአንድ እጃቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ።ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል ህፃናቶች በደስታ ይቦርቃሉ።በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ ይተርክለታል ።
✨በዚ ኣይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፈ ። አንድ ማለዳ ገላቸው ሊታጠቡ ውሀ ይዛ መጣች።
😭 ከመስኮቱ አጠገብ የነበረ ህመምተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲህ አዘነ።ሬሳው በተሎ እንዲያነሱ ሌሎች ነርሶች ጠርታ አዘዘቻቸው።
◎ያብቻው የቀረው በጀርባው የተኛ በሽተኛ አልጋው ከመስኮት አጠገብ እንዲወሰድለት ጠይቆ ወሰድለት ።ሟች የነገረው በሙሉ በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩለዋል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድ ግዳ ብቻ ነው።ደነገጠ ምን ሁነክ ነው አለቹው ነርስዋ።
ሰውዬው ብዙ መስኮት አስደሳች ነገሮች ይመለከት ነበረ አላት።
😥 #አረ_ሰውየው_ኮ _ማየት የማይችል_አይነ_ስውር_ነበረ ስትል በመገረም መለሰችለት ።ልብ የሚነካ ነገር ስቅ ስቅ ብሎ አለቀሰ።
🌿 #ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።
💪 አንድን ለማጠንከር ወይም ለማበርታተሰ የኛ ጥንካሬና ብርታት አስፈላጊ ነው።
#ለሰዎች ቀናና ደግ ነገር በማድረግ የተጨነቀ አይሙራቸው እረፍት እንስጥ።
🍎 ታሪኩን እንደወደዳቹት አልጠራጠርም
🥀🥀🍿☕️🫖🥀🥀
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
ልብህ በምስጋና ሲሞላ የህይወት ውበት መገለጥ ይጀምራል!
በህይወት ውስጥ ልብን ከሚሞሉ ነገሮች አንዱ የምስጋና ስሜት ነው።
የምስጋና ስሜት ማለት ያለህን ነገር ማድነቅ፣ በዙሪያህ ያሉትን መልካም ነገሮች ማስተዋል እና በውስጥህ ሰላምን መፍጠር ማለት ነው።
በችግሮች እና ውጥረቶች ተወስደን ያለንን መልካም ነገሮች መዘንጋት እንችላለን። ነገር ግን ለማመስገን የሚያስችሉን ብዙ መልካም ነገሮች ሁልጊዜም አሉ።
ለምስጋና ብዙ መነሻዎች አሉ።
ፀሀይ ስትወጣ፣ ወፎች ሲዘምሩ፣ ንጹህ አየር ስትተነፍስ... እነዚህ ሁሉ በየቀኑ የምናገኛቸው ግን ብዙ ጊዜ የማናስተውላቸው ውበቶች ናቸው።
የምስጋና ስሜትን በህይወትህ ውስጥ ማካተት ብዙ መንገዶች አሉት።
በምስጋና ስሜት መኖር የህይወትን ውጣ ውረድ በቀናነት እንድንመለከት ይረዳናል። ደስተኛነትም ይሁን ስኬታማ ለመሆን የምስጋና ስሜት የጉዞው ወሳኝ አካል ነው። ልብህ በምስጋና ሲሞላ የህይወት ውበት መገለጥ ይጀምራል።
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12
272
አንዳዴ ነገሮችን ለመቀየር ከመታገል ይልቅ መተው እና ምን እንደሚፈጠር መመልከት ያ ማለት ለነገሩ ትኩረት አለመስጠት ሳይሆን ለሁሉም ጥያቄ ፈጣሪ መልስ አለው እና ለእርሱ መስጠት ነው እኛ ከተጨነቅነው በላይ ውብ አድርጎ ይፈታዋል እና ሲጨንቃችሁ ለእርሱ ስጡት ።
✨🍿☕️🫖✨
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
✨ ከውድቀታችንን ማገገም
🌿ስኬት እና ውድቀት ሁሌም በዙሪያችን ናቸው። በህይወታችን ውድቀትን መፍራት የለብንም። የተሳካላቸውን ሰዎች ብንመለከት ብዙ ጊዜ ወድቀው ተነስተዋል። ስኬታማ ሰዎችን ከሌሎች የሚለያቸው ከውድቀታቸው ቶሎ ማገገማቸው ነው። ከውድቀቸው እየተማሩ እንደ አዲስ መጀመር ሲኖርባቸው ይጀምራሉ እንጂ ተስፋ አይቆርጡም። እኛም ውድቀት ሲያጋጥመን ቁጭ ብለን ከመጸጸት ይልቅ ከወድቀታችን ተምረን አንገታችንን ቀና አድርገን ጉዟችንን መቀጠል አለብን።
🥀🍿☕️🫖🍿☕️🫖🥀
🌺🌸🌺መልካም ቀን🌺🌸🌺
🌺🌺🌺☕️
🌸🌸🌸☕️
🌺🌺🌺☕️
🌸 🌸🌸☕️
🌺🌺🌺☕️
🌸🌸🌸☕️
🌺🌺🌺☕️
🌸🌸🌸☕️
🌺🌺🌺☕️
🌸🌸🌸☕️
✍️https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ሁሉንም ማስደሰት አይቻልም
በህይወታችን ስህተት የምንሰራው ሁሉንም ሰው ለማሰደሰት ስንሞክር ነው። እንዲህ ለማድረግ ስንሞክር ከዓላማችን እንስታለን፣ በራሳችን ያለን እምነት ይቀንሳል። የማናምንበትን ነገር እንዳናደርግ ከሚያስገድዱን ነገሮች አንዱ ሁሉን ለማስደሰት የመሞከር መጥፎ አባዜ ነው። አንዳንድ ውሳኔዎቻችን ወደድንም ጠላንም የተወሰነውን ሲያስደስቱ፣ የተወሰኑትን የቅርብ ወዳጆቻችንን ሊያስከፉ ይችላሉ። ይህ ሁሌም የሚኖር የህይወት ዑደት ነው።
በዚህ ዓለም ማስደሰት የሚቀለው እራስን ብቻ ነው። በእራሳችን እንደሰት። በእኛ ደስታ ውስጥ በራስ መተማመናችን ጎልቶ ይወጣል። ይህ ሲሆን ሌሎች ስለ እኛ የሚያስቡት ቅንጣት አያስጨንቀንም። ማሰብ ያለብን ሁሉንም ሰው ስለማስደሰት ሳይሆን ትክክል የመሰለንን ነገር ሌሎች ሰዎችን ሆነ ብለን ሳንጎዳ ስለ መወሰን ነው።
272
የሚደረስባቸው ግቦች መቅረጽ
ከአቅማችን በላይ የሆኑ እጅግ የተለጠጡ ግቦች መቅረጽ ላለአስፈላጊ ጭንቀት ይዳርጉናል። የምንፈልገውን ውጤት ከማምጣት ይልቅ እራሳችንን እንድንወቅስና እንድንፀፀት ያደርጉናል። የምንቀርጻቸው ግቦች አቅማችንን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው። በዙ ጊዜ ቁጭ ብለን ስናስብ በአዕምሮአችን የሚመጣው ሀሳብ፣ በ24 ሰዓት ብዙ ነገር ማከናወን እንደምንችል ነው። ይህ ደግሞ ከእውነታው ይርቃል።
በጣም የተለጠጡ እና ከአቅማችን በላይ የሆኑ ግቦች ለውጤት ከማነሳሳት ይልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ። ብዙ ጊዜ ያለንን ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ዕውቀት እና የመሳሰሉት ሀብቶችን ያላገናዘቡ ዕቅዶች ስለምናቅድ፣ ከዕቅዳችን አንድ ሶስተኛውን እንኳን ማከናወን ከባድ ይሆንብናል። ስለዚህ በልካችን ልንደርስበት የምንችላቸውን ግቦች በመቅረጽ ለስኬት መስራት ይኖርብናል። ይህም ጭንቀትን አርቆ መነቃቃትን ፈጥሮ ለበለጠ ስኬት ያነሳሳናል።
🥀🍿☕️🫖🥀
https://t.me/successseket
