uz
Feedback
የጥበብ እመቤት 📜

የጥበብ እመቤት 📜

Kanalga Telegram’da o‘tish

╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️‍🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
272
Obunachilar
-124 soatlar
+77 kunlar
+15230 kunlar
Postlar arxiv
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ትዕግስትና ፅናት የምኞታችን መሠረቶች ናቸው ። በሕይወት ጉዞ ውስጥ ስኬት በአንድ ጀምበር የሚገኝ ድል ሳይሆን፣ የብዙ ውጣ ውረዶች ውጤት ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ሁለት
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ትዕግስትና ፅናት የምኞታችን መሠረቶች ናቸው ። በሕይወት ጉዞ ውስጥ ስኬት በአንድ ጀምበር የሚገኝ ድል ሳይሆን፣ የብዙ ውጣ ውረዶች ውጤት ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ሁለት ታላላቅ መሣሪያዎች ያስፈልጉናል፦ ትዕግስት እና ፅናትትዕግስት (Patience) ትዕግስት ማለት ዝም ብሎ መጠበቅ ሳይሆን፣ በሚጠብቁበት ጊዜ ትክክለኛውን አመለካከት ይዞ መቆየት ነው። ዘር ተዘርቶ ወዲያው እንደማይታጨደው ሁሉ፣ ሕልሞችም ፍሬ ለማፍራት ጊዜ ይፈልጋሉ። ትዕግስት በፈተናዎች መካከል ስንገፋ ትክክለኛውን ውሳኔ እንድንወስንና አቅጣጫችንን እንዳንስት ይረዳናል። ፅናት (Perseverance) ፅናት ደግሞ እንቅፋቶች ቢበዙም ጉዞን አለማቆም ነው። በወደቅንበት ቁጥር የመነሳት፣ በደከመን ጊዜ የማረፍ እንጂ ያለመተው ጥበብ ነው። ፅናት ካለ፣ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች ሁሉ የሚቻሉ ይሆናሉ። ታላላቅ ስኬቶች የተመዘገቡት ከአቅም በላይ በሆኑ ፈተናዎች ውስጥ በፀኑ ሰዎች ነው።
"ትዕግስት መራራ ናት፤ ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ነው።"
#Never_give_up https://t.me/payattetion12

ሀገር እንደሌለን ... ድህነት ልናመልጥ በሰው ሀገር ተሯርጠን ,, ቀን ቢጥል በጨላማ ተረግጠን,, ተደፈረን እህቶቻችን ተገደድ,, አባት የሌለው ዲቃላ ወለድ,, ተናቅን ወንድሞቻችን ተገረፉ,, እድሚያቸው በእስር ቤት አሳለፉ,, ተስፋችን ተቀጨ,, ህይወታችን ተቋጨ,, ህልማችን ቅዠት ሆነ ,, በሰው ሀገር ተበድሎ... እንዳልሆነ,, ( ደግሞም አለን ) ከመከራው ሀገር ሳይደርሱ,, በእባብ መርዝ የተነከሱ,, በሻሩክ ምላስ የተላሱ,, በገጀራ የተቀደድ በጥይት የተበሱ,, አካላቸው የተሸጠ ተበልቶ,, ለጥንብ አንሳ ጥንብ ሆነ ሬሳችን ሸቶ,, እናት አባት አያውቁ,, ልጆቻቸው እንዴትና ነት እንደወደቁ,, በድህነት ተኮማትሮ በናፍቆት ሲማቅቁ,, የማይመጣ .የማትመጣ . የማይመጡ ሲጠብቁ,, ብቻ ድህነት ነው ጠላታችን ለኛ,, ብቻ አለማወቅ ነው የከፋብን እኛ,, ሀገራችንማ ምን አንስቷት ተፈጥሮ,, ተስማምተን ብንኖር ብንሰራበት ኑሮ,🥹 ✍️ስደተኛዋ

𝙞𝙛 𝙮𝙤𝙪 𝙬𝙖𝙣𝙩 𝙩𝙤 𝙢𝙖𝙠𝙚 𝙖 𝙥𝙚𝙧𝙢𝙖𝙣𝙚𝙣𝙩 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙜𝙚.𝙨𝙩𝙤𝙥 𝙛𝙤𝙘𝙪𝙨𝙞𝙣𝙜 𝙤𝙣 𝙩𝙝𝙚 𝙨𝙞𝙯𝙚 𝙤𝙛 𝙮�
𝙞𝙛 𝙮𝙤𝙪 𝙬𝙖𝙣𝙩 𝙩𝙤 𝙢𝙖𝙠𝙚 𝙖 𝙥𝙚𝙧𝙢𝙖𝙣𝙚𝙣𝙩 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙜𝙚.𝙨𝙩𝙤𝙥 𝙛𝙤𝙘𝙪𝙨𝙞𝙣𝙜 𝙤𝙣 𝙩𝙝𝙚 𝙨𝙞𝙯𝙚 𝙤𝙛 𝙮𝙪𝙤𝙧 𝙥𝙧𝙤𝙗𝙡𝙚𝙢𝙨 𝙖𝙣𝙙 𝙨𝙩𝙖𝙧𝙩 𝙛𝙤𝙘𝙪𝙨𝙞𝙣𝙜 𝙤𝙣 𝙩𝙝𝙚 𝙨𝙞𝙯𝙚 𝙤𝙛 𝙮𝙤𝙪 !! 🍿☕️🫖🥀 https://t.me/successseket

ህይወት  ትምህርት ቤት ናት.... ◍የታየህ አሳይ " ያልታየህን አጣራ። ◍በደምብ ያልተረዳከው አታስተምረው። ◍ ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ◍ የሰማከው ሁሉ አትመን ◍ያየከው ሁሉ ስጡኝ ያየሆው ሁሉ ፍፁም አትበል። ◍ የሰጠከው እርሳ እንጂ አታውራ። ◍ፍፃሜው ሳታይ አታመስግን ◍ ነገ ላይ እንድትደርስ የትላንቱ አትርሳ ◍ የምትሄድበት እንዳይጠፋብህ የመጣህበት አትዘንጋ ◍ የአባቶች መልካም ስራ አብነት አድርግ። ◍ካሳለፉት ህይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ◍ክፋት አይሙቅህ መልካም ነገር ብርድ ብርድ አይበልህ ◍ ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገር አቅም አለህናተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት። ◍ ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብ ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉም ነገር ገንዘብ ያስገኛል ብለህ አታስብ። ◍ላለው አትሩጥ ምፅዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ◍ድሀም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ◍በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። ◍ያንተን ድርሻ ከጨረስክ ያልተጨረሰ የሌሎች ድርሻ ፈፅምላቸው። ◍ለሀብታም አትሳቅ የድሀ ጉልበት አይለፍብህ። ◍ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ። 👉 የወጣህበት መሳልል አትገፍትር ለመውረድ ያስፈልግሀል። ◍ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ባልጠሩህ ስፍራ አቤት አትበል ◍እውር እንዳይሉህ ያልታየኽ አያለሁ አትበል ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህ ጭኮት ሰማለሁ አትበል። ◍ንፍግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል። ◍ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህ እንደገባህ አድርገህ አትለፍ። ◍አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበት እንደ ኖርክበት አትቁጠረው። ◍ስልጣን ሲሰጥህ መሬ እንጂ አለቃ አትሁን። 👉 ከፊት እየቀደምክ አስከትል እንጂ ከኋላ ሁነህ አትቅደም። ◍በዓላማ ኑር እንቅፋቶች የሚያፀኑህ እንጂ ተግባርህ የሚያስተውህ አይሆኑም። ◍ህይወት ትምርት ቤት መሆኑ ባለ ማወቅ ብዙ ትምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ። ◍የመከራ ቀን ወዳጅህ አትርሳ። የዛሬው  ሰው ብቻ አትሁን የትላንቱን አስብ። አንገት የተፈጠረው ዙሮ ለማየት ነውና  ። 👉 ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፀሀይ ዝናብ ተከትላ ትፈነጥቃለች። #ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆነሀልና በርታ። የተመቻቹ እና የሄ ምታምኑበት በ like 👍 አሳውቁኝ 😳 🍎 መልካም የንባብ ጊዜ🍎🍿☕️🫖

ትልቅ ነገር ተመኝ... በአይምሮህ ውስጥ ትልቅ ነገር አስብ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ እኛ የምንሆነው በአይምሯችን ውስጥ በምስጢር የምናስበው ነው። ለዚህም ነው ሰዎች የሚታዩበት ቦታ ሳይሆን የማይታሰቡበት ቦታ የሚደርሱን። ህይወት ትርጉም የሚኖራት ሁሌም ንቁና ጠንካራ ስንሆን ግብ ስናዘጋጅ እና በየጊዜው ዓላማችን ከግብ ለመድረስ የሚያስፈልገውን መስዋአትነት በዘላቂነትና በቁርጠኝነት ስንከፍል ነዌ። ብዙ ጊዜ ደስታ ማጣት በህይወት ግልፅ የሆኑ ትርጉምና ዓላማ ከማጣት ይመጣል። 🌿 እያንዳንድ የሚገጥሙን ፈተናዎች ህይወትን ተወዳጅ የሚያደርጓት መጣፈጫ ቅመም ናቸው። ህይወትን ትርጉም ያላት የምናደርጋት ደሞ የሚሰነዘሩበትን ፈተናዎች በብቃትና በስሌት መቋቋም ስንችል ነው። 🌿 ለመለወጥን ካሰብን ግልፅ የሆነው ግብ እና በራስ የመተማመን መንፈስም ሊኖረን ይገባል። የስኬታማነት አንድ አስፈላጊ ሚስጢርበራስ መተማመን ነው በራስ ለመተማመን አስፈላጊ መሳርያ ደግሞ የማያቋርጥ ዝግጅትነት ነው። በራስ ላይ እምነት ማጣት ከሌሎች ውጫዊ እንቅፋቶች ይልቅ የአንድ ሰው አቅምና ችሎታ ሸባ ያደርጋል። 🍿☕️🫖🥀 https://t.me/successseket

#ለመኖር ስትል ትናንት የጣሉህን ትዝታዎች ወደሀላ ትተህ፣ ዛሬ ለሚፈነጥቀው አዲስ ተስፋ እጅህን መስጠት አለብህ። በውስጥህ ✅የሚነደውን የጥርጣሬ እሳት በፅናትና በውስጣዊ ሰላም እያበረድክ፣ እያንዳን
#ለመኖር ስትል ትናንት የጣሉህን ትዝታዎች ወደሀላ ትተህ፣ ዛሬ ለሚፈነጥቀው አዲስ ተስፋ እጅህን መስጠት አለብህ። በውስጥህ ✅የሚነደውን የጥርጣሬ እሳት በፅናትና በውስጣዊ ሰላም እያበረድክ፣ እያንዳንዱን ፈተና የጥንካሬህ መማሪያ ልታደርገው ይገባል። ኑሮ ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ ባይሆንም፣ በነስጋትና በደስታ መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ 🌱መጓዝ የህይወት ትልቁ ጥበብ ነው። ራስህን ሳታጣና ማንነትህን ሳትቀይር፣ ለነገው ማንነትህ የተሻለ መሠረት ለመጣል በየቀኑ በፈገግታ መደፈር ያስፈልጋል። ምክንያቱም መኖር ማለት እንዲሁ መተንፈስ ብቻ ሳይሆን፣ በችግሮች ውስጥ አልፎ የራስን የህይወት ትርጉም በራስ ቀለም መሳል ማለት ነው።🌺 🍿☕️🫖 #Never_give_up https://t.me/successseket

እኔ ማውቀው አለማወቄ ነው... ብዙ ነገር ለመማር መሞከር እይታህ ይሰፋል። የእይታህ አድማስ ሲሰፋ ደግሞ አንተ እያነስክ ነው ምትሄደው። ሰፊ ከሆነው ዓለም አንተ ምን ያህል ኢምንት እንደሆንክ ትረዳ
እኔ ማውቀው አለማወቄ ነው... ብዙ ነገር ለመማር መሞከር እይታህ ይሰፋል። የእይታህ አድማስ ሲሰፋ ደግሞ አንተ እያነስክ ነው ምትሄደው። ሰፊ ከሆነው ዓለም አንተ ምን ያህል ኢምንት እንደሆንክ ትረዳለክ ። እያወቅክ ስትሄድ ትልቅነትህ ሳይሆን ትንሽነትህ ነው ምትረዳው። እያወቅክ ስትሄድ በዓለም ዙርያ በተፈጠረው እውቀት ውስጥ አንተ ትንሽ መሆንክ ይገበሀል። 🍿☕️🫖🥀 https://t.me/successseket

🥺 በ30 ዓመቱ ሞተ በ60 ዓመቱ ተቀበረ.... አንድ ሰው ቀትርፍ ጊዜው ቡዙ ሙታን ወደተቀበሩበት መቃብር ስፍራ ላይ የተፃፈፉትን ፅሁፎች በማንበብ ላይ ሳለ በአንድ ሰው መቃብር ላይ አንድ ግር የሚል ፅሁፍ አነበበ.... ፁሁፉ በ30 ዓሠቱ ሞተ በ60 ዓመቱ ተቀበረ ይላል ። ግር ብሎት ማስተዋል ጀመረ እንድ ሰው በ30 ዓመቱ ሞቶ እንዴት በ 30 ዓመታት ሳይቀበር ሊቆይ ቻለ? የሄ እያሰበ የፅሁፍ ትርጉሙ የሚያውቅ አንድ ሰው ደረሰ። ምን እንደምታስብ ገብቶኛል "" አለው ፅሁፉን እያነበበ 🥺 የሄ ሰው እጅግ በጣም የሚያስገርም ራእይና ዓላማ የነበረው ሰው ነበር። ብዙ ነገሮች የመስራት እቅድ የነበረውና በዚ ትጋቱ በህብረተሰብ ዘንድ እጅግ የታወቀና ለትልቅ ነገር የሚጠበቅ ሰው ነበረ። ልክ 30 ዓመቱ ሲሞላው በተለያዩ ወጣ ውረዶች በማለፍ ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ዓላማው ሁሉ ትቶ ከርታታ ሰው ለመሆን በቃ ።የሚቀጥለው 30 ዓመታት እንዲሁም በየ ቦታው ሲንቀዋለል ነው ያሳለፈው ካለ ምንም ዓላማ። የፅሁፉ ትርጉም የሄ ነው። 🌿 ሰውየው ሞተ ብለው የሚያምኑት ራአዩ በጣለበትና ጊዜው በተራ ነገር ማሳለፍ በጀመረበት በ30 ዓመቱ ነው። በአካል ቢኖርም ሙቷል ነው አባባላቸው። ልክ በ60 ዓመቱ ታምሞ አካላዊ ሞት ሲሞት ያን ጊዜ ተቀበረ ማለታቸው ነው ። በአካል መኖር ብቻው ኖሯል አያስብልም ነው። ህያው የሚያደርገን ረአይና የመኖር ዓላማ እንጂ ቆሞ መሄድ አይደለም። ቆሞ ለመሄድ በአራት እግር ሆኖ እንጂ አህያም ይሄዳል። አህያ ግን የሰው ስራ ከማቅለል ውጪ የራሱ ራአይ የለውም። ስለሌለው የሌሎች ባርያ ሁኖ ይኖራል። ዓላማ የለሽ ህይወት ሞት እንጂ ህይወት አይደለም። ዓላማ አልባ ሰውም ለመቅበር ነፋሱ ከስጋው እስክትነጠል ይጠብቃል እንጂ ሙትማ ሙት ነው። ሰውን ህያው ሚያደርገው #ህልሙ_ነው_የሚል ይመስላሉ_ፀሀፊዎች ።ልክ ነው !!
ዓላማ ያለው ሰው መሆንና በዓላማው ሚፀና ሰው መሆን ሁለቱ #የስኬት ቁልፎች ናቸው። ስኬታማ ሰዎች ባለ ራዓይ ናቸው ለፈተናም ሁነ ለየተኛው ነገር በቀላሉ እጅ አይሰጡም ። እጅ አለመስጠታቸው የህያውነት ምልክት ፤ የስኬታቸው ጠቋሚ ነው ። ከዓላማ ውጭ የሚኖር ህይወት ከህይወት አይቅጠርም።
#Never_give_up ✍️ https://t.me/successseket

ኪሳራን አለመፍራት ( 𝙧𝙞𝙨𝙠 𝙩𝙖𝙠𝙚𝙧𝙨 ) ስኬታማ ሰዎች ኪሳራን አይፈሩም። ይልቁንም ስኬትን በማሰብ ሌሎች የማይደፍሩትን ሀሳብ ይደፍራሉ። ኪሳራን የሚፈሩ ሰዎች ደግሞ ከቆሙበት ፈቀ
ኪሳራን አለመፍራት ( 𝙧𝙞𝙨𝙠 𝙩𝙖𝙠𝙚𝙧𝙨 ) ስኬታማ ሰዎች ኪሳራን አይፈሩም። ይልቁንም ስኬትን በማሰብ ሌሎች የማይደፍሩትን ሀሳብ ይደፍራሉ። ኪሳራን የሚፈሩ ሰዎች ደግሞ ከቆሙበት ፈቀቅ ሳይሉ አመታት ያልፋሉ። እነርሱ ፈርተው የተውትን ሀሳብ ሌሎች ኪሳራ የማይፈሩ ሰዎች ተጠቅመውበት ሲያዩ በፀፀት ይንገበገባሉ። ኪሳራን አለመፍራት ማለት ግን ግልብ የሆነ ውሳኔ በመወስን ኪሳራ ውስጥ መግባትን አያካትትም። ድፍረታችን በመረጃ እና በስሌት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። ኪሳራን አለመፍራታችን ያላየናቸውን መልካም አጋጣሚዎች አጥርተን እንድናይ ዓይናችንን ይከፍትልናል። ለምሳሌ የአፕል መስራች ስትቭ ጆብስ ኪሳራን አለመፍራትና በጥናት ላይ የተመሰረተ ድፍረት አይፎን የተባለውን ዝነኛ ስልክ እና ሌሎች ተወዳጅ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ለአለማችን አስገኝቷዋል። #Never_give_up ✍️https://t.me/successseket

🛑 የድብርት ስሜት መንስኤዎች .... 🌿 ድብርት ስሜት እና የመንፈስ ጭንቀት ዋነኛ መንስኤዎች ምንድናቸው ❓ ◍ ያለፈው ታሪክና ያለፈው ጥቃት በሞት የምንወዳቸው ሰዎች ማጣት። ◍ ባለፊው ነገሮች
🛑 የድብርት ስሜት መንስኤዎች .... 🌿 ድብርት ስሜት እና የመንፈስ ጭንቀት ዋነኛ መንስኤዎች ምንድናቸው ❓ ◍ ያለፈው ታሪክና ያለፈው ጥቃት በሞት የምንወዳቸው ሰዎች ማጣት። ◍ ባለፊው ነገሮች መሸማቀቅና ማፈር እንዲሁም መፀፀት። ◍ የተለያዩ ስሶችና የአልኮል መጠጦች። ◍ ከሰዎች ጋር መጣላት ◍ስራ ማጣት ◍ በስራ ላይ ስኬት ማጣት። ◍ ብቸኝነትና ጓደኛ ማጣት ። ◍ አሰልቺና ድግግሞሽ ህይወት መኖር። ◍ በሴት ላይ በሆርሞን መለዋወጥ በእርግዝና እና በሚኒስትሬሽን ወቅት። ◍ እንቅልፍ ማጣት ◍ በስራ ላይ መጨናነቅ ማብዛት። ◍ መረበሽና መናደድ ◍ የራስ ምታት ህመም ። 🛑 ከድብርት መንሴኤዎች ጥቂቶች እነዚ የመስላሉ።

🦋 የሙድ መዋዠቅና ብስጩ መሆን 🦋 የተለመደ ስራችን ለመስራት ፍላጎት ማጣት 🦋 ሀሳባችን ለመሰብሰብ መቸገር 🦋 ውሳኔ ላይ መድረስ መቸገር 🦋 የምንወደው ላይ ፍላጎት ማጣት 🦋 ከሰው መራቅና
🦋  የሙድ መዋዠቅና ብስጩ መሆን 🦋 የተለመደ ስራችን ለመስራት ፍላጎት ማጣት 🦋  ሀሳባችን ለመሰብሰብ መቸገር 🦋 ውሳኔ ላይ መድረስ መቸገር 🦋 የምንወደው ላይ ፍላጎት ማጣት 🦋 ከሰው መራቅና ለብቻ ጊዜ ማሳለፍ 🦋 መፍዘዝና እና ትኩረት ማጣት 🦋 ድካምና ራስ ምታት 🦋 ራስህን ለመጠበቅና ለምግብ ፍላጎት ማጣት 🦋 ትካዜና ሀዘን ማብዛት በፀፀት ራስ መውቀስ 🦋  ነገሮች ወደ መጥፎ መተንተን 🦋  ብሞት ይሻለኛል እና ራስ  ስለ ማጥፋት ማሰብ 🦋  መጥፎ ሰው ነኝ ብሎ ማሰብ 🦋 ዝቅተኛ ስሜት ለራስ መስጠት 🦋 ጉልበት ማጣትና ደስታ ከራሳችን ማራቅ የድብርትና የጭንቀት ስሜት ምልክት ናቸው

😞 ዝም ያለ ዝምታ ከግርግር ዓለም ከብዙ ጫጫታ ግርማ ሞገስ አለው ያስፈራል ዝምታ፣ ውል ከሌለው ጩኸት ከውሸት ፈግግታ፣ ልብን ይማርካል ጀግና ነው ዝምታ ከወሽካች ግርግር ከምላስ ጋጋታ፣ እኔን የሚ
😞 ዝም ያለ ዝምታ ከግርግር ዓለም ከብዙ ጫጫታ ግርማ ሞገስ አለው ያስፈራል ዝምታ፣ ውል ከሌለው ጩኸት ከውሸት ፈግግታ፣ ልብን ይማርካል ጀግና ነው ዝምታ ከወሽካች ግርግር ከምላስ ጋጋታ፣ እኔን የሚያስፈራኝ ፅጥ ያለ ዘምታ! ሳይደማመጡ በጋራ ከሚያብዱ፣ ዝም! ያለ ዝምታ! ቅኔ ነው ከባዱ

➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ትዕግስት ማለት አንድ ነገር እስኪሳካ ድረስ መጠበቅ ወይም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በጽናት መቋቋም ነው። ትዕግስት የጥበብ ምልክት ሲሆን፣ በህይወት ውስጥ የሚገጥሙንን ፈተናዎች እ
#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ትዕግስት ማለት አንድ ነገር እስኪሳካ ድረስ መጠበቅ ወይም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በጽናት መቋቋም ነው። ትዕግስት የጥበብ ምልክት ሲሆን፣ በህይወት ውስጥ የሚገጥሙንን ፈተናዎች እንድንቋቋም ይረዳናል። ችኮላ ሳይኖርበት በትዕግስት የሚሰራ ሰው የተሻለ ውጤት የማግኘት እድሉ ሰፊ ነው። ትዕግስት ሰላምን ያመጣል፣ ጭንቀትን ይቀንሳል፣ እና ለተሻለ ውሳኔ እንድንደርስ ያስችለናል። ታጋሽ ስንሆን፣ ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለማየት እና መፍትሄ ለማግኘት እንችላለን። ትዕግስት ለስኬት ወሳኝ መሠረት ሲሆን፣ በግል ህይወታችንም ሆነ ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ትልቅ ሚና ይጫወታል። #Never_give_up https://t.me/payattetion12

𝙩𝙝𝙚 𝙣𝙤. 𝙞 𝙧𝙚𝙖𝙨𝙤𝙣 𝙥𝙚𝙤𝙥𝙡𝙚 𝙛𝙖𝙞𝙡 𝙞𝙣 𝙡𝙞𝙛𝙚 𝙞𝙨 𝙗𝙚𝙘𝙖𝙪𝙨𝙚 𝙩𝙝𝙚𝙮 𝙡𝙞𝙨𝙩𝙚𝙣 𝙩𝙤 𝙩𝙝𝙚𝙞𝙚𝙧
𝙩𝙝𝙚 𝙣𝙤. 𝙞 𝙧𝙚𝙖𝙨𝙤𝙣 𝙥𝙚𝙤𝙥𝙡𝙚 𝙛𝙖𝙞𝙡 𝙞𝙣 𝙡𝙞𝙛𝙚 𝙞𝙨 𝙗𝙚𝙘𝙖𝙪𝙨𝙚 𝙩𝙝𝙚𝙮 𝙡𝙞𝙨𝙩𝙚𝙣 𝙩𝙤 𝙩𝙝𝙚𝙞𝙚𝙧 𝙛𝙩𝙞𝙣𝙙𝙨..𝙛𝙖𝙢𝙞𝙡𝙮 𝙖𝙣𝙙 𝙣𝙚𝙞𝙜𝙝𝙗𝙤𝙧𝙨.. 𝙮𝙚𝙨 👍 𝙤𝙧 𝙣𝙤 😡

𝙨𝙤𝙢𝙚 𝙥𝙚𝙥𝙤𝙡𝙚 𝙖𝙙𝙫𝙞𝙨𝙚 𝙮𝙤𝙪 𝙬𝙝𝙖𝙩 𝙩𝙤 𝙙𝙤 𝙖𝙣𝙙 𝙨𝙤𝙢𝙚 𝙥𝙚𝙤𝙥𝙡𝙚 𝙛𝙤𝙧𝙗𝙞𝙙 𝙬𝙝𝙖𝙩 𝙣𝙤𝙩 𝙩𝙤 �
𝙨𝙤𝙢𝙚 𝙥𝙚𝙥𝙤𝙡𝙚 𝙖𝙙𝙫𝙞𝙨𝙚 𝙮𝙤𝙪 𝙬𝙝𝙖𝙩 𝙩𝙤 𝙙𝙤 𝙖𝙣𝙙 𝙨𝙤𝙢𝙚 𝙥𝙚𝙤𝙥𝙡𝙚 𝙛𝙤𝙧𝙗𝙞𝙙 𝙬𝙝𝙖𝙩 𝙣𝙤𝙩 𝙩𝙤 𝙙𝙤 𝙗𝙪𝙩 𝙩𝙝𝙚 𝙜𝙚𝙣𝙪𝙞𝙣𝙚 𝙥𝙚𝙤𝙥𝙡𝙚 𝙟𝙪𝙨𝙩 𝙖𝙨𝙠 𝙮𝙤𝙪 𝙞𝙛 𝙩𝙝𝙚𝙮 𝙘𝙖𝙣 𝙙𝙤 𝙖𝙣𝙮𝙩𝙝𝙞𝙣𝙜 𝙛𝙤𝙧 𝙮𝙤𝙪..... https://t.me/successseket

🌿 ሳያቋርጡ መሞከር፣ ተስፋ አለመቁረጥ ቶማስ ኤዲሰን አምፖልን ለመፍጠር 1000 ጊዜ እንደሞከረ ይነገራል። ከ1000 ሙከራዎች በኋላ ተሳክቶለት አምፖልን ፈጥሯል። ቶማስ ሰለቸኝ ብሎ ሙከራውን መሀል ላይ አላቋረጠም፣ ተስፋ ሳይቆርጥ ተጋ። ስኬታማ ሰዎች በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጡ ሰዎች አይደሉም። በጨለማ ውስጥ እንኳን ሆነው ትንሿን የብርሃን ጭላንጭል አሻግረው ማየት ይችላሉ። ሁኔታዎች ምቹ ሲሆኑም ሳይሆኑም የጀመሩትን ከግብ ለማድረስ ይተጋሉ። የስኬት ጉዞ በውጣ ዉረድ የተሞላ መንገድ ነው፤ ስኬታማ ሰዎች ሁሌም ውድቀት በዙሪያቸው እንዳለ ያምናሉ።ለስኬታማ ሰዎች መውደቅ የስኬት ዋዜማ ነው። ከውድቀታቸው እየተማሩ አዲስ ተስፋ እየሰነቁ ወደፊት ይጓዛሉ። ሰለዚህ ሰኬታማ እንድንሆን በቀላሉ ተሰፋ የማንቆርጥ መሆን ይገባናል። በእያንዳንዱ የስኬት ጎዳና ወድቆ መነሳት መኖሩን በማመን ተስፋ ሳንቆርጥ መትጋት አለብን። #Never_give_up ✍️https://t.me/successseket

🔵የስኬት ሰው ...... 🛑 🔵 🍂🍂 ዓላማን አለመሳትና አለመዘንጋት በዚህ አለም ከትኩረታችን የሚያዘናጉን ነገሮች ብዙ ናቸው። መዘናጋት ደግሞ የአንተ፣ የአንቺ ችግር ብቻ ሳይሆን የብዙዎች መሠረታዊ ችግር ነው። ስኬታማ ሰዎች ግን ከግባቸው ለሴኮንድ እንኳን አይዘናጉም። ከላይ እንደተጠቀሰው ቀናችንን በዕቅድ መጀመር እንዳንዘናጋ ያደርገናል። ያቀድነውን ነገር በሰዓቱ መከወን ይገባል። በተቻለንም መጠን በዕቅዳችን ላይ ባስቀመጥነው የጊዜ ማእቀፍ ስራችን መስራት አለብን። የሚያዘናጉንን ነገሮች መለየት እና ከእነርሱ መራቅ። ለምሳሌ አዝናኝ የሆኑ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብለን በማየት መዝናናት እንችላለን። መዝናናት አስፈላጊ ነው፤ ሆኖም በስራ ሰዓት አልያም የሆነ የምንሰራው ነገር እያለ ጉዳያችንን ሳንፈጽም ቴሌቭዥን እያዩ መዋል ለኑሯችን ፋይዳ የለውም። ሰለዚህ ይህን የመሰሉ በሚያዘናጉ ነገሮች ውስጥ ከመዘፈቃችን በፊት ቆም ብለን ዓላማችንን ለማሳካት ምን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ መመዘን ይገባል። 🌿☘️🌿መልካም ቀን🌿☘️🌿 https://t.me/successseket

ናፍቆት ማለት ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት፣ ግን ልብን የሚከብድ ጣፋጭ ህመም ነው።
ናፍቆት ማለት ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት፣ ግን ልብን የሚከብድ ጣፋጭ ህመም ነው።

ሌሊቱ ሲመጣና ዓለም ፀጥ ስትል፣ ናፍቆትሽ እንደ ማዕበል ይነሳል። ድምፅሽን በስልክ ከመስማት በላይ፣ ትንፋሽሽን በአካል የምሰማበትና እጅሽን የምይዝበት ቀን ናፈቀኝ። ትዝታሽ ብቻውን ብርድ አይከላከል
ሌሊቱ ሲመጣና ዓለም ፀጥ ስትል፣ ናፍቆትሽ እንደ ማዕበል ይነሳል። ድምፅሽን በስልክ ከመስማት በላይ፣ ትንፋሽሽን በአካል የምሰማበትና እጅሽን የምይዝበት ቀን ናፈቀኝ። ትዝታሽ ብቻውን ብርድ አይከላከልም፣ ግን ለነገ ተስፋ ይሆነኛል። የምር ናፍቀሽኛል ሄዋኔ!!

➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ✍️ለአንዳንዶች ስኬት ማለት ከሌሎች በሀብት፣ በዝና፣ በስልጣን፣ በችሎታ...ወዘተ በልጦ መገኘት ይመስላቸዋል፣ ለእኔ ግን ስኬት ከትላንቱ ማንነቴ የተሻልኩ ሆኜ መገኘት ነው..
#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ✍️ለአንዳንዶች ስኬት ማለት ከሌሎች በሀብት፣ በዝና፣ በስልጣን፣ በችሎታ...ወዘተ በልጦ መገኘት ይመስላቸዋል፣ ለእኔ ግን ስኬት ከትላንቱ ማንነቴ  የተሻልኩ ሆኜ መገኘት ነው..!! ስኬት ከሌሎች ጋር ሳይሆን ከራስ ጋር ያለንን ውድድር ነው፣ ከትላንት ማንነታችን ላይ ለውጥ ማሳየት ነው። ትላንት በቁጣ፣ በፍርሃትና በማመንታት የተቆጣጠረው ማንነታችን ዛሬ በትዕግስት፣ በፍቅርና በጥንካሬ መቆጣጠር ከቻልን ይህ ታላቅ ስኬት ነው። ስኬት የእውቀት ጥልቀት እና የራስ ግንዛቤ ነው፣ የራስ ድክመትና ብርታት፣ ህልምና ፍላጎት መረዳትና መምራት ነው። #Never_give_up https://t.me/payattetion12