uz
Feedback
የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

Kanalga Telegram’da o‘tish

📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
3 387
Obunachilar
+4824 soatlar
+1687 kun
+30830 kun
Postlar arxiv
በጥቅሉ ማህበረሰብ ላይ ትኩረት እንድታደርጉ እመክራችኋለሁ!! ——— ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዑበይድ አል-ጃቢሪይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በጥቅሉ ማህበረሰብ ትኩረት በማድረግ ላይ እመክራችኋለሁ!! ባረከላሁ ፊኩም!። ስለ ዲኑ የጠለቀ እውቀት በሌለው ጥቅል በሆነው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ ትኩረት አድርጉ!፣ የጠለቀ የዲን እውቀት የሌላቸው ጥቅሉ ሙስሊም ማህበረሰብ ክፍሎች ሠለፊይ ከሆኑ የዲን ተማሪዎች እዝነትና ርህራሄን፣ መተናነስን፣መልካም ግብረገብነትንና የፊት ፈገግታን ካገኙ ይወዱታል ከእርሱም ይሆናሉ። በተቃራኒው ደግሞ ማስበርገግን፣ፊተ ጨፍጋጋነትን፣ ጨካኝነትን፣ልበ ደረቅነትንና መጥፎ ስነ-ምግባርን ሲያገኙ ይሸሹታል፣ ከኋላቸውም ያለው አካል እንዲሸሽ ያደርጉታል!!።” = ጥቅል የሆነውን ማህበረሰብ ሰበብ አድርገን በቢድዐህ ተቋማት ሳንርመጠመጥና ሙጃመለህ ሳናደርግ በርህራሄና በለሰላሳ ግብረገብነት ልናቀርባቸውና ሐቁን እንዲገነዘቡ ልናደርጋቸው ይገባል። ዲናዊ ክፍተቶቻቸውን በጥበብና በለስላሳ አንደበት በመንገር ልንመክራቸውና ልናቀርባቸው ልጆቻቸውንም ትኩረት ሰጥተን በማስተማርም ይሁን ወደ ሱና መድረሳዎች ወስደው እንዲያስተምሩ በመጠቆም ልንመክራቸውና ልናግዛቸው ይገባል። አልፎ አልፎ አንዳንዶች ባልገባቸውና ውዥንብር በፈጠረባቸው መንሀጃዊ ነጥቦች ላይ በሚያነሷቸው ጥያቄዎችም አዕምሯቸውን በሚመጥን መልኩ ማስገንዘብ እንጂ ማስበርገግ ትልቅ አደጋ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል!!። 🔴 እንዲህ ያሉትን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ክፍሎች አያያዝህን ካላስተካከልክና ካስበረገግካቸው ለአህባሽ፣ ለኢኽዋንና ለሙመይዐህ እያስረከብካቸው መሆኑንም አስምርበት!!። ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

🔷በሐቅ ላይ ታገሱ ፣ ተበራቱ የመጨረሻ ውጤቱ አላህን ለሚፈሩት ነው ሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "ታገሱ ፣ (ከጠላቶቻችሁ የበለጠ) ተበራቱም ፣  (በትግል ኬላዎች  ላይ) ተሰለፉም፡፡ ይህ መንገድ ረጅም ነው ፤ ነገር ግን የነብያትና የኡለማ መንገድ ነው። አንድ ሰው ሊሰቃይ  ፤ ሊወነጀል ይችላል፤  ሊዋጉት ይችላሉ። ግን የመጨረሻ ውጤቱ አሏህን ለሚፈሩት ነው። ሱናን አጥብቆ የያዘ ይድናል፤ ከእርሷ የዞረ ይጠፋል። ከእርሷ ውጭ ክብርን የሚሻ አሏህ ያዋርደዋል።" تحفة المجيب ص/٩٩ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

《كونوا قدوة للناس يادعاة التوحيد》 ‏✍قال شيخنا العلامة زيد بن محمد بن هادي  المدخلي -رحمه الله تعالى- : "فينبغي للداعية إلى الله أن يكون أول العاملين بما يدعو إليه : _ من امتثال أوامر الله، _ واجتناب نواهيه، _ ومتابعة رسوله صلى الله عليه وسلم، في العقيدة والعبادة والمعاملة والأخلاق، والسلوك ظاهراً وباطناً. وقد سئل بعض زعماء العرب عن سبب إسلامه؛ فكان جوابه : إني وجدت محمداً - صلى الله عليه وسلم  - ما دعا إلى شيء إلا كان أول الفاعلين له، ولا نهى عن شيء إلا كان أول المجتنبين له". 📚[المنهج القويم في التأسي بالرسول الكريم صلى الله عليه وسلم، الطبعة الثانية، دار المنهاج، ص٢٢، ص،٢٣].

🔷ከታች ከተዘረዘሩት ኪታቦች በህይወታቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀራቹት ኪታብ የቱ ነው? እስኪ ንኩት እና የሚመጣላቹን የሱና ቻናሎች ይቀላቀሉ

Repost from Abdusomed Muhamed
📌በሙሀመድ ሀሚድን ላይ የተሰጠ ረድ! ሙሀመድ ሀሚድን ከተሳሳታቸው ስህተቶች በትንሹ ለመገለፅ ተሞክሯል። 🎙በ አቡ ፊርደውስ አብዱሶመድ ሙሀመድ https://t.me/abdu_somed https://t.me/abdu_somed

"አብዛኞቻችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለክብራችን ስንል፣በፈተና ወድቀን ሌሎችንም በፈተና የጣልንበት መራር እውነታ..." ኢብኑል-ቀይም -ረሒመሁላሁ ተዓላ- እንዲህ አለ፦ "አንተን የበደለ ሰው፣ከዚያም ይቅርታ እየጠየቀህ ቢመጣ፣ ይቅርታውን ለመቀበል (ዐውፍ ለማለት) ትህትናን (ተዋዱዕ) ይጠይቃል፤በልቡ ወስጥ ያለውን ለአላህ ተወው...”
📚[መዳሪጅ አስ-ሳሊኪን፣ 2/338]
https://t.me/semirEnglish

⛔️አኽላቅን ማስተካከል ከሰለፊይነት  ዋናው  ክፍል ነው ❗️ ➧አንድ ሰለፊይ ሰለፊይ በመሆኑ ብቻ ትልቁን የአኽላቅ ማስተካከል እርከንን ተሻግሯል የሚቀርበት በሱ እነ በመኽሉቆች መካከል ያለውን መስተጋብር   ማስተካከል ነው እሱም ሰለፎች በነበሩበት መልኩ ልሆን ይገባዋል ። ➥ከሰዎች ጋር ቅርበቱም ርቀቱም ውዴታውም ጥላቻውም በስሜቱ ወይም በሸይኹ  ወይም በጀመዐው ስሌት ሳይሆን  ሰለፎች በተገበሩትና በተገነዘቡት መሰረት መሆን አለበት ይህ ከልሆነ በኢስላም መመሪያ መሰረትሰዎች ምግባረ ሰናይ ብለው በአንድ ድምፅ ብያሞግሱት እሱ ምግባረ ብልሹ መሆኑ አይቀሬ ነው ። ◉በኢስላም አስተምህሮት መሰረት አንድ ሰው ምግባረ ሰናይ ነው ከተባለ ትክክለኛ ሰለፊይ እሱ ነው _ለሰዎች ተማኝ ቃሉን አክባሪ _ታላቁን አክባሪ _ለተናሹ አዛኝ _ለአማኞች ተናናሽ _በቢደዕ ሰዎች ብርቱ ጠንካራ _በመልካም የሚያዝ በመጥፎ የሚከለክል _ሀቅን የማይደብቅ በሄደበት ሁሉ የኸይር ነገር መፍቻ ቁልፍ የሚሆን ➨
ለሙስሊሞች ለዲናቸውም ለዱንያቸው መበላሸት ምክንያት የሚሆንን ሸር ሁሉ ለማስቀረት በመታገል ለሙስሊሞች ያለውን ተማኝነት በተግባር ማሳየት
◊በአላህ መንገድ ለይ የወቃሾችን ወቀሳ የማይፈራ የአላህን ፊት ፈልጎ ለለውጥ መትጋት ◉ላወቀውም   ለላወቀውም   ሙስሊም ሰላምታ ማቅረብ ➧ከወንድሙ በሚገናኝበት ሰዐት  ፈገግታ በተላበሰ ፊት የሚያናግር ➽ለሙስሊም ወንድሙ በመልካም ስራዎች ሁሉ በቻለው መጠን አጋዥ ጡንቻ የሚሆንለት እነ እንቅፋቶችን የሚጠራርግለት ➫ከግል ጥቅሞቹ የሙስሊሞችን ጥቅም የሚያስቀድም ግትርና ስግብግብ አለመሆን ➨የተጣሉ ወዳጆችን የሚያስታርቅ ዝምድናን መቀጠል 👉በልጆቹ መካከል ፍትሐዊ መሆን ➫
ለአላህ ብሎ የቢደዕ ሰዎችን የሚያዋርድ
➳ አሉ ተባለ የማይበግረው የውስጥ ጥንካሬ ያለው! ➵ሙስሊሞችን ከቀደምት ደጋጎች ጋር የሚያስተዋውቅ ራሱን አጉልቶ ውለታ ዋይ አድርጎ የማያይ ለሙስሊሞች ሁለንተናዊ ለውጥ መንቀሳቀስ ለሙስሊሞች መተናነስ 🤲ሁላችንንም አላህ ለመልካም ስነምግባር ይግጠመን ❗️ 📝#የቴሌግራም Channeሉን #join በማለት  #ይቀላቀሉ➷➷➷➷➷ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

አንዳንድ ሙስሊም እህቶች ግን አላህ ይዘንላችሁ! እንደው ድካሙ ድርሻችሁ ሆኖ እንጂ ባዳ ፀጉር ተሸክሞ የራስ ማስመሰል ለማን ይጠፋዋል ብላችሁ ነው እራስን ከማታለል በስተቀር እህት አለም ቅጥፈቱ ይቅርብሽ ይህንን ግም አውልቀሸ ወርውሪ እና ያችንው ፀጉርሽን ተንከባከቢያት አላህ ያሳድግልሻል ። አንድን ሐራም ነገር ለአላህ ብሎ የተወ ሰው አላህ የተሻለውን ይተካለታል ብለዋል ረሱላችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ! ✍በኡስታዝ አቡ ኑህ

በአላህ ዲን ላይ ከመቀያየር ተጠንቀቅ!! ——— ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- “ከፍ ባለው አላህ ዲን ላይ ከመቀያየር ወዮልህ ተጠንቀቅ!!። በእርግጥም ብዙ ወደ ደዕወቱ ሠለፊየህ የሚጠጉ የነበሩ ፍጡሮች በተምይዕ ባህር በመግባት ተፈትነዋል፣ ይህም ተወጋጅ የሆነችውን ክብር በመከጀል ነው። ልቦች በአላህ እጅ ላይ ናቸው፣ አላህን ፅናት እንጠይቀዋለን! ዘዴም ሆነ ሀይልም በአላህ ቢሆን እንጂ የለም!!።” [ኸምሱነ ነሲሀ ሊጦላብ አል-ዒልም 22] #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

🔷እወቅ - አሏህ ለስኬት ያብቃህ - ዶክተር ሸይኽ ሁሴን ብን ሙሐመድ አስ'ስልጢ - ሐፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "ሸሪዓዊ  እውቀት ፈላጊ በኑሮው ከሰዎች ሁሉ በጣም መልካሙ ፣ (ለሐቅ) ልቦናው በጣም ክፍት ነው። እንዴት እንደዚህ አይሆን?! አሏህ አሊሞቹ እሱን የሚፈሩ መሆናቸውን ራሱ መስክሯል። የእውቀት ፈላጊ ሁሉን ቻይ ስለሆነው አሏህ ፣ ስለ ስሞቹ እና ባህሪያቱ ፣ ለእርሱ ስለሚገባውና ከእርሱ ላይ ስለሚከለከለው እውቀቱ በጨመረ ቁጥር ለእርሱ ያለው ፍርሀት በጣም ይበረታል።" الدورة العلمية : بعنوان "خمسون نصيحة لطلاب العلم" ص/١ ، التي ألقيت في مركز (دار السنة) أديس أبابا https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

አልሀምዱሊላህ ቢኒዕመቲሂ ተቲሙ ሷሊሃት!! 💎 ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ኮርስ እጅግ ባማረና በደመቀ መልኩ ተጠናቋል!!። ለዚህ ኮርስ መሳካት በአካል መታደምን ጨምሮ በቻላችሁት ሁሉ ከ
አልሀምዱሊላህ ቢኒዕመቲሂ ተቲሙ ሷሊሃት!!
💎 ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ኮርስ እጅግ ባማረና በደመቀ መልኩ ተጠናቋል!!። ለዚህ ኮርስ መሳካት በአካል መታደምን ጨምሮ በቻላችሁት ሁሉ ከጎናችን ለሆናችሁ አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ!! ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል አዲስ አበባ አለምባንክ መስከረም 3/2019 ሊንኩን በመጫን ቋሚ ደርሶችን መከታተል ይችላሉ። 📱⇘⇘⇘⇘⇘ t.me/DarASSunnah1444 t.me/DarASSunnah1444

Repost from N/a
⭕️ ቀላል ጥያቄ ውድ ስጦታ ⁉️ 📖 ይህ ቃሪእ ሚቀራውን ሱራ (سورة) ላወቀ አካል ተወዳጅ እና ተፈላጊ የኢትዮጵያ ከ75+ የሰለፊዮችን ቻናል በነፆ እና በደስታ ይገባል‼️

قال العلامة مقبل الوادعي -رحمه الله :_ "اصبـروا وصـابـروا ورابطـوا، فـإنّ هـذا الطـريـق طـويـل، ولكنـه طـريـق الأنبيـاء والعُلمـاء، قـد يُبتلـى الإنسـان ويُتهـم ويُحـارب، ولكـن العـاقبـة للمُتقيـن، ومَـن تمسّـك بـالسُّنّـة نجـا، ومَـن أعـرض عنهـا هـلك، ومَـن ابتغـى العِـزّة فـي غيـرهـا أذلّـه اللـه." 📚 تحفـة المجيـب (ص: ٩٩).

🔴 ቀጥሏል بعنوان:- خمسون نصيحة ووسائل الوقاية من الوقوع في الفتن وتجنب تمزيق الصف السلفي. للشيخ الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله تعالى. ርእስ:- በፊትና ላለመውደቅና የሠለፊዮችን አንድነት (ሰፍ) ከመበጣጠስ ለመጠበቅ የሚጠቅሙ አምሳ ምክሮች!! 🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ↘️↘️↘️↘️ https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=

ተጀምሯል بعنوان:- فضل العلم وآداب طلبه... للشيخ طه بن خضر الجمي حفظه الله تعالى. ርእስ:- የእውቀት ደረጃውና የመማር ስርኣቱ… 🎙በሸይኽ ጧሃ ቢን ኸድር (ሀፊዘሁላህ) ገባ ገባ በሉ ↘️↘️↘️↘️ https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=

አዲስ pdf (ኮርስ እየተሰጠበት ያለው ሪሳላ ነው) عنوان:- خمسون نصيحة لطلاب العلم والوقاية من الوقوع في الفتن والبدع وتجنب تمزيق الصف السلفي. للشيخ الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله تعالى. ርእስ:- በፊትና ላለመውደቅና የሠለፊዮችን አንድነት (ሰፍ) ከመበጣጠስ ለመጠበቅ የሚጠቅሙ አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች!! በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ↘️↘️↘️ t.me/DarASSunnah1444 t.me/DarASSunnah1444 هذه الرسالة من أنفع الرسائل التي كتبها الشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد،حفظه الله تعالى لما اشتملت عليه من نصحٍ وتوجيهٍ وعلاجٍ لأمراضٍ كثيرةٍ منتشرةٍ بين الشباب في هذا الزمان، وستكون ـ بإذن الله تعالى ـ دواءً نافعًا  لكثيرٍ من تلك الآفات ونسأل الله أن يجعلها مباركة ويثبت كاتبهاعلى الصراط المستقيم والمنهج القويم  ونسأله تعالى أن يحفظ عقيدةالمسلمين  ومنهجهم في كل زمان  وفي كل مكان  من  الانحراف  والتضليل عن سبيل  الله ✍🏻الشيخ محمد حيات حفظه الله

ጥበበኛው ንጉስና 3ቱ ሚኒስቴሮቹ ——— በአንድ ወቅት አንድ ንጉስ ነበረ ይባላል፣ ካሉት ሚኒስትሮቹ 3ቱን መፈተን ፈልጎ አስጠርቷቸው ለ3ቱም ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ ከረጢት ሰጥቶ ወደ ማሳ ገብታችሁ አለ የሚባል ልዩ ልዩ ጠዕም ያላቸውን ፍራፍሬዎችን ያለ አንድም አጋዥ አካል በራሳችሁ እጅ መርጣችሁ አምጡ አላቸው። 3ቱም የተሰጣቸውን ከረጢት ይዘው ወደ ማሳ ገቡ፣ 1ኛው ጥበበኛና ስራውን አጥርቶ የሚሰራ ታማኝ ሰው ነበረ ይባላል "ንጉሱማ ይህን ለሆነ ጠንካራ አላማ ቢሆን እንጂ ዝም ብሎ አያዝም…" አለና ልዩ ጠዓምና ጥራት ያላቸውን ፍራፍሬዎችን መርጦ እየለቀመ ትንሽም ችግር ያለበትን እየዘለላ አሉ ከሚባሉ ቆንጆና ልዩ ጠዓም ካላቸው ፍራፍሬዎች ከረጢቱን ሞላው፣ 2ኛው ደግሞ ብልህ ሰው ነው ግን ስልቹ ነበር ይባላል አሰበና በሚገባ ትኩረት ሰጥቶ ሳይመርጥ እንደነገሩ እያደረገ ጤነኛውንም የተበላሸውንም ሳይመርጥ ከረጢቱን ሞላው፣ 3ኛው አታላይና አጭበርባሪ የነበረ ሰው ነበር ይባላል፣ "ንጉሱማ ስንትና ስንት ልዩ አቅም አለው፣ ስንት busy የሚያደርግ ጉዳይ አለበት፣ ምን አጥቶ ነው ይህን ሚያዘን?! ብንወስድለትም ከረጢቱን ከፍቶም አያየውም…" ብሎ አሰበና ምንም የማይረባውን ሳሩንም፣ድንጋዩንም ምኑንም አድርጎ ከረጢቱን ሞልቶ የየራሳቸውን ይዘው ወደ ንጉሱ ሄዱ፣ ንጉሱም 3ቱንም ከረጢት ከፍቶ ተመለከተውና ጠባቂዎችን ጠርቶ እነዚህን ውሰዱና ከነ ከረጢታቸው ለየ ብቻ ለ1 ወር ያክል ያለ ምግብ እሰሩዋቸው፣ በየ ከረጢታቸው የሰበሰቡትን ይብሉ አለ። ሁሉም ከየ ራሳቸው መጥፎም ይሁን ጥሩ ሰብስበው ከሞሉት ከረጢት ታሰሩ። 1ኛው ሚኒስቴር የሰበሰበውን ልዩ ጠዓም ያለውን ፍራፍሬ እየተመገበ በተሻለ ጤንነትና ጠንካራ ሰውነት ላይ ሆኖ የእስር ጊዜውን ጨርሶ ወጣ። 2ኛው ግን በስልቹነቱ ጥራት የሌለውን የተበላሸውንም ፍራፍሬ ሳይቀር ሰብስቦ ነበርና እሱን እየበላ ታሞ እየተሰቃየ ቆይቶ በሽተኛ ሆኖ ወጣ። ጤነኛውን ብቻ መርጦም እንዳይበላ የእስሩ ጊዜ ረጀም ነው አይበቃውም። 3ኛው ደግሞ የባሰ ሆነ፣ የሰበሰበው ምንም ጤና የነበረውና ለመመገብ የሚሆን ነገር ስላልነበረው ብዙም ሳይቆይ በረሃብ ሞተ። ዋናው ቁምነገር… - የፍራፍሬው (የአትክልታ አትክልቱ) ማሳ ምሳሌ ዱኒያ ናት - ፍራፍሬዎቹ በዱኒያ ላይ ሆነን የምንሰበስበው ስራ ነው… - እስር ቤቱ የሰው ልጅ በህይወት እያለ የሰበሰበውን ብቻ የሚያገኝበት ቀብር ወይም ሂሳብ ምንደረገው ነገር ነው… - ዛሬ እንሰበስባለን ነገ ደግሞ ከሰበሰብነው ውጤት ነው ምንመገበው እንጂ ከየትም አይመጣልንም! ስለዚህ ለእራሳችን ብለን ስራችን በጥራት እንስራ! - ነገ በአኼራ የምንበላውን ነገር (ስንቅ) ለማግኘት ለራሳችን ብለን ዛሬ ዱኒያ ላይ የምንመርጠውን እናሳምር!! - ሁሉም ለነገ ስንቁ በቆራጥነት ይስራ! ነገ የሂሳብ እንጂ የስራ ጊዜ የለም! ወደፊትም ወደ ኋላ የማይባልባት ቁርጧ ቀን ድንገት ነው ምትመጣውና የነገውን ስንቅ በአግባቡ ለመሰብሰብ ጮሌና ፈጣኖች እንሁን!! የፅሁፉ ሀሳብ ከዐረቢኛ ወደ አማርኛ ✍🏻በኢብን ሽፋ የተመለሰ ነው #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

Repost from N/a
🔴አስቸኳይ የቅጥር ማስታወቂያ ቢላል ኢብኑ ረባህ  መድረሳ ኡስታዞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ። #⃣ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች - የሰለፊያን መንሀጅ የሚከተል ፤ ከቢድዐ እና ከሙበተዲዖች የራቀ። - ቁርአን  በጥሩ ተጅዊድና ሙራጅዓ የሀፈዘና የማስተማር ልምድ ያለው  :: - መሰረታዊ የተጅዊድ ህግጋቶች ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሮት ማስተማር የሚችል ። - ለተማሪዎች በሁለንተናው ጥሩ አርአያ መሆን የሚችል ። - ለመድረሳው ህግና ደንብ ተገዢ የሆነ - ከቃኢደቱ-ኑራኒያ ጀምሮ ሙኽተሰር ኪታቦችን ማቅራት የሚችል - ሸሪዐዊ አለባበስን የሚከተል - የስራ ሰአት፦ ከሰዐት 10:00-12:20 ከሰኞ-ሐሙስ እና ቅዳሜን ጨምሮ እንዲሁም እሁድ ጠዋት ከ 1:30 - 3:30 - አድራሻ፦ ካራ ቆሬ ሳሌ ህንጻ ጀርባ - ደመወዝ፦ በመድረሳው ስኬል መሰረት -መድረሳው ላይ ማደር፤ምግብ ማብሰል  ይፈቀዳል   - የምንፈልገው የአስተማሪ ብዛት - 2 ➡️ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ከታች ባለው ስልክና ዩዘር ኔም  ያናግረን ። ☎️+251937948156 ☎️0995473737 ⌛️@Abureslan02  @abdu2791 https://t.me/bilalibnurebahmedresa

+1
አዲስ pdf (ኮርስ እየተሰጠበት ያለው ሪሳላ ነው) عنوان:- خمسون نصيحة لطلاب العلم والوقاية من الوقوع في الفتن والبدع وتجنب تمزيق الصف السلفي. للشيخ الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله تعالى. ርእስ:- በፊትና ላለመውደቅና የሠለፊዮችን አንድነት (ሰፍ) ከመበጣጠስ ለመጠበቅ የሚጠቅሙ አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች!! በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ↘️↘️↘️ t.me/DarASSunnah1444 t.me/DarASSunnah1444

(☝️🔫) የቁባእ መስጂድ" ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም "የመስጂድ አን-ነበዊ" አስተማሪ (ሙደሪስ) የሆኑት ዶክተር አሽ-ሸይኽ ሱለይማን አር-ሩሀይሊይ (ሀፊዘሁላሁ ተዓላ) በየመን እየተካሄደ ባለው ጦርነ
(☝️🔫) የቁባእ መስጂድ" ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም "የመስጂድ አን-ነበዊ" አስተማሪ (ሙደሪስ) የሆኑት ዶክተር አሽ-ሸይኽ ሱለይማን አር-ሩሀይሊይ (ሀፊዘሁላሁ ተዓላ) በየመን እየተካሄደ ባለው ጦርነት አስመልክተው በ-"X" አካውንታቸው ላይ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል፦ በጦርነት ውስጥ የተወሰነ ስቃይ (ህመም) መኖሩ አይቀሬ ነው፤ ነገር ግን የሐቅ ባለቤቶች ስቃይ (ህመም) እንደ የባጢል ባለቤቶች ስቃይ አይደለም። የሐቅ ባለቤቶች ይጎዳሉ፣ ከዚያም በተጎዱት ጉዳት ደግሞ ምንዳ (አጅር) ያገኛሉ፣ ከዚያም ድል ያደርጋሉ፤ መልካም ፍፃሜም በአላህ ፍቃድ ቅርብ ነው። ለባጢል ባለቤቶች እና ለደጋፊዎቻቸው ደግሞ ጩኸትና ውሸቶች እንጂ ሌላ የላቸውም።ጌታችንም እንዲህ አለ፦ "ሰዎቹንም በመፈለግ አትስነፉ፡፡ (ስትቆስሉ) የምትታመሙ ብትኾኑ እናንተ እንደምትታመሙ እነሱም ይታመማሉ፡፡ የማይከጅሉትንም ከአላህ ትከጅላላችሁ፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [ኒሳእ:104] የሃይላችን ወንዶች ሆይ!፤ የምንወዳችሁ የየመን ህዝቦች ሆይ! ፅናት!፣ ፅናት! ትብብር፣ ትብብር! ጥንካሬ፣ ጥንካሬ! እውነት (ሐቅ) ከእናንተ ጋር ነውና። የጠላቶቻችሁ ስራቸው በእነርሱ ላይ ፀፀት ይሆንባቸዋል..." https://t.me/semirEnglish https://t.me/semirEnglish