uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ሕያው ቃል ➟ 📖

ሕያው ቃል ➟ 📖

Kanalga Telegram’da o‘tish

🕊️ ሕያው ቃል | Living Word 📖✨ "የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም ነው..." (ዕብ 4፥12) ➢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችና ጥያቄዎች 🔍 ➩ መንፈስን የሚያድሱ ትምህርቶችና ጥቅሶች 💡 ➠ ሕይወትን የሚቀይሩ ምሳሌዎችና መልእክቶች 🌱 🎬 YouTube 👤 አስተያየትና ጥያቄ ለመላክ፦ @EDIWOLDE

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
335
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+97 kun
+4630 kun
Postlar arxiv
#ገብርኤል_አምልኮ_ይገባዋል ካልን ገብርኤል ገብርኤል መሆኑ ቀርቶ #ሰይጣን ሆኗል እያልን ነው። ከመላዕክት መካከልም ሆነ የትኛውንም ፍጥረት #ስግደት_ይገባዋል ካልን፣ ያንን ፍጥረት ወደ ሰይጣንነት ለመቀየር እየሞከርን ነው። ሰይጣንም እኮ መልዓክ ነበር፤ ግን ደግሞ ሰይጣን አሁን ላለበት ማንነት ያበቃው ምን እንደሆነ ሁላችንም ጠንቅቀን የምናውቅ ይመስለኛል። ምናልባት የማናውቅ ካለን፦ ሰይጣንን ሰይጣን ያደረገው ለመመለክ መፈለጉ ነው።
ከአንዱ ከእግዚአብሔር ውጪ አምልኮን የሚፈልግ እርሱ ከእግዚአብሔር ወገን አይደለም፤ የእግዚአብሔር ጠላት እንጂ።
SHARE & JOIN ➥ @LIVINGWORD11

ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ፤ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና። (ቆላስይስ 2:2-3) Hallelujah 🙏🙏 SHARE | SHARE TELEGRAM ∞ TIKTOK ∞ FACEBOOK

ተስፋ ለመቁረጥ በቂ ምክንያት፡ ለመቀጠልም በቂ ምክንያት አለን። ነገሩ እንደየእይታችን ነው። እየታየን ያለው የሚታየው ሁሉ ሳይሆን አይኖቻችንን የተከልንበትን ነው። 📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

እሺ ጌታ ፍቀዱ ከሆነ በቅርቡ እንጀምራለን😊

⚡ Mᴜʟᴛɪᴘʟᴇ Rᴇᴀᴄᴛɪᴏɴs Wᴏʀᴋɪɴɢ Sᴍᴏᴏᴛʜʟʏ ʙʏ @PhxMultiReactionbot ✅ Yᴏᴜʀ Cʜᴀɴɴᴇʟ Eɴɢᴀɢᴇᴍᴇɴᴛ ɪs 100% Mᴀɪɴᴛᴀɪɴᴇᴅ ɪɴ Lᴀsᴛ 24 Hᴏᴜʀs.

⚡ Mᴜʟᴛɪᴘʟᴇ Rᴇᴀᴄᴛɪᴏɴs Wᴏʀᴋɪɴɢ Sᴍᴏᴏᴛʜʟʏ ʙʏ @PhxMultiReactionbot ✅ Yᴏᴜʀ Cʜᴀɴɴᴇʟ Eɴɢᴀɢᴇᴍᴇɴᴛ ɪs 100% Mᴀɪɴᴛᴀɪɴᴇᴅ ɪɴ Lᴀsᴛ 24 Hᴏᴜʀs.

⚡ Mᴜʟᴛɪᴘʟᴇ Rᴇᴀᴄᴛɪᴏɴs Wᴏʀᴋɪɴɢ Sᴍᴏᴏᴛʜʟʏ ʙʏ @PhxMultiReactionbot ✅ Yᴏᴜʀ Cʜᴀɴɴᴇʟ Eɴɢᴀɢᴇᴍᴇɴᴛ ɪs 100% Mᴀɪɴᴛᴀɪɴᴇᴅ ɪɴ Lᴀsᴛ 24 Hᴏᴜʀs.

ሀሳባችሁን በReact ሰይሆን በcomment አስቀምጡልኝ 👇👇

🤔 እኔ የምላችሁ እስት በዝህ ቻናል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን እየጠየኩ በትክክል ለሚመልሱ እና ለምያብረሩ አባላት ከነሱ መካከል እድለኛ የሆኑትን መርጬ የሞባይል ካርድ ሽልማት ብሰጥ ምን ይመስላችኋል? 🎁📱
📖✨ ዓላማው በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችንን ማሳደግ፣ አብረን መማር እና በቃሉ መበርታት ነው። 🙏💚
👇 እስቲ የእናንተን አስተያየት ንገሩኝ! ✅ ይህ ሀሳብ ይስማማችኋል? 🎁 በዚህ የሽልማት ውድድር መሳተፍ ትፈልጋላችሁ? 💬 አስተያየታችሁን ከታች Comment ላይ አስቀምጡልኝ። 👇❤️

✍️በመሪና በተመሪ መካከል ፍርሃት ካለ አምባገነንነት እና ኩነኔ አለ ማለት ነው። ✍️በመካከላቸው ፍቅር ካለ ግን ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል። ➭ የአምባገነን መሪ ተከታዮች መሪያቸውን ፈሪ እና ከመሪያቸው ቁጣና ቅጣት ለመዳን ሲሉ - ያልሆኑትን "ሆነናል" - የማይወዱትን "እንወዳለን" - የማያውቁትን "እናውቃለን" - ሳይታመሙ "ታመናል" - ታመው "አልታመምንም" - ሳይደሰቱ "ተደስተናል" የሚሉ አሰመሳዮች ናቸው። ❗የሆኑትን ሳይሆን መሪያቸው እንዲሆኑለት የሚፈልገውን ነገር "ሆነናል" ብለው ይነግሩታል።❗ ➥ የአፍቃሪ መሪ ተከታዮች ግን በመሪያቸው ፊት ሁሉንም ነገር በድፍረት የሚያደርጉ የሚሞክሩም ጭምር ናቸው። ➥ የሆኑትን "ሆነናል" የሚሉ እና ሊሆኑ የሚፈልጉትን "ልንሆን ፈልገናል" የሚሉ እውነተኞች ናቸው። 📍አንተም በምትመራበት በየትኛውም ስፍራ አምባገነን ከሆንክ ተከታዮችህ ምናልባት - ወዳጅ የሚመስሉ ጠላቶች - የቆሙ የሚመስሉ ግን የወደቁ - ጤነኛ የሚመስሉ በሽተኞች - የተማሩ የሚመስሉ መሃይሞች ሊሆኑ ይችላሉ። “…ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም…”  1ኛ ዮሐ 4፥18        📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

እግዚአብሔርንም ሆነ ሰውን መውደድህ የሚጨምረው "መውደድ አለብህ!" ስለተባልክ ሳይሆን እግዚአብሔር ምን ያህል እንደወደደህ እየተረዳህ በሄድክ ልክ ነው። 📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

➠ ዝንብና ንብ ተገናኝተው እያወሩ በወሬያቸው መሃል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት ➥ " ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል፣ ይገድሉኛል። በሚጠጡት ነገር ውስጥ ከተገኘሁ ያንን መጠጥ ይደፉታል። በሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ደግሞ ያረፍኩበትን ቦታ ቆርሰው ይጥሉታል፤ ወይ ደግሞ ጭራሽ ምግቡንም አይበሉትም። ➪ አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም፤ እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም ደስ ይላቸዋል፤ በእርሻቸውም ቤት ሰርተው ያስቀምጡሻል ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ለንብ ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ ብላ መለሰች 👉 "…ውሎሽ የት ነው?" 📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

🙏 ሰው ቢተውህም እግዚአብሔር አይተውህም። ሁሉም በአንተ ላይ ተስፋ ቢቆርጥም እርሱ ግን አሁንም ይወድሃል። ❤️ አትፍራ፣ ተስፋም አትቁረጥ። ዛሬ የምታልፈው ፈተና የነገ ምስክርነትህ ሊሆን ይችላል። በእግዚአብሔር ታመን፣ ጸልይ፣ በእምነትም ቀጥል። 🙌
📖 «እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።» — ኢሳይያስ 41፥10
❤️ ለሌሎችም ያጋሩ! 📲 Join & Share                👇👇👇👇 @LIVINGWORD11 @LIVINGWORD11

🎵 ነገዬ|Negeye Bereket Megersa #New #Amharic Gospel Song|2026 → Join🔥 @LIVINGWORD11 🎵 Audio (mp3) 📲 Join & Share                👇👇👇👇 https://t.me/LIVINGWORD11

ሙሉ መዝሙር ➥👇👇

የስጋቴን ተንኳ አስምጦ ውጦታል...🙌 📲 Join & Share                👇👇👇👇 https://t.me/LIVINGWORD11

ምሳሌ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³² አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፤ መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው። ³³ ትምህርቴን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸል አትበሉትም። ³⁴ የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ። ³⁵ እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛልና። ³⁶ እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፤ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።

photo content

📲 Join & Share        👇👇👇👇 https://t.me/LIVINGWORD11

💬 የእርስዎ ሃሳብ ለእኛ አስፈላጊ ነው! ውድ የሕያው ቃል ቤተሰቦች እንደዚህ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችና የመንፈሳዊ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች በዚህ ቻናላችን ላይ ዘወትር እንዲለቀቁ ይፈልጋሉ? እባካችሁ ሃሳባቸውንና አስተያየታችሁን ከታች👇 ባለው Comment ማድረጊያ ላይ ያስቀምጡልን! 👇