ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ሕያው ቃል ➟ 📖

ሕያው ቃል ➟ 📖

الذهاب إلى القناة على Telegram

🕊️ ሕያው ቃል | Living Word 📖✨ "የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም ነው..." (ዕብ 4፥12) ➢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችና ጥያቄዎች 🔍 ➩ መንፈስን የሚያድሱ ትምህርቶችና ጥቅሶች 💡 ➠ ሕይወትን የሚቀይሩ ምሳሌዎችና መልእክቶች 🌱 🎬 YouTube 👤 አስተያየትና ጥያቄ ለመላክ፦ @EDIWOLDE

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
335
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+167 أيام
+4630 أيام
أرشيف المشاركات
ተስፋ ለመቁረጥ በቂ ምክንያት፡ ለመቀጠልም በቂ ምክንያት አለን። ነገሩ እንደየእይታችን ነው። እየታየን ያለው የሚታየው ሁሉ ሳይሆን አይኖቻችንን የተከልንበትን ነው። 📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

እሺ ጌታ ፍቀዱ ከሆነ በቅርቡ እንጀምራለን😊

⚡ Mᴜʟᴛɪᴘʟᴇ Rᴇᴀᴄᴛɪᴏɴs Wᴏʀᴋɪɴɢ Sᴍᴏᴏᴛʜʟʏ ʙʏ @PhxMultiReactionbot ✅ Yᴏᴜʀ Cʜᴀɴɴᴇʟ Eɴɢᴀɢᴇᴍᴇɴᴛ ɪs 100% Mᴀɪɴᴛᴀɪɴᴇᴅ ɪɴ Lᴀsᴛ 24 Hᴏᴜʀs.

⚡ Mᴜʟᴛɪᴘʟᴇ Rᴇᴀᴄᴛɪᴏɴs Wᴏʀᴋɪɴɢ Sᴍᴏᴏᴛʜʟʏ ʙʏ @PhxMultiReactionbot ✅ Yᴏᴜʀ Cʜᴀɴɴᴇʟ Eɴɢᴀɢᴇᴍᴇɴᴛ ɪs 100% Mᴀɪɴᴛᴀɪɴᴇᴅ ɪɴ Lᴀsᴛ 24 Hᴏᴜʀs.

⚡ Mᴜʟᴛɪᴘʟᴇ Rᴇᴀᴄᴛɪᴏɴs Wᴏʀᴋɪɴɢ Sᴍᴏᴏᴛʜʟʏ ʙʏ @PhxMultiReactionbot ✅ Yᴏᴜʀ Cʜᴀɴɴᴇʟ Eɴɢᴀɢᴇᴍᴇɴᴛ ɪs 100% Mᴀɪɴᴛᴀɪɴᴇᴅ ɪɴ Lᴀsᴛ 24 Hᴏᴜʀs.

ሀሳባችሁን በReact ሰይሆን በcomment አስቀምጡልኝ 👇👇

🤔 እኔ የምላችሁ እስት በዝህ ቻናል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን እየጠየኩ በትክክል ለሚመልሱ እና ለምያብረሩ አባላት ከነሱ መካከል እድለኛ የሆኑትን መርጬ የሞባይል ካርድ ሽልማት ብሰጥ ምን ይመስላችኋል? 🎁📱
📖✨ ዓላማው በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችንን ማሳደግ፣ አብረን መማር እና በቃሉ መበርታት ነው። 🙏💚
👇 እስቲ የእናንተን አስተያየት ንገሩኝ! ✅ ይህ ሀሳብ ይስማማችኋል? 🎁 በዚህ የሽልማት ውድድር መሳተፍ ትፈልጋላችሁ? 💬 አስተያየታችሁን ከታች Comment ላይ አስቀምጡልኝ። 👇❤️

✍️በመሪና በተመሪ መካከል ፍርሃት ካለ አምባገነንነት እና ኩነኔ አለ ማለት ነው። ✍️በመካከላቸው ፍቅር ካለ ግን ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል። ➭ የአምባገነን መሪ ተከታዮች መሪያቸውን ፈሪ እና ከመሪያቸው ቁጣና ቅጣት ለመዳን ሲሉ - ያልሆኑትን "ሆነናል" - የማይወዱትን "እንወዳለን" - የማያውቁትን "እናውቃለን" - ሳይታመሙ "ታመናል" - ታመው "አልታመምንም" - ሳይደሰቱ "ተደስተናል" የሚሉ አሰመሳዮች ናቸው። ❗የሆኑትን ሳይሆን መሪያቸው እንዲሆኑለት የሚፈልገውን ነገር "ሆነናል" ብለው ይነግሩታል።❗ ➥ የአፍቃሪ መሪ ተከታዮች ግን በመሪያቸው ፊት ሁሉንም ነገር በድፍረት የሚያደርጉ የሚሞክሩም ጭምር ናቸው። ➥ የሆኑትን "ሆነናል" የሚሉ እና ሊሆኑ የሚፈልጉትን "ልንሆን ፈልገናል" የሚሉ እውነተኞች ናቸው። 📍አንተም በምትመራበት በየትኛውም ስፍራ አምባገነን ከሆንክ ተከታዮችህ ምናልባት - ወዳጅ የሚመስሉ ጠላቶች - የቆሙ የሚመስሉ ግን የወደቁ - ጤነኛ የሚመስሉ በሽተኞች - የተማሩ የሚመስሉ መሃይሞች ሊሆኑ ይችላሉ። “…ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም…”  1ኛ ዮሐ 4፥18        📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

እግዚአብሔርንም ሆነ ሰውን መውደድህ የሚጨምረው "መውደድ አለብህ!" ስለተባልክ ሳይሆን እግዚአብሔር ምን ያህል እንደወደደህ እየተረዳህ በሄድክ ልክ ነው። 📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

➠ ዝንብና ንብ ተገናኝተው እያወሩ በወሬያቸው መሃል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት ➥ " ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል፣ ይገድሉኛል። በሚጠጡት ነገር ውስጥ ከተገኘሁ ያንን መጠጥ ይደፉታል። በሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ደግሞ ያረፍኩበትን ቦታ ቆርሰው ይጥሉታል፤ ወይ ደግሞ ጭራሽ ምግቡንም አይበሉትም። ➪ አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም፤ እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም ደስ ይላቸዋል፤ በእርሻቸውም ቤት ሰርተው ያስቀምጡሻል ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ለንብ ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ ብላ መለሰች 👉 "…ውሎሽ የት ነው?" 📲 Join & Share                           👇👇👇👇                      @LIVINGWORD11                      @LIVINGWORD11

🙏 ሰው ቢተውህም እግዚአብሔር አይተውህም። ሁሉም በአንተ ላይ ተስፋ ቢቆርጥም እርሱ ግን አሁንም ይወድሃል። ❤️ አትፍራ፣ ተስፋም አትቁረጥ። ዛሬ የምታልፈው ፈተና የነገ ምስክርነትህ ሊሆን ይችላል። በእግዚአብሔር ታመን፣ ጸልይ፣ በእምነትም ቀጥል። 🙌
📖 «እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።» — ኢሳይያስ 41፥10
❤️ ለሌሎችም ያጋሩ! 📲 Join & Share                👇👇👇👇 @LIVINGWORD11 @LIVINGWORD11

🎵 ነገዬ|Negeye Bereket Megersa #New #Amharic Gospel Song|2026 → Join🔥 @LIVINGWORD11 🎵 Audio (mp3) 📲 Join & Share                👇👇👇👇 https://t.me/LIVINGWORD11

ሙሉ መዝሙር ➥👇👇

የስጋቴን ተንኳ አስምጦ ውጦታል...🙌 📲 Join & Share                👇👇👇👇 https://t.me/LIVINGWORD11

ምሳሌ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³² አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፤ መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው። ³³ ትምህርቴን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸል አትበሉትም። ³⁴ የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ። ³⁵ እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛልና። ³⁶ እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፤ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።

photo content

📲 Join & Share        👇👇👇👇 https://t.me/LIVINGWORD11

💬 የእርስዎ ሃሳብ ለእኛ አስፈላጊ ነው! ውድ የሕያው ቃል ቤተሰቦች እንደዚህ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችና የመንፈሳዊ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች በዚህ ቻናላችን ላይ ዘወትር እንዲለቀቁ ይፈልጋሉ? እባካችሁ ሃሳባቸውንና አስተያየታችሁን ከታች👇 ባለው Comment ማድረጊያ ላይ ያስቀምጡልን! 👇

📌 የትናንቱ መንፈሳዊ ጥያቄ ትክክለኛ መልስና ማብራሪያ 📌 ✨✅ ትክክለኛ መልስ፦ ➥ ሐዋርያው ጳውሎስ "በኤፌሶን 1፥17-19" ላይ የጥበብና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣቸው ከጸለየ በኋላ አማኞች እንዲያውቋቸው የፈለጋቸው ሦስቱ ዋና ዋና እውነቶች፦ ➥ "የመጥራቱ ተስፋ" ምን እንደሆነ እንዲያውቁ ➥ በቅዱሳን ዘንድ ያለው "የርስቱ ባለጠግነት" ምን ያህል እንደሆነ እንዲረዱ ➥ በሚያምኑት ውስጥ የሚሠራው "የኃይሉ ታላቅነት" ምን ያህል እንደሆነ እንዲረዱ ነው። 💡 ማብራሪያ፦ ➭ ይህ ጥያቄ አማኞች በክርስቶስ ያላቸውን ማዕረግና ማንነት፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ጥሪ እንዲሁም በውስጣቸው የሚሠራውን የትንሣኤን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመረዳት በልበ ሙሉነትና በጽናት እንዲመላለሱ የሚያስተምር ጥልቅ አዲስ ኪዳናዊ እውነት ነው። 🙌 ቃሉን አብረን ስለምንመረምር እግዚአብሔር ይባርከን! ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ማድረጋችሁን አትርሱ። 🙏 📲 Join & Share 👇👇👇👇 https://t.me/LIVINGWORD11

⭐ የዕለቱ የመንፈሳዊ ጥያቄ ⭐ ሰላም የተወደዳችሁ የሕያው ቃል ቤተሰቦች! 👋 ዛሬም ከእግዚአብሔር ቃል የተወሰደ አጭርና አስተማሪ ጥያቄ ይዘን መጥተናልል። 👉 የጥያቄው ሁኔታ፦ ጥያቄው የተዘጋጀው ለእውቀት እድገት እና ቃሉን ይበልጥ ለመመርመር ነው (ምንም ዓይነት የገንዘብ ሽልማት የለውም)።   በማንኛውም ሰዓት ገብተው ጥያቄውን መመልከት እና መመለስ ይችላሉ።
ለሌሎች ወንድሞችና እህቶች እንዲደርስ ቻናላችንን ሼር (Share) በማድረግ ያካፍሉ 🙏
⭐ ጥያቄ 01 ⭐ 👉 በኤፌሶን መጽሐፍ መሠረት ጳውሎስ ለአማኞች የጸለየላቸው የመጀመሪያው ነገር ምንድን ነው? ❌ መልሶቻችሁን ከታች👇 "መልስ ለመመለስ" የምለውን በመንከት ይጻፉልን!   ❌ መልሶቻችሁን በተቻለ መጠን ግልጽ እና ቀጥተኛ ለማድረግ ሞክሩ!   ⚠️ edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት የለውም!   🙏 መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ! የእግዚአብሔር ቃል ማስተዋልን ይስጠን! 🙏