የቀጠናው ተመልካች
رفتن به کانال در Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 330
مشترکین
+2824 ساعت
+307 روز
-4230 روز
آرشیو پست ها
4 330
- 🇺🇸 /🇵🇰/ 🇮🇷 ኢራናዊው ጋዜጠኛ ከኢስላማባድ - ኩሽነር እና ዊትኮፍ ለምን ወደ ኢስላማባድ እንደሚላኩ አናውቅም፣ ከእነሱ ጋር የሚደረግ ምንም ዓይነት ስብሰባ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አጀንዳ ውስጥ የለም። በተጨማሪም፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እነሱ እዚህ እስኪደርሱ ፓኪስታንን ለቆ ሊሄድ ይችላል።
4 330
- 🇮🇱 /🇱🇧/ 🇮🇷 አዲስ፡ በደቡባዊ ሊባኖስ፣ ቢንት ጅቤይል በተባለች ከተማ መሃል፣ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአንድ ህንፃ ውስጥ የተከበቡ ስድስት የሂዝቦላህ ተዋጊዎች፣ የእስራኤል ጦር በቅርብ ርቀት ውጊያ ደጋግሞ ሊያጠፋቸው ባለመቻሉ፣ በአየር ድብደባ ገድሏቸዋል።
4 330
CNN: ትራምፕ፣ ልዑኮቹን ዊትኮፍ እና ኩሽነርን፣ ወደ ኢስላምአባድ የኢራንን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዲገናኙ ልኳቸዋል።
ከሰዓታት በፊት አልጀዚራ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ከአሜሪካ ልዑካን ጋር በምንም መልክ መገናኘት ዕቅዱ እንዳልሆነ ዘግቦ ነበር።
4 330
🇮🇷🚫🇺🇸 የኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን ጦርነቱ ዳግም ከተነሳ ኢላማ ይደረጋል ያለውን የኢነርጂ ተቋማት ዝርዝር አውጥቷል።
• 🇶🇦 በኳታር ውስጥ Ras Gas እና Ras Laffan LNG መገልገያዎች
• 🇦🇪 በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ Das እና Zirku ደሴቶች (ዋና የባሕር ዳርቻ የነዳጅ እና ጋዝ ማዕከሎች)
• 🇸🇦 በሳውዲ አረቢያ ውስጥ Ab Qayk, Safaniya እና Kurais የነዳጅ እና ጋዝ መሠረተ-ልማቶች እና መገልገያዎች
• 🇰🇼 በኩዌት ውስጥ የ Burgan የነዳጅ ዘይት መሬቶች።
🔴 እነዚህን IRGC እንደሚያጠቃ አሳስቧል።
4 330
🇮🇷🇵🇰🇴🇲🇷🇺⚡️ - የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራክቺ፣ ኢስላማባድን በሚጎበኙበት ወቅት ከአሜሪካ ጋር ምንም ዓይነት ውይይት ወይም ግንኙነት አያደርጉም። ይልቁንም፣ በሁለትዮሽ - በኢራን እና በፖኪስታን- ግንኙነት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን አልጀዚራ አንድ ከፍተኛ የኢራን ምንጭን ጠቅሶ ዘግቧል።
➡️ ሞስኮ፣ ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባቱን ለመፍታት የሚረዱ ሀሳቦች ሊኖሯት ይችላልም ተብሏል። ኦማን ከቴህራን ጋር ያላት የጠበቀ ግንኙነትም እንዲሁ፣ ኢራን ወደ ድርድር እንድትመለስ በማመቻቸት ረገድ ሚና ሊጫወት ይችላል።
ኢራን 'ከአሜሪካ ጋር አልደራደርም' በሚለው አቋሟ እስካሁን እንደፀናች ነው።
4 330
+2
🇷🇺 🌎ሩሲያ አዳዲስ የምድር ምስሎችን ለቅቃለች።
የሩሲያ ስፔስ ተቋም፣ Elektro-L. በተባለች ሳተላይቱ የተነሱ አዳዲስ የምድር ምስሎችን አጋርቷል።
4 330
- 🇮🇷 / አዲስ፡ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራክቺ ከኢራቅ ኩርዲስታን ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝቶ፣ ድንበር ተሻጋሪ ሽብርተኝነትን ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አሳውቋል። አራክቺ በተጨማሪም፣ ኢራን ኩርዶች ከጠላት አሜሪካ ጋር እየተባበሩ ነው ብላ ባሰበችበት ጊዜ ሁሉ፣ በቦምብ ለመምታት እና በኤርቢል የአሸባሪ መሪዎችን ለማጥፋት ወደ ኋላ እንደማትል ተናግሯል።
4 330
🇺🇸🇮🇷Pets Hegseth በኢራን ወደቦች ላይ ስላለው እገዳ -
የአሜሪካ ጦር ተወዳዳሪ የለውም - ኃይልን ማቀድ፣ ለተቃዋሚዎች መተላለፍን መከልከል እና በመረጥነው ጊዜ እና ቦታ ፍላጎታችንን መጠበቅ እንችልበታለን። ከዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ፈቃድ ውጭ፣ ማንም ከሆርሙዝ የባሕር መስመር ወደ የትኛውም የዓለም ክፍል የሚጓዝ የለም።
4 330
🇺🇸❌🇮🇷- የአሜሪካ ጦር ሚንስቴር Pete Hegseth አሁን: የኢራን ጦር ወደ የባሕር ወንበዴዎች ቡድን ተቀይሯል፣ እነሱም አሸባሪዎች ናቸው።
4 330
🇺🇸⚔️🇮🇷 US Central Command (ማዕከላዊ እዝ)፡ ከብዙ አሥርተ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አውሮፕላኖች አጓጓዦች ደምሳሽ መርከቦች በመካከለኛው ምስራቅ በአንድ ጊዜ እየሠሩ ነው። የ US አውሮፕላን አጓጓዥ መርከቦች፣ አብርሃም ሊንከን (ሲቪኤን 72)፣ ጄራልድ ፎርድ (ሲቪኤን 78) እና ጆርጅ ኤችደብሊው ቡሽ (ሲቪኤን 77)፣ ከ200 በላይ አውሮፕላኖችን እና 15,000 መርከበኞችን እና የባሕር ኃይል ወታደሮችን አቅፈው በቀጠናው እየተንቀሳቀሱ ናቸው።
4 330
🇺🇸❌🇮🇷🛢 - ኢራን የድፍድፍ ዘይት የማከማቻ አቅሟ እያለቀ በመምጣቱ፣ የድሮውን የነዳጅ መርከብ Nasha ን ከጡረታ አውጥታ ወደ ሥራ መልሳለች።
የ30 ዓመቱ ታንከር ለብዙ ዓመታት ባዶ ሆኖ በመልህቁ ታስሮ ቆይቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን እንደ የባሕር ዳርቻ ማከማቻነት እንዲያገለግል ሆኖ ወደ ሥራ ገብቷል።
የአሜሪካ እገዳ እየጠነከረ ነው፣ ኢራንም በአብዛኛው ዘይት ወደ ውጭ መላክ አልቻለችም። በመሆኑም ኢራን የማከማቻ አቅሟን አሟጣ ከተጠቀመች በኋላ፣ የነዳጅ ጉድጓዶቿን መዝጋት ሊኖርባት ይችላል። ይህ ደግሞ በጣም ከባድ እና ውስብስብ ሥራ ሲሆን፣ መልሶ ለመክፈት ወራቶችን ይወስዳል።
4 330
🇺🇸🇮🇷 "አሜሪካ ከኢራን ጋር የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለመቅደድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፣ የጥቃት ዒላማዎችንም እያዘጋጀች ነው CNN
ከዒላማዎቹ መካከል በሆርሙዝ ወሽመጥ የኢራን የባሕር ኃይል ይገኝበታል።"
4 330
🇸🇦 🤝 🇺🇸 ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ የአሜሪካ ግዙፍ ወታደራዊ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች፣ እጅግ በብዛት ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል። በአሁኑ ጊዜ፣ በአየር ላይ ቢያንስ ስድስት "የሚበሩ ታንከሮች" እንዳሉ ይታያል። ይህም በተዘዋዋሪ፣ በኢራን ላይ ሌላ ዙር ድብደባ ሊጀመር ቋፍ ላይ እንደተደረሰ እና ዛሬም እነ ሳዑዲ ለአሜሪካ ጦር ሽፋን እየሰጡ እንደሆነ አመላካች ነው።
4 330
🇵🇸 🇱🇧
ከእስራኤል በፊት ያልነበረችው እና በኋላ የተፈበረከችው ዮርዳኖስ እና ሁሉም ከፍልስጤም የመጡ እና ቃል በቃል ወንድሞቻችን ብለን የምንጠራቸው ዮርዳኖሳውያን፣ እንደ ሊባኖስ ሕዝብ ከእኛ (ፍልስጤማዊያን) ጋር አልቆሙም።
አዎ! ሊባኖሶች ጎረቤታችን ናቸው፣ ግን ዮርዳኖሳዊያን ለእኛ በጣም ይቀርቡን ነበር። ወደ 70% የሚሆኑት ከፍልስጤም የመጡ ናቸው። ድርጊታቸውን ላየ ግን፣ በጭራሽ እንደዚያ አይመስሉም። ሊባኖስን ሁሌም እናመሰግናለን።" Palestinian Observer
4 330
🇵🇦 የፓናማ የባሕር መተላለፊያ ክፍያ በሦስት እጥፍ ጨምሯል፣ Financial Times
የሆርሙዝ ባሕር መዘጋት የአማራጭ መንገዶችን ፍላጎት ጨምሯል፣ የዓለም አቀፍ የኃይል ማጓጓዣ ወጪዎችንም እንዲሁ። የፓናማ የባሕር ወሽመጥ ክፍያ፣ ከ130,000 ዶላር ወደ 385,000 ዶላር (3 እጥፍ) እና በአንዳንድ ሁኔታዎች እስከ 4 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።
4 330
🇺🇸🇮🇱❌🇮🇷❗️ - እንደ እስራኤሉ ቻናል 13 ዘገባ ከሆነ፣ የእስራኤል ባለስልጣናት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚያደርገውን ጥቃት ዳግም እንዲጀምር በማሳመን ላይ ለመዘጋጀት፣ ከኔታንያሁ ጋር ተገናኝተዋል።
📺 ቻናል13
4 330
🇸🇦 🇶🇦 🇧🇭 🇰🇼 🇦🇪 የገልፍ አገራት እና የሳዑዲ ዓረቢያ የጀት ነዳጅ አቅርቦት፣ በ 80 በመቶ አሽቆልቁሏል ተብሏል።
ከእነዚህ አገራት ወደ ውጭ የሚላከው የጀት ነዳጅ፣ በመጋቢት ወር በ80 በመቶ ቀንሷል። በቀን ይላክ ከነበረው ከ605,000 በርሜል ፍጆታ፣ አሁን ላይ ወደ 127,000 በርሜል ወርዷል። በዓለም ሁለተኛዋ ትልቋ የጀት ነዳጅ አቅራቢ የሆነችው ኩዌት፣ አቅርቦቷ በ97 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፣ የአገራቱ የዓለም አቀፍ የጀት ነዳጅ አቅርቦት ድርሻ፣ ከጦርነቱ በፊት ከነበረበት 32 በመቶ በሚያዝያ ወር ወደ 3.7 በመቶ ወርዷል።
4 330
🇱🇧🇮🇱🇺🇸 "የሊባኖስ ህዝብ፣ የእስራኤል ሕዝብ፣ ጎረቤታማቾች ናቸው፣ እና መግባባት ይፈልጋሉ" - Mike Huckabee በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር። ነገር ግን በመሃላቸው፣ በሰፈር ውስጥ የሚኖር ረባሽ ትንሽ ልጅ አለ፣ በጎረቤቶቹ መስኮት ላይ ድንጋይ የሚወረውር (ያስቸገራቸው እሱ ነው)።
ሂዝቦላህ ማለቱ ነው።
4 330
🇮🇱 የእስራኤሉ ጋዜጣ፣ Haaretz እንደዘገበው፣ የእስራኤል ወታደሮች በደቡባዊ ሊባኖስ በሰፊው ዘረፋ እየፈጸሙ ሲሆን ሞተር ሳይክሎችን፣ ቴሌቪዥኖችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዲሁም የቤት እቃዎችን እየወሰዱ ነው።
⚠️ ይህ የሆነበት ምክንያት፣ አንዳንድ ወታደራዊ የጥበቃ ኬላዎች ስለተወገዱ እና አንዳንዶቹም ፈጽሞ ስላልነበሩ፣ ለዝርፊያውም ምንም ዓይነት ቅጣት ስለሌለባቸው ነው፣ ብሏል።
