የቀጠናው ተመልካች
Kanalga Telegram’da o‘tish
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 317
Obunachilar
-324 soatlar
-127 kun
-7530 kun
Postlar arxiv
4 317
🇺🇦🇷🇺⚡️የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን - እጅ ከሰጠን ወይም ከሩሲያ ጋር ስምምነት ለማድረግ ከሞከርን፣ ይህ ጦርነት በዩክሬን ድንበር ላይ ይቆማል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ተሳስተዋል።
የአህጉራችን ታሪክ የመገዛት ዋጋን አስተምሮናል። ይህ ስህተት እንዲደገም አንፈቅድም።
*-*-*-
አይ አጭሬ፣ ቦታ አግኝታ ረዘመች።
4 317
🇺🇦⚡️ጦርነቱ ካለቀ በኋላ፣ ዩክሬን አጋሮቿን ሁሉንም ዕዳዎቿን ይቅር እንዲሉላት እና "በንጹህ ሰሌዳ" እንድትጀምር እንዲያደርጉ መጠየቅ አለባት - የዩክሬን ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ Yuriy Kamelchuk.
4 317
🇩🇪 የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ እንደተናገረው፣ ኪየቭ እና አጋሮቿ ከሩሲያ ጋር ያለው ግጭት ካበቃ በኋላ ዩክሬን የምታገኘውን የደህንነት ዋስትናዎችን ይወስናሉ። ሞስኮ በዚህ ሂደት ውስጥ 'አትሳተፍም' ሲል ተናግሯል።
4 317
🇷🇺⚡️አውሮፓ፣ በዩክሬን ላይ ሩሲያ እና አሜሪካ የደረሱበትን ስምምነት፣ ለማዳከም እየሞከረች ነው፣ ሲል ላቭሮቭ ተናገረ።
እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የአውሮፓ ሀገራት በአላስካ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል የተደረጉትን የሰላም ስምምነቶች ለማዳከም "ጨዋታዎችን እየተጫወቱ" ነው።
*-*-*-
ኢዲየት! ዛሬም ስለ አላስካ ታወራለህ፣ ሞቶ ስለተረሳ ነገር? የአውሮፓንንስ ጠላትነት፣ አዲስ እንደደረስክበት ነገር የምታወራው፣ እስከዛሬ ሳታውቁ ቀርታቹህ ነው? ወይስ ሕዝብ ላይ እያላገጣችሁ ነው?
ማርኮ ሩቢዮ በአላስካ ምንም አይነት ስምምነት እንዳልነበረ አስቀድሞ አላብራራም? አሜሪካ የለም ያለችውን፣ ዩክሬን እና የአውሮፓ አጋሮቿ ወዲያውኑ ውድቅ ያደረጉትን፣ እንዴት ነው ሩሲያና አሜሪካ በአላስካ ተስማምተናል የምትለው? ተስማማህ እንበል፣ ለምን ዛሬ አሜሪካ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለች?
ሩሲያ እነዚህን የጀፈጀፉ ዘገምተኛ መሪዎቿን ይዛ፣ እንደው እያየናት ተበልታ ልትቀር ነው።
4 317
🇮🇷❌🇰🇼🇺🇸 - IRGC በኩዌት አብዱላህ ወደብ አካባቢ የሚገኘውን የKGL ሎጅስቲክስ ድጋፍ ማዕከልን በሌሊት ጥቃቶቹ ማውደሙን ተናገረ።
➡️ የናሳ የሳተላይት የእሳት ካርታ መረጃ በተመሳሳይ ቦታ ላይ አሁንም ድረስ እሳቶች እንዳሉ ያረጋግጣል።
➡️ KGL ሎጅስቲክስ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የፔንታጎን ኮንትራቶችን የያዘ ሲሆን፣ ይህም ከባድ ወታደራዊ ትራንስፖርትን፣ የወታደር ምግብ ስርጭትን እና በቀጠናው ላሉ የአሜሪካ ኃይሎች የወደብ እና የመጋዘን ድጋፍን ይሸፍን ነበር።
4 317
🇸🇦🇾🇪 የየመን አንሳር አላህ (ሁቲዎች)፣ የሳዑዲ ዓረቢያን ቻይና ሰራሽ ረጅም ርቀት ድሮንን፣ በተሳካ ሁኔታ መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል።
4 317
🇸🇦🇾🇪 የየመን አንሳር አላህ (ሁቲዎች)፣ የሳዑዲ ዓረቢያን ቻይና ሰራሽ ረጅም ርቀት ድሮንን፣ በተሳካ ሁኔታ መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል።
4 317
🇮🇷🇧🇭⚡️ አዳዲስ ፍንዳታዎች በባሕሬን ይሰማሉ።
*-*-*
ስለ ባሕሬን ትንሽ፡ ኢራን በባሕሬን ላይ፣ እስከ 1970 እንደ ፈረንጆች፣ የይገባኛል ጥያቄ ስታነሳ ኖራለች። በታሪክ ባሕሬን የኢራን ክፍለ ሀገር ነበረች። ሕዝቦቿ ሺዓ እስልምና የሚከተሉ ናቸው፣ ንጉሦቿ ደግሞ ሱኒ እስላሞች ናቸው። የንጉሣዊው ቤተሰብ የሚጠበቀው እና የሚሾመው በሳዑዲ ዓረቢያ ነው። በመሬት ድንበር ስላላቸው፣ በባሕሬን የሕዝብ ሰልፍ፣ ቅሬታ ቢኖር፣ በፓትሮል ገብተው የፀጥታ ሥራ (ማፈን) የሚሠሩት የሳዑዲ ፖሊሶች ናቸው።
የኢራኑ ንጉሥ፣ መሐመድ ረዛ ባሕላቪ፣ የባሕሬንን የይገባኛል ጥያቄን ትቶ፣ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ድንበር ያሰመረው በ1971 ነበር።
4 317
🇮🇷🇦🇪⚡️የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የተመታው መጋዘን ሳይሆን የአሜሪካ ኤምባሲ ነው በማለት ላይ ናቸው። ለአሁን፣ የተመታው ምንነት ግልፅ አይደለም።
4 317
⚡️🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራንን በተመለከተ የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል- FOX NEWS
- የኃይል መሠረተ-ልማት ዒላማዎችን ለበኋላ አስቀምጣለሁ። ነገር ግን፣ በመጨረሻ የኃይል መሠረተ-ልማቶቻቸውን መምታታችን የማይቀር ነው። አዎ፣ ዛሬ ማታ በጣም እንመታቸዋለን። ነገ ማታ በጣም እንመታቸዋለን። በማግስቱ በጣም እንመታቸዋለን። እና በሚቀጥለው ሳምንት ለእነሱ በጣም መጥፎ ይሆናል፣ ምክንያቱም በሚቀጥለው ሳምንት የኃይል ማመንጫዎቻቸው ይመጣሉ። በሚቀጥለው ሳምንት ድልድዮቻቸው ይመጣሉ። ሁሉንም የኃይል ማመንጫዎቻቸውን እናጠፋለን ። ጠረጴዛው ላይ መጥተው ካልተደራደሩ በስተቀር፣ ሁሉንም ድልድዮቻቸውን እናጠፋለን!
4 317
🇮🇷🇺🇸🇧🇭🇰🇼⚡️IRGC ምሽቱን በቀጠለው ጥቃቱ፣ ባሕሬንና ኩዌት የሚገኙ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ሚሳዬሎችን እና ድሮኖችን ሲያስወነጭፍ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ አሁን ለቅቋል።
4 317
🇮🇷🇺🇸🇧🇭⚡️በባሕሬን የአሜሪካ 5ኛው የባሕር ሐይል ዋና ጦር ሰፈር፣ በቀጥታ በወደቁ በርካታ የኢራን ሚሳዬሎች ምሽቱን ተመትቷል።
በምስሉ፣ ነዋሪዎች በደስታ በሚመስል መልኩ፣ ሲጮሁ ይሰማሉ።
4 317
🇺🇸 / 🇮🇷 ባለፉት 3 ምሽቶች እና ባለፈው ወር ከ6 ጊዜ በላይ በየምሽቱ በአሜሪካ የአየር ድብደባ ኢላማ የተደረገው በሲሪክ የሚገኘው የቴሌኮሙኒኬሽን ግንብ፣ አሁንም እንደ ቆመ ነው።
*-*-*-
ወይ ብንክች፣ ነው ይሄ።
4 317
🇮🇷🇺🇸 "አሜሪካ፣ 'እናሳልፍሃለን' ብላ ቃል የገባችለት መርከብ በእንዲህ መልኩ እየሰመጠ ነው፣ 'አትለፉ' ብለን ስንል ስሙን!"- ኢራን
4 317
🇺🇸🇮🇷⚡️ዩናይትድ ስቴትስ፣ በኢራን ላይ አዳዲስ ወታደራዊ ጥቃቶችን፣ የባሕር እገዳውን ዳግም ከመጣሏ በፊት፣ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።
ጦሩ፣ "የኢራንን ባሕሩን የመዝጋት አቅም የሚያዳክም፣ ብሎም እስከመጨረሻው የሚያስቀር" ሲል የገለፀውን ወታደራ እርምጃ፣ አጠናክሮ ቀጥሏል።
እንደ አሜሪካ ጦር መረጃ መሠረት፣ የባሕር ሐይሉ ባለፉት ጥቂት ቀናት፣ ለ140 መርከቦች የይለፍ ሰጥቷል፣ ትዕዛዝ የጣሱ 9 መርከቦችን እንዳይንቀሳቀሱ አድርጎ መትቷል እና ለ50 የንግድ መርከቦች እጀባ ሰጥቷል፣ ብሏል።
4 317
+2
🇮🇷🇺🇸⚡️ተራው የአሜሪካ ነው፡ የአሜሪካ ጦር ሃይሎች፣ በምድር ከአረብ ሀገሮች፣ ከኩዌት እና ከባሕሬን (ኳታርና ኤሜሬት ፀባይ የገዙ ይመስላሉ) በሚወነጨፉ ሚሳዬሎቻቸው፣ በሚነሱ አይሮፕላኖቻቸው እና በባሕሮቻቸው ከሚንሳፈፉ መርከቦቻቸው፣ የኢራንን ወደቦች (ሆርሙዝ፣ ሲሪክ፣ ከሽም) የባሕር ዳርቻ ክፍለ ሀገሮችን (አህቫዝ እና ኩዚስታን) እና የሀገሪቱን የደቡብ ክፍል፣ በከፍተኛ ደረጃ በመደብደብ ላይ ናቸው።
4 317
🇺🇸🇷🇺🇺🇦⚡️ - በሴኔተር ሊንዚ ግራሃም ሞት የሩሲያ ባለስልጣናት እና የክሬምሊን ደጋፊ ተንታኞች፣ ግራሃም በሰፊው የኮንግረሱ ዋና የሩሲያ ነቃፊ (ጭልፊት) ተደርጎ ስለሚወሰድ፣ ዋሽንግተን በሞስኮ ላይ ያላት አቋም ሊለሰልስ እንደሚችል ተስፋ እያደረጉ ነው ሲል The Washington Post ዘግቧል።
➡️ በሩሲያ ላይ አዲስ የማዕቀብ ፓኬጅ ካስተዋወቀ በኋላ ከኪየቭ እንደተመለሰ የሞተው ግራሃም፣ በ2023 በሩሲያ "አሸባሪዎች እና ጽንፈኞች" ዝርዝር ውስጥ ተቀምጧል።
➡️ የሩሲያ ባለስልጣናት ንግግሩ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን እንደጎዳ ሲናገሩ የመንግስት ሚዲያዎቻቸው በመሞቱ በግልፅ እየፈነደቁ ነው።
➡️ በሞስኮ ውስጥ ያሉ አንዳንዶች፣ የግራሃም እና የታመመው ሴኔተር ሚች መካኔል አለመኖራቸውን፣ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እንደ እድል አድርገው ይመለከቱታል።
4 317
🇮🇷🇺🇸🇧🇭 በባሕሬን በአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ የተሰሙት የሚሳዬሎቹ ፍንዳታ ኃይል፣ በኳታር ነዋሪዎች የተሰሙ መርገብገቦችን ፈጥረው ነበር።
በጥቁሉ፣ 40 የሚሆኑ ሚሳዬሎች በቀጥታ ወድቀዋል።
የአሜሪካ የአየር መቃወሚያ ብቃትና አቅም፣ እንደ ዩክሬን ተሽመደመደ እንዴ? ይሄ ሁሉ መሬት ሲነካ … ከባድ ነው።
*-*-*
አንተ ቻይና! ምናባህ ትሰራለህ፣ ውጣ ከሀገሬ!
