es
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Ir al canal en Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 318
Suscriptores
-824 horas
-117 días
-8230 días
Archivo de publicaciones
🇺🇦 ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ፣ ዛሬ ጠዋት፣ በዩክሬን ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን የመከላከያ ሚኒስቴሩን፣ Mykhailo Fedorovን በማባረሩ፣ በመንግሥቱ እና በጦር ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈ
+1
🇺🇦 ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ፣ ዛሬ ጠዋት፣ በዩክሬን ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን የመከላከያ ሚኒስቴሩን፣ Mykhailo Fedorovን በማባረሩ፣ በመንግሥቱ እና በጦር ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈል እና ሽኩቻ ተነስቷል። እንደ KIYV INDEPENDENT እና The New York Times ዘገባ መሠረት፣ በጦሩ ውስጥ ያለው ሽኩቻ የቆየ ሲሆን፣ ሲብላላ መጥቶ፣ አሁን ከሚኒስትሩ መባረር ጋር፣ እንዳይባባስ ተፈርቷል። በአንዳንድ የዩክሬን ከተሞች፣ ሕዝቡ የዘለንስኪን ውሳኔ በመቃወም ሰልፍ ለመውጣት እየተነጋገሩ ናቸው።

🇺🇦 ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ፣ ዛሬ ጠዋት፣ በዩክሬን ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን የመከላከያ ሚኒስቴሩን በማባረሩ፣ በመንግሥቱ እና በጦር ሠራዊት ከፍተኛ መከፋፈል እና ሽኩቻ ተነስቷል። በአንዳንድ
+1
🇺🇦 ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ፣ ዛሬ ጠዋት፣ በዩክሬን ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን የመከላከያ ሚኒስቴሩን በማባረሩ፣ በመንግሥቱ እና በጦር ሠራዊት ከፍተኛ መከፋፈል እና ሽኩቻ ተነስቷል። በአንዳንድ የዩክሬን ከተሞች፣ ሕዝቡ የዘለንስኪን ውሳኔ በመቃወም ሰልፍ ለመውጣት እየተነጋገሩ ነው።

🇰🇼🇮🇷🇺🇸⚡️ኩዌት እና ባሕሬን ግዛታቸውን ለአሜሪካ ሰጥተው ኢራንን እያስመቱ ናቸው። በሌላ አባባል፣ ኢራንን እያጠቁ ያሉት ባሕሬንና ኩዌት ናቸው። እነ ሳዑዲ፣ ኳታር እና ኤሜሬት፣ ለአሁን አርፈው ተቀምጠዋል። ግዛቶቻቸውን ለአሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት እንድትከፍት እያስጠቀሙ አይደሉም፣ ከመጀመሪያው ዙር ጦርነት ኢራን በአሳማሚ ቅጣት ትልቅ ትምህርት አስተምራቸዋለችና። አሁን ለኢራን ያስቸገሩት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ሀገሮች ናቸው። እንደ እኔ፣ ኢራን እነዚህን ሀገሮች በቶሎ አንድ ነገር ካላደረገቻቸው፣ አሜሪካ በእነሱ በኩል ትወራታለች። ትውረራቸው ይሆን? የማይቻል አይደለም። በ91 ሳዳም ኩዌትን በሁለት ሰዓታት ኩዌትን መውረር ችሏል።

+4
🇮🇷🇺🇸⚡️የአሜሪካ ማዕከላዊ ወታደራዊ ዕዝ፣ CENTCOM, አዳዲስ ጥቃቶችን በኢራን ላይ አወጀ። ኢራን በበኩሏ፣ በሰሜን ኢራቅ ኩርዶችን፣ በባሕሬን እና በኩዌት፣ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን፣ ስትመታ አምሽታለች። *-*-*- በነገራችን ላይ፣ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ሲደረጉ የነበሩ የኢራን ጥቃቶች፣ በአሜሪካ የጦር ንብረቶች (ራዳሮች፣ ሚሳዬል መተኮሻዎች፣ ሎጀስቲክ መጋዘኖች እና ድሮን ጣቢያዎች) ላይ፣ በሳተላይ በተረጋገጡ ምስሎች፣ ዒላማቸውን በመምታት አውድመዋል። እንዲህ ያሉ ዒላማዎችን፣ ነጥሎ በቀጥታ ከሺኪሎሜትሮች በላይ በሚተኮሱ ሚሳዬሎችና ድሮኖች መምታት ቀላል ነገር አይደለም። እጅግ ከባድ ነው፣ ይህን ለመፈፀም፣ ከመሬት ወይም ከሰማይ የተረጋገጠ እና የማያወላውል የቦታዎቹን ኮኦርድኔታዊ አድራሻዎችን ማግኘትን ይጠይቃል። ምናልባት አሜሪካዎች እንደሚጠረጥሩት ሩሲያዎች መረጃዎችን ከሳተላይት እያነበቡ ይሰጧቸው ይሆን ለኢራኖች? መቼስ ፑቲን አሜሪካ በዩክሬን በኩል እያደማችው ያለውን፣ በኢራን ካልተበቀላት፣ ከብት እንደሆነ ይቀጥላል። በሌላ በኩል፣ ኢራኖች በጦርነት ቴክኖሎጂ ማንም ከሚገምተው ሳይሄዱ አይቀሩም። እርዳታም ላያስፈልጋቸው ይችላል።

🇺🇸🇨🇺 CBS ኒውስ፡ የUS የመከላከያ ባለስልጣናት፣ በኩባ ላይ የአየር ወለድ ጥቃትን ጨምሮ ወታደራዊ እርምጃ ሊወስዱ የሚችሉ የአደጋ ጊዜ ዕቅዶችን እየገመገሙ ናቸው፣ ምንም እንኳን ውሳኔ ባይ
🇺🇸🇨🇺 CBS ኒውስ፡ የUS የመከላከያ ባለስልጣናት፣ በኩባ ላይ የአየር ወለድ ጥቃትን ጨምሮ ወታደራዊ እርምጃ ሊወስዱ የሚችሉ የአደጋ ጊዜ ዕቅዶችን እየገመገሙ ናቸው፣ ምንም እንኳን ውሳኔ ባይሰጥም።

🇺🇦🇷🇺⚡️የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን - እጅ ከሰጠን ወይም ከሩሲያ ጋር ስምምነት ለማድረግ ከሞከርን፣ ይህ ጦርነት በዩክሬን ድንበር ላይ ይቆማል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ተሳስተዋል። የአህጉራችን ታሪክ የመገዛት ዋጋን አስተምሮናል። ይህ ስህተት እንዲደገም አንፈቅድም። *-*-*- አይ አጭሬ፣ ቦታ አግኝታ ረዘመች።

🇺🇦⚡️ጦርነቱ ካለቀ በኋላ፣ ዩክሬን አጋሮቿን ሁሉንም ዕዳዎቿን ይቅር እንዲሉላት እና "በንጹህ ሰሌዳ" እንድትጀምር እንዲያደርጉ መጠየቅ አለባት - የዩክሬን ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ Yuriy K
🇺🇦⚡️ጦርነቱ ካለቀ በኋላ፣ ዩክሬን አጋሮቿን ሁሉንም ዕዳዎቿን ይቅር እንዲሉላት እና "በንጹህ ሰሌዳ" እንድትጀምር እንዲያደርጉ መጠየቅ አለባት - የዩክሬን ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ Yuriy Kamelchuk.

🇩🇪 የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ እንደተናገረው፣ ኪየቭ እና አጋሮቿ ከሩሲያ ጋር ያለው ግጭት ካበቃ በኋላ ዩክሬን የምታገኘውን የደህንነት ዋስትናዎችን ይወስናሉ። ሞስኮ በዚህ ሂደት ውስጥ '
🇩🇪 የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ እንደተናገረው፣ ኪየቭ እና አጋሮቿ ከሩሲያ ጋር ያለው ግጭት ካበቃ በኋላ ዩክሬን የምታገኘውን የደህንነት ዋስትናዎችን ይወስናሉ። ሞስኮ በዚህ ሂደት ውስጥ 'አትሳተፍም' ሲል ተናግሯል። 

🇷🇺⚡️አውሮፓ፣ በዩክሬን ላይ ሩሲያ እና አሜሪካ የደረሱበትን ስምምነት፣ ለማዳከም እየሞከረች ነው፣ ሲል ላቭሮቭ ተናገረ። እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የአውሮፓ ሀገራት በአላስካ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል የተደረጉትን የሰላም ስምምነቶች ለማዳከም "ጨዋታዎችን እየተጫወቱ" ነው። *-*-*- ኢዲየት! ዛሬም ስለ አላስካ ታወራለህ፣ ሞቶ ስለተረሳ ነገር? የአውሮፓንንስ ጠላትነት፣ አዲስ እንደደረስክበት ነገር የምታወራው፣ እስከዛሬ ሳታውቁ ቀርታቹህ ነው? ወይስ ሕዝብ ላይ እያላገጣችሁ ነው? ማርኮ ሩቢዮ በአላስካ ምንም አይነት ስምምነት እንዳልነበረ አስቀድሞ አላብራራም? አሜሪካ የለም ያለችውን፣ ዩክሬን እና የአውሮፓ አጋሮቿ ወዲያውኑ ውድቅ ያደረጉትን፣ እንዴት ነው ሩሲያና አሜሪካ በአላስካ ተስማምተናል የምትለው? ተስማማህ እንበል፣ ለምን ዛሬ አሜሪካ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለች? ሩሲያ እነዚህን የጀፈጀፉ ዘገምተኛ መሪዎቿን ይዛ፣ እንደው እያየናት ተበልታ ልትቀር ነው።

+4
🇮🇷❌🇰🇼🇺🇸 - IRGC በኩዌት አብዱላህ ወደብ አካባቢ የሚገኘውን የKGL ሎጅስቲክስ ድጋፍ ማዕከልን በሌሊት ጥቃቶቹ ማውደሙን ተናገረ። ➡️ የናሳ የሳተላይት የእሳት ካርታ መረጃ በተመሳሳይ ቦታ ላይ አሁንም ድረስ እሳቶች እንዳሉ ያረጋግጣል። ➡️ KGL ሎጅስቲክስ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የፔንታጎን ኮንትራቶችን የያዘ ሲሆን፣ ይህም ከባድ ወታደራዊ ትራንስፖርትን፣ የወታደር ምግብ ስርጭትን እና በቀጠናው ላሉ የአሜሪካ ኃይሎች የወደብ እና የመጋዘን ድጋፍን ይሸፍን ነበር።

🇸🇦🇾🇪 የየመን አንሳር አላህ (ሁቲዎች)፣ የሳዑዲ ዓረቢያን ቻይና ሰራሽ ረጅም ርቀት ድሮንን፣ በተሳካ ሁኔታ መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል።
🇸🇦🇾🇪 የየመን አንሳር አላህ (ሁቲዎች)፣ የሳዑዲ ዓረቢያን ቻይና ሰራሽ ረጅም ርቀት ድሮንን፣ በተሳካ ሁኔታ መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል።

🇸🇦🇾🇪 የየመን አንሳር አላህ (ሁቲዎች)፣ የሳዑዲ ዓረቢያን ቻይና ሰራሽ ረጅም ርቀት ድሮንን፣ በተሳካ ሁኔታ መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል።

🇮🇷🇧🇭⚡️ አዳዲስ ፍንዳታዎች በባሕሬን ይሰማሉ። *-*-* ስለ ባሕሬን ትንሽ፡ ኢራን በባሕሬን ላይ፣ እስከ 1970 እንደ ፈረንጆች፣ የይገባኛል ጥያቄ ስታነሳ ኖራለች። በታሪክ ባሕሬን የኢራን ክፍለ ሀገር ነበረች። ሕዝቦቿ ሺዓ እስልምና የሚከተሉ ናቸው፣ ንጉሦቿ ደግሞ ሱኒ እስላሞች ናቸው። የንጉሣዊው ቤተሰብ የሚጠበቀው እና የሚሾመው በሳዑዲ ዓረቢያ ነው። በመሬት ድንበር ስላላቸው፣ በባሕሬን የሕዝብ ሰልፍ፣ ቅሬታ ቢኖር፣ በፓትሮል ገብተው የፀጥታ ሥራ (ማፈን) የሚሠሩት የሳዑዲ ፖሊሶች ናቸው። የኢራኑ ንጉሥ፣ መሐመድ ረዛ ባሕላቪ፣ የባሕሬንን የይገባኛል ጥያቄን ትቶ፣ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ድንበር ያሰመረው በ1971 ነበር።

🇮🇷🇦🇪⚡️የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የተመታው መጋዘን ሳይሆን የአሜሪካ ኤምባሲ ነው በማለት ላይ ናቸው። ለአሁን፣ የተመታው ምንነት ግልፅ አይደለም።

⚡️⚡️🇮🇷🇰🇼 የኢራን ሸሂድ ድሮን በኩዌት 'የመሳሪያ መጋዘን' ሲመታ የሚያሳይ እብድ ቀረጻ።

⚡️🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራንን በተመለከተ የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል- FOX NEWS
- የኃይል መሠረተ-ልማት ዒላማዎችን ለበኋላ አስቀምጣለሁ። ነገር ግን፣ በመጨረሻ የኃይል መሠረተ-ልማቶቻቸውን መምታታችን የማይቀር ነው። አዎ፣ ዛሬ ማታ በጣም እንመታቸዋለን። ነገ ማታ በጣም እንመታቸዋለን። በማግስቱ በጣም እንመታቸዋለን። እና በሚቀጥለው ሳምንት ለእነሱ በጣም መጥፎ ይሆናል፣ ምክንያቱም በሚቀጥለው ሳምንት የኃይል ማመንጫዎቻቸው ይመጣሉ። በሚቀጥለው ሳምንት ድልድዮቻቸው ይመጣሉ። ሁሉንም የኃይል ማመንጫዎቻቸውን እናጠፋለን ። ጠረጴዛው ላይ መጥተው ካልተደራደሩ በስተቀር፣ ሁሉንም ድልድዮቻቸውን እናጠፋለን!

🇮🇷🇺🇸🇧🇭🇰🇼⚡️IRGC ምሽቱን በቀጠለው ጥቃቱ፣ ባሕሬንና ኩዌት የሚገኙ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ሚሳዬሎችን እና ድሮኖችን ሲያስወነጭፍ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ አሁን ለቅቋል።

🇮🇷🇺🇸🇧🇭⚡️በባሕሬን የአሜሪካ 5ኛው የባሕር ሐይል ዋና ጦር ሰፈር፣ በቀጥታ በወደቁ በርካታ የኢራን ሚሳዬሎች ምሽቱን ተመትቷል። በምስሉ፣ ነዋሪዎች በደስታ በሚመስል መልኩ፣ ሲጮሁ ይሰማሉ።

🇺🇸 / 🇮🇷 ባለፉት 3 ምሽቶች እና ባለፈው ወር ከ6 ጊዜ በላይ በየምሽቱ በአሜሪካ የአየር ድብደባ ኢላማ የተደረገው በሲሪክ የሚገኘው የቴሌኮሙኒኬሽን ግንብ፣ አሁንም እንደ ቆመ ነው። *-*-*
 🇺🇸 / 🇮🇷 ባለፉት 3 ምሽቶች እና ባለፈው ወር ከ6 ጊዜ በላይ በየምሽቱ በአሜሪካ የአየር ድብደባ ኢላማ የተደረገው በሲሪክ የሚገኘው የቴሌኮሙኒኬሽን ግንብ፣ አሁንም እንደ ቆመ ነው። *-*-*- ወይ ብንክች፣ ነው ይሄ።