የቀጠናው ተመልካች
Kanalga Telegram’da o‘tish
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 327
Obunachilar
+2824 soatlar
+307 kun
-4230 kun
Postlar arxiv
4 330
🇲🇱⚡በማሊ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ፣ Kidal፣ ሠፍረው የነበሩ የሩሲያ ወታደሮች፣ በፈረንሳይ ለሚደገፉት በሳህል የአልቃዒዳ አማፂያን እጃቸውን ከሰጡ በኋላ በበርካታ ወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ከተማውን ለቅቀው ወጥተዋል።
በማሊ እየሆነ ያለው እየወጡ እንዳሉት መረጃዎች ከሆነ፣ ለሩሲያ እያመጣ ያለው ፖለቲካዊ እና ገፅታዊ ኪሳራ ከባድ ይሆናል።
4 330
🇲🇱⚡- ሰበር: Assimi Goita, የማሊ መሪ ከዋናው ከተማ Bamako አቅራቢያ ከምትገኘው Kati ከተማ, በተደጋጋሚ ጥቃት ምክኒያት ወዳልታወቀ ሥፍራ ጥሎ መሸሹ ታወቀ። Radio France International reports
ሩሲያ፣ የአልቃዒዳ ክንፍ የሆነውን የሳህል አማፂ ቡድንን፣ የዩክሬን እና የፈረንሳይ ወታደሮች በውጊያ እየረዱ ናቸው ስትል ከሳለች። በሌላ በኩል፣ ሩሲያ፣ ከማሊ መንግሥት ጎን በመቆም አማፂያኑን በመዋጋት ላይ ናት።
4 330
🇺🇸❌🇮🇷🇨🇳 - FOX NEWS ቻይና ኢራንን እየረዳች እንደሆነ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጠይቋል
ቻይና አሁን ኢራንን እየረዳች ነው ብለው ያስባሉ?ዶናልድ ትራምፕ፡
እየረዱ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ፣ ግን ብዙ አያሳስበኝም። የበለጠ ሊረዱ ይችላሉ። በድጋሜ፣ ምንም አይመስለኝም ቢረዱም። እኛ ሌሎች ሀገሮችን እንረዳለን። ዩክሬንን ረድተናል፣ ያን ያህል መርዳት ባይኖርብንም። መርዳት አልነበረብንም።
4 330
+2
🇦🇪 የኤሜሬት F-16 ተዋጊ ጀቶች የሶሪያን ፕሬዝዳንት ለጉብኝት በመጣ ጊዜ አይሮፕላኑን አጅበውት ታይተዋል። ፎቶዎቹን በአትኩሮት ለተመለከተ፣ አንድ ነገር ያስተውላል። የጀቶቹን ምንነት የሚለይ ምንም ዓይነት ምልክት አይታይባቸውም። seriel ቁጥራቸው፣ ሎጎው እና ባንዲራው በቅብ ተሸፍኗል። ይህ የሆነበት ምክኒያት በኢራን ዳግም ለሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ፣ አይሮፕላኖች የኤሜሬት መሆናቸው እንዳይታወቁ ሊሆን ይችላል፣ የሚሉ ምልከታዎች አሉ።
* ባንዲራና ሎጎ የሚታይበት አንደኛው ምስል የበፊት ነው።
4 330
🇲🇱 🇫🇷 🇷🇺 የማሊ መከላከያ ሚንስትር Sadio Kamara፣ በትናንቱ የአማጺያን ጥቃት መገደሉ ተሰማ።
ከሳህል በረሃ የተነሱት የማሊ አማጺያን፣ በቀጠናው የአልቃዒዳ ክንፍ ሲሆኑ በትናንትናው ዕለት በርካታ ትልልቅ የማሊ ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ዋናው ከተማ Bamako መድረስ ችለዋል።
የማሊ መንግሥትን የሚረዳው የሩሲያ Africa Corps የተባለው ኃይል፣ በዋና ከተማው የአማጺያኑን ጥቃት በአየር ጭምር መመከት የቻለ ቢሆንም፣ እየወጡ እንዳሉ መረጃዎች፣ እነዚሁ የሩሲያ ኃይሎች አብዛኞቹን ከተሞች ለቅቀው ሲወጡና ገሚሱ ሲማረኩ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጩ ታይተዋል።
አማጺያኑ የአልቃኢዳ በቀጠናው ቅርንጫፍ ይሁኑ እንጂ፣ በፈረንሳይና በእንግሊዝ እንደሚደገፉ የማሊ መንግሥት ተናግሯል። ይህንም፣ አማጺያኑም ሆኑ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አልደበቁም።
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ፈረንሳይ በአካባቢው የነበራት ተጽእኖ፣ በተለይ በማሊ፣ በተደረጉ ተከታታይ መፈንቅለ-መንግሥቶች ምክኒያት የጠፋ ሲሆን አዲሱ አገዛዞች በይፋ ፈረንሳይን ከሀገራቸው አስወጥተው ከሀገሪቱ ጋር የነበራቸውን ማንኛውንም ግንኙነት አቋርጠው ነበር። በምትኩም፣ ከሩሲያ ጋር ቁርኝት ፈጥረዋል።
ይሄ፣ ምዕራባዊያንን አስቆጥቶ የነበር ሲሆን፣ አሁን በበቀል በሳህል አልቃኢዳ በኩል እርምጃ እየወሰዱ ይመስላል ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት የማሊ መንግሥት ዋና ከተማውን ላለማስነጠቅ እና በሥልጣኑ ለመቆየት ከፍተኛ የሞት ሽረት ትግል ላይ ነው።
4 330
🇮🇱 🤝 🇦🇪 Axios: እስራኤል Iron Dome የተሰኘውን የአየር መከላከያ ሥርዓቷን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን፣ በድብቅ ወደ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አሰማርታለች።
ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት እስራኤል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአየር መከላከያ ሥርዓቷን ከሀገሪቱ ውጭ አሰማርታለች። Iron Dome ከእስራኤል ኦፕሬተሮች ጋር በመሆን በቀጠናው በኢራን ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ወደ ደረሰበት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ተልኳል።
4 330
+1
🇺🇸 DC & Capitol Police፡ "ተኳሹ ዕድሜው 31 ነው፣ ከካሊፎርኒያ ነው የመጣው። በሆቴሉ ተጠቃሚ እንግዳ ነበር። አንድ ጠመንጃ፣ ሁለት ሽጉጦች እና ሁለት ጩቤዎች ይዟል። ይህን ያደረገው አስቦና አቅዶበት ነው ብለን እናምናለን፣ ለዚሁ ሲባል መሳሪያውን ቀድሞ ወደ ሆቴሉ ሳያስገባ አይቀርም። ብቻውን ነበር፣ምናልባት ሌሎችም አብረውት ሊኖሩ ይችላሉ። እያጣራን ነው። በመጪው ቀናት ሁሉም የሚገለጥ ይሆናል።"
4 330
🇺🇸 ⚡️ —የዋሽንግተን ዲሲ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ Jeanine Pirro፡ ተጠርጣሪው በሁለት የጦር መሳሪያን ለግድያ በመጠቀም ክስ እና የፌዴራል ፀጥታ አስከባሪ ላይ በመተኮስ ወንጀል ተከሷል።
4 330
+1
🇺🇸 ምስሉ፣ ተኳሹ እንደተያዘ የተነሳ ነው። አልቆሰለም፣ አልተመታም። ፖሊስ ታግሎ ነው የጣለው። ተጠርጣሪው በሆቴሉ እንግዳ ነበር።
4 330
🇺🇸 በዛሬው ምሽት፣ ዋይት ሃውስ በWashington Hotel ባዘጋጀው ዓመታዊ የእራት ግብዣ ላይ የተኩስ እሩምታ መሰማቱ ተነገረ። ተኳሹ፣ በሆቴሉ የፖሊስ ጥበቃን አልፎ መሮጥ የቻለ ቢሆንምና ፕሬዝዳንቱ ከነበረበት 150 ሜትር ርቀት ድረስ መድረስ ቢችልም፣ በፀጥታ ኃይሎች ትግል ከመሬት ላይ ወድቆ ሳይተኮስበት ሊያዝ ችሏል። በርካታ መሳሪያዎችንም ታጥቆ እንደነበር ታውቋል። ይኸው ግለሰብ ከፍቶ በነበረው ተኩስ በአንድ ፖሊስ ላይ ቀላል የመቁሰል አደጋ ያደረሰ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ ከቦታው በፍጥነት በጠባቂዎቹ ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዱ ተሰምቷል።
4 330
Repost from Donald J. Trump
Quite an evening in D.C. Secret Service and Law Enforcement did a fantastic job. They acted quickly and bravely. The shooter has been apprehended, and I have recommended that we “LET THE SHOW GO ON” but, will entirely be guided by Law Enforcement. They will make a decision shortly. Regardless of that decision, the evening will be much different than planned, and we’ll just, plain, have to do it again. President DONALD J. TRUMP
4 330
+1
🇮🇷🛸🚫🇺🇸 'የአሜሪካ ስስ ብልት'፣ (The Achilles' heel of the USA) ጣሊያናዊ ዲዛይነር እንደገለፀው።
የኢራን "ሸሂድ" ድሮን ከአሜሪካ ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ያለውን ጦርነት እንዴት በሆነ ስልታዊ መንገድ 'በአቻ' እንዲቋጭ እንዳደረገ፣ እንደ ጣልያናዊው ሰዓሊ።
4 330
🇺🇸 🇮🇶 ኩርዶች አሜሪካንን በኢራን ጦርነት ለመርዳት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው፣ የትራምፕ አስተዳደርን ክፉኛ አስቆጥት እንደነበር ይታወሳል።
እንደሚታወሰውም፣ ከሳምንት በፊት ትራምፕ
አሜሪካ ለኩርዶች በመሬት ኢራንን እንዲወሩ 'ጥሩ ጥሩ መሳሪያዎች' ሰጥተናቸው ነበር፣ እናም ጊዜው ደርሶ በሉ ጀምሩ ስንላቸው፣ መሳሪያውን ይዘው ተሰወሩ፣ ለዚህ ክህደታቸው ደግሞ ይከፍሏታልብሎ ነበር። በዛሬው ዕለት የአሜሪካ ፍትህ ሚንስትር፣ Beverly Hills ካሊፎኒያ የሚገኘውን የኩርድ ፕሬዝዳንት መስዑድ ባርዛኒን መኖሪያ ቤት እና 'ቤተመንግሥቱ' እንዲወረሱ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን፣ በገንዘብ ዝርፊያም ባርዛኒን ከነ ልጁ ከሷል።
