uz
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Kanalga Telegram’da o‘tish

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 293
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-217 kun
-9130 kun
Postlar arxiv
— 🇺🇸/🇮🇷 ትራምፕ ኢራን ለቅርብ ጊዜ ሀሳቡ ምላሽ ለመስጠት ሦስት ቀናት ያህል እንደሚወስድባት ተነግሮታል፤ አንድ ባለስልጣን 'ቃል በቃል በዋሻ ውስጥ ናቸው፣ ኢሜይል አይጠቀሙም' ብሏል – Axios

🇮🇷⚡️— የኢራን IRGC የባሕር ኃይል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በIRGC የባሕር ኃይሎች በተደረገ ቅንጅት እና ደህንነት የነዳጅ ታንከሮችን፣ የኮንቴይነር መርከቦችን እና ሌሎች የንግድ መርከቦች
🇮🇷⚡️— የኢራን IRGC የባሕር ኃይል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በIRGC የባሕር ኃይሎች በተደረገ ቅንጅት እና ደህንነት የነዳጅ ታንከሮችን፣ የኮንቴይነር መርከቦችን እና ሌሎች የንግድ መርከቦችን ጨምሮ 28 መርከቦች በደህና ሁኔታ የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋርጠዋል ብሏል።

+5
🇮🇱❌🇱🇧— የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ዛሬ ቀኑን ሙሉ በደቡብ ሊባኖስ በሚገኘው በታይር ከተማ ላይ በተከታታይ ኃይለኛ የአየር ጥቃቶችን አካሂደዋል።

⚡🇺🇳 ቻይና ክፍያዎቿን እያዘገየች በመሆኑ እና አሜሪካ ማንኛውንም ነገር ለመክፈል ፈጽሞ ፈቃደኛ ባለመሆኗ፣ የተባበሩት መንግስታት ገንዘብ እያለቀ ነው፣ በነሐሴ አጋማሽ የተባበሩት መንግስታት የገንዘብ አቅርቦቱ ያልቃል።

🇮🇷— በቴህራን ኤንግሌሃብ አደባባይ በተካሄደ የመንግስት ደጋፊ ሰልፍ ወቅት፣ IRGC "27 Rajab" የሚባል አዲስ ፈጣን የጥቃት ጀልባ አሳይቷል። የኢራን ሚዲያ፣ 27 Rajab፣ እስከ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ዒላማ መምታት የሚችሉ ሁለት የክሩዝ ሚሳይሎችን የመተኮስ፣ በሰዓት እስከ 200 ኪ.ሜ የመጓዝ እና እስከ 3 ሜትር ከፍታ ያላቸውን ማዕበሎች የመቋቋም አቅም እንዳለው ዘግቧል።

+1
🇮🇱⚡️🇱🇧 'የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ቤን-ግቪር ስለ ሊባኖስ፦ 'እነሱን የሚጎዳው ዳሂየህ ነው፣ ዳሂየህ መደምሰስ አለበት… ዳሂየህ ጥፍጥፍ ጥፍጥፍ ብሎ መጥፋት አለበት— ጥፍጥፍ፣ ጥፍጥፍ፣ እንደገና ጥፍ ጥፍ!' ** ዳሂየህ በስተ ደቡብ ያለ የቤሩት ከተማ ክፍል ነው።

🇺🇸⚡️ትራምፕ፦ አያችሁ፣ እነሱ የእልፍኝ አዳራሽ አላቸው — የቻይና ታላቅ አዳራሽ ተብሎ ይጠራል! በጣም ትልቅ እና ውብ ነው። ሰዎች የተሻለ ነገር ለመሥራት በማሰቤ ለምን ይቃወሙኛል? Dumboክራ
🇺🇸⚡️ትራምፕ፦ አያችሁ፣ እነሱ የእልፍኝ አዳራሽ አላቸው — የቻይና ታላቅ አዳራሽ ተብሎ ይጠራል! በጣም ትልቅ እና ውብ ነው። ሰዎች የተሻለ ነገር ለመሥራት በማሰቤ ለምን ይቃወሙኛል? Dumboክራቶች እብድ ናቸው!

+2
🇫🇷 የፓሪስ ከተማ ክለብ የአውሮፓ ዋንጫ አሸነፈ ብለው በደስታ ከተማ የሚያቃጥሉት የሦስተኛው ዓለም ስደተኞች፣ በሩጫ ላይ።

🇲🇦 🇿🇦 ጥቁር አፍሪካ በአፍሪካ አንደኛነቱን ተቀማ። ሞሮኮ ደቡብ አፍሪካን በማለፍ የአፍሪካ ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ ሆናለች።

🇺🇸🇺🇦🇷🇺 የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት እንዳሉት አሜሪካ ዩክሬን በጦር ሜዳ የምትፈልገውን ሁሉ እንድታገኝ የጦር መሳሪያ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ አቅዳለች። ** ፑቲን ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ ጦርነቱን በበላይነት ከማጠናቀቅ ይልቅ ፈራ ተባ ሲል፣ እንዲያውም እንገፋበታለን አሉ ጠላቶቹ። ጫናውን ይችለዋል? የኾነ ቦታ ቋ ብሎ ጦሩ እስኪሰበር እየጠበቁት ነው። ይፍጠን! ያለበለዚያ ታሪካዊ ውርደት ይመጣ ይመስላል!

🇺🇸 ⚡️Discombobulated ትርጉም፡ እጅግ ግራ መጋባት፣ መወዛገብ፣ መደነጋገር … እኔ ብቅ ስል፣ ዓለሙ የሚገባበት ጠፋው፣ እያለ ነው ትራምፕ።
🇺🇸 ⚡️Discombobulated ትርጉም፡ እጅግ ግራ መጋባት፣ መወዛገብ፣ መደነጋገር … እኔ ብቅ ስል፣ ዓለሙ የሚገባበት ጠፋው፣ እያለ ነው ትራምፕ።

🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶሻል ገጹን በፖስት አጥለቅልቆታል። 'ቤተሰብ መመስረት እና ልጅ መውለድ ኋላ ቀር ነው ተብሎ እናንተን ለማሳመን በቢሊዮኖች ፈሰስ ተደርጓል' እያለ ነው በአንዱ ፖስቱ።
+3
🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶሻል ገጹን በፖስት አጥለቅልቆታል። 'ቤተሰብ መመስረት እና ልጅ መውለድ ኋላ ቀር ነው ተብሎ እናንተን ለማሳመን በቢሊዮኖች ፈሰስ ተደርጓል' እያለ ነው በአንዱ ፖስቱ። በአሜሪካ በአሁኑ ሰዓት መውለድን ለማበረታታት በሚወለድ ልጅ $1000 ሺ ዶላር ይሰጣል። ይህን ትራምፕ፣ ወደ $5000 ሺ ዶላር ለማሳደግ እቅድ ይዟል። ልጅ ማስወረድ በአሜሪካ ወንጀል ተደርጎ ተደንግጓል፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ መቃምም ቢሆን እንዲሁ፣ እንደ ልብ እንዳይገኝ ተደርጓል። የጠንካራ ወንድ መገለጫ ልጅ ማስወለድ እና አባት ሆኖ በኃላፊነት ማሳደግ የሚለው ሲሆን ለሴት ደግሞ እናትነት ከምንም በላይ የሚያስከብራት እንደሆነ፣ በአሜሪካ በአሁን ጊዜ በየ ሚዲያው የሚነገር ጉዳይ ነው። ይህን 'ተፈጥሯዊ ሕግና ውነታ'፣ መጥፎ ነገር እንደሆነ እና በዚህም ቤተሰብን ሆን ተብሎ ለማፍረስ እና ማሕበረሰብን ለማጥፋት፣ ሰይጣናዊ አጀንዳ ያነገቡ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ ከ1960ዎቹ ጀምሮ ሆን ብለው ሲሰሩበት የኖሩት ነው፣ ብለው ዛሬ ብዙዎች፣ በተለይ ሪፐብሊካኖች፣ ይከሳሉ። በአፍሪካ እና እንደ ኢትዮጵያ ባሉ 'የደሃ ደሃ ሦስተኛው ዓለም' ሀገሮች ግን፣ የወሊድ መቆጣጠሪ እና 'የቤተሰብ ምጣኔ'፣ ያለ ውይይት፣ ያለ ገደብ እና ያለ ምርጫ፣ በሴት እህቶቻችን እና በእናቶቻችን ላይ በግድ ሲጫኑ እናያለን። የጨነገፈው ህፃን እና የመከነው ፅንስ ቢቆጠር፣ በራሱ፣ በሕዝብ ላይ የተፈጸመ ዘር ማጥፋት ወይም ጀኖሳይድ ሊባል ይችላል። የአፍሪካ መሪዎች የማይወዱትን የሕዝብ ዘር ለማጥፋት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ ይሄ ነው። ወሊድ ቁጥጥር እና ቤተሰብ ምጣኔን እንደ መሳሪያ ይጠቀሙበታል በዚህ ጉዳይ በሰፊው ወደ ፊት እንመጣበታለን።

🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቶማስ ማሲ፣ በማርጀሪ ቴይለር ግሪን፣ በራንድ ፖል፣ በተከር ካርልሰን፣ በካንድስ ኦዌንስ እና በሎረን ቦበርት ላይ ሙድ ይዟል።
🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቶማስ ማሲ፣ በማርጀሪ ቴይለር ግሪን፣ በራንድ ፖል፣ በተከር ካርልሰን፣ በካንድስ ኦዌንስ እና በሎረን ቦበርት ላይ ሙድ ይዟል።

🇸🇦🇺🇸⚡️🇮🇷 የሳዑዲ ዓረቢያ ኤክስፐርት ሙባረክ አል አቲ ለCNN ፕሬዝዳንት ትራምፕ የወረቀት ላይ ነብር ነው። ሳዑዲ፣ ትራምፕ ወደ ጦርነት ተመልሶ የጀመረውን እንዲጨርስ እና 'እስላማዊ'
🇸🇦🇺🇸⚡️🇮🇷 የሳዑዲ ዓረቢያ ኤክስፐርት ሙባረክ አል አቲ ለCNN ፕሬዝዳንት ትራምፕ የወረቀት ላይ ነብር ነው። ሳዑዲ፣ ትራምፕ ወደ ጦርነት ተመልሶ የጀመረውን እንዲጨርስ እና 'እስላማዊ' የሚባለውን የአያቶላዎችን ሲስተም እንዲያወድም ትፈልጋለች። ያንን ማድረግ ባለመቻሉ ግን፣ በዓለም አቀፍ መድረክ አሜሪካ ደካማ መስላ እንድትታይ ምክኒያት ሆኗል። ለሳዑዲ እና ለገልፍ ሀገሮች የአሜሪካ ደካማ ሆኖ መታየት፣ ለወደፊቱ ህልውናችንን እና ደህንነታችንን በእሷ ላይ እንዳንጥል አደጋ ጋርጧል። ትራምፕ ጠንካራ ቢሆንና ጦርነቱን መጨረስ ቢችል ኖሮ፣ ሳዑዲ ከእስራኤል ጋር በፍቅር እና በትብብር በተመሠረተ ወዳጅነት ላይ፣ በአብርሃም ስምምነት ጥላ ሥር ለመደመር አታቅማማም ነበር።

⚡️🇮🇱— 'በሰሜን፣ ሰዎች በዚህ ሁለት ቀን ለአንድ ደቂቃ እንኳን አልተኙም ወይም አላረፉም።' በእስራኤል ሚዲያ ዘገባ መሠረት፣ 'በእያንዳንዱ ቅጽበት የማንቂያ ድምጾች፣ ፍንዳታዎች፣ መከላከያዎች፣ ጥቃቶች እና ወደ መጠለያዎች መሮጥ ይከሰታል። ሂዝቦላ ከተጠበቀው በላይ ረብሿል።'

እንደ ሐሳብ፡ የኢትዮጵያ መሪዎች ትኩረት በጣም ይፈልጋሉ፣ ይሄን እናውቃለን። በአንድ ወቅት የኖቤል ተሸላሚው ዓለምን አስታርቃለሁ ሲል እንደነበር፣ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፣ መጀመሪያ ከራስህ ጋር ተታረቅና ና ተብሎ ከዓለም መድረክ ላይ ከመባረሩ በፊት። ዛሬ ደቡብ ሱዳንና ጅቡቲም የሚደውሉ አይመስለኝም። እናም፣ አሁን ላይ ትኩረትን ፍለጋ ከላይ ወርደው የዑጋንዳንና የአሜሪካ ባሪያዎችን ስፖንሰር በማድረግ ወደ ሀገር እያመጡና እየቀወጡት ከመፈጥፈጥ፣ ሌላ ዘዴ ቢቀይሱ፣ እንደ ሀገርም ብንቀይስ፣ እንደኔ ጥሩ ነው እላለሁ። ስለዚህ፣ ዛሬ ካዛኪስታን እንዳደረገችው፣ የኛዎቹም የመጣው ይምጣ ብለው፣ የኢራንን ዩራኒየም በቢሾፍቱ ግምጃ ቤት በአደራ ለማስቀመጥ ፈቃደኛነታቸው ይግለጡ ለዓለም። ከመቶ ሺ ቲክቶከራም ይሄ አንድ ንግግር በቂ፣ ከበቂም በላይ በቂ ትኩረት ይስባል። ሰሞኑን እያሉን እንዳሉት "ቅዠታሞች" አይበሉን እንጂ፣ እርሶም ይሞክሩት ነው ነገሩ።

🇰🇿🇮🇷🇺🇸 ካዛኪስታን የኢራንን የዩራኒየም ክምችት በአደራ ለማስቀመጥ ጥያቄ አቅርባለች የተባበሩት መንግስታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ፣ ዛሬ ለፋይናንሺያል ታይምስ በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ ዋሽንግተን እና ቴህራን በኢራን አወዛጋቢ የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ስምምነት ከደረሱ፣ ካዛክስታን የኢራንን የዩራኒየም ክምችት ለማስቀመጥ ሀሳብ አቅርባለች።

🇹🇷 ቱርክ KAAN (ካን) የተባለ ተዋጊ ጀት መሥራት ጀምራ ነበር፣ ነገር ግን ሥራው እክል ገጠመው። 🇺🇸 የጀቱ ሞተር የአሜሪካ F1110 ጀት ሞተር ነው፣ ያንን ደግሞ አሜሪካ ለመስጠት ሳትፈቅ
🇹🇷 ቱርክ KAAN (ካን) የተባለ ተዋጊ ጀት መሥራት ጀምራ ነበር፣ ነገር ግን ሥራው እክል ገጠመው። 🇺🇸 የጀቱ ሞተር የአሜሪካ F1110 ጀት ሞተር ነው፣ ያንን ደግሞ አሜሪካ ለመስጠት ሳትፈቅድ ቀረች። 🇹🇷🛠 "ሀገር-በቀል" ሞተር ለማምረት፣ የቱርክ ሂሳብ ጠበብቶች እና ሮኬት ሳይንቲስቶች 2035 ላይ ምናልባት ብለዋል። 🇬🇧🇪🇺 አዲስ ሞተር እንኳ ብትሠራ፣ UK እና EU፣ ቱርክ ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንዳታደርግ እንደሚይዟት ተናግረዋል። *** ቱርክም፣ ሜቴክ አላት ማለት ነው እንደኛ። ሞተር ከቻይና፣ ላሜራ እና ብየዳ ከሀገር፣ ከዚያ Made In የራስህ። ሌላውን ስፔርፓርት ሁሉ ከውጭ አስገባ፣ ችግር የለውም። ሞተርን የሚያክል ዋናውን ግን ከውጭ እንዳለ አምጥተህ ከገጠምክ በኋላ፣ እኔ ነኝ የፈበረኩት?

photo content

🇺🇦⚡️🇷🇺 ይህን የሚገርም ቪዲዮ ተመልከቱት፣ ምሽቱን የተፈጸመ ነው። ዩክሬን የሩሲያን አድሚራል ኤሰን የተባለን የክሩዝ ሚሳይል ተሸካሚ የጦር መርከብን፣ በኖቮሮሲይስክ የባሕር ኃይል ጣቢያ በFPV-ድሮኖች አጥቅታለች። ይህ ጥቃት በመርከቡ ላይ ለአራተኛ ጊዜ የተፈጸመ ጥቃት ነው። ምስሉ በአቅራቢያው ካለ መርከብ የተወሰደ ሲሆን፣ ድሮኑ መርከቡን ከመምታቱ በፊት ከባድ የፀረ-አውሮፕላን ተኩሶችን ሲያመልጥ ይታያል።