የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 290
订阅者
+124 小时
-157 天
-8430 天
帖子存档
4 290
—❗️🇺🇸/🇮🇷 ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የተጣለውን የአሜሪካ የባሕር ኃይል እገታ ሊያቆም መሆኑን ፍንጭ ሰጥቷል።
በምላሹ፣ ኢራን ብዙ ነገሮችን እንድታደርግ ይጠይቃል — ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎቹ የተስማሙባቸው አይደሉም፣ የበለጸገ የዩራኒየም ክምችት አሳልፎ መስጠትን ጨምሮ።
ትራምፕ በአሁኑ ሰዓት በስችዌሽን ሩም የመጨረሻውን ውሳኔ ለመወሰን ተቀምጫለሁ፣ ብሏል።
ምሽቱን የመጨረሻው ውሳኔ ይጠበቃል።
4 290
⚡️🇮🇷🇺🇸🇮🇱 ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ አዛዥ ሙሕሲን ረዛይ ኢራን በድርድር ወይም በቀጥታ እርምጃ የባህር ኃይል እገታውን እንደምትሰብር ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ዶግማ፣ ኢራን ሳትወድቅ ሊሳካ የማይችል አዲስ የቀጠና ሥርዓት ማስቀመጥ እንደሆነ ተናግረዋል።
“ዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል እገታውን እንድታቆም እናስገድዳታለን – ወይ በድርድር ወይም ከተቃወሙ፣ በቀጥታ እርምጃ በመውሰድ” ሲሉ ረዛይ ተናግረዋል።
በተጨማሪም፣ በአስር ዓመታት ውስጥ የአሜሪካ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ ወደ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛነት እንደሚወርድ ተንብየው፣ የኢራን ኢኮኖሚያዊ የወደፊት ተስፋ ግን ብሩህ እና ተስፋ ሰጪ ብለዋል።
4 290
🇮🇱⚔️🇱🇧 ከሮይተርስ የተገኘ አዲስ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ እስራኤል 20% የሚሆነውን የሊባኖስን ክፍል የሚሸፍኑ የመልቀቂያ ትዕዛዞችን በነዚህ ቦታ ለሚኖረው ሕዝብ ሰጥታለች፣ ይህም ከዚህ ቀደም ከተናገረችው እስከ ሊታኒ ወንዝ ካለው "Buffer Zone"ም በላይ ተሻግሮ የሚሄድ ነው።
የጋዛ ታክቲክ በሊባኖስ።
4 290
🇺🇸🇮🇷 — የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ሊደረግ የሚችለውን ስምምነት መፈረም አለመፈረምን ለመወሰን ጥቂት ቀናት እንደሚያስፈልገው ለአማካሪዎቹ አሳውቋ— CNN
**
ትራምፕ ሰነዱን መፈረም ፈርቷል። በአሜሪካ ከሁሉም አቅጣጫ፣ ከሚዲያው፣ ከአማካሪዎቹ፣ ከሴኔቱ፣ ከኮንግረስ እና ከሌሎችም፣ ሰነዱ ኢራንን የሚጠቅም፣ አሜሪካን ደግሞ ተሸናፊ የሚያስመስል ነው የሚል ቅሬታ እየተወረወረበት ነው።
ኦባማ በኢራን ድርድር ወቅት፣ የድርድሩ አካል የሆነን $1.7ቢሊዮን ዶላር በካሽ ሰጥቷቸዋል እያለ በየቀረበበት መድረክ ኦባማን ሲያብጠለጥለው የኖረው ትራምፕ፣ በዚህ በአሁኑ ድርድር፣ ለኢራን እስከ $300 ቢሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ሊፈርም ነው እየተባለ ተቸግሯል።
አለመፈረምም አይችልም፣ ምክኒያቱም ምርጫ እየመጣበት ነው፣ የግሮሰሪ ዋጋ ከፍ ብሏል፣ ጦርነቱም በሕዝቡ ተጠልቷል፣ ስለዚህ ለአሜሪካ መጥፎ ስምምነትም ቢሆን ከጦርነቱ እስካስወጣው ድረስ መፈረም ይኖርበታል። አጣብቂኝ ውስጥ ነው።
4 290
🇺🇳❌🇷🇺 - አንድ ድሮን ከመንገዱ ወጥቶ በሮማንያ በሚገኝ የአፓርታማ ሕንፃ ላይ ከወደቀ በኋላ ኔቶ 'የሩሲያን ግድየለሽነት' አውግዟል።
4 290
🇪🇹⚡️ኢትዮጵያ፡ የአብይ አሕመድ መገላለጥ፣ ከሰላም ዋንጫ አሸናፊነት እስከ ብልጽግና ወንጌል አራማጅነት AFP
'አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ፣ ብዙ ተስፋዎችን ሰንቆ ነበር። ዛሬ ግን፣ ተስፋዎቹ ሁሉ ወደ ስጋት እና ብሶት ተለውጠዋል። እርሱም፣ ጠንካራ የጴንጤ ቆስጤ እምነት አቀንቃኝ፣ ወደ ሃይማኖት ዋሻ ምሽግ ገብቷል። የፖርቲውንም ስያሜ በቀጥታ ከሚከተለው የወንጌል መስመር ቀድቶ፣ ብልፅግና ሲል ጠርቶታል። ነገሮች ከዚያ በኋላ መስመራቸውን ስተው ዛሬ አለ።
የቀጠናው ባለሙያዎች፣ "ሃይማኖቱን በመንግሥት አስተዳደሩ ውስጥ አስገብቶ የሚጨፍር መሪ፣ ሌሎች ድምፆችን ሊያስተናግድ ወይም ሊታገስ አይችልም። ምክኒያቱም እንዲህ ያለ መሪ አስተዳደራዊ መንገዴ ከጌታ ነው፣ እናንተ እነማናችሁና ሌላ ትነግሩኛላችሁ ስለሚል" ይላሉ።
በዚህም የተነሳ በትግራይ፣ በዐማራ፣ በኦሮሚያ እና በከተሞች ቀውስ፣ ጦርነት እና ችጋር ተንሰራፍቷል።'
4 290
🇺🇸⚡️ የናሳ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ጨረቃ ላይ ጣቢያ ለመገንባት እና ሰዎችን ወደ ጨረቃ ለመመለስ ያለው እቅድ፣ የጄፍ ቤዞስ Blue Origin ኩባንያ የኒው ግሌን ሮኬት በፍሎሪዳ በተደረገ ሙከራ ላይ ከፈነዳ በኋላ አደጋ ላይ ወድቋል።
ናሳ፣ በጨረቃ ላይ በ$20 ቢሊዮን ዶላር ሊገነባ ላቀደው ጣቢያ በዚህ ዓመት ሦስት ጊዜ ቁሳቁስ የጫኑ ሮኬቶችን ለማስወንጨፍ ያሰበ ሲሆን፣ ለዚሁ ሥራ ጄፍ ቤዞስ (የአማዞን ባለቤት) ኮንትራቱን እንዳሸነፈ የተናገረው ባሳለፍነው ማክሰኞ ነበር።
4 290
+2
❗️🇷🇴/🇷🇺 ሰበር ዜና፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሩሲያ ድሮን በኔቶ አባል ሀገር ሮማኒያ ውስጥ፣ በምሥራቃዊዋ ትንሽ ከተማ ጋላቲ ላይ፣ ፈንድቷል።
4 290
🇪🇹⚡️በአማራ፣ በትግራይ ያለው ቀውስ መጪውን የኢትዮጵያ 'ምርጫ' ሸፍኖታል።
'የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከላይ ሲያዩት ጤናማ እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለ የሚያስመስል አሃዝ ከሰሞኑ ለቅቋል: 47 የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 11 ሺ ተመራጭ እጩዎች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች። ነገር ግን ጠጋ ብሎ ለመረመረ፣ ሁሉንም የብላኔ ሆኖ ያገኘዋል። DW
**
ቃል፡ ብላኔ
ፍቺ፡ ጨበራ
4 290
🇪🇹⚡️በኢትዮጵያ የንፁሃኖች ፍጅት እንደቀጠለ ነው። 12 ተሳፋሪዎች ተገድለዋል!
በኦሮሚያ ክልል ከጎሀፅዮን ቱሉ ሚልክ መሀከል - በአንድ የሕዝብ ባስ ሲጓዙ በታጣቂዎች ከታገቱት ተሳፋሪዎች መካከል፣ 12ቱ፣ መኪና ውስጥ እያሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን እንዳጡ ተገልጿል!
የንፁሃን ፍጅት በኢትዮጵያ በአብዛኛው ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት የሚፈጸም ነው።
በዚህ ግድያ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት፣ የመንግሥት ሚሊሺያ መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች በግድያዎቹ ሲሳተፉ እና ለገዳዮቹ ሽፋን ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል። እንዲህ ያሉ ክሶች ከዓይን እማኞች እና ከተጎጂ ቤተሰቦች ሲመጡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዚህም፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም በፍጅቶቹ የመንግሥቱን ሚና የሚያሳይ ነው።
በኢትዮጵያ፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን እና በሚያስደነግጥ ሁኔታ "የግል ሚዲያዎች"ም ጭምር፣ ይህን መሰል የንፁሃን ግድያዎችን ሲዘግቡ አይታዩም፣ ከዘገቡም በዘገባቸው ብሄርን ይመርጣሉ።
እነዚህ የሕዝብ እልቂቶች እየተፈፀሙ ያሉት በሰሜን በሚኖሩ የሀገሩ ሕዝብ ላይ ነው፣ በዋናነት በዐማራ ሕዝብ ላይ፣ በመሆኑም ዜናውን ከመዘገብ ይቆጠባሉ።
እንዲህ ያሉ የንፁሐን እልቂቶች የሕዝብ ብሶትን በማባባስ ለውጥን ቢያፋጥኑ እንጂ አያዳፍኑም!
4 290
— 🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ ዜና፦ ኢራን በቡሸህር ግዛት በጃም አቅራቢያ የአሜሪካን ድሮን ጥላለች -- እንደ ኢራን መገናኛ ብዙሃን Tasnim ዘገባ።
4 290
🇱🇧⚡️🇮🇱 በ$100 ዶላር ድሮን፣ $100 ሚሊዮን ዶላር መሳሪያን ማውደም።
ሂዝቦላ፣ ዛሬ በለቀቀው አዲስ ቪዲዮ፣ በደቡብ ሊባኖስ ቀጠና ውስጥ ሁለት የIron Dome መሳሪያ ሲስተሞችን በFPV ድሮን ሲያጠቃ ታይቷል።
4 290
— 🇮🇷/🇦🇲 አርሜኒያ፣ የኢራን ሥሪት የሆነውን ‘መጂድ’ AD-08 የተባለውን የአየር መቃወሚያ መሳሪያን መግዛቷ ታወቀ።
ትናንት በነበረው የአርሜኒያ ጦር ሠራዊት ትዕይንት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ይህ የአየር መቃወሚያ፣ የአሜሪካንን F-15 የጦር ጀት በኢራን አየር ላይ መትቶ መጣል የቻለ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ የዚህ መሳሪያ ዝና በዓለም አቀፍ ደረጃ ንሯል። በተመሳሳይ ክስተት ፔንታገንን ያስደነገጠ ነበር።
**
4 290
⚡️🇮🇱 “ትራምፕ የዘመነ መሲህነት ሂደቱን ጀምሯል።” – ራባይ ሜንደል ኬሲን
በመሲሃዊው ዘመን፣ ራቢ ኬሲን እንደሚያብራሩት፣ ኤሳቭ (ማለትም፣ ነጭ ክርስቲያኖች) የአይሁድን ዘር ማገልገል [ኤሩቪን 43B] እና በማንኛውም ፍላጎታቸው ላይ መርዳት አለባቸው።
ትራምፕም በተደጋጋሚ፣ የኢራን ጦርነት በተጀመረ ሰሞን፣ 'የመጨረሻው ዘመን ማብሰሪያ ጦርነት (አርማጌዶን)' እያለ ይገልጸው እንደነበር ይታወሳል።
4 290
🇺🇸 ትራምፕ፣ መጪውን የአሜሪካ 250ኛ የልደት በዓልን በተመለከተ፣ በ$250 ዶላር ላይ ፎቶዬ ይለጠፍ ማለቱን ገፍቶበታል። የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ይህን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
4 290
🇺🇸🇮🇷🇴🇲⚡- "የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ፣ ትራምፕ የሆርሙዝ ባሕር ቀረጥ ቁጥጥርን በተመለከተ፣ ኦማን እንደ ጎረቤቶቿ አረቦች አርፋ ለአሜሪካ ካልተገዛችና ካልተቀመጠች፣ ሀገሪቱን 'ለማፍረስ' መዛቱን ተከትሎ ኢራን ከኦማን ጎን በአንድ እንደምትቆም ተናገረ" - አል-ጀዚራ።
4 290
🇸🇩⚡️የሱዳን መንግሥት ጦር በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና በኤሜሬት የሚደገፉ አማፂያን ላይ በብዙ ቦታዎች ድል ቀንቶአቸዋል። በጠቅላይ ሚንስቴሩ የሚደገፉት በዘር ማጥፋት የተከሰሱት አማፂያን፣ ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ናቸው።
የመንግሥት ኃይሎች ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው ኩርሙክ ከተማ እየተቃረበ መሆናቸውን ገለጸዋል‼️
የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በብሉ ናይል ግዛት ሥር ወደ ምትገኘው ኩርሙክ ከተማ እየተቃረበ መሆኑን ሐሙስ ዕለት አስታወቀ። የሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው፤ ጦሩ ወደ ሥፍራው እያመራ ያለው በአካባቢው ያሉና “የአማፂያን የመጨረሻ ምሽጎች” ሲል የገለጻቸውን ቦታዎችን ከተቆጣጠረ በኋላ ነው።
የሱዳን ጦር “ከአጋር ኃይሎች” ጋር በመሆን “በኩርሙክ ዙሪያ የነበሩትን የመጨረሻዎቹን የአማፂያን ምሽጎች ማውደማቸውን እና ከተማዋን ለመቆጣጠር መቃረባቸውን” ገልጿል።
ጦሩ አክሎም፤ ከኩርሙክ በስተደቡብ በሚገኘው አል-ባርካ ጣቢያ ላይ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) የተሰነዘረውን ጥቃት ማክሸፉን አስታውቋል። በጥቃቱ ወቅት በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ላይ “ከፍተኛ የሰው ኃይል ጉዳት” ማድረሱን እንዲሁም በርካታ የጦር ተሽከርካሪዎችንና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መማረኩን ገልጿል።
እንደ ዘገባው ከሆነ፤ የሱዳን ጦር ኃይሎች በከተማዋ ውስጥ ያሉ ተዋጊዎችን ለመክበብ አልመው በዘረጉት ባለ ሁለት አቅጣጫ ስትራቴጂካዊ ጥቃት ከሰሜን እና ከደቡብ አቅጣጫዎች "ወደ ኩርሙክ እየገሰገሱ" ይገኛሉ።
4 290
🇺🇸⚡️🇮🇷🇴🇲 ኦማን ድጋሜ ከአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷታል፡ 'ኦማን፣ አርፈሽ ብትቀመጪ ይሻላል፣ ከኢራን ጋር ባሕሩ ላይ ኬላ ዘርግቼ ቀረጥ እሰበስባለው ብትይ፣ ዋ! ትመቻለሽ' የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር።
