የቀጠናው ተመልካች
Kanalga Telegram’da o‘tish
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 327
Obunachilar
+2824 soatlar
+307 kun
-4230 kun
Postlar arxiv
4 329
🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ ጦር ከአሜሪካ እና ከአውሮፓና 16 C-17A "Globemaster IIIs" የተባሉ ወታደራዊ ጫኝ አይሮፕላኖችን አስነስቷል፣ ተብሏል። በአሁኑ ሰዓት ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየደረሱ ናቸው። ከቀናት በፊት ጀምሮ፣ እንደ አዲስ፣ አሜሪካ ጦሯን ወደ ኢራን በማስጠጋት ላይ ትገኛለች።
4 329
—❗️🇺🇸/🇮🇷 አዲስ: የአሜሪካ ባሕር ኃይል ጦር ‘MT TIFFANY’ የተባለችውን የኢራንን መርከብ በኢንዶፓስፊክ ቀጠና ውስጥ መያዙን አስታውቋል።
ኢራን ይህን የአሜሪካ የባሕር ላይ "የቀን ጠራራን ውንብድና እና ዘረፋ፣ በአንድም በሌላም መንገድ ኃይል ተጠቅሜ አስቆመዋለሁ" ብላለች።
4 329
በእስራኤል የሚደገፈው እና "ሕዝባዊ ኃይሎች" በመባል የሚታወቀው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ፓትሮሎች፣ በጋዛ የራፋ ክፍሎችን እየተዘዋወሩ ሲጠብቁ ታይተዋል። ይህም በIDF ጥበቃ ሥር ከሚገኙ ዞኖች ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘታቸውን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።
"ይህ በእስራኤል የተቋቋመው "ሕዝባዊ ኃይሎች" ከ700-1200 የፍልስጤም ተዋጊዎች ያሉት ሲሆን ሓማስን እና ሌሎች የሓማስ ደጋፊ ታጣቂ ቡድኖችን ለመዋጋት በእስራኤል የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል።
በደቡብም ሆነ በሰሜን ጋዛ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው ተብሏል።
4 329
🇮🇷🇺🇸 የኢራን ጠቅላይ መሪ ሙጅተባ ኻሚኒይ፣ በኢስላማባድ ፓኪስታን ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር፣ 'አረንጓዴ መብራት' ሰጥተዋል። የኢራን ልዑካን ቡድንም ረቡዕ ፓኪስታን ይገባል-- Axios
በዚህ ጉዳይ የ Axios ን ዘገባ ሙሉ በሙሉ ማመን አይገባም። ኢራን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በድርድሩ እንደማትሳተፍ ነው በይፋ የተናገረችው።
4 329
The Wall Street Journal -
🇩🇪 ጀርመን ኢኮኖሚዋን ወደ ጦርነት ጊዜ ኢኮኖሚ ለመቀየር እና Mercedes-Benz, BMW, MAN, እና Volkswagen ፋብሪካዎችን ወደ ጦር መሳሪያ አምራችነት ለማዞር በዝግጅት ላይ ነች።
የጀርመን አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ረጅም ጊዜ የተባለ ውድቀት አጋጥሞታል፣ እንደ ዘገባው። የፋብሪካዎች ማምረቻ መስመሮች ለወታደራዊ ምርት እንደገና እየተዋቀሩ ነው -
▪️ Volkswagen ለእስራኤል አየር መቃወሚያ "Iron Dome" እና ለመሰል ሥሪቶች መለዋወጫዎችን ለማምረት አቅዷል።
▪️ የመኪና መለዋወጫ አምራች Scheffler ለድሮን ሞተሮች፣ ለወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ ለሶፍት ዌር ስርዓቶች እና ለውትድርና አውሮፕላኖች የሚሆኑ መለዋወጫዎችን ማምረት ጀምሯል።
▪️በበርካታ ኩባንያዎች ውስጥ የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች ለማምረት ሦስተኛው ፈረቃ ተጨምሯል። የአሜሪካ አየር መቃወሚያ ሚሳዬሎች (Partriot Interceptors) በቅርቡ በጀርመን ይመረታሉ።
❗️ከጀርመን የጦር መሳሪያ ወደ ውጭ የሚላከው አንድ አራተኛ የሚሆነው ወደዩክሬን ይሄዳል።
✨⭐️ይህ እየሆነ ያለው፣ በጀርመን ውስጥ ብቻ እንዳልሆነ አጽንኦት መስጠት አስፈላጊ ነው። እንደ Rheinmetall ያሉ ድንበር ተሻጋሪ ኮርፖሬሽኖች መላውን አውሮፓ ሸፍነው ይገኛሉ። በየጊዜውም ምርታቸውን እያሳደጉ ነው።
4 329
🇷🇺🇮🇷🇮🇱 የእስራኤል ሚዲያ Yedioot Ahronot፡ "የተቃዋሚ የሩሲያ ድረ-ገጽ እንደዘገበው፣ የሞስኮ ባለስልጣናት ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት "ተሳትፈዋል" በሚል ክስ ወደ 40 የሚጠጉ እስራኤላውያንን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ሪፖርቱ፣ ተጠርጣሪዎቹ በሞስኮ አውሮፕላን ማረፊያ ያለ ምግብና ውሃ ለሰዓታት ተይዘው የነበሩ ሲሆን፣ "በኢራን ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ የማስጠንቀቂያ ሰነዶችን" ከፈረሙና ስልኮቻቸውን ከፍተው ካስፈተሹ በኋላ መለቀቃቸውን ገልጿል።
4 329
🇺🇸⚡️🇮🇷 Shoja-2 የተባለች የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ በዚህ ሰዓት እገዳውን ጥሳ ለማለፍ እየሞከረች ነው። የመጪው ድርድር እጣ ፋንታ፣ ምናልባትም፣ በዚህ ክስተት ሊወሰን የሚችል ይሆናል።
4 329
🇱🇧 "የእስራኤል ወራሪ ጦር፣ በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን ሆን ብሎ በእሳት ማንደዱ፣ የጦር ወንጀል ነው!" የሊባኖስ ጠቅላይ ሚንስቴር።
4 329
🇮🇶 የኢራቅ መንግስት አካላት፡ በኢራቅ እና በሶሪያ ድንበር አካባቢ እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ ሁለት ጊዜ ሪፖርት አድርገው እንዳረጋገጥነው፣ "ISIS 2.0" የሚመስል አዲስ ቡድን እየተቀረጸ መሆኑን እና ይህ ቡድኑ፣ በአሜሪካ አካላት የሚዘወር እና አንዳንድ የእስራኤል ደህንነቶች እንዳሉበት ደርሰንበታል።
ቡድኑ፣ ኢራንን መሬት ላይ በመዋጋት እና በመውረር ላይ የሚሰለጥን ይመስላል።
4 329
የኢራን መንግስት ደጋፊ አክቲቪስቶች ለመንግስታቸው፡
✅ | አሜሪካውያን የኢራን ልዑካንን ኢላማ ለማድረግ አቅደዋል፣ ስለላዎቻቸውን እና የ GPS ወጥመዶቻቸውን ዘርግተው በአይሮፕላኖቻቸው ክትትል እያደረጉ ነው።
ኢራናውያን ጥያቄያቸውን ላለመቀበል ቋፍ ላይ መሆናቸውን ቢያውቁም፣ አሁንም የኢራን ቡድን ወደ ኢስላማባድ እንዲገባ ጫና እያደረጉ እንደሆነ ግልጽ ነው። ልዑካኖቻችን የግድያ ስጋት ላይ ናቸው፣ እና እነሱን ለመግደል ሴራቸው አልቋል። ባለሥልጣናቱ ይህንን ሁኔታ እንዲያውቁ እና በአደገኛ እና በተሰላ ሴራ ውስጥ እንዳይወድቁ እናሳስባለን!
4 329
🇭🇺❌🇮🇱 - አዲሱ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የICC ውሳኔን ከተቃወሙት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በተለየ መልኩ፣ በኔታንያሁ ላይ የቀረበውን የእስር ማዘዣ እንደሚያከብር እና ኔታኒያሁ በሃንጋሪ ከመጣ እንደሚታሰር ተናግሯል።
4 329
🇵🇰🇮🇷🇺🇸⚡️ - "ፓኪስታን፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ውይይት ላይ፣ ባለቀ ሰዓትም ቢሆን እንድትሳተፍ ማድረግ እንደምትችል እርግጠኛ ነች" ሲል ሮይተርስ የፓኪስታን መንግስትን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
"ከኢራን አዎንታዊ ምልክት ደርሶናል። ነገሮች በመስመራቸው እየሄዱ ናቸው፣ ነገ ወይም ከአንድ ቀን በኋላ ውይይቱን ስንጀምር እዚህ እንዲገኙ እየሞከርን ነው" ማለቱን ሮይተርስ ጨምሮ ተናግሯል።
4 329
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 — Wall Street Journal እንደዘገበው፡ ወታደራዊ አማካሪዎች፣ የተከሰከሰውን የአሜሪካ ፖይለት ለማዳን በተወሰደው ነፍስ-አድን ዘመቻ ወቅት፣ ተገማች ያልሆነውን የትራምፕን ቁጣ በመፍራት ሆን ብለው ትራምፕን Situation Room ውስጥ እንዳይገባ አድርገው ነበር።
4 329
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 የኢራን ተደራዳሪ ልዑካን አባል የፓርላማ አባል ማህሙድ ናባቪያን - "በዛቻ፣ በጥቃት እና በተኩስ አቁም ጥሰት ጥላ ሥር፣ ከክፉ የአሜሪካ አገዛዝ ጋር መደራደር ትርጉም የለሽ ብቻ ሳይሆን ጎጂም ነው እናም ጠላት የበለጠ ስግብግብ እንዲሆን ያበረታታል።"
ለነገው የኢስላማባድ ድርድር አሜሪካ ልዑካኗን የላከች ቢሆንም፣ እስካሁን ኢራን ለመደራደር ፈቃደኛ ባለመሆኗ፣ ልዑካኖቿን እስካሁን አላከችም።
