fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 330
مشترکین
+2824 ساعت
+307 روز
-4230 روز
آرشیو پست ها
— 🇺🇸/🇮🇷 : ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ‘እገዳው እጅግ በጣም ተሳክቷል።"

🇺🇸⛔️🇮🇷 — ፕሬዝዳንት ትራምፕ:
ቬኔዝዌላን በ 45 ደቂቃ ነው የወሰድኩት። ኢራን አስቸጋሪ ሕዝብ ነው ያለው፣ ተዋጊ ነው።

🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ ጦር ከአሜሪካ እና ከአውሮፓና 16 C-17A "Globemaster IIIs" የተባሉ ወታደራዊ ጫኝ አይሮፕላኖችን አስነስቷል፣ ተብሏል። በአሁኑ ሰዓት ወደ መካከለኛው ምስራቅ
🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ ጦር ከአሜሪካ እና ከአውሮፓና 16 C-17A "Globemaster IIIs" የተባሉ ወታደራዊ ጫኝ አይሮፕላኖችን አስነስቷል፣ ተብሏል። በአሁኑ ሰዓት ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየደረሱ ናቸው። ከቀናት በፊት ጀምሮ፣ እንደ አዲስ፣ አሜሪካ ጦሯን ወደ ኢራን በማስጠጋት ላይ ትገኛለች።

🇺🇸🏴‍☠️⚔️🇮🇷 የአሜሪካ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም፡ “በማንኛውም ሰዓት በኢራን ላይ ዳግም ዘመቻ ለመክፈት ዝግጁ ነን።"

—❗️🇺🇸/🇮🇷 አዲስ: የአሜሪካ ባሕር ኃይል ጦር ‘MT TIFFANY’ የተባለችውን የኢራንን መርከብ በኢንዶፓስፊክ ቀጠና ውስጥ መያዙን አስታውቋል። ኢራን ይህን የአሜሪካ የባሕር ላይ "የቀን ጠራራን ውንብድና እና ዘረፋ፣ በአንድም በሌላም መንገድ ኃይል ተጠቅሜ አስቆመዋለሁ" ብላለች።

+2
በእስራኤል የሚደገፈው እና "ሕዝባዊ ኃይሎች" በመባል የሚታወቀው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ፓትሮሎች፣ በጋዛ የራፋ ክፍሎችን እየተዘዋወሩ ሲጠብቁ ታይተዋል። ይህም በIDF ጥበቃ ሥር ከሚገኙ ዞኖች ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘታቸውን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል። "ይህ በእስራኤል የተቋቋመው "ሕዝባዊ ኃይሎች" ከ700-1200 የፍልስጤም ተዋጊዎች ያሉት ሲሆን ሓማስን እና ሌሎች የሓማስ ደጋፊ ታጣቂ ቡድኖችን ለመዋጋት በእስራኤል የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል። በደቡብም ሆነ በሰሜን ጋዛ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው ተብሏል።

🇮🇷🇺🇸 ተጨማሪ ሌላ የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ እገዳውን በመጣስ በሆርሙዝ ወሽመጥ አልፏል።

🇮🇷🇺🇸 የኢራን ጠቅላይ መሪ ሙጅተባ ኻሚኒይ፣ በኢስላማባድ ፓኪስታን ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር፣ 'አረንጓዴ መብራት' ሰጥተዋል። የኢራን ልዑካን ቡድንም ረቡዕ ፓኪስታን ይገባል-- Axios
🇮🇷🇺🇸 የኢራን ጠቅላይ መሪ ሙጅተባ ኻሚኒይ፣ በኢስላማባድ ፓኪስታን ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር፣ 'አረንጓዴ መብራት' ሰጥተዋል። የኢራን ልዑካን ቡድንም ረቡዕ ፓኪስታን ይገባል-- Axios በዚህ ጉዳይ የ Axios ን ዘገባ ሙሉ በሙሉ ማመን አይገባም። ኢራን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በድርድሩ እንደማትሳተፍ ነው በይፋ የተናገረችው።

🚨 🇺🇸🇮🇷🇮🇱 የቀድሞ የአሜሪካ ጦር አባላት፣ ከኢራን ጋር የሚደረገውን ጦርነት በመቃወም በ Capitol Hill ተሰልፈዋል።

The Wall Street Journal - 🇩🇪 ጀርመን ኢኮኖሚዋን ወደ ጦርነት ጊዜ ኢኮኖሚ ለመቀየር እና Mercedes-Benz, BMW, MAN, እና Volkswagen ፋብሪካዎችን ወደ ጦር መሳሪያ
The Wall Street Journal - 🇩🇪 ጀርመን ኢኮኖሚዋን ወደ ጦርነት ጊዜ ኢኮኖሚ ለመቀየር እና Mercedes-Benz, BMW, MAN, እና Volkswagen ፋብሪካዎችን ወደ ጦር መሳሪያ አምራችነት ለማዞር በዝግጅት ላይ ነች። የጀርመን አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ረጅም ጊዜ የተባለ ውድቀት አጋጥሞታል፣ እንደ ዘገባው። የፋብሪካዎች ማምረቻ መስመሮች ለወታደራዊ ምርት እንደገና እየተዋቀሩ ነው - ▪️ Volkswagen ለእስራኤል አየር መቃወሚያ "Iron Dome" እና ለመሰል ሥሪቶች መለዋወጫዎችን ለማምረት አቅዷል። ▪️ የመኪና መለዋወጫ አምራች Scheffler ለድሮን ሞተሮች፣ ለወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ ለሶፍት ዌር ስርዓቶች እና ለውትድርና አውሮፕላኖች የሚሆኑ መለዋወጫዎችን ማምረት ጀምሯል። ▪️በበርካታ ኩባንያዎች ውስጥ የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች ለማምረት ሦስተኛው ፈረቃ ተጨምሯል። የአሜሪካ አየር መቃወሚያ ሚሳዬሎች (Partriot Interceptors) በቅርቡ በጀርመን ይመረታሉ። ❗️ከጀርመን የጦር መሳሪያ ወደ ውጭ የሚላከው አንድ አራተኛ የሚሆነው ወደዩክሬን ይሄዳል። ✨⭐️ይህ እየሆነ ያለው፣ በጀርመን ውስጥ ብቻ እንዳልሆነ አጽንኦት መስጠት አስፈላጊ ነው። እንደ Rheinmetall ያሉ ድንበር ተሻጋሪ ኮርፖሬሽኖች መላውን አውሮፓ ሸፍነው ይገኛሉ። በየጊዜውም ምርታቸውን እያሳደጉ ነው።

🇷🇺🇮🇷🇮🇱 የእስራኤል ሚዲያ Yedioot Ahronot፡ "የተቃዋሚ የሩሲያ ድረ-ገጽ እንደዘገበው፣ የሞስኮ ባለስልጣናት ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት "ተሳትፈዋል" በሚል ክስ ወደ 40 የሚጠጉ እስራኤላውያንን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ሪፖርቱ፣ ተጠርጣሪዎቹ በሞስኮ አውሮፕላን ማረፊያ ያለ ምግብና ውሃ ለሰዓታት ተይዘው የነበሩ ሲሆን፣ "በኢራን ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ የማስጠንቀቂያ ሰነዶችን" ከፈረሙና ስልኮቻቸውን ከፍተው ካስፈተሹ በኋላ መለቀቃቸውን ገልጿል።

🇺🇸⚡️🇮🇷 Shoja-2 የተባለች የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ በዚህ ሰዓት እገዳውን ጥሳ ለማለፍ እየሞከረች ነው። የመጪው ድርድር እጣ ፋንታ፣ ምናልባትም፣ በዚህ ክስተት ሊወሰን የሚችል ይሆናል
🇺🇸⚡️🇮🇷 Shoja-2 የተባለች የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ በዚህ ሰዓት እገዳውን ጥሳ ለማለፍ እየሞከረች ነው። የመጪው ድርድር እጣ ፋንታ፣ ምናልባትም፣ በዚህ ክስተት ሊወሰን የሚችል ይሆናል።

🇱🇧 "የእስራኤል ወራሪ ጦር፣ በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን ሆን ብሎ በእሳት ማንደዱ፣ የጦር ወንጀል ነው!" የሊባኖስ ጠቅላይ ሚንስቴር።

🇮🇶 የኢራቅ መንግስት አካላት፡ በኢራቅ እና በሶሪያ ድንበር አካባቢ እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ ሁለት ጊዜ ሪፖርት አድርገው እንዳረጋገጥነው፣ "ISIS 2.0" የሚመስል አዲስ ቡድን እየተቀረጸ መሆኑን እና ይህ ቡድኑ፣ በአሜሪካ አካላት የሚዘወር እና አንዳንድ የእስራኤል ደህንነቶች እንዳሉበት ደርሰንበታል። ቡድኑ፣ ኢራንን መሬት ላይ በመዋጋት እና በመውረር ላይ የሚሰለጥን ይመስላል።

የኢራን መንግስት ደጋፊ አክቲቪስቶች ለመንግስታቸው፡ ✅ | አሜሪካውያን የኢራን ልዑካንን ኢላማ ለማድረግ አቅደዋል፣ ስለላዎቻቸውን እና የ GPS ወጥመዶቻቸውን ዘርግተው በአይሮፕላኖቻቸው ክትትል እያደረጉ ነው። ኢራናውያን ጥያቄያቸውን ላለመቀበል ቋፍ ላይ መሆናቸውን ቢያውቁም፣ አሁንም የኢራን ቡድን ወደ ኢስላማባድ እንዲገባ ጫና እያደረጉ እንደሆነ ግልጽ ነው። ልዑካኖቻችን የግድያ ስጋት ላይ ናቸው፣ እና እነሱን ለመግደል ሴራቸው አልቋል። ባለሥልጣናቱ ይህንን ሁኔታ እንዲያውቁ እና በአደገኛ እና በተሰላ ሴራ ውስጥ እንዳይወድቁ እናሳስባለን!

🇭🇺❌🇮🇱 - አዲሱ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የICC ውሳኔን ከተቃወሙት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በተለየ መልኩ፣ በኔታንያሁ ላይ የቀረበውን የእስር ማዘዣ እንደሚያከብር እና ኔታኒያሁ በሃንጋሪ ከመጣ እንደሚታሰር ተናግሯል።

🇵🇰🇮🇷🇺🇸⚡️ - "ፓኪስታን፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ውይይት ላይ፣ ባለቀ ሰዓትም ቢሆን እንድትሳተፍ ማድረግ እንደምትችል እርግጠኛ ነች" ሲል ሮይተርስ የፓኪስታን መንግስትን ከፍተኛ
🇵🇰🇮🇷🇺🇸⚡️ - "ፓኪስታን፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ውይይት ላይ፣ ባለቀ ሰዓትም ቢሆን እንድትሳተፍ ማድረግ እንደምትችል እርግጠኛ ነች" ሲል ሮይተርስ የፓኪስታን መንግስትን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። "ከኢራን አዎንታዊ ምልክት ደርሶናል። ነገሮች በመስመራቸው እየሄዱ ናቸው፣ ነገ ወይም ከአንድ ቀን በኋላ ውይይቱን ስንጀምር እዚህ እንዲገኙ እየሞከርን ነው" ማለቱን ሮይተርስ ጨምሮ ተናግሯል።

—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 — Wall Street Journal እንደዘገበው፡ ወታደራዊ አማካሪዎች፣ የተከሰከሰውን የአሜሪካ ፖይለት ለማዳን በተወሰደው ነፍስ-አድን ዘመቻ ወቅት፣ ተገማች ያልሆነውን የትራምፕ
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 — Wall Street Journal እንደዘገበው፡ ወታደራዊ አማካሪዎች፣ የተከሰከሰውን የአሜሪካ ፖይለት ለማዳን በተወሰደው ነፍስ-አድን ዘመቻ ወቅት፣ ተገማች ያልሆነውን የትራምፕን ቁጣ በመፍራት ሆን ብለው ትራምፕን Situation Room ውስጥ እንዳይገባ አድርገው ነበር።

—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 የኢራን ተደራዳሪ ልዑካን አባል የፓርላማ አባል ማህሙድ ናባቪያን - "በዛቻ፣ በጥቃት እና በተኩስ አቁም ጥሰት ጥላ ሥር፣ ከክፉ የአሜሪካ አገዛዝ ጋር መደራደር ትርጉም የለሽ ብ
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 የኢራን ተደራዳሪ ልዑካን አባል የፓርላማ አባል ማህሙድ ናባቪያን - "በዛቻ፣ በጥቃት እና በተኩስ አቁም ጥሰት ጥላ ሥር፣ ከክፉ የአሜሪካ አገዛዝ ጋር መደራደር ትርጉም የለሽ ብቻ ሳይሆን ጎጂም ነው እናም ጠላት የበለጠ ስግብግብ እንዲሆን ያበረታታል።" ለነገው የኢስላማባድ ድርድር አሜሪካ ልዑካኗን የላከች ቢሆንም፣ እስካሁን ኢራን ለመደራደር ፈቃደኛ ባለመሆኗ፣ ልዑካኖቿን እስካሁን አላከችም።

+1
🇷🇺 ዩክሬን በሩሲያ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ ባደረሰችው ጥቃት፣ ነዳጅ ይዘንብ እንደነበር ነዋሪዎች ገልፀዋል።