uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም 2ተኛ ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
1 841
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+227 kun
+12330 kun
Postlar arxiv
በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጻጊያና ትግበራ ባለሙያ አቶ ግርማ ደቻሳ የድጋፍና ክትትሉን ግብረ መልስ ሪፖርት አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል። Bara Barnootaa 2019tti Sirni Barnoota Afaan Oromoo Sadarkaa Barbaadamuun Hojii Irra Ooluuf, Hoggantoonni Manneen Barnootaa Gahee Isaanii Sirnaan Bahachuu Qabu jedhame. (Fulbaana 30, 2019 A.L.I.) Daayirektoreetii Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo, Biiroo Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee, manneen barnootaa mootummaa sadarkaa duraa fi giddu galeessaa bulchiinsa magaalichaa keessatti hojiilee deeggarsaa fi hordoffii bara barnootaa kanaa kurmaana jalqabaa irratti gaggeeffaman ilaalchisee, hoggantoota garee hojiirra oolmaa sirna barnoota Afaan Oromoo sadarkaa bulchiinsa kutaa magaalaa, ogeessota, suupervaayizaroota aanaalee fi itti gaafatamtoota manneen barnootaa sadarkaa duraa hirmaachisuun marii gaggeesse. Daayirektarri Daayirektoreetii Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo, Biiroo Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee, Doktar Balaachoo Bayyanaa, ergaa baniinsaa marii kanaa irratti dabarsaniin, daayirektoreetichi kurmaana jalqabaa keessatti manneen barnootaa mootummaa sadarkaa tokkoffaafi giddu galeessaa hunda keessatti bara barnootaa 2019 A.L.I. barattoota simachuu irraa eegalee hanga raabsaa kitaaba barattootaa,barruuleefi uffata seeraa barattootaafi manneen barnootaa naannoo baruu fi barsiisuu barattootaaf mijataa ta’e uumamuu isaa mirkaneessuutti hojiiwwan deeggarsaa fi hordoffii gaggeessuu ibsaniiru. Daayirektarri kun itti dabaluunis, mariin har’aa kun ciminaalee hojii deeggarsaa fi hordoffii manneen barnootaa keessatti gaggeeffameen adda ba’an caalaatti cimsanii itti fufuuf, akkasumas hanqinoota adeemsa hojii keessatti mul’atan sirreessuun gara fuulduraatti hojii fooyya’aa hojjechuuf kan gargaaru ta’uu ibsaniiru. Kana malees, sirni barnoota Afaan Oromoo sadarkaa barbaadamuun hojii irra oolee barattoonni bu’aa gaarii akka galmeessan taasisuuf, hoggantoonni manneen barnootaa xiyyeeffannoo addaa kennanii hojjechuu akka qaban hubachiisaniiru. Sagantaa kana irratti, ogeessi Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo kan Daayirektoreetii Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo, Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee, Obbo Girmaa Dachaasaa, gabaasa duub-deebii deeggarsaa fi hordoffii dhiyeessaniiru. Itti aansuunis, hirmaattonni gabaasa dhiyaate irratti mariin bal’aan gaggeeffameera. ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

በ2019 የትምህርት ዘመን የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን ርዕሳነ መምህራን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ተጠቆመ። (መስከረም 30/2019 ዓ.ም)
+9
በ2019 የትምህርት ዘመን የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን ርዕሳነ መምህራን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ተጠቆመ። (መስከረም 30/2019 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባካሄደው የ1ኛ ሩብ አመት የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ የክፍለ ከተማ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የወረዳ ሱፔርቫይዘሮች እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን በተገኙበት ውይይት አካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር በላቸው በየነ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስራ ክፍሉ በ1ኛ ሩብ አመት በሁሉም የመንግስት የቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ አቅርቦት፣የተማሪ ደብተርና ድምብ ልብስ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ አከባቢ እየፈጠሩ እንደሆኑ ለማረጋገጥ የሚያስችል የድጋፍና ክትትል ስራ መስራቱን አስታውቀዋል። ዳይሬክተሩ አያይዘውም የዛሬው ውይይት በትምህርት ተቋማቱ በተካሄደው የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ የቀረቡትን ጥንካሬዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም በአሰራር ሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ ሆኖ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ርዕሳነ መምህራን ትኩረት አድርገው መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

የተከታታይ ምዘና እና የፈተና እቅድ አዘገጃጀት ጽንሰ ሀሳብን በአግባቡ በመገንዘብ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 30/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት
+7
የተከታታይ ምዘና እና የፈተና እቅድ አዘገጃጀት ጽንሰ ሀሳብን በአግባቡ በመገንዘብ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 30/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ጋር በመተባበር ከክፍለከተማ የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎች ፤ ከፈተና ባለሙያዎች እና አስተባባሪዎች እንዲሁም ከአዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ጋር በተከታታይ ምዘና ጽንሰ ሀሳብ እና በፈተና እቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን ገልጻል ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ በከተማ አስተዳደሩ ስታንዳርዱን የጠበቀ ፈተና እና ጥራቱ የተረጋገጠ የፈተና እቅድ ለማዘጋጀት ታስቦ ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በትኩረት በመስራት ጋር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም ተሳታፊዎች በየትምህርት ቤቱ በመገኘት ሙያዊ የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን በመግለጽ ከባለድርሻ አካላት ጋርም በትኩረት መስራት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የማስተካከያ ሀሳቦችን በማካተት ጥራቱ የተረጋገጠ የትምህርት በሬዲዮ ለትምህርት ተቋማት ተደራሽ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል። Biiroon Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee bara barnootaa 2019tti barnoota qulqullina qabu raadiyoodhaan barattoota biraan ga'uuf xiyyeeffannoon hojjechaa jiraachuun ibsame. (Fulbaana 30, bara 2019 A.L.I.) Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinneetti daayirekotreetiin Tamsaasafi Misooma Qabiyyee Miidiyaa sirna barnootaa haaraa irratti hundaa'uun, gosa barnootaa barnootni raadiyoo Kanaan dura hin qopheefnef, iskiriiptii barnoota raadiyoo qophaa'ee waraabbiin isaa xumurame gamaggamaa jiraachuu beeksise. Daayirektara Daayirektoreetii Tamsaasafi Misooma Qabiyyee Miidiyaa Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee kan ta’an Aadde Yewubdaar Ayyaalew, yaada kennaniin gamaggamni kun barsiisota duraan akkaataa sirna barnootaa haaraa irratti hundaa'uun barnoota raadiyootiif iskiriiptii qopheessaniin gaggeeffamaa jiraachuu ibsaniiru. Gamaaggamni kun barsiisota iskiriiptii qopheessaniin gaggeeffamuun isaa, sagaleen barnootaaf waraabame iskiriiptii qophaa'e waliin sirriitti kan walsimu ta'uu mirkaneessuuf akka gargaarus eeraniiru. Aadde Yewubdaar itti dabaluunis, barnootni raadiyoo gamaggamamaa jiru kun barattoota Afaan Amaaraafi Afaan Oromoon barataniif Afaan Oromoofi Afaan Amaaraa akka afaan lammaffaatti, barnoota Safuufi Sirna Gadaa, barnoota Safuu, Afaan Ingiliffaa akkasumas barnoota bu'uuraa ga'eessotaa Afaan Amaaraa fi Afaan Oromootiin qophaa'e irratti kan xiyyeeffate ta'uu ibsaniiru. Barnoota Afaan Ingilizii kanaan dura sadarkaa federaalaatti qophaa'aa ture, Biiroon Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee itti gaafatamummaan fudhatee qopheessuun isaa, qophii barnoota raadiyoo bara kanaa adda kan taasisu ta'uusaa aadde Yewubdaar ibsaniiru. Akkasumas, Gamaaggamni gaggeeffamaa jiru hojii bulchiinsi magaalichaa barnoota qulqullina qabu raadiyoodhaan barattoota biraan ga'uuf hojjechaa jiru bu'a qabeessa akka ta'uuf kan gargaaru ta’uu hubachiisaniiru. Dhumarrattis, yaadota sirreeffamaa gamaggama kana irratti kennaman sirreessuun barnoota raadiyoo qulqullinni isaa mirkanaa'e dhaabilee barnootaaf kan dhaqqabsiifamu ta’uu ibsaniiru. ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት አመት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በሬዲዮ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። (መስከረም 30/2019 ዓ.ም)
+8
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት አመት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በሬዲዮ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። (መስከረም 30/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በአዲሱ ስርአተ ትምህርት መሰረት የትምህርት በሬዲዮ ላልተዘጋጀላቸው የትምህርት አይነቶች የተቀረጸ የትምህርት በሬዲዮ በማስገምገም ላይ መሆኑን አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘ ት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የውብዳር አያሌው ግምገማው ቀደም ሲል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት መሰረት የትምህርት በሬዲዮ ባልተዘጋጀላቸው የትምህርት አይነቶች ስክሪፕት ባዘጋጁ መምህራን አማካይነት በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸው ግምገማው ስክሪፕቱን ባዘጋጁ መምህራን መካሄዱ የተቀረጸው ድምጽ በተዘጋጀው ስክሪፕት መሰረት ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል አመላክተዋል ። ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም ግምገማው አማርኛን እና አፋን ኦሮሞን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የትምህርት አይነት ጨምሮ በግብረ ገብ ፣ሰፉ፣ እንግሊዘኛ እና በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የተዘጋጀውን የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት መሰረት አድርጎ በተዘጋጀው ስክሪፕት መሰረት በመካሄድ ላይ መሆኑን አስረድተዋል። ቀደም ሲል በፌደራል ደረጃ ሲዘጋጅ የነበረውን የእንግሊዘኛ ትምህርት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊነት ወስዶ ማዘጋጀቱ የዘንድሮው የትምህርት በሬዲዮ ዝግጅት ለየት እንደሚያደርገው ዳይሬክተሯ ገልጸው ግምገማው በከተማ አስተዳደሩ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በሬዲዮ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ የሚገኘውን ተግባር ውጤታማ እንደሚያደርገው በመጠቆም በቀጣይ በግምገማው የሚሰጡ የማስተካከ

📢 ማስታወቂያ! በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊ ምደባ ሂደቱ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ ተጠናቆ ምላሽ የተሰጠ በመሆኑ፣ በጊዜያዊነት የ
📢 ማስታወቂያ! በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊ ምደባ ሂደቱ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ ተጠናቆ ምላሽ የተሰጠ በመሆኑ፣ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሃ-ግብር መሠረት በጊዜያዊነት ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሄድ ትምህርታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ። እንዲሁም የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ከመሄዳቹህ በፊት በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባት https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ እንድታረጋግጡ ይሁን አዲስ ተማሪዎች፡ የምደባ ቦታችሁን https://student.ethernet.edu.et/view-placement/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ፦ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ስለሆነ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን መቀጠል የምትፈልጉ ተማሪዎች(በጊዜያዊነት የተመደባችሁትን ጨምሮ) ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያወጡትን የጥሪ ማስታወቂያ በመከታተል ትምህርታችሁን በነበራቹሁበት መቀጠል እንደምትችሉ እናሳውቃለን። ትምህርት ሚኒስቴር

ማስታወቂያ! በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ፤ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባቋቋማቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ1
ማስታወቂያ! በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ፤ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባቋቋማቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሂደቱን እያከናወነ ይገኛል። ሚኒስቴሩ በትምህርት ቤቶቹ የሚገኙ ተጨማሪ ክፍት ቦታዎችን በመጠቀም ተጨማሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ዕድል አመቻችቷል። በመሆኑም በትምህርት ቤቶቹ ባሉ ክፍት ቦታዎች ተመድባችሁ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው የምዝገባ ሊንክ በመግባት እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply የትምህርት ሚኒስቴር

ቢሮው በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የድጋፍና ክትትል ተግባር ማከናወኑ ተገለጸ። (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) ድጋፍና
+9
ቢሮው በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የድጋፍና ክትትል ተግባር ማከናወኑ ተገለጸ። (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና እና የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬቶች የ2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ ባዘጋጁት ቼክ ሊስት መሰረት የተካሄደ ሲሆን ስራ ክፍሎቹ ቀደም ብለው ድጋፍ ክትትል ለሚያካሂዱ የቢሮ ባለሙያዎች የድጋፍና ክትትል አካሄዱን በተመለከተ ገለፃ አካሂደዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የመማክርት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ከመማክርት ጉባኤው ስራ አስፈጻሚ አባላትና ከቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ ጋር በመሆን በተወሰኑ ተቋማት ተገኝተው የድጋፍና ክትትል ሂደቱን ተመልክተዋል። ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት ተቋማቱ በአንደኛ ሩብ አመት በእቅድ ዝግጅት ጀምሮ አፈጻጸማቸው ያለበትን ደረጃ በመለየት የተሻለና ተቀራራቢ አፈፃፀም አስመዝግበው የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ማሻሻል እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የመማክርት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ጠቁመው ቢሮው በቀጣይ ከድጋፍና ክትትሉ ባሻገር በተቋማቱ በመገኘት ምዘና የሚያካሂድ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የቢሮው ሰራተኞች የስነ ምግባራዊ ተግባቦት ጽንሰ ሀሳብን በአግባቡ ተገንዝበው ተቋሙን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት
+9
የቢሮው ሰራተኞች የስነ ምግባራዊ ተግባቦት ጽንሰ ሀሳብን በአግባቡ ተገንዝበው ተቋሙን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ከከተማ አስተዳደሩ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ስነ ምግባራዊ ተግባቦት ለውጤታማ የትምህርት አመራርና ተቋማዊ ስኬት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስልጠና ለቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞቸ ሰጠ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በርካታ ሰራተኞችን እና ከፍተኛ በጀት የሚያስተዳደር ተቋም እንደመሆኑ የቢሮው ሰራተኞች የስነ ምግባራዊ ተግባቦት ጽንሰ ሀሳብን በአግባቡ ተገንዝበው ተቋሙን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬት አቶ አስራት ሽፈራው በበኩላቸው ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው ስነ ምግባራዊ ተግባቦት ለውጤታማ የትምህርት አመራርና ተቋማዊ ስኬት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስልጠና የዚሁ አካል መሆኑን በመግለጽ የቢሮው ሰራተኞች በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መአዛ መንግስቱ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ ለሀገራችን ሁለተናዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ታስቦ ስራ እንደመጀመሩ የክፍለከተማው አስተዳደር ተቋሙ የቋቋመበት አላማ ግቡን እንዲመታ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የምስራቅ ጎህ የሳይንስ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት እንዲችል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ
+9
የምስራቅ ጎህ የሳይንስ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት እንዲችል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መአዛ መንግስቱ ጋር በመሆን በመሀል ካሳንችስ በሚገኘውና ዘንድሮ የልህቀት ማዕከል ሆኖ በአዲስ መልክ ስራ በጀመረው ምስራቅ ጎህ የሳይንስ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የመማር ማስተማር ስራውን በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ትምህርት ቤቱ በ2019 ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡና በሳይንስ ትምህርት ተሰጥኦ ያላቸዉን ተማሪዎች በመቀበል ዘንድሮ የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩን ጠቁመው ብቃታቸው የተረጋገጠ የትምህርት አመራሮችና መምህራን ተመድበው በስራ ላይ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡ ኃላፊው አያይዘውም በተቋሙ ስታንዳርዱን የጠበቀ የትምህርት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ግብዓት የማሙዋላትን ጨምሮ ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን ገልጸው የትምህርት ቤቱ በዚህ ልክ ስታንዳርዱን ጠብቆ የመማር ማስተማር ስራ እንዲጀምር መደረጉ ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠዉን ልዩ ትኩረት ከማሳየቱ ባሻገር ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበ
+9
በከተማ አስተዳደሩ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በከተማ አስተዳደሩ በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ አድርገው ትራንስፎርም ካደረጉ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው የልቤ ፋና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የመማር መስተማር ስራዉን ተምልክተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የመንግስትና የግል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶችን ሞዴል ለማድረግ በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት አብዛኛዎቹ በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ ትራንስፎርም ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ ለምክትል ከንቲባው ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ጠቁመው ተቋማቱ በጫወታ የማስተማር ስነዘዴን እንዲተገበሩ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ግብአት እንዲማላላቸው ከመደረጉ ባሻገር መምህራንን ጨምሮ ለተለያዩ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው በጉብኝታቸው የተማሪዎችን የመማሪያና ማሸለቢያ ክፍሎችን ጨምሮ መመገቢያ አዳራሹን እና ምድረግቢውን ተዘዋውረው በመመልከት ህጻናቱን አበረታተዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት፣ ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ። ይህ በዓል በመላው ሀገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች እንደሚከበር የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ይከበራል፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥ
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ይከበራል፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በተገኙበት ይከበራል፡፡ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” ቀኑ የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ ይከበራል። ይህ በዓል ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበር እና ክብሯን ለማስጠበቅ ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩት ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የሚከበርበት ቀን ነው። ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ በዋናነት የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫና አርማ መሆኑን ምክር ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል። ቀኑ ለሠንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበትና በሀገራዊ አንድነትና ህብረ ብሔራዊነት መግባባትን የሚፈጥሩበት ሁነት ነው። ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ከጀመረ 18 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነትና አስተባባሪነት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡ በዚህም መሠረት የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ዕለቱን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን መልዕክት በማስተላለፍ በንግግር ከከፈቱ በኋላ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት በመላው ሀገሪቱ ዜጎች በሠንደቅ ዓላማው ፊት ቃለ መሃላ የሚፈጸምበት ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ እና ክብር ዘብ ታጅበው በፕሬዘዳንቱ አማካኝነት ሠንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ይከናወናል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 4 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለ2019 የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ። (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደረ ለ2019 የትምህርት
+9
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 4 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለ2019 የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ። (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደረ ለ2019 የትምህርት ዘመን ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ ግንባታቸው ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ ከሆኑ ተቋማት መካከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የሚገኙት 4 ትምህርት ቤቶች አቤቤ ቱፋ ቅድመ አንደኛ ፣ አቤቤ ቱፋ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ፣ አቤቤ ቱፋ ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ ደረጃ እና አረዳ ኦዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጠቃሽ ናቸው። በትምህርት ቤቶቹ የመማሪያ ክፍሎችን ፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መጽሐፍትን እንዲሁም የአይ ሲቲ ክፍልን ያካተቱ ባለ አራት ወለል ህንጻዎችን ጨምሮ ለአስተዳደር ስራዎችን የሚያገለግሉ ባለ ሁለት ወለል ሁለገብ ህንጻ እንዲሁም የመመገቢያ አዳራሽና ደረጃቸውን የጠበቁ የመጸዳጃ ቤቶችን አካቶ በከፍተኛ በጀት ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪ ኢንጅነር ሙሉነህ ተክለብርሀን አስታውቀዋል ። በድን መሪው አያይዘውን በትምህርት ቤቶቹ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ባለ ሁለት ወለል ህንጻና የመመገቢያ አዳራሽ ግንባታ ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራ ዝግጁ መደረጉን ጠቁመው ከህንጻዎቹ ባሻገር የአጥር እና ምድረ ግቢን የማስዋብ ስራ መከናወኑን አመላክተዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ በበኩለቸው ማኑዋሎቹ በሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወጥ የሆነ የመማሪያ ጥጎች ተግባራዊ ለማድረግ እና የህጻናቱን ሁለንተናዊ እድገት በአግባቡ ለመመዘን የሚያስችል የመመዘኛ መስፈርት ለማዘጋጀት የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቁመው ስራ ክፍሉ ሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች ማኑዋሎቹን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የህጻናት እድገትና የትምህርት ምዘና መመሪያ እንዲሁም የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት ማኑዋልን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ (መስከረም 29
+6
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የህጻናት እድገትና የትምህርት ምዘና መመሪያ እንዲሁም የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት ማኑዋልን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ባዘጋጀው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የህጻናት እድገትና የትምህርት ምዘና መመሪያ እንዲሁም የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀትና አጠቃቀም ማኑዋልን መሰረት በማድረግ ለክፍለከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች፤አስተባባሪዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዳል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አበራ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የህጻናት ሁለንተናዊ እድገት መሰረት የሚጣልበት የትምህርት ደረጃ ከመሆኑ በሻገር ተማሪዎቹ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዝግጁ የሚሆኑበት መሆኑን አስታውሰው በሁለቱ ማኑዋሎች ላይ በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ በሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊውን የክትትልና ድጋፍ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ 2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ግምገማ አካሄዱ:: (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ
+2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ 2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ግምገማ አካሄዱ:: (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል:: በውይይቱ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጌታሁን ለማ አማካኝነት በሩብ አመቱ የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም ሥራዎቹ ሲከናወኑ የነበሩ ጥንካሬዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች በሪፖርቱ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ ቀደም ሲል በየሥራ ክፍሉና በየዘርፉ ግምገማ የተካሄደበት መሆኑን ገልፀው ሪፖርቱ የዝግጅት ምዕራፍ ስራው በተቀመጠው እቅድ መሰረት በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል:: አክለውም በጋራ ውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ተካተው በቀጣይ ለፕሮሰስ ካውንስል እና ጠቅላላ ሰራተኛ ውይይት እንደሚቀርብ መሆኑን ተናግረዋል:: ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc