አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
Відкрити в Telegram
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም 2ተኛ ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
1 845
Підписники
Немає даних24 години
+337 днів
+13130 днів
Архів дописів
1 845
+7
ቢሮው በ2019 የትምህርት አመት 25 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደረጃ 4 እንዲገቡ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑ ተገለጸ።
(ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማዊ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት እና አጠቃቀም ማኑዋል እንዲሁም ተቋማቱን ሞዴል ለማድረግ መከናወን በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ ለተመረጡ የቅድመ አንደኛ ደረጃ አስተባባሪዎችና መምህራን መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ጥላዬ ዘውዴ ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስትና የግል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶችን ሞዴል ለማድረግ ባከናወናቸው የተለያዩ ተግባራት አብዛኛዎቹ ተቋማት በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ ትራንስፎርም ማድረጋቸውን ጠቁመው ሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሞዴል ሆነው የተማሪዎቻቸውን ሁለንተናዊ እድገት እንዲያስቀጥሉ ከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ በጀት ያቀረባቸውን ግብአቶች ለታለመለት አላማ ማዋል እንዲችሉ ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማዊ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ስራ ክፍሉ
1 845
+9
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ልምዱን አካፈለ፡፡
(ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ለመጡ ልዕካን ቡድኖች በትምህርት ዘርፉ እያከናወናቸዉ በሚገኙ ስራዎች ላይ ልምድን አካፍላል፡፡
በልምድ ልውውጡ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፣ የቢሮ ዳይሬክተሮችና ከሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመጡ ልዕካን ቡድኖች ተሳተፉ ሲሆኑ በዋናነት ቢሮ ከስርዓተ ትምህርት ዝግጀትና ትግበራ ፣ ከትምህርት ቴክኖሎጂ መሰረት ልማትና ትምህርት ረገድ ፣ ከትምህርት ቤት መሻሻልና ግንባታ ስራዎች አካያ እንዲሁም ከለውጥ ስራዎች ትግባራ አንጻር የተከናወኑ ስኬታማ ስራዎች ለልዑካን ቡድኖች እንዲቀርብ ተደርጋል፡፡
በልምድ ልውውጡ የተካፈሉ ልዑካን ቡድኖች ለተደረገላቸው አቀባበልና ላገኙት ተምክሮ ምሰጋና አቅርበው ቢሮ በትምህርት ዘርፍ ስራዉ ላይ እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች አመርቂና ውጤታማ መሆናቸዉን ብሎም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገሩና ትልቅ አሻራን እያሳረፉ የሚገኙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
1 845
በአንድነትና በልማት ዛሬም እንደትናንቱ ከፍ ልናደርገው ይገባል ብለዋል።
ብሔራዊው የሰንደቅ አላማ ቀን በየአመቱ የጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪያው ቀን በተለያዩ መርሀግ ብሮች እንደሚከበር ይታወቃል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
1 845
+9
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነታችን" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከበረ፡፡
(ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሰራተኞች በጋራ ባከበሩት 19ኛው ሰንደቅ ዓላማ ቀን የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር እና ሰንደቅ ዓላማን በክብር በመሰቀል ተከብሩዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በመርሀግብሩ ባስተላለፉት መልእክት የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የህዝቦቿን አንድነት የሚገልጽ የኩራታችን ምንጭ መሆኑን ገልጸው ቀኑ ሲከበር ሁሉም ሰራተኛ በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ሀገሪቱ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
በተጨማሪም የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓዋጅ ቁጥር 863/2008 በህግ ተደንግጎ የሚከበር በዓል መሆኑንም ገልጸዋል። አክለውም ሰንደቅ ዓላማችን የሀገር ዳር ደንበር ያስከበሩ አባት እናቶቻችን በክብር ያስረከቡን የሁላችንም የወል ምልክት መሆኑንም አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ኤልያስ ከበደ በበኩላቸው የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ጥልቅ የብሔራዊ ስሜት የሚቀሰቀስበትና የጋራ ቃልኪዳን የሚታደስበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ሰንደቅ ዓላማችን የጽናታችን የነጻነታችን የሉዓላዊነታችን የተስፋችን ምልክት ነው። የአባት እናቶቻችን የአጥንታና የደም የታተመበት ልዩ የኩራት ዐይከናችንን በቃል ብቻ ሳንወሰን
1 845
ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን! 🇪🇹
እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሰን!
የ2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ማንነታችን፣ የሉዓላዊነታችን አርማና የአንድነታችን ምልክት ነው። ልዩነቶቻችንን በውይይት እንፍታ፤ አንድነታችንን በመግባባት እናጠናክር፤ ሀገራችንንም በጋራ ጥረት እንገንባ!
ዛሬ ሰንደቃችንን ከፍ ስናደርግ፣ ነገ የኢትዮጵያን ክብር፣ ሰላምና ብልጽግና ከፍ ለማድረግ ቃል እንግባ!
ኢትዮጵያ በዜጎቿ አንድነት ትጠናከራለች፤ በጋራ ቁርጠኝነታችንም ለትውልድ ትጸናለች!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1 845
+1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን
“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን”
ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው። ሠንደቅ ዓላማችንም የጋራ ታሪካችንን፣ ሉዓላዊነታችንና በልዩነቶቻችን መካከል በጋራ የመቆም አቅማችንን የሚያስታውስ የብሔራዊ አንድነታችን ምልክት ነው።
በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆማቸው፣ በታላቅ ገድላቸው የዓለምን ትኩረት መሳብ ችለዋል።
አባቶቻችን በፈተናዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ይህ በጋራ የመቆም ጥሪ መቼም ቢሆን ተቋርጦ አያውቅም፤ እያንዳንዱም ትውልድ ለዚህ ጥሪ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል።
መደመር ሁላችንንም አንድ ቀላል ጥያቄ ይጠይቀናል፤ እኛ የሀገራችንን እጣ ፈንታ ከዳር ቆመን የምንታዘብ ተመልካቾች ነን? ወይንስ “ይህች ሀገሬ ናት፤ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም ያሳስበኛል” ማለት የምንችል ባለቤቶች?
ቋንቋዎቻችን፣ ሃይማኖቶቻችን እና ማንነቶቻችን ለዘመናት በጋራ በምናልፍበት ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ አብረው ተሰናስለው የተሸመኑ የአንድ ሸማ ክሮች ናቸው።
ለሀገር መቆም ከትንንሽ የድፍረት እርምጃዎች ይጀምራል፤ ከራስ አልፎ ሰፊ ርዕይ ይዞ መሥራትንም ይጠይቃል። ያለፉት ትውልዶች ሀገሪቱን እንድንረከብ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ዛሬ በጋራ የምናጸናትን ሀገር ነው ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው።
ስለሆነም ዛሬ ራስዎን ይጠይቁ፤ ለሀገርዎ አንድነትና ብልጽግና ምን አበረክታለሁ?
1 845
በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጻጊያና ትግበራ ባለሙያ አቶ ግርማ ደቻሳ የድጋፍና ክትትሉን ግብረ መልስ ሪፖርት አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።
Bara Barnootaa 2019tti Sirni Barnoota Afaan Oromoo Sadarkaa Barbaadamuun Hojii Irra Ooluuf, Hoggantoonni Manneen Barnootaa Gahee Isaanii Sirnaan Bahachuu Qabu jedhame.
(Fulbaana 30, 2019 A.L.I.) Daayirektoreetii Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo, Biiroo Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee, manneen barnootaa mootummaa sadarkaa duraa fi giddu galeessaa bulchiinsa magaalichaa keessatti hojiilee deeggarsaa fi hordoffii bara barnootaa kanaa kurmaana jalqabaa irratti gaggeeffaman ilaalchisee, hoggantoota garee hojiirra oolmaa sirna barnoota Afaan Oromoo sadarkaa bulchiinsa kutaa magaalaa, ogeessota, suupervaayizaroota aanaalee fi itti gaafatamtoota manneen barnootaa sadarkaa duraa hirmaachisuun marii gaggeesse.
Daayirektarri Daayirektoreetii Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo, Biiroo Barnoota Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee, Doktar Balaachoo Bayyanaa, ergaa baniinsaa marii kanaa irratti dabarsaniin, daayirektoreetichi kurmaana jalqabaa keessatti manneen barnootaa mootummaa sadarkaa tokkoffaafi giddu galeessaa hunda keessatti bara barnootaa 2019 A.L.I. barattoota simachuu irraa eegalee hanga raabsaa kitaaba barattootaa,barruuleefi uffata seeraa barattootaafi manneen barnootaa naannoo baruu fi barsiisuu barattootaaf mijataa ta’e uumamuu isaa mirkaneessuutti hojiiwwan deeggarsaa fi hordoffii gaggeessuu ibsaniiru.
Daayirektarri kun itti dabaluunis, mariin har’aa kun ciminaalee hojii deeggarsaa fi hordoffii manneen barnootaa keessatti gaggeeffameen adda ba’an caalaatti cimsanii itti fufuuf, akkasumas hanqinoota adeemsa hojii keessatti mul’atan sirreessuun gara fuulduraatti hojii fooyya’aa hojjechuuf kan gargaaru ta’uu ibsaniiru. Kana malees, sirni barnoota Afaan Oromoo sadarkaa barbaadamuun hojii irra oolee barattoonni bu’aa gaarii akka galmeessan taasisuuf, hoggantoonni manneen barnootaa xiyyeeffannoo addaa kennanii hojjechuu akka qaban hubachiisaniiru.
Sagantaa kana irratti, ogeessi Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo kan Daayirektoreetii Qophiifi Raawwii Sirna Barnoota Afaan Oromoo, Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee, Obbo Girmaa Dachaasaa, gabaasa duub-deebii deeggarsaa fi hordoffii dhiyeessaniiru. Itti aansuunis, hirmaattonni gabaasa dhiyaate irratti mariin bal’aan gaggeeffameera.
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
1 845
+9
በ2019 የትምህርት ዘመን የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን ርዕሳነ መምህራን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ተጠቆመ።
(መስከረም 30/2019 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባካሄደው የ1ኛ ሩብ አመት የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ የክፍለ ከተማ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የወረዳ ሱፔርቫይዘሮች እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን በተገኙበት ውይይት አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር በላቸው በየነ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስራ ክፍሉ በ1ኛ ሩብ አመት በሁሉም የመንግስት የቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ አቅርቦት፣የተማሪ ደብተርና ድምብ ልብስ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ አከባቢ እየፈጠሩ እንደሆኑ ለማረጋገጥ የሚያስችል የድጋፍና ክትትል ስራ መስራቱን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም የዛሬው ውይይት በትምህርት ተቋማቱ በተካሄደው የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ የቀረቡትን ጥንካሬዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም በአሰራር ሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ ሆኖ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ርዕሳነ መምህራን ትኩረት አድርገው መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።
1 845
+7
የተከታታይ ምዘና እና የፈተና እቅድ አዘገጃጀት ጽንሰ ሀሳብን በአግባቡ በመገንዘብ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
(መስከረም 30/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ጋር በመተባበር ከክፍለከተማ የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎች ፤ ከፈተና ባለሙያዎች እና አስተባባሪዎች እንዲሁም ከአዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ጋር በተከታታይ ምዘና ጽንሰ ሀሳብ እና በፈተና እቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን ገልጻል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ በከተማ አስተዳደሩ ስታንዳርዱን የጠበቀ ፈተና እና ጥራቱ የተረጋገጠ የፈተና እቅድ ለማዘጋጀት ታስቦ ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በትኩረት በመስራት ጋር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ተሳታፊዎች በየትምህርት ቤቱ በመገኘት ሙያዊ የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን በመግለጽ ከባለድርሻ አካላት ጋርም በትኩረት መስራት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
1 845
የማስተካከያ ሀሳቦችን በማካተት ጥራቱ የተረጋገጠ የትምህርት በሬዲዮ ለትምህርት ተቋማት ተደራሽ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል።
Biiroon Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee bara barnootaa 2019tti barnoota qulqullina qabu raadiyoodhaan barattoota biraan ga'uuf xiyyeeffannoon hojjechaa jiraachuun ibsame.
(Fulbaana 30, bara 2019 A.L.I.) Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinneetti daayirekotreetiin Tamsaasafi Misooma Qabiyyee Miidiyaa sirna barnootaa haaraa irratti hundaa'uun, gosa barnootaa barnootni raadiyoo Kanaan dura hin qopheefnef, iskiriiptii barnoota raadiyoo qophaa'ee waraabbiin isaa xumurame gamaggamaa jiraachuu beeksise.
Daayirektara Daayirektoreetii Tamsaasafi Misooma Qabiyyee Miidiyaa Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee kan ta’an Aadde Yewubdaar Ayyaalew, yaada kennaniin gamaggamni kun barsiisota duraan akkaataa sirna barnootaa haaraa irratti hundaa'uun barnoota raadiyootiif iskiriiptii qopheessaniin gaggeeffamaa jiraachuu ibsaniiru. Gamaaggamni kun barsiisota iskiriiptii qopheessaniin gaggeeffamuun isaa, sagaleen barnootaaf waraabame iskiriiptii qophaa'e waliin sirriitti kan walsimu ta'uu mirkaneessuuf akka gargaarus eeraniiru.
Aadde Yewubdaar itti dabaluunis, barnootni raadiyoo gamaggamamaa jiru kun barattoota Afaan Amaaraafi Afaan Oromoon barataniif Afaan Oromoofi Afaan Amaaraa akka afaan lammaffaatti, barnoota Safuufi Sirna Gadaa, barnoota Safuu, Afaan Ingiliffaa akkasumas barnoota bu'uuraa ga'eessotaa Afaan Amaaraa fi Afaan Oromootiin qophaa'e irratti kan xiyyeeffate ta'uu ibsaniiru.
Barnoota Afaan Ingilizii kanaan dura sadarkaa federaalaatti qophaa'aa ture, Biiroon Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee itti gaafatamummaan fudhatee qopheessuun isaa, qophii barnoota raadiyoo bara kanaa adda kan taasisu ta'uusaa aadde Yewubdaar ibsaniiru.
Akkasumas, Gamaaggamni gaggeeffamaa jiru hojii bulchiinsi magaalichaa barnoota qulqullina qabu raadiyoodhaan barattoota biraan ga'uuf hojjechaa jiru bu'a qabeessa akka ta'uuf kan gargaaru ta’uu hubachiisaniiru.
Dhumarrattis, yaadota sirreeffamaa gamaggama kana irratti kennaman sirreessuun barnoota raadiyoo qulqullinni isaa mirkanaa'e dhaabilee barnootaaf kan dhaqqabsiifamu ta’uu ibsaniiru.
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
1 845
+8
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት አመት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በሬዲዮ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
(መስከረም 30/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በአዲሱ ስርአተ ትምህርት መሰረት የትምህርት በሬዲዮ ላልተዘጋጀላቸው የትምህርት አይነቶች የተቀረጸ የትምህርት በሬዲዮ በማስገምገም ላይ መሆኑን አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘ ት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የውብዳር አያሌው ግምገማው ቀደም ሲል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት መሰረት የትምህርት በሬዲዮ ባልተዘጋጀላቸው የትምህርት አይነቶች ስክሪፕት ባዘጋጁ መምህራን አማካይነት በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸው ግምገማው ስክሪፕቱን ባዘጋጁ መምህራን መካሄዱ የተቀረጸው ድምጽ በተዘጋጀው ስክሪፕት መሰረት ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል አመላክተዋል ።
ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም ግምገማው አማርኛን እና አፋን ኦሮሞን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የትምህርት አይነት ጨምሮ በግብረ ገብ ፣ሰፉ፣ እንግሊዘኛ እና በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የተዘጋጀውን የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት መሰረት አድርጎ በተዘጋጀው ስክሪፕት መሰረት በመካሄድ ላይ መሆኑን አስረድተዋል።
ቀደም ሲል በፌደራል ደረጃ ሲዘጋጅ የነበረውን የእንግሊዘኛ ትምህርት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊነት ወስዶ ማዘጋጀቱ የዘንድሮው የትምህርት በሬዲዮ ዝግጅት ለየት እንደሚያደርገው ዳይሬክተሯ ገልጸው ግምገማው በከተማ አስተዳደሩ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በሬዲዮ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ የሚገኘውን ተግባር ውጤታማ እንደሚያደርገው በመጠቆም በቀጣይ በግምገማው የሚሰጡ የማስተካከ
1 845
📢 ማስታወቂያ!
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡
በጊዜያዊ ምደባ ሂደቱ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ ተጠናቆ ምላሽ የተሰጠ በመሆኑ፣ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሃ-ግብር መሠረት በጊዜያዊነት ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሄድ ትምህርታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።
እንዲሁም የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ከመሄዳቹህ በፊት በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባት https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ እንድታረጋግጡ ይሁን
አዲስ ተማሪዎች፡
የምደባ ቦታችሁን https://student.ethernet.edu.et/view-placement/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፦ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ስለሆነ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን መቀጠል የምትፈልጉ ተማሪዎች(በጊዜያዊነት የተመደባችሁትን ጨምሮ) ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያወጡትን የጥሪ ማስታወቂያ በመከታተል ትምህርታችሁን በነበራቹሁበት መቀጠል እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
ትምህርት ሚኒስቴር
1 845
ማስታወቂያ!
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ፤
ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባቋቋማቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሂደቱን እያከናወነ ይገኛል።
ሚኒስቴሩ በትምህርት ቤቶቹ የሚገኙ ተጨማሪ ክፍት ቦታዎችን በመጠቀም ተጨማሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ዕድል አመቻችቷል።
በመሆኑም በትምህርት ቤቶቹ ባሉ ክፍት ቦታዎች ተመድባችሁ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው የምዝገባ ሊንክ በመግባት እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት
የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply
የትምህርት ሚኒስቴር
1 845
+9
ቢሮው በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የድጋፍና ክትትል ተግባር ማከናወኑ ተገለጸ።
(መስከረም 29/2019 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና እና የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬቶች የ2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ ባዘጋጁት ቼክ ሊስት መሰረት የተካሄደ ሲሆን ስራ ክፍሎቹ ቀደም ብለው ድጋፍ ክትትል ለሚያካሂዱ የቢሮ ባለሙያዎች የድጋፍና ክትትል አካሄዱን በተመለከተ ገለፃ አካሂደዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የመማክርት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ከመማክርት ጉባኤው ስራ አስፈጻሚ አባላትና ከቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ ጋር በመሆን በተወሰኑ ተቋማት ተገኝተው የድጋፍና ክትትል ሂደቱን ተመልክተዋል።
ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት ተቋማቱ በአንደኛ ሩብ አመት በእቅድ ዝግጅት ጀምሮ አፈጻጸማቸው ያለበትን ደረጃ በመለየት የተሻለና ተቀራራቢ አፈፃፀም አስመዝግበው የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ማሻሻል እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የመማክርት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ጠቁመው ቢሮው በቀጣይ ከድጋፍና ክትትሉ ባሻገር በተቋማቱ በመገኘት ምዘና የሚያካሂድ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
