هداية القلوب (የልቦች መሪ)
Kanalga Telegram’da o‘tish
228
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+177 kun
+1530 kun
Postlar arxiv
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
⭕️የምናባችሁ አስጨናቂ እባብ🐉 ገመድ ነው ።
ምሽት ነው መንገዱ ጭልምልም ብሏል። ብቻህን እየተጓዝክ ነው። በድንገት መሬት ላይ ተጠቅልሎ የተቀመጠ "እባብ" አየህ‼️
ልብህ በሃይል መምታት ጀመረ፣
እግሮችህ ተንቀጠቀጡ፣
በድንጋጤ ላብ አጠመቀህ።
.........ለመሸሽ አሰብክ ግን በፍርሃት ደነዘዝክ። "ሊነድፈኝ ነው" ብለህ አመንክ። ስቃዩንና መርዙን ገና ሳይነክስህ በሃሳብህ ቀመስከው።
.........ነገር ግን በዚህ ሁኔታህ ላይ አንድ ሰው የባትሪ ብርሃን አበራልህ። ያ እባብ🐍 መስሎህ ሊገድልህ የነበረው ነገር ተራ "ገመድ" ነበር‼️
በዚያች ቅጽበት ፍርሃቱ የት ገባ⁉️
ጭንቀቱስ የት ሔደ⁉️ ወዲያው መረጋጋት ጀመርክ! እባቡ ፈጽሞ እዚያ አልነበረም፤ የነበረው ያንተ "የተሳሳተ አመለካከት" ብቻ ነበር።
👉በህይወታችን ብዙ ጊዜ የሚያሰቃየንና እንቅልፍ የሚነሳን "የሚገጥመን ሁኔታ" ሳይሆን፣ ለሁኔታው የምንሰጠው "ትርጉም" ነው።
"ስራ ባጣስ?" (እባብ ነው)
"ሰዎች ቢንቁኝስ?" (እባብ ነው)
"ብወድቅስ?" (እባብ ነው)
እውነታው ግን እነዚህ ሁሉ በጭንቀት ጨለማ ውስጥ የታዩ "ገመዶች" ናቸው። አእምሯችን የሌለ ስጋት በመፍጠር እውነተኛ ስቃይ ውስጥ ይከተናል። ፍርሃትህ የሚመነጨው ከሁኔታው ሳይሆን ካንተ አመለካከት ነው።
👉ዛሬ ራስህን ጠይቅ፦ አሁን የሚያስጨንቅህ ነገር በእውነት "እባብ" ነው ወይስ አእምሮህ የፈጠረው "ገመድ"? መጀመሪያ ፍርሃትህን በብርሃን (በእውነት) መርምረው፤ ብዙ ጊዜ የምንሰቃየው በምናባችን ውስጥ እንጂ በእውነተኛው ዓለም አይደለም!
ብርሃኑን አብራ‼️ 💡
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
"አንድ ሰው ሀፍረቱ (ጨዋነቱ) የቀነሰ ሆኖ ካየኸው፣ በትውልድ ሀረጉ ላይ ችግር እንዳለ እወቅ።" ይህ የሆነበት ምክንያት መልካም ዘር በአብዛኛው በሰውየው ላይ መልካምነትን ስለሚያሳድር ነው፣ ተቃራኒውም እንዲሁ ነው። ለዚህም ነው ነቢያት በህዝቦቻቸው መካከል ካሉ ምርጥ የዘር ሀረጎች የተላኩት። ይህ "ሂረቅል" ታሪክ ውስጥ (ኢብኑ አባስ በዘገቡት) ተጠቅሷል፤ ነቢያት በዘር ሀረጋቸው ከፍተኛ ከሚባሉት ወገኖች ይላካሉ። ምክንያቱም መልካም ዘር በአጠቃላይ ከመልካም ስነ-ምግባር ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው፣ ይህም በአብዛኛው ሁኔታ የሚታይ እውነታ ነው።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
🖱በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኮርስ ፕሮግራማችን
ተ
ጀ
መ
ረ
https://t.me/Multeka_Selefiyin?videochat=2e627e4c5e3b291250
እነርሱ ስላሉሽ ሳይሆን አንቺ መሆን ያለብሽን ሁኚ!
ስለሰዎች አሉቧልታ ከመጨነቅ ይልቅ ራስሽን በመገምገም በራስሽ መንገድ በቀጥታ ለመጓዝ ሞክሪ! ፅኚም!
#ኸልዋ
ከሰው መቀላቀል፣ ውስጤ ቢያምረውም፤
ሳቅና ጨዋታን፣ ልቤ ቢናፍቅም።
እኔ ግን ጌታዬ!! መገለልን መረጥኩ፤
ካንተ ጋር ላወጋ፣ ብቻዬን ተነጠልኩ።
#አላህዬ......
ከሰዎች እንድርቅ-ምክንያት የሆነኝን፣
ብቻዬን አድርጎ -ደጅህ ያጠናኝን፣
እንቅልፍ አሳጥቶ-ሚከነክነኝን፣
በሀሳብ ባህር ውስጥ-የሚያሰምጠኝን።
ሀጃዬን ሙላልኝ- እባክህ ያአሏህ፤
ጉዳዬን አግራልኝ-ለደካማ ባሪያህ!!
https://t.me//munajah0
https://t.me//munajah0
ተከታታ ቲላዋ ረጋ ባለ አቀራር
በተለይ ለጀማሪዎች ይጠቅማቹሀል
ሱረቱ አልነህል ካለፈው የቀጠለ ሁለት ሰፍሀ
🎙በወንድም ጀላሉ ሁሰይን (አቡ ዚክራ)
👉 ቁርአን ያማረ አፅናኝ‼
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/quran_yamare_atsnagn
በእውቀትም ሆነ በገንዘብ ወይም በሌላ ነገራቶች ካለሽበት ደረጃ ከፍ የማያደርግሽን ወንድ አትግቢ
እድሜየ ሄደ ምናምን እያልሽ ያልሆነ ህይወት ውስጥ አትግቢ
ፀባዩ ጥሩ ከሆነ ገንዘብ ተሰርቶ ይመጣል አትበይ ገንዘብ ሲያገኘ ፀባዩ እንደሚቀየር አትርሽ እኔ ምንም አይቸግረኘ ለልጀ መሆን አያቅተኘም አትበይ ልጅን ገንዘብ ስላለሽ ብቻ አታሳድጊውም መልካም አባት ያስፈልገዋል
ወንዶች ደግሞ ሴቶች ገንዘብ ይወዳሉ አትበሉ የወንድነት መገለጫቹህኮ ገንዘብ ሰርታቹህ ሴቶችን ልጆችን ማስተዳደር ነው
ሴት ሰርታ እያሳደረችህ አንተ ምኑ ላይ ነው ወንድነትህ ምንህን ነው እንድታከብርልህ የምትፈልገው?
ሰው ስለሆንክ ታከብርሀለች የባልነት ደረጃ ግን አታገኘም
منقول
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በዚህ ሁኔታ ላይ አልፎ ከዚያ ሲሞት ድረሱልን ይሉታል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
بشرى سارة:
إخوتنا وأخواتنا المسلمون الأعزاء، يسرّنا أن نعلن بكل سرور أن لسان السلفيين "ملتقى السلفيين للدعوة والإرشاد" مجموعة تيليغرام، قد نظّم دورة دروس تستمر لمدة ثلاثة أو أربعة أيام، وذلك ابتداءً من يوم الجمعة القادم [29 شوال 1447 هـ].
الدروس المقدَّمة والأساتذة المشاركون:
١. نواقض الإسلام - بأبي ريان
٢. تبصير الخلف - بأبي عبد الرزاق
٣. جناية التميع - بأبي عبد الرحمن
٤. قصيدة الحائية - بأبي لقمان
٥. من أصول عقيدة أهل السنة.. للشيخ صالح الفوزان - بأوّل أحمد منيو
وسيُدار البرنامج إن شاء الله بواسطة محمد أياليو وأبي عمران.
الوقت: الساعة 2:30 مساءً بتوقيت إثيوبيا.
رابط مجموعة التليغرام: t.me/Multeka_Selefiyin
አስደሳች ዜና
የተከበራቹህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች የሰለፊዮች ልሳን የሆነው "ሙልተቃ የቴሌግራም ግሩፕ" የፊታችን ጁሙዓ [ሚያዝያ 09,2018] ጀምሮ ለሶስት ወይም ለአራት ቀን የሚቆይ የደርስ ኮርስ ማዘጋጀቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
የሚሰጡ ደርሶችና የሚያቀርቡልን ኡስታዞች፦
1. ነዋቂዱል ኢስላም - በአቡ ረያን
2. ተብሲሩል ኸለፍ - በአቡ ዓብዲረዛቅ
3. ጂናየቱ ተመዩዕ - በአቡ ዓብዲረሕማን
4. ቀሲደቱል ሓኢየህ - በአቡ ሉቅማን
5. ሚን ኡሱል - በአወል አሕመድ መነዮ
ፕሮግራሙ በሙሐመድ አያሌውና በአቡ ዒምራን ይመራል ኢንሻአላህ።
ሰዓት፦ 2:30pm, በኢትዮ
=
የቴሌግራም ግሩፕ
t.me/Multeka_Selefiyin
t.me/Multeka_Selefiyin
Repost from 🎀قناة بنت عبدالله🎀
👉“የልብ መረጋጋት የሚጀምረው፤ ነገሮች በሰዎች እጅ አለመሆናቸውን ስትረዳ ብቻ ነው።”
=
وما توفيقِ إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب
ፈገግ እያልሺ ስሪ !
አንች ውዷ እህቴ ስደት ላይ ያለሺው፡
በስራ መብዛት የተገላታሺው፡
በሀሳብ ትካዜ ሰምጠሺ የገባሺው፡
መጨነቅ መጠበብ በጣም ያበዛሺው፡
አይዞሺ አብሺሪ አትጨናነቂ፡
እቅድሺ ተሳክቶ ስደትም ይበቃል
የምታርፊበት ቀን በቅርቡ ይመጣል፡
ይሄም ነገር አልፎ ለታሪክ ይወራል።
ብቻ ጥንክር በይ እቅድሺ ይሳካል፡
እንዳትቸኩይ በሶብር ይደርሳል፡
ይሄን የሚያስረሳ መልካም ቀን ይመጣል
ፈገግ እያልሺ ስሪ ሁሉም ነገር ያልፋ
ብቻ አብሺሪ ኢንሻ አላህ !!
قال ابن القيم :(رحمه الله)" من شاء أن يسكن في رياض الجنة ( في الدنيا ) فليستوطن مجالس الذكر . الوابل الصيب ١٤٨
ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል።
"በዱንያ ላይ ሆኖ የጀነትን ጨፌ መኖር የፈለገ የኢልም መድረኮች ይሳተፍ።" (منقول
https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk
