✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Kanalga Telegram’da o‘tish
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
194
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-730 kun
Postlar arxiv
Repost from MuhammedSirage M.Noor
ሰዎችን መጠየቅ ...
በተቻለ አቅም ሰዎችን ከመጠየቅ እና ከማስቸገር እንቆጠብ ... ሰዎች በተጠየቁ ግዜ የጠያቂው ክብር እነሱ ዘንድ እየወረደ ይመጣል .... አለመጠየቅ / አለማስቸገር / ዲን እና ክብር ይጥጠበቅበታል !
አንገብጋቢ ጉዳይ ገጥሞ ካልሆነ በቀር ሰዎችን ከነገሮቻቸው መጠየቅ አያስፈልግም !
መጠየቁ ግድ በሆነ ግዜ ደግሞ ቅርቦችንና የተቅዋ ባለቤቶችን ብቻ መጠየቁ ይምመከራል !
https://t.me/msirage4
ሸይኽ ፈውዛን ሐፊዞሁሏህ እንዲህ አሉ፦
"ረመዳንን ያገኘ በርሱም እንዲጠቀምበት ያምቻቸለት ሰው!
ምንም ነገር የማይነፃፀራትን ፀጋ አሏህ ውሎለታል።"
[መጃሊሱ ረመዷን (11)]
..
አላህ ሆይ! በሰላም በኢማንና በጤና ለተከበረው ወር አድርሰን።ካሰብነውም በላይ በመልካም ስራ የምንተጋበት ወር አድርግልን።
ከኢብኑ ተይሚያህ መልእክቶች..
ثُمَّ أَوْرَثْنَا الْكِتَابَ الَّذِينَ اصْطَفَيْنَا مِنْ عِبَادِنَا ۖ فَمِنْهُمْ ظَالِمٌ لِّنَفْسِهِ وَمِنْهُم مُّقْتَصِدٌ وَمِنْهُمْ سَابِقٌ بِالْخَيْرَاتِ بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ (32) سورة الفاطر
በቁርአን ዉስጥ እንደዚች አይነት ተስፋ ሰጪ ምንም አንቀጽ የለም። ከፊል ዑለማኦች በዚች አንቀጽ የተገለጸው መልእክት ልዩ ስለሆነ በወርቅ ብእር ጎልቶ መጻፍ አለበት ይላሉ።
በአንቀጹ ዉስጥ ራሳቸውን በዳይ መካከለኛና በበጎ ስራ ቀዳሚወቹ አማኞች የአላህ ምርጥ ባሮች እንደሆኑ፣ ቁርአንንም የተሰጡበት ዋነኛው ምክንያት በዚህ ምርጥነታቸው እንደሆነ፣ ፍጻሜያቸውም በወርቅ ጌጦች አሸብርቀው፣በሀር ልብሶች ተውበው፣ በስሮቿ ፈሳሽ ወንዞች ካሉባት፣ መከራና ድካም ከማይታሰብባትና ዝንታለም ከማትጠፋው ጀነት ዉስጥ እንደሆነም አበስሯቸዋል።
የእነዚህ ሶስት አይነት ቡድኖች መገለጫ ምንድን ነው? ለሚለው ሸይኹል ኢስላም መጅሙዑል ፈታዋቸው ላይ የሚከተለውን ብለዋል።
ራሳቸውን በዳይ የተባሉት፦ሃራሞችን ሲዳፈሩ የነበሩና ትእዛዛቶች ላይ ቸልተኛ የሆኑት ናቸው።
መካከለኛ አማኞች የተባሉት ግዴታዎችን የተወጡና ክልከላዎችን የራቁት ናቸው።
በመልካም ስራ ቀዳሚ አማኞች የተባሉት ደግሞ በግዴታዎችና በተወዳጅ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበሩና በክልከላዎች ብቻ ሳይሆን በተጠሉ ተግባራቶች ላይ ከመዘፈቅ የታቀቡ ናቸው።
እንደ ኢብኑ ጁዚይ ማብራሪያ በቁርአን አንቀጹ ራሳቸውን በዳዮቹን መጀመሪያ መጥቀሱ ወንጀለኞች ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማነሳሳት ሲሆን በበጎ ስራ ቀዳሚዎቹን መጨረሻ ላይ ማስቀመጡ ደግሞ በመልካምነታቸው እንዳይደነቁና እንዳይሸወዱ ለማስተማር ጭምር ነው።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ትብብራችሁ ይፈለጋል
~
ወሎ ውስጥ አመቱን በተለያዩ አካባቢዎች ቂርአት ላይ ተሰማርተው የሚቆዩ ደረሶች ረመዷን ላይ ይበተናሉ። ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ፊቅህ፣ ነሕው፣ ሶርፍ፣ ተፍሲር፣... ሲማሩ ቢቆዩም ዐቂዳ የሚማሩበት እድል በብዛት አያገኙም። እነዚህ ደረሶች ክፍተታቸው ቢሞላ ጥሩ አቅም ያላቸው በመሆናቸው ለሕዝብ የሚኖራቸው ፋይዳ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የተመረጡ ደረሶች የዘንድሮውን ረመዷን ዐቂዳን በመማር እንዲያሳልፉ አስበናል። መሻይኾችን አናግረን ደስ ብሏቸው ሰፊ ጊዜያቸውን ሊሰጡ ፈቃደኞች ሆነዋል።
ነገር ግን የደረሶቹ ወጭ መሸፈን ያስፈልጋልና እንድታግዙን እንፈልጋለን። ይሄ ትልቅ ሶደቀቱን ጃሪያ ነው አይለፋችሁ።
ዋና ዋና ወጪዎች:-
① ጤፍ 4 ኩንታል *11,500=46,000
② ማሽላ 1 ኩንታል*8000=8,000
③ በርበሬ 50 kg *800=40,000
④ ሽሮ 25kg= 25,000 ብር
⑤ ዱቄት 1 ኩንታል *10,500= 10,500
⑥ ምስር 25kg= 8000 ብር
⑦ ሩዝ 2 ኩንታል= 25,000 ብር
⑧ ጨው 10kg= 1200 ብር
⑨ ቴምር 5 እሽግ*4000= 20,000
①∅ ዘይት አንድ ሀያ አምስት ሊትር= 10,000 ብር
①① ሽንኩርት 2 ኩንታል= 10,000 ብር
①② ቲማቲም 50kg= 5000 ብር
①③ እንጨት= 25,000 ብር
①④ የሰራተኛ=25,000
①⑤ ውሃ በግዥ ነው የሚቀርበው፣ የመሻይኮቹ ትራንስፖርት አለ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጭዎች ይኖራሉ።
~
ድምር= 400,000 አካባቢ ነው የታቀደው።
* የሚማሩባቸውን ኪታቦች የሚገዛልን አግኝተናል (አላህ ጀዛውን ይክፈለው።)
* አካውንቱ በሸይኽ ሙሀመድ አሚን እና ሸይኽ ሙሀመድ መኪን ስም ተከፍቷል።
1000547235968
ንግድ ባንክ
ርብርብ ካደረግን ብሩ ትንሽ ነው።
ሼር በማድረግ አግዙን ባረከላሁ ፊኩም።
ጠያቂ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ በላይ ማግባት ይቻላል?!!!
መላሽ፦ እንዴ አታቅም እንዴ እስከዛሬ
በል ክፈትና መጽሀፍ ቅዱስ ላይ ላመላክትህ!!!!!ከመፅሐፋቸው ጋር የሚታኮሱ 'ፃድቃኖች'!!
~
በኢስላም አንድ ወንድ ከቻለ እስከ አራት ሴት የሚያገባበት አግባብ እንዳለ የሚታወቅ ነው፡፡ በርካታ ክርስቲያኖች ይህን መነሻ በማድረግ ኢስላምን ሲያብጠለጥሉ መስማት የተለመደ ነው፡፡ ይህ አካሄዳቸው ሰዎቹ ምን ያክል ለመፅሐፎቻቸው ወይ ባይተዋር ወይ ደግሞ ሽፍታ እንደሆኑ በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡ እንጂ በመፅሐፎቻቸው ይሄ ጉዳይ እጅግ በተጋነነ እና ኢስላም ከሚፈቅደውም በራቀ መልኩ የሚገኝ ነው፡፡ ነብያት ሳይቀሩ ብዙ ሚስቶች እንደነበሯቸው ተገልጿል፡፡ ለምሳሌ ያክል፡-
1. ”ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፣ አንዲቱም የተጠላች ሁለት #ሚስቶች ቢኖሩት…” [ዘዳግም 21:15]
2. “ዔሳው ከከነዓን ልጆች #ሚስቶችን አገባ፡፡” [ኦሪት ዘፍጠረት 36፡2]
3. “ላሜሕም #ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው..” [ኦሪት ዘፍጥረት 4፡23]
4. “ለጌዴዎንም #ብዙ_ሚስቶች ነበሩትና…” [መፅሃፈ መሳፍንት 8:30]
5. “የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራሀም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።” [ኦሪት ዘፍጠረት 16:3]
6. “ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን #ቁባቶቹን_ናሚስቶቹን ከእየሩሳሌም ወሰደ፣…” [መፅሐፈ ሳሙኤል ካልእ፡ 5፡13]
7. “ያዕቆብም ተነሳ፣ ልጆቹንና #ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፡፡” [ኦሪት ዘ ፍጥረት 31፡ 17]
8. 14 ሚስቶች!!! “አብያም ጸና፣ #አስራ_አራትን #ሚስቶች አገባ…” [መፅሐፈ ዜና መዋእል ካልእ 13፡21]
9. “ሮብአምም ከሚስቶቹና ከእቁባቶቹ ሁሉ የአቤሴሎምን ልጅ ሞአብን ወደደ #18ሚስቶች #60እቁባቶች ነበሩት፡፡” [መፅሃፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 11:21]
10. 700 ሚስቶች እና 300 ቁባቶች ለሰሎሞን!!! “ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ #700ሚስቶች #300ምቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።” [መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 11:3]
ክርስቲያኖች ሆይ! ይቺ ነገር የሙሐመድ ብትሆን እንዴት እንደምታራግቧት እስኪ ህሊናችሁን ጠይቁ! እምነታችሁ እንዲህ አይነት ፍርደ ገምድልነትን ያዛችኋልን?
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 28/2009)
=
የቴሌግራም ቻናል
http://t.me//IbnuMunewor
مَّن ذَا الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ
(الحديد11)
ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድር ለእርሱም (አላህ) የሚያነባብርለት ሰው ማነው?
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ትብብራችሁ ይፈለጋል
~
ወሎ ውስጥ አመቱን በተለያዩ አካባቢዎች ቂርአት ላይ ተሰማርተው የሚቆዩ ደረሶች ረመዷን ላይ ይበተናሉ። ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ፊቅህ፣ ነሕው፣ ሶርፍ፣ ተፍሲር፣... ሲማሩ ቢቆዩም ዐቂዳ የሚማሩበት እድል በብዛት አያገኙም። እነዚህ ደረሶች ክፍተታቸው ቢሞላ ጥሩ አቅም ያላቸው በመሆናቸው ለሕዝብ የሚኖራቸው ፋይዳ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የተመረጡ ደረሶች የዘንድሮውን ረመዷን ዐቂዳን በመማር እንዲያሳልፉ አስበናል። መሻይኾችን አናግረን ደስ ብሏቸው ሰፊ ጊዜያቸውን ሊሰጡ ፈቃደኞች ሆነዋል።
ነገር ግን የደረሶቹ ወጭ መሸፈን ያስፈልጋልና እንድታግዙን እንፈልጋለን። ይሄ ትልቅ ሶደቀቱን ጃሪያ ነው አይለፋችሁም።
ዋና ዋና ወጪዎች:-
① ጤፍ 4 ኩንታል *11,500=46,000
② ማሽላ 1 ኩንታል*8000=8,000
③ በርበሬ 50 kg *800=40,000
④ ሽሮ 25kg= 25,000 ብር
⑤ ዱቄት 1 ኩንታል *10,500= 10,500
⑥ ምስር 25kg= 8000 ብር
⑦ ሩዝ 2 ኩንታል= 25,000 ብር
⑧ ጨው 10kg= 1200 ብር
⑨ ቴምር 5 እሽግ*4000= 20,000
①∅ ዘይት አንድ ሀያ አምስት ሊትር= 10,000 ብር
①① ሽንኩርት 2 ኩንታል= 10,000 ብር
①② ቲማቲም 50kg= 5000 ብር
①③ እንጨት= 25,000 ብር
①④ የሰራተኛ=25,000
①⑤ ውሃ በግዥ ነው የሚቀርበው፣ የመሻይኮቹ ትራንስፖርት አለ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጭዎች ይኖራሉ።
~
ድምር= 400,000 አካባቢ ነው የታቀደው።
* የሚማሩባቸውን ኪታቦች የሚገዛልን አግኝተናል (አላህ ጀዛውን ይክፈለው።)
* አካውንቱ በሸይኽ ሙሀመድ አሚን እና ሸይኽ ሙሀመድ መኪን ስም ተከፍቷል።
1000547235968
ንግድ ባንክ
ርብርብ ካደረግን ብሩ ትንሽ ነው።
ሼር በማድረግ አግዙን ባረከላሁ ፊኩም።
ማህበራዊ ኑሯችን(ሙአመላ)!!!!
-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_
ትንሽ ላስታውሳችሁ ጥቆማ ሰጥቼ፣
ሙዓመላን እና ቲምሳልን ለይቼ፣
-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_
ሙአመላ ማለት የዱኒያ ትድድር፣
እንደ ጉርብትና ተስማምቶ መኗኗር፣
እቃ እንደመዋዋስ ብር እንደማበደር፣
አማራጭ ሲታጣ አብሮም እንደመማር፣
ድኑ በሚፈቅደው መኖር ከሰዎች ጋር፣
-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_
ይህ ነው ሙዓመላ ያለው በእስልምና፣
አስተንትን ወንድሜ ድንህን አጥራና፣
እህቴም አስተዊ ድንሽን አጥሪ ና ፣
=======_=======_=======
ተምሲል ሲባል ደግሞ አለው ብዙ ጣጣ፣
በኢስላም ህግጋት ያስከትላል ቁጣ፣
እምነት ተንተርሶ ነውና እሚመጣ፣
-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_
በካፊር በአል ቀን እኩል አብሮ ማክበር ፣
እንኳን የሚል ቃላት ደጋግሞ መናገር፣
ልደቱን ጥምቀቱን ስቅለቱን ማጋፈር፣
ሰው ኢስላምን ይዞ ትንሽ አለማፈር ❗️
-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_
እነሱን መከተል እንደ ጅል አፍጥጦ፣
ስይጥይናን መምረጥ ከኢስላም አብልጦ፣
ዘመንኛ መሆን የኛን ኢስላም ውጦ፣
///////////_////////_/////////
ለሸይጧን መገዛት በሚጠራን ማዝገም፣
ኋላ ቀር አድርጎ ኢስላምን መገምገም፣
ይህ ነው ትልቅ ጥፋት የሚያስገባ ጀሂም፣
በረሱል(ሶ ዐ ወ)አንደበት ተነግሯል ተዓለም፣
ቃል በቃል ሀድሱን እየው ወንድማለም፣
وعن ابن عمر رضي الله عنهما قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: "مَن تَشَبَّهَ بِقَومٍ فهو مِنهُم"
=======_=======_=======
ኢብኑ ባዝ ሲያብራሩ ተሸቡህን ለሰው፣
እንድህ ነበር ያሉት ይህን ሀድስ ጠቅሰው፣
በልብስ አለባበስ በዓልን ጠቁመው፣
በምግብ በመጠጥ መመሳሰል ከሰው፣
በምንም ሁኔታ ለሙስሊም ክልክል ነው፣
ከተሸቡህ መሸሽ ትልቅ አጅር አለው፣
ለተመሳሰለ ቅጣትም እንዳለው፣
የረሱሉ ሀድስ በቂ ማስረጃ ነው፣
"مَن تَشَبَّهَ بِقَومٍ فهو مِنهُم"
ኢማሙል ቡኻሪ የሀድሱ አስኳል፣
ሀድሱን ሲያብራሩ ይሄንን ብለዋል፣
በካፊር በዓላት መታደም ከነሱ፣
ልደትም ይበሉት ወይም ክሪስማሱ፣
ሌላም ቢሰይሙት ሃራም ነው ራሱ፣
አጥብቃችሁ ሽሹ አትሂዱ ከነሱ፣
ማስታወሻ‼
========================
⇛በየቀኑ እና ለረጅም ሰዓት ሶሻል ሚዲያው ላይ ተጥዶ መዋልም ሆነ ማደር መልካም አይደለም። ዕድሜና ጊዜን ይፈጃል። ዕድሜ ማለቁ የማይቀር የሚቆጠር እስትንፋስ ነው። እስትንፋስህን በዉድ ዋጋ እንጂ አትሽጥ።
⇛ራስህን ከትልቅ ቦታና ዉጤት ለማድረስ ብልህ ሁን። አንዳንዴም ከግርግሩ ሜዳ ገለል ብለህ ዉስጥህን የምታይበት ጊዜ ይኑርህ። ዛሬ ላይ ሥራ የሚያስፈቱ ነገሮችም ሰዎችም በዝተዋል። ዩ ቱዩቡና ሶሻል ሚዲያው፣ ዜናዉና የፖለቲካ ወሬው… ሰዎች ረጅም ጊዜ ሰጥተው ሰዓታቸውን የሚፈጁበት ነገር ሆኗል።
⇛በዚህ ዓይነቱ ጊዜ ነቃ በል። በመሃል የሚወስዱህ ነገሮች ቢኖሩ እንኳ "ዋናውን ሥራህን" አትጣል። ሰዎች በብዛት ስለተጠመዱበትና ስለሠሩት ብቻ አንድ ነገር ምርጥ ነው ማለት አይደለም። ባይሆን ከብዙዎች ለየት በል። በዝምታ ሥራ። ለዱንያም ለአኺራም ብዙ ትርፍ ሊያስገኙልህ በሚችሉ ነገሮች ላይ አተኩር።
⇛የሚዲያው ዓለም ባህር ነው። ሁሉ ነገሩ ይስባል። ሁሉ ነገሩ እዩኝ ይላል። ያዘናጋሃል፣ ጠልፎ ያስቀርሃል፣ ገብተህ መውጫው ይጠፋሃል። ከዚህ አንፃር ጠንካራ እና ራሱን መቆጣጠር የሚችል ብርቱ ሁን። ከገባህም በቀላሉ መውጣት የምትችል ጎበዝ ሁን። በዚህም በዚያም ልብህ አይሰረቅ። የሚስቡና የሚያስፈልጉ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም እጅግ በሚጠቅሙህ ነገሮች ላይ ብቻ አተኩር። ያብለጨለጨ ሁሉ ወርቅ አይደለም። ደምቆ ርዕሱ የተፃፈ ዜና ሁሉ ፍሬ ላይኖረው ይችላል። እናም ጥቂት ብትዘናጋ እንኳ ቶሎ ብለህ ወደ ዋናው ጣቢያህ ተመለስ።
•ዋናው ጣቢያችን የቁርአንና ሐዲሥ አስተምህሮ ነው።
አቡ ሱፍያን
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦
"ዱዓ ስታደርጉ ዱዓችሁን አላህ እንደሚቀበላችሁ እርግጠኛ ሆናችሁ አድርጉ።"
(ቲርሚዚ )
ተውሒድ ምድራዊ እና አኼራዊ ጭንቀቶችን ያስወግዳል።
ኢብኑል ቀዪም ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
“ተውሒድ የአላህ ጠላቶቹም ሆነ ወዳጆቹ መሸሻ ነው። ጠላቶቹን፤ ምድራዊ ከሆነው ጭንቅ ያወጣቸዋል አላህ እንዳለው፦ “በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል፡፡ (ከጭንቅ በማውጣት) ወደ የብስ ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን ከአላህ ጋር) ያጋራሉ፡፡” (አል ዐንከቡት፤65)
ወዳጆቹንማ፤ ከምድራዊም ሆነ ከአኼራዊ ጭንቀቶች ያድናቸዋል…
እንደ ተውሒድ ያለ ምድራዊ ጭንቀቶች እና መከራዎችን ሊያስወግድ የሚችል ነገር የለም። ለዚም እኮ ነው፤ የጭንቅ ጊዜ ዱዓ ተውሒድ የሆነው። ማንኛውም ሰው የአሳ ነባሪው ባለቤት (የነቢዩላህ ዩኑስ ) ዱዓ አድርጎ ጭንቀቱ የማይወገድለት ሰው የለም። እሱም(ዱዓው) በውስጡ ተውሒድን ያዘለ ነው። ሺርክ ካልሆነ ከባባድ ጭንቀቶች እና መዐቶች ላይ የሚጥል ምን አለ?! ከሱም የሚያድን እንደ ተውሒድ ያለ ምን አለ?! ተውሒድ የፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ መሸሻ ነው። መጠበቂያ ምሽግም ነው።”
"ሰደቃ
ከሰማይ የሚመጣ መዓትን፣ዐይን ናስ እና የምቀኛ ተንኮልን በመመከት ላይ እጅግ የሚገርም አዎንታዊ ተፅዕኖ አለው።"
ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ
[ በዳኢዑ አልፈዋኢድ (2/234)]
Repost from SadatKemal Abu Meryem
ሑዘይፋ ኢብኑል የማን መስጂድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000680622543
አቢሲንያ ባንክ: 115183818
አዋሽ ባንክ: 01437999853200
ሒጅራ ባንክ: 1000034780001
ዘምዘም ባንክ: 0054754710301
ዳሸን ባንክ: 2959082956711
+251 911 678 186
👉ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በባልና በሚስት መካከል ፍች በዝቷል። መንስኤው ምንድን ነው???
ለሴቶች ምክር
#ከባልሽ_ጋር_ሊኖሩሽ_የሚገቡ_አደቦች‼️
==========================
✍1. ባልሽን ከማስቆጣት አላህን ፍሪ።
✍2. በክብሩ፣ በገንዘቡና በልጆቹ ላይ ታማኝ ሁኚ።
✍3. የግል ችሎታዎቹንና ተሰጥኦዎቹን አወድሽለት።
✍4. እሱ ከቤት እያለ ያለ ፍቃዱ የሱና ፆም አትፁሚ።
✍5. ልጆችሽን ሷሊሖች እንዲሆኑ ተንከባከቢያቸው።
✍6. ምክንያትሽ ምንም ቢሆን ያለ ፍቃዱ ከቤት አትውጪ።
✍7. ቅርብ ዘመድ ቢሆንም ያለ ፍቃዱ ሌላን ሰው ወደ ቤቱ አታስገቢ።
✍8. በቁጥር አንድ ላይ ትኩረት የምትሰጭው ሰው ባልሽ ይሁን።
✍9. አላህን ከማመፅ ውጭ በሆነ ነገር ሁሉ ታዘዢው።
✍10. ካንች ጋር የሚቆይበትን ሁኔታ አመቻችለት።
✍11. በውበትሽ ሁሌ አድስ ሙሽራ ሁኚ።
✍12. ገንዘቡን ያለ ፍቃዱ አታባክኚበት።
✍13. አብሮሽ ሲቀመጥ ፀጥ አትበይ።
✍14. መልካም ሲሰራ አመስግኚው።
✍15. በመልካም ንግግር ቀልጅው።
✍16. ወሬ አታብዢ።
✍17. ግልፅ ሁኚ፣ አትዋሺ።
✍18. ከባልሽ ውጭ አትመልከቺ።
✍19. ሲስቅ ሳቂ፣ ሲያለቅስ አልቅሺ።
✍20. የሚወደውን ምግብ አዘጋጅለት።
✍21. የሚያስደስተውን ንግግር ተናገሪ።
✍22. ሀሳቡን አክብሪ፣ በተለይ ከሰዎች ፊት።
✍23. የማይችለውን ነገር በመጠየቅ አታስቸግሪው።
✍24. ከቤት ሲሆን ከሱ ጋር ተቀመጪ፣ ሲወጣ ወደ ስራሽ ሂጂ።
✍25. ያሉሽን ችግሮች ለመናገር አመቺ ወቅት ምረጪ።
✍26. ጭንቀቱን በመልካም ንግግር አስወግጅለት።
✍27. ከሱ እንደምትበልጪ አይነት አትሁኚ።
✍28. ስታጠፊ በፍጥነት ይቅርታ ጠይቂ።
✍29. ያለ አግባብ ከመቅናት ተጠንቀቂ።
✍30. ሚስጢሩን አታውጪ።
✍31. ሳይተኛ በፊት አትተኚ።
✍32. ቀድመሽው ከእንቅልፍሽ ተነሺ።
✍33. ብዙ ነገር ሲያመጣ አመስግኝው።
✍34. ትንሽ ነገር ሲያመጣ አበርክችው።
✍35. ሲያለቅስ አትሳቂ፣ ሲስቅ አታልቅሺ።
✍36. ሲታመም እንቅልፍሽን ትተሽ እደሪ።
✍37. ሲወጣ ሸኚው።
✍38. ሲቸገር ከጎኑ ቁሚ።
✍39. በዲኑ ላይ እገዢው።
✍40. ሲገባ በፈገግታ ተቀበይው።
✍41. ቀጠሮ ሲኖረው አስታውሽው።
✍42. ስለ ሌላ ሴት ባህሪ አታውሪው።
ግለሰቧ "እስልምናን ለቅቄ ወጣሁ" ስትል አስቀድሞም በእምነቱ ውስጥ በስነ-ምግባርም ሆነ በዕውቀት አልነበረችም። እርግጠኛ ሁኜ የምነግራችሁ ይህ ድርጊቷ ለታዋቂነት፣ በማህበራዊ ሚዲያ የሰዎችን ቀልብ ለመሳብ እና ተገላልጣ ለመጨፈር የተደረገ ድራማ እንጂ በእውነተኛ ፍለጋና በውሳኔ የተደረገ የሃይማኖት ለውጥ አይደለም።
ሲቀጥል አዳኝና ፈዋሽ አላህ (ሱ.ወ) ብቻ መሆኑን የእስልምና አስተምህሮ ብቻ ሳይሆን ክርስቲያኖች የሚመሩበት ባይብልም በግልጽ ይመሰክራል። "ማርያም አዳነችኝ" የሚለው ንግግር ከባይብል አስተምህሮ ጋር እንደሚከተለው ይጋጫል፦
አዳኝ እግዚአብሔር ብቻ ነው በኢሳይያስ 43፥11 ላይ "እኔ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም" ይላል። ማርያም አዳኝ ናት ካሉ ባይብልንን እየካዱ ነው።
ፈዋሽ እግዚአብሔር ብቻ ነው፦ በመዝሙር 103፥3 ላይ "ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽን ሁሉ የሚፈውስ" ተብሎ የተገለጸው ፈጣሪ ብቻ ነው። ፍጡርን ፈዋሽ ማድረግ ፈጣሪን መጋፋት ነው።
አማላጅ አንድ ብቻ ነው፦ በ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 ላይ "በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው አማላጁ ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" ይላል። ማርያምን አማላጅ ማድረግ "አንድ" የሚለውን የባይብል ቃል መቃረን ነው።
እስልምና ንጹህ ሃይማኖት ነው። የአንድ ግለሰብ መውጣት ወይም መግባት ለእስልምና የሚጨምረው ወይም የሚቀንሰው ነገር የለም። "መጥፎ ዕቃ ከቤቱ ይወገዳል" እንዲሉ፣ በእስልምና ስም እየኖሩ የእስልምናን ስነ-ምግባር የማይከተሉ ሰዎች መለየታቸው ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥራት ነው። እውነትን ለሚፈልግ ሰው ግን ቀጥተኛው መንገድ አላህን (ሱ.ወ) ብቻ በብቸኝነት ማምለክ ነው።
+1
በቅርቡ በቲክቶክ ስሟ "ደይማ እርጎዬ" የምትባል ግለሰብ "ከእስልምና ወደ ክርስትና ተለወጥኩ" በማለት የምታሰራጨው ወሬ እና አንዳንድ የክርስትና እምነት ተከታዮች "ማርያም አዳነቻት" በማለት እያደረጉት ያለው የድል አድራጊነት ስሜት በእውነታው ሚዛን ሲታይ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ነው።
ዳይማ እርጎዬ የምትባለው ግለሰብ የትውልድና የዕድገት ስፍራዋ በትግራይ ክልል በደቡባዊ ራያ (ራያ ዓዞቦ፣ ሂጅራ እና ራያ አላማጣ) አካባቢዎች ነው። የግለሰቧን የሃይማኖት ለውጥ "ትልቅ ክስተት" አድርገው ለሚሰብኩ ወገኖች የዳይማን ቤተሰባዊ ዳራ ማወቅ እውነቱን ለመረዳት ይረዳል። አባቷ ሙስሊም ሲሆኑ እናቷ ወ/ሮ ፋና ሰለምቴ (ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ) ናቸው። ይህም ማለት በእናት በኩል ያሉ የቅርብ ቤተሰቦቿ በሙሉ ክርስቲያኖች ናቸው። በመሆኑም ግለሰቧ ከልጅነቷ ጀምሮ በሁለቱም እምነቶች ተጽዕኖ ስር የነበረች እንጂ እስልምናን በሚገባ አውቃና ተረድታ የምትኖር ጠንካራ ሙስሊም አልነበረችም።
በተጨማሪም ደይማ "የራያን ባህል እያስተዋወቅኩ ነው" በሚል ሰበብ የምታሳልፈው የዕለት ተዕለት ሕይወት ከእስልምና መርሆዎች ጋር ፍጹም የሚጋጭ ነበር። ግለሰቧ በተለያዩ የመጠጥ ቤቶችና የጭፈራ ስፍራዎች ከወንዶች ጋር ስትጨፍር የምትውል፣ ከእስልምና ስነ-ምግባር ይቅርና ከኢትዮጵያዊ ሴት ጨዋነትና ባህል ጋር የማይሄዱ ተግባራትን ስታከናውን የነበረች ናት። ከአለባበስ አንጻርም ቢሆን አንዲት ሙስሊም ሴት ልትለብሰው የሚገባውን ሂጃብ ይቅርና፣ የራያ ሴቶች እንኳን ለክብር የሚለብሱትን "ጉፍታ" በትክክል አታደርግም።
