es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ጲንኤል

ጲንኤል

Ir al canal en Telegram

ጲንኤል ...አንዳንድ ጦርነቶች በውስጣችን ይካሄዳሉ። ይህ ቻናል እነዚያ ጦርነቶች በቃላት የሚገለጹበት፣ ሰው ከራሱ ጋር የሚገናኝበት፣ ሀሳብ፣ ትዝታ እና ውስጣዊ ግጭቶች የሚጻፉበት ገጽ። ✍️ እስራኤል ሰይፉ

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
190
Suscriptores
-124 horas
-37 días
-430 días

Cargando datos

Canales Similares
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
nov '26
noviembre '260
en 0 canales
octubre '26
+6
en 2 canales
Get PRO
septiembre '26
+4
en 1 canales
Get PRO
agosto '26
+1
en 0 canales
Get PRO
julio '26
+6
en 2 canales
Get PRO
junio '26
+56
en 3 canales
Get PRO
mayo '260
en 0 canales
Get PRO
abril '26
+6
en 0 canales
Get PRO
marzo '26
+145
en 1 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
02 noviembre0
01 noviembre0
Publicaciones del Canal
🎂👑 HAPPY BIRTHDAY TO MR. NOBODY! 👑🎂 ዛሬ ተራ ቀን አይደለም ዛሬ Nobody ወደ Somebody የተሸጋገረበት፣ ዓለምም አንድ ልዩ ሰው mr. Xን (Saxን🙄) የተቀበለችበት ታሪካዊ ቀን ነው! በእውነቱ ስምህ Nobody ቢሆንም፣ በሕይወታችን ያለህ ቦታ ግን Nobody አይደለም። Somebody ብቻም አይደለህም፤ Somebody Special! አንድ ግን ልብ በል፤ Nobody ስትሆን ሁሉም ያልፍልሃል፣ Somebody ስትሆን ግን ሁሉም ያውቅሃል። ላስታውስህ! ዕድሜ ሲጨምር ጥበብ ይጨምራል ይባላል፤ አንተ ግን ዕድሜህ እየጨመረ ሲሄድ የሳክስህ መጠን እንዳይጨምር ብቻ ነው ስጋቴ! 😂🎂 ውድ ወንድሜ፣ በዚህ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ስኬት መለያህ፣ ደስታ ጓደኛህ፣ ጤና ሀብትህ፣ ፍቅር መኖሪያህ ይሁን። ዛሬ የምታገኘው ሁሉ ከምትመኘው በላይ ይሁንልህ። እና አንድ ነገር አትርሳ፤ ስምህ Nobody ነው ብለህ የልደት ቀንህን ዝም አትበል፤ እኛ ግን የምናውቅህ Somebody ሆነህ ነው! From Nobody to Somebody, from Somebody to Somebody Special, and from Somebody Special to a LEGEND! መልካም ልደት ወንድሜ! ❤️ ዓለም ትወቅህ፣ ታሪክ ይጥራህ፣ ስኬት ያክብርህ! LONG LIVE THE LEGEND MR. NOBODY! 🔥👑🥂

2
በጨለማ ውስጥ የበራው 888 የፍቅር ብርሃን... አንዳንዴ ህይወት የራሷ የሆነ ሚስጥራዊ ህመም አላት ለእኔም የልደቴ ቀን ያው ሚስጥሬ ነበር። አንዳንድ ህመሞች አይነበቡምና ቀኑ በዝምታ እንዲያልፍ፣ የማስታወሻው ገጽ ሳይገለጥ እንዲዘጋ ብቻ ነበር የምመኘው... ነገር ግን እናንተ የዜሮ ፕላን (0 Plan) ውድ ቤተሰቦቼ ከእኔ ዝምታ ይልቅ የልቤን ስብራት ቀድማችሁ አነበባችሁት። ቀኑ ከሄደ ከአራት ቀናት በኋላ በዚያ ጨለማ ክፍል ውስጥ ያበራችሁት 888 ሻማ የልደቴን ማለፍ ሳይሆን የእናንተን ጥልቅና ድንቅ ፍቅር ነበር የሚያበስረው። እኔን ለማስደሰት የሄዳችሁበት ርቀት፣ የተጋራችሁት ቅንነትና የተከበበው ፍቅር ያንን ጨለማ ክፍል በብርሃንና በሞቅታ ሞላው። "የተሰማህን ተናገር..." ስትሉኝ፣ አፌ ቃላትን ማውጣት ተሳነው። ነገር ግን ከአይኖቼ የፈሰሰው ያ የደስታና የድንቅ ስሜት እምባ በአለም ላይ ያሉ ገጣሚያንና ጸሐፊዎች ሊገልጹት የማይችሉትን ጥልቅ የልብ ምስጋና ዝምታ ተረከው። ዝምታን የመሰለ ተራኪ ግን የት ይገኛል? ለእኔ የሰጣችሁት ስጦታ ከቁሳቁስ በላይ የሆነ በልቤ ሸራ ላይ የተሳለ ዘላቂ የፍቅር ስዕል ነው። ዜሮ ፕላን የክበብ ስም ብቻ ሳይሆን የተሰበሩ ስሜቶች የሚጠገኑበት እውነተኛ የመንፈስ ቤት እንደሆነ ዳግም አረጋገጥኩ። 888 ቁጥሩ የራሱ የሆነ የተዘጉ ቀለበቶች ያሉት በመሆኑ (ሲገለበጥ የኢንፊኒቲ ምልክት ነው ደግሞ በርቶም ወድቆ ነበር😁) ይህም ህይወቴ በአዲስ እይታና በሰላም እየተቃኘ መሆኑን አሳይቶኛል። በደንብም ቃኝታችሁልኛልም። እኔ ከንቱ ለሆንኩ እና ለማልረባው ወንድማችሁ የማይገባ ትልቅ ነገር ብታደርጉም  ለእያንዳንዱ ጥረት፣ ላዘጋጃችሁልኝ የማይረሳ ምሽት እና ለዚያ ልብ የሚነካ ሰርፕራይዝ ከልብ አመሰግናለሁ! (ኧረ ወገን ቃል አጣሁኝ እኮ... በቃ ምስጋና እንዲህ ነው? ጀመርኩ እንጂ አልጨረስኩም በጣ......ም ብዙ የምለው ነበረኝ ግን...😭) ብቻ አሁንም ቢሆን ቃላት ባይኖሩኝም አንድ ነገር ብቻ ማለት እችላለሁ! መልካም ወንድሞችና እህቶች ስላላችሁኝና በህይወቴ መንገድ ላይ ውብ ነፍሳትን ላገናኘኝ አምላክ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው! ❤️ ሁላችሁንም ከልቤ እወዳችኋለሁ🥰🥰🥰 ክበሩልኝ🙏 #0Plan #ArtOfLove #Surprise #FamilyFirst #Gratitude
91
3
+4
Sin texto...
82
4
“የሚፈራው ወንዝ” ​አንድ ሰው ወደ ኦሾ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “መምህር ሆይ፣ ለውጥን እፈራለሁ። ሕይወት ወደ ፊት በገፋችኝ ቁጥር እቃወማታለሁ። አዲስ ነገር በጀመረ ቁጥር ፍርሃት ይሰማኛል።” ​ኦሾ ወደ አንድ ወንዝ ይዞት ሄደ። የሚፈሰውን ውሃ እያሳየውም ጠየቀው፦ “ይህን ወንዝ ታየዋለህ?” ሰውየውም “አዎ” ብሎ መለሰ። ​“ድንጋዮቹን ይጋፋል?” ሲል ኦሾ ጠየቀ። “አይ።” “የመሬቱን ጠማማነትስ ይታገላል?” “አይ።” “የሚሄድበትን አቅጣጫ ለመቆጣጠር ይሞክራል?” “አይ።” ​ኦሾ ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦ “ነገር ግን ሁልጊዜ ውቅያኖስ ላይ መድረሱ አይቀርም።” ​ሰውየው ዝም አለ። ኦሾም ንግግሩን ቀጠለ፦ “ወንዙ መድረሻውን አያውቀውም፣ ነገር ግን ፍሰቱን (The Flow) ያምነዋል። ፍርሃት የሚመጣው ከመቆጣጠር ፍላጎት ነው። ሰላም የሚመጣው ደግሞ ከእምነት ነው። የምትፈራው ሕይወት አደገኛ ስለሆነች አይደለም የምትፈራው ሕይወትን ለመቆጣጠር ስለምትሞክር ነው።” ​ሰውየውም ጠየቀ፦ “ታዲያ ምን ላድርግ?” ​ኦሾ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እንደ ወንዝ ሁን። ተንቀሳቀስ፣ ግን አታስገድድ። ፍሰስ፣ ግን አትፍራ። ተለወጥ፣ ግን አትቃወም። እመን፣ ግን አትጣበቅ። ሕይወት የሚፈታ እንቆቅልሽ አይደለችም — የምትኖር ፍሰት እንጂ።” ​ከዚያም ኦሾ በለሰለሰ ድምፅ እንዲህ ሲል አከለ፦ “የምትሰምጠው ወንዝ ውስጥ ስለወደቅክ አይደለም። የምትሰምጠው ፍሰቱን ተቃውመህ ለመቆም ስለሞከርክ ነው።”
72
5
እስራኤል ወንድሜ የጥንት የጠዋቱ ልደትህ ትላንት እንደነበር ዛሬ ነው ያስታወስኩት። ይቅርታ እንግዲህ አረጀህ እንጂ አልረሳሁህም😁 እኔ እንኳን ልደትህን በጊዜው ባልደርስም አንተ ግን እድሜህን በጊዜው ጨምረሃል 🙂 ለማንኛውም እንኳን ለሌላ አመት የሕይወት ጉዞህ በሰላም አደረሰህ ወንድሜ ፈጣሪ ረጅም እድሜ ጤና ሰላም ደስታና ስኬት ይስጥህ። የልብህ መሻት ሁሉ ይሳካልህ የምትመኘውን ሁሉ በራስህ ጥረት እንድታገኝ መድሀኒአለም ይርደህ። በሕይወትህ ውስጥ የደስታ ቀኖችህ ከሀዘን ቀኖችህ ይብዙ የምትስቅባቸው ምክንያቶችህም ከምታስብባቸው ቀናቶች ይብዙ 🙂 እድሜህ ሲጨምር ገንዘብህም አብሮ ይጨምር ውበትህም አይቀንስ (አንተ የወንድ መናሊዛ🤣) ችግርህም በራሱ ጡረታ ይውጣ እና አንድ ነገር አትርሳ እኔ ልደትህን በማግስቱ ባስታውስም የማያስብልህ ጓደኛህ መሆኔን አትጠራጠር 😁 ሳጠቃልልህ ሁሌም ፈገግታህ አይጥፋ ደስታህ አይቀንስ እንደ መቱሳላ እድሜ የረዘመ ይሁንልህ ስኬትህም ያለ ድንበር ይሁን ኬክህን ስትበላ(ከበላህ😭) የኔን ድርሻ አትርሳ አለዚያ የሚቀጥለውን ልደትህን ከአንተ በኋላ ሳይሆን ከአንተ በፊት እመጣለሁ 🤍 😂
71
6
"ስለ ወዳጅነት እጅግ የተሳሳተ አመለካከት አለን። ወዳጅነት ከፍቅር በላይ ያለ ከፍተኛ የመንፈስ ደረጃ ነው። እሱ የፍቅር እውነተኛ ዋና ውህድና ማዕከል ነው። በእውነቱ፣ ፍቅር በጥልቀት እያደገ ሲሄድ ወደ ወዳጅነት ይለወጣል። ​እኛ ግን ስለ ወዳጅነት የተሳሳተ አመለካከት አለን። ወዳጅነት ዝም ብሎ ላዩን የሚደረግ ውጫዊ ትውውቅ፣ ፍቅር ግን እጅግ ጥልቅ እንደሆነ እናስባለን። ነገር ግን እውነተኛ ወዳጅነት ምን እንደሆነ አታውቀውም። ፍቅር የራሱ የሆነ ውጣ ውረድና ሁከት አለበት፤ ወዳጅነት ግን እጅግ የረጋና ሰላማዊ ነው። ምንም ዓይነት የከፍታና የዝቅታ ውዥንብር የለውም። አዎ፣ ፍቅር ያለው ዓይነት ስሜታዊ ጫፍ (Peak) ላይኖረው ይችላል፤ ነገር ግን ከዚያ ከፍታ በኋላ የሚከተለው ጥልቅ ሸለቆና ስቃይም አይኖርበትም። ​ፍቅር እረፍት ማጣት ነው፤ ወዳጅነት ግን እጅግ ታላቅ እረፍትና ሰላም ነው። አፍቃሪዎች ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም፣ በሂደትና በዝግታ ወደ ወዳጅነት ይለወጣሉ። በመጀመሪያው ላይ ስለዚሁ ነገር የተሳሳተ አመለካከት ካለህ ግን ልብህ ሊሰበር ይችላል። ​በከንቱ ራስህን እያሳዘንክ ነው። ፍቅርን አውቀኸዋል፣ ከእሱ ጋርም ጥልቅ ቅርበት ነበረህ። አሁን ደግሞ ወዳጅነትንም ለማወቅ ሞክር፤ እሱንም ቅመሰው። ​ስለዚህ ነገሩን በምንም ዓይነት አሉታዊ መንገድ አትመዝግበው። የሚያምመው ከወዳጅነት ይልቅ ለፍቅር ከፍተኛ ዋጋ ስለምንሰጥ ነው፤ ይህም በእኛ የተሳሳተ ምዘና ምክንያት የመጣ ነው። ያለዚያማ ወዳጅነት ማለት የጎለመሰና የበሰለ የፍቅር ከፍተኛ ደረጃ ነው። ፍቅር ደስታንና ኀዘንን አሳልፎ ሲበስል፣ ሲጎለምስ ወዳጅነት ይሆናል። ​ፍቅር በውስጡ ብዙ ስቃዮች አሉበት፤ የተቀላቀለ ደስታ ነው። እጅግ የተደበላለቀና ግራ የገባው ሁኔታ ነው—በፍቅር ስም ብዙ ባለቤት የመሆን አባዜ (Possessiveness)፣ ቅናት፣ የበላይነት የመጫን ፍላጎት፣ የኢጎ ትግልና ሺህ አንድ ውዥንብሮች ይካሄዳሉ። ​ወዳጅነት ግን ሙሉ በሙሉ የተለየ ነው። ነገር ግን ወዳጅነት ሊፈጠር የሚችለው ከራሱ ከፍቅር እድገት ብቻ ነው። ስለዚህ አትጨነቅ። ተቀበለው፣ እቅፍ አድርገህ ተቀበለው፤ አሁን ፍቅር ይበልጥ ወደ ጥልቅ ደረጃ እንዲሸጋገር ፍቀድለት—በዚህም ትጠቀማለህ።" ኦሾ/Osho
63
7
ጀግና በፍርሃት አይሸበርም፤ ይልቁኑ ፍርሃት ራሱ የጀግናውን ወኔና ቁርጠኝነት አይቶ ይደነግጣል! ጀግንነት ማለት በቃል ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፣ ህይወትን በጥበብ በመምራት፣ ችግሮችን በጽናት በመሻገርና
ጀግና በፍርሃት አይሸበርም፤ ይልቁኑ ፍርሃት ራሱ የጀግናውን ወኔና ቁርጠኝነት አይቶ ይደነግጣል! ጀግንነት ማለት በቃል ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፣ ህይወትን በጥበብ በመምራት፣ ችግሮችን በጽናት በመሻገርና በዙሪያውላሉት ሰዎች ብርሃን በመሆን የሚኖር ህያው ታሪክ ነው። በጥበብ ያጌጠ ህይወት ደግሞ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እንደ ወይን ጠጅ እያደገ፣ እየጣፈጠ እና እያበራ ይሄዳል። ዛሬ ደግሞ የዚሁ ድንቅና ባለጥበብ ጀግና የልደት ቀን ነው! መንገድህ ሁልጊዜም በብርሃንና በጥበብ ይሙላ፤ የቆምክበት ምድር ሁሉ ለሌሎች ተስፋና ጥንካሬ ይሁን። በፍርሃት ቦታ የሌለው ወኔህ፣ በታላቅ ጥበብ ያጌጠው ህይወትህ እና ደግነትህ ለብዙዎች አርአያ ሆኖ ይቀጥል። በሄድክበት ሁሉ ስኬት፣ ደስታ፣ ሰላምና ረጅም ዕድሜ አብረውህ ይሁኑ። መልካም ልደት! 🎂🎉
63
8
.....እሷም ትንፋሹ አንገቷን እየፈጃትም ቢሆን የሚላትን የቦን እውነተኛ መጸጸት አይታ ይቅር አለችው። ከዚያች ምሽት በኋላ ቦ... ተቀየረ። ከዛን ቀን ጀምሮ በእንስሳቱ ውስጥ በሰላም የሚኖር አስተዋይና ደስተኛ ልጅ ሆኖ ህይወቱን ሊቀጥል ለራሱ ቃል ገባ። https://t.me/Oct13wed
64
9
የጠፋው ቦ... ✍️እስራ ...ጸሐይ በስተምዕራብ በሚገኙት ግዙፍ የዛፍ ጫፎች ላይ ወርቃማ ቀለም የምታፈስበት ያ አመሻሽ እጅግ ልዩ ነበር። የከሬብ ጫካ እንደወተሮው በወፎች ዝማሬ እና በዱር እንስሳት የደስታ ድምፅ ተሞልቷል። አልፎ አልፎም ከማዶ የሚሰማ የስሥላሴ ደወል ድምጽ እና ቅርብ ያለው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የእጣን ሽታ ቦታውን ልዩ እና ተናፋቂ ያደርገዋል። ዘወትር ሰርክ 11 ሰዓት ላይ ከሚመጡ ሁለት ሰዎች በቀር ቦታው ሁሌም ጭር ያለ ነው። ኋላ ላይ እነሱም ቀሩና ማንም ዝር የማይልበት ዝም ያለ ለምለም ጫካ ሆኖ ቀረ እንጂ። በዚህ ሰፊና ለምለም ጫካ ውስጥ 'ቦ...' የተባለ ትንሽዬ ጦጣ ከወዳጁ ጋር ይኖር ነበር። ቦ... ሲያጫውቱት ተጫዋች ቢሆንም ግን ዝምተኛ እና የማወቅ ጉጉቱ ገደብ የሌለው ልጅ ነው። ከዛፍ ወደ ዛፍ እየተወዛወዘ አበቦችን መቅጠፍ እና ፍራፍሬዎችን መለቃቀም የዘወትር ተግባሩ ነው። ነገር ግን ወዳጁ ሁልጊዜ ማታ ማታ ምትሀት በሆነ እቅፏ አቅፋው በቁጭትና በፍቅር የምታስጠነቅቀው አንድ ነገር ነበር.... "ወዳጄ.." ትላለች አይኖቿን ጨፍና ማለቂያ ወደሌለው  ልቧ እያተኮረች። "...ወደ ታችኛው ወንዝ ማዶ እንዳትሄድ። ቦታው የጨለማና የአዳኞች ሀገር ነው። ከእኔ ከተለየህ ደግሞ መንገድህን አጥተህ ለአደጋ ትጋለጣለህ።" ቦ.. ሁልጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ ሆኖ አንገቱን ቢወዘውዝም፣ በልቡ ውስጥ ግን ያ ሁልጊዜ የሚነገረው የታችኛው ወንዝ... ምን ይመስል ይሆን የሚል ምስጢራዊ ፍላጎት ያበቅል ነበር። ያ እጣን ሽታ ግን በአመት አንዴ እጣኑ ከተጨሰ አንድ ቀን በኋላ ለልደቱ ቀን ብቻ ነበር የሚሸተው። ያ በራሱ ሌላ ምስጢር ሆኖበታል። በአንድ ልደቱ ቀን ላይ ታድያ ቦ.. ከወዳጁ ጎን ሆኖ የበሰሉ የጫካ በለሶችን እየቀጠፈ ሳለ፣ ከየት መጣች ሳትባል አንዲት ባለ ብዙ ቀለም ቢራቢሮ በፊቱ ላይ አለፈች። ክንፎቿ እንደ አልማዝ ያበሩ ነበር። ቦ የቆረጠውን ፍሬ ጥሎ ቢራቢሮዋን በአይኑ ተከተላት። ቢራቢሮዋ ወደ ታች፣ ከዚያም ወደ ላይ እያለች ወደ ታችኛው ወንዝ አቅጣጫ መብረር ጀመረች። ቦ የወዳጁን ማስጠንቀቂያ ረሳው። እግሮቹ በራሳቸው ጊዜ ቢራቢሮዋን ተከተሉ፤ ከዛፍ ወደ ዛፍ፣ ከቁጥቋጦ ወደ ቁጥቋጦ እየዘለለ ሳያስበው በጣም ሩቅ ተጓዘ። ወደ ወንዙ ዳርቻ ሲደርስ፣ የእጣኑ መአዛ ውስጡን ዘልቆ ተሰማው። ልደቱ መሆኑ ነው። ቆም እንዳለም ከዛፉ ቅርንጫፍ ላይ ተቀምጣ የነበረችው ኒ የተባለች ብልህ ወፍ አየችው። ደንግጣ ወደ እሱ አየችና... "ቦ! እባክህን ቁም!" አለችው ድምጿ እየተንቀጠቀጠ። "ከዚህ በላይ አትሂድ! ወንዙን መሻገር አደገኛ ነው። ወዳጅህ የነገረችህን አላሰብከውም?" ቦ.. በቦታው ቆመ። በውስጡም ትልቅ ግብግብ ተፈጠረ። በወጣትነት መንፈስ እና እኔ አውቃለሁ በሚል ኩራት ደረቱን ነፋ። የኒ ማስጠንቀቂያ ለሱ እንደ ቀላል  ታየው። እሱ የራሱን እይታ ብቻ ያውቅ ስለነበር ሊሰማት አልፈቀደም። "ምን?" አለ ቦ፣ ድምፁን ከፍ አድርጎ በአየር ላይ እየተወዛወዘ። "ወዳጄም ሆነች አንቺ እኔን እንደ ትንሽ ልጅ ስለምታዩኝ ነው! እኔ እኮ ብልህና ጎበዝ ነኝ! እኔ ያሰብኩትን ማድረግ እንደምችል ለእናንተን አሳያችኋለሁ!" ፈራችለት ኒ። "ቦ! እባክህን እልህ አትያዝ፣ እልህ ያጠፋሃል። ሁኔታህ ሁሉን እንድትችል እንዳሰብክ ያስታውቃል። እባክህን በቃህ! እንዳትችልም እወቀው!" ብላ ኒ.. ብትጮህም፣ የቦ... ጆሮዎች ተደፍነው ነበር። "እልህ ይዞኛል! የቻልኩትን ሁሉ እሞክራለሁ! ለራሴም ህግ አወጣለሁ! እናም ማንም ሊያስቆመኝ አይችልም!" በማለት ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ በእልህ ተወጥሮ፣ ከፊቱ ያለውን የበሰበሰ እንጨት ሳይመለከት ወደ ወንዙ መሃል ዘለለ። ክራክ!....የሚል የመስበር ድምፅ ተሰማ። ቦ.. የረገጠው እንጨት በእድሜ ብዛት የበሰበሰ ነበር። ረገጣው እንደተከሰተ እንጨቱ ተሰበረ። ቦ...ም  በቀጥታ ወደሚያጓራውና ወደሚንደረደረው የጥልቁ ወንዝ ውኃ ውስጥ አሽቆለቆለ። "አድኑኝ! አድኑኝ!" ብሎ ጮኸ። የወንዙ ማዕበል ወደ ታች ይስበው ነበር። በውስጡ ተነሳሽነት ተሞልቶ ያደረገው ውሳኔ አሁን ምንም ዓይነት ኃይል ወይም ድል አላመጣለትም። ይልቁንም በፍርሃትና በጭንቀት ተወጠረ። ከብዙ እግረ ሙቅ ትግል በኋላ፣ ውኃው ይዞት ሲሄድ በጫፉ ላይ የነበረን አንድ እሾሃማ ቁጥቋጦ በግድ ጨበጠ። አካሉ በሙሉ በእሾህ ተወጋ። ውኃው ልብሱንና ፀጉሩን አልፎም ልቡን አረሰረሰው። ከውኃው ወጥቶ መሬት ሲረግጥ ውስጡ የነበረው ስሜት በሙሉ ቅዝቅዝ ሲል ይታወቀው ነበር። ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ጠልቃ ጫካው በጨለማ ተውጧል። በዚያ ቅጽበት፣ በእልህ የተነሳ የያዘው ድፍረት በሙሉ እንደ ጢስ ተነነ። በእልሁ ያተረፈው ነገር ቢኖር... አካሉ በእሾህ መቁሰሉን፣በቅዝቃዜ መንቀጥቀጡን፣በጨለማ ውስጥ ብቻውን መቅረቱን፣ እና ወዳጁን ማጣቱን ብቻ ነበር! እልህ ያመጣለት ምንም ዓይነት አዎንታዊ ውጤት አልነበረም፤ ይልቁንም ሙሉ በሙሉ መንገድ አጠፋው። ደሀ... አይጣላ ከውሀ... እንዳለ ገጣሚ.. ከወንዝ ጋ ጸብ አልሆነለትም። ቦ... በዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ተሸብቦ በፍርሃትና በእንባ ተሞልቶ ማልቀስ ጀመረ። ሲያለቅስ ሳለም፣ በድንገት በዛፎቹ መሃል የሚያንፀባርቁ ሁለት ግዙፍ የቢጫ ቀለም አይኖች ተከፈቱ። አዛውንቱና ብልሁ ጉጉት ነበር። ጉጉቱ በዝግታ ወደ ቦ አቅራቢያ በረረና ተቀመጠ። "ታናሹ ቦ ሆይ..." አለ ጉጉት፣ በረጋና በከባድ ድምፅ። "በዚህ አደገኛ ምሽት፣ በዚህ የጨለማ ቦታ ብቻህን ምን ታደርጋለህ?" ቦ እንባውን እየጠረገ፣ ድምፁ እየተቆራረጠ መለሰ፦ " ጉጉት ሆይ... የወዳጄንና የጓደኛዬን ምክር አልሰማሁም። በጉጉትና በእልህ ተነሳስቼ ወንዙን ተሻገርኩ። እልህ ይዞኝ ያደረግኩት ነገር እራሴን ለአደጋ ከመዳረግ ውጭ ምንም ያመጣልኝ ነገር የለም። አሁን መንገዴ ጠፍቷል... ወዳጄንም ሳጣት በጣም ፈራሁ!" ጉጉት በሃዘን አንገቱን ወዘወዘና እንዲህ አለ፦ "ልጄ ሆይ! እልህ ማለት አእምሮን የሚጋርድ የታወረ መጋረጃ ነው። በጉጉት ተነሳስተህ የምታደርገው ማንኛውም ነገር ውድቀትንና ጥፋትን እንጂ ፍሬ አያፈራም። ሆኖም ግን፣ ስህተትህን ማወቅህና እልህ አጥፊ እንደሆነ መረዳትህ ትልቅ የጥበብ ጅምር ነው። አትፍራ፣ እኔ ወዳጅህን ባላውቅም ወዳጅ የሆነችህን ግን እንድታገኝ እመራሃለሁ።" አለ። ጉጉት በሌሊት የማየት ተፈጥሮአዊ ስጦታ ስላለው ኒ እያስፈለገችው እንደሆነ አይቷል። በሰማዩ ላይም በዝግታ እየበረረ መንገዱን ማሳየት ጀመረ። ቦ..ም  በዚህ ጊዜ ጉጉቱን ትቶ፣ በጥንቃቄና በትህትና  ጉጉትን ተከተለ። ...ከብዙ ጉዞ በኋላ፣ በሩቅ በርካታ የብርሃን ነጥቦች ታዩ። ኒ የጫካውን እንስሳት በሙሉ ሰብስባ እያስፈለገችው ነበር። ችቦ አበራርተው፣ በጭንቀት "...ቦኤዝ! ...ቦኤዝ!..." እያሉ ሲጮሁ ደረሱ። እንደደረሱም ቦ... ኒን እንደተመለከተ፣ እግሮቹ ባላቸው ኃይል በሙሉ እየሮጠ ሄዶ ደረቷ ላይ ተለጠፈ። እሷም በደስታ ተሞልታ ውዷን እቅፍ አድርጋ አሞቀችው። "...ይቅርታ" አለ ቦ፣ አንገቷ ስር  ሆኖ። "እባክሽን ይቅር በይኝ! የራሴን ጉጉት እያዳመጥኩ የተናገርኩትና ያደረግኩት ነገር እራሴን ለጉዳትና ለፍርሃት ዳርጎ ወዳጅ አሳጣኝ እንጂ ምንም አላተረፈልኝም። ከእንግዲህ ወዲህ በራሴ እይታ ብቻ አልመራም፤ ምክርሽን እና ቃልሽን ሁልጊዜ እሰማለሁ። ወዳጄ የት እንዳለች ባላውቅም አንቺን የመሰለ ወዳጅ እዚህ በመምጣቴ አግኝቻለሁና ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ!"
64
10
ሚስት ባሏን በስሱ ትጠረጥረዋለች... ብዙ አይደለም አለ አይደል አንዳንዴ ስልኩን ትፈታትሻለች፤ የስልኩን ፓስወርድ አልደበቃት ፣ ሁልጊዜ ክፍት ነው፣  ወይ የሆነ የሚያስጠረጥር ነገር አላደረገ ግን በቃ ለወንድ ልጅ መዘናጋት አያስፈልግም "ቅድመ ውስለታን መከላከል" የሚል መርህ አላት። ግን ስልኩ ሰላም ነው።  ሁልጊዜ ከቴሌና እርሷ ራሷ  ከስድስት ዓመት በፊት "ምጣድ ለሚሰራው ሰውየ ደወልክለት?" ብላ ከላከችለት ቴክስት  በስተቀር ማንም ቴክስት ልኮለት አያውቅም። አንዳንዴ "ማንም የማይፈልገው ሰው ነው እንዴ ያገባሁት?"  የሚል ሀሳብ ውል ይልባታል። ሲታመኑ መከራ ሲክዱ መከራ! ከሰባት ዓመት የትዳር ቆይታ በኋላ አንድ ምሽት ውሃ ልትደፋ ስትወጣ አጋጠማታ!! ባሏ ጨለም ያለ ቦታ ቁሞ በሹክሹክታ ስልክ ሲያናግር ተገጣጠሙ፤ ድንብርብሩ ወጥቶ ስልኩን ዘጋው። ወደቤት ገብቶ ሳትጠይቀው "ከመስሪያ ቤት አለቃየ ደውሎ  ..." ምናምን ከማለቱ  ወደስልኩ ተደጋጋሚ ቴክስት ሲገባ ተሰማ ..ጢን. ጢን! "ዘንድሮ አለ ነገር አለች። " ብልህ " ስለሆነች እስኪተኛ ምንም እንዳልተፈጠረ ተረጋግታ ቆየች። ካለወትሮው ሲገላበጥ አምሽቶ ሲተኛ በቀስታ ስልኩን አንስታ ወደሳሎን ሄደችና ከፍታ አየችው...ምንም የለም... ዋትስ አፕ ላይ ሄደች አገኘችው! የድምፅ መልዕክት ተልኳል.... ድምፁን ቀንሳ ከፈተችው .... "ሰላም ግርምሽ የፅግየ እናት አርፈዋል በጧት መጥተን ስለምናረዳት በሆነ ሰበብ አዘጋጃት" ፅግየ ራሷ ናት።
126
11
‹‹ያየን ሁሉ ተሰናክለን የማናውቅ ይመስለው ዘንድ የተረጋጋና ዝም ብሎ የሚሄድ ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ አያውቁትም። ማንም ምን ያህል እንደደከመን አይገነዘብም። በዝምታ ፈገግ ማለታችንና የተስተካከለ ቁመናችንን ስላዩ ብቻ ምን ያህል የድካም ዝርዝሮችን እንደተሸከምን አያውቁም፤ ቢያውቁም ማንም ስለዛ ጉዳዩ አይደለም። በቃ አይረዱኋችሁም.. ሺህ ማይል እያሰብን የተራመድንበትን ነገር አፍ አውጥተን ብናወራው እነሱ አንድ እርምጃ እራሱ ስላልተራመዱ አይሰማቸውም። በልባችን ውስጥ ቤት ስለሰሩት የለሊት ሃሳቦች ሚሊዮን ጊዜ ብናስረዳ የልባቸውን በር አንዷን ሌሊት እንኳን አያንኳኳም። በዚህ ምክንያት አንድ ሰው ተቀብሎ ባለመኖር እና ሳይቀበሉት በመኖር መካከል ይሞታል››                         ―አህመድ ካሊድ ታውፊቅ              
131
12
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣ የፍልስፍናና የእግዚአብሔር ምስጋና ታላቅ መንፈሳዊ ሀብት ነው። ታላቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ምስጋናና ስለ መንፈሳዊ ዜማ ሲናገር፣ የምስጋና ድምፅ የሰውን ልብ ከምድር ከንቱነት ወደ ሰማያዊው ምስጢር እንደሚያሸጋግርና ነፍስን ከአምላኳ ጋር እንደሚያገናኝ ያስተምራል። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ «በገናን አንሱ፤ በበገናም ለእግዚአብሔር ዘምሩ» እያለ እንደተናገረው፣ በገና የንጉሡ የዳዊት እጆች ያረፉበት፣ የነቢያት መንፈስ የፈሰሰበት፣ የቅዱሳን ማኅሌትና የእግዚአብሔር ምሕረት መጠየቂያ ታላቅ የዜማ ዕቃ ነው። እኛም የዚህን ታላቅ መንፈሳዊ ሀብትና ጥበብ መሠረት በመጣስ ሳይሆን በመጠበቅ፣ ትውልድ ከመንፈሳዊ ሥሩ እንዳይደናቀፍና የቅዱስ ዳዊትን በገና ድርደራ በጥበብና በፍልስፍናው መንገድ እንማር ዘንድ ይህን ታላቅ የትምህርት መንገድ ያሻናል። የበገና ድርደራ ድምፅን ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ነፍስን የማንጻት፣ ምስጢርን የማስተዋልና ከአምላክ ጋር የጠበቀ ቅርበት የመፍጠር ጥበብ ነው። በኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤት የ1ኛ ዙር የበገና ሥልጠና ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ይህ ታላቅ ጥበብ ከተራ የዓለም ድምፅ ተለይቶ ወደ እግዚአብሔር ቅድስና የሚመራበትን ምስጢር ለመቅሰም፣ በዚሁ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ እንድትሳተፉና የዚህ ታላቅ ጥበብ አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። https://t.me/Oct13wed
744
13
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣ የፍልስፍናና የእግዚአብሔር ምስጋና ታላቅ መንፈሳዊ ሀብት ነው። ታላቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ምስጋናና ስለ መንፈሳዊ ዜማ ሲናገር፣ የምስጋና ድምፅ የሰውን ልብ ከምድር ከንቱነት ወደ ሰማያዊው ምስጢር እንደሚያሸጋግርና ነፍስን ከአምላኳ ጋር እንደሚያገናኝ ያስተምራል። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ «በገናን አንሱ፤ በበገናም ለእግዚአብሔር ዘምሩ» እያለ እንደተናገረው፣ በገና የንጉሡ የዳዊት እጆች ያረፉበት፣ የነቢያት መንፈስ የፈሰሰበት፣ የቅዱሳን ማኅሌትና የእግዚአብሔር ምሕረት መጠየቂያ ታላቅ የዜማ ዕቃ ነው። እኛም የዚህን ታላቅ መንፈሳዊ ሀብትና ጥበብ መሠረት በመጣስ ሳይሆን በመጠበቅ፣ ትውልድ ከመንፈሳዊ ሥሩ እንዳይደናቀፍና የቅዱስ ዳዊትን በገና ድርደራ በጥበብና በፍልስፍናው መንገድ እንማር ዘንድ ይህን ታላቅ የትምህርት መንገድ ያሻናል። የበገና ድርደራ ድምፅን ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ነፍስን የማንጻት፣ ምስጢርን የማስተዋልና ከአምላክ ጋር የጠበቀ ቅርበት የመፍጠር ጥበብ ነው። በኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤት የ1ኛ ዙር የበገና ሥልጠና ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ይህ ታላቅ ጥበብ ከተራ የዓለም ድምፅ ተለይቶ ወደ እግዚአብሔር ቅድስና የሚመራበትን ምስጢር ለመቅሰም፣ በዚሁ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ እንድትሳተፉና የዚህ ታላቅ ጥበብ አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
1
14
Sin texto...
1
15
አዲሱ ዓመት 2019፦ ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤ ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ ፍትሕ የሚገኝበት፤ ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤ ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤ ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤ ወጥተን የማንቀርበት፤ በአጠቃላይ ሀገራችን ከጫፍ እስከጫፍ ሰላም እና ተስፋ የሚነግስበት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን። የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ ፣ የሚወዱትን ከአጠገባቸው የተነጠቁ ወገኖችን በማፅናናት ፣ የታመሙትን በመጠየቅ ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን። መልካም አዲስ ዓመት !
104
16
"አንተሰ አንተ ክመ ወዓመቲከኒ ዘኢየኀልቅ!" መዝ ፻፪ የዓመታትና የዘመናት ባለቤት            🇪🇹✞እንኳን✞🇪🇹 ከዘመነ ማርቆስ  ወደ  ዘመነ ሉቃስ     በሰላም በጤና አሸጋገራችሁ! 🇪🇹 መልካም አዲስ ዓመት 🇪🇹    🇪🇹 ሰናይ 🌻 በዓል 🇪🇹
190
17
የዓመቱ የመጨረሻ ቀናት ሁልጊዜም የተለየ የሕሊና ድምፅ አላቸው። እነዚህ ጥቂት ቀናት አልፈው አዲሱ ዓመት ከመግባቱ በፊት በአሮጌው ዓመት ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የምናደርጋቸው እና የምንሰማቸው ነገሮች በሙሉ የራሳቸው የሆነ ከባድ ሚዛንና የራሳቸው የሆነ ጥልቅ ትርጉም አላቸው። ይህን ትርጉም ከልቤ መጋራት እንድጀምር አስቤ ይሆን አልያም የአመቱ መጨረሻ ካደረከው የምታስታውሰውን ተናገር ብባል ከአፌ (ይጥበቅ) ጋር አውርቻለሁ ለማለት ባላውቅም ወደሳቸው ቤት አቀናሁ። (አፌ(ይጥበቅ) ማለት እድሜአቸው ወደ ሰማንያዎቹ የሚሆኑ ጎረቤታችን ናቸው) አፌ ቤት እንደደረስኩ ሁለት ሰዎች ቁጭ ብለው አፌን እያስወሯቸው ነበር። ስገምት የንስሀ ልጆቻቸው ናቸው። ቤት ገባሁና መስቀል ተሳልሜ ''...ይቅርታ ረበሽኩ መሰል..'' ብዬ ልወጣ ስል... ''...እንደውም ስፈልግህ ነበር ቁጭ በል!..'' አሉኝ አፌ። ቁጭ እንዳልኩ ለሰዎቹ የጀመሩላቸውን ማውራት ቀጠሉ... ''... እና እንዳልኳችሁ ሰው በሕይወቱ ጎዳና ሲመላለስ እንደ ዓመቱ መቃረቢያ ያለ የጸጥታ ጊዜ አያገኝም። ቀኖቹ እያለቁ ሲሄዱ አየሩ ሳይቀር የለውጥና የምስጢር ጠጠሮችን የተሞላ ይመስላል። በነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የምንተንፍሰው የአሮጌው ዓመት አየር፣ ለመጨረሻ ጊዜ የምናያቸው የጨለማና የብርሃን ቅያሬዎች፣ እንዲሁም ለመጨረሻ ጊዜ የምናስባቸው የኃዘንና የደስታ ትዝታዎች በሙሉ የነፍስን ደጅ ያንኳኳሉ። ለመጨረሻ ጊዜ ሰውን ይቅር ማለት፣ ለመጨረሻ ጊዜ የቆየን ቂም ከልብ አውጥቶ መጣል፣ ለመጨረሻ ጊዜ በነበረን ነገር ሁሉ ላይ ረክቶ ማመስገን እነዚህ ሁሉ የዓመቱን በር የመዝጊያ ቁልፎች ናቸው። ​ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በስበከቱ እንደሚያስተምረን የጊዜ መለወጥ የሰማያዊውን መንገድ የሚያስታውስ፣ የሰው ልጅም በዚህ ምድር ላይ እግረኛና አላፊ መንገደኛ እንጂ ነዋሪ አለመሆኑን የሚያስረዳ ትልቅ ትምህርት ቤት ነው። ፍትሐ ነገሥትም ቢሆን የሰውን ልጅ የሕይወት ዘመንና የጊዜን ፍሰት ሲያመላክት፣ ሰው እያንዳንዱን ቀንና እያንዳንዱን የተሰጠውን አጋጣሚ በንጹሕ ልብና በበጎ ምግባር ሊፈጽመው እንደሚገባ ያስረዳል። በዓመቱ ማጠቃለያ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ የሚደረግ መልካም ነገር፣ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ የነበሩትን ጉድለቶች በሙሉ አልፎ የሚሸፍን፣ የነፍስን ቁስል የሚያድን ታላቅ ቅባት ይሆናል። ​አሮጌው ዓመት ሲሸኝ ለመጨረሻ ጊዜ የምናፈስሰው የንስሐ እንባና ለመጨረሻ ጊዜ የምንዘረጋው የምጽዋት እጅ፣ ወደ አዲሱ ምዕራፍ የምንዞርበትን ብርሃን ያበራል። የሰዓቱ እጆች ወደፊት እየተራመዱ አሮጌውን ዓመት ወደ ታሪክ መዝገብ ሲሸኙት፣ ሰውም በውስጡ ያለውን አሮጌ ማንነት ለመጨረሻ ጊዜ ትቶ፣ በይቅርታና በምስጋና ታጥቦ፣ በአዲስ ተስፋና በንጹሕ ሕሊና ወደ አዲሱ ዘመን ይሻገራል። እናንተም ታድያ እንዲሁ ልትሆኑ ይገባል። አሁን ጊዜውም እየመሸ ነው መሰል። ለማንኛውም በሰላም ያሳድረንና ነገ ከቅዳሴ በፊት በሰፊው እንነጋገራለን። መልካም አዳር ይሁንላችሁ! በሉ ተነሱ! እንደው ሻይ ቡናም ሳልል ዝም ብዬ በደረቁ አስቀመጥኳችሁ ልጆቼ ይቅር በሉኝ!.'' አሉ በተማጽኖ... ..ልጆቹም ብድግ ብለው ''...ኧረ አባቴ ምንም አያስፈልግም ከዚህ በላይ ምን አለና። ደህና እደሩ!'' ብለው መስቀል ተሳልመው ወጡ። እንደወጡም ወደ እኔ ዞረው ''...እንዴት ያሉ መልካም ሰዎች መሰሉህ። ስለ እውነት።  የተባረኩ ልጆች።.... እኔማ የፈለኩህ...'' አሉና መጥፋቴ ትዝ ብሏቸው እንደመገረም አሉና  "..ኧረ እንደው እስራኤል ልክ አልሰራህም። ስለእውነት ልክ አልሰራህም። መች ነው የመጣህ? ዛሬ ይኸው አምስተኛ ቀንህ። ወይንስ ጻጉሜ አይቆጠርም?..'' አሉና በእጃቸው የያዙትን የአጽዋማትና የበአላት ማውጫ እየሰጡኝ '' በል እስቴ ይህንን አንብብልኝ። ልጆቹንም ብጠይቅ አላወቁትም መሰል መልሰው ሰጡኝ። ያው የዘንድሮ ሰው አላውቅም አያውቅም። እኔም እንደምታየው አይኔ ከቀን ወደ ቀን እየደከመ ነው።'' ተቀብዬ ቀኑን እየጠየቁኝ እመልሳለሁ። አበቅቴ? ...፳፫ መጥቅዕ? ...፯ ''...ኧረ ባክህ?...'' እዎ እንደዛ ነው የሚል። ምነው? ''አበቅቴ ሲጨምር ጾመ ሀዋርያት ይቀንሳል ብዬ ነው ቀጥል እሺ... ቀጠልኩ... ጨረስኩላቸው። የገረመኝን ጥያቄ አስከተልኩ ''...እኔ የምሎት አፌ ይህንን ቀመር አባቶቻችን እንዴት ቀምረው እንደሚያውሉት ሳስብ ግርም ይለኛል። እንዴት ነው ግን?" አልኳቸው። የአያቶቻችንን እውቀት ጥልቅ መሆኑን ባውቅም ጥያቄዬ ግን የጅል አይነት መሰለኝ። ''...ኧይ እስራኤል እንደው ይንህን ትተህ እኮ የየእለት እና ወር ጸባዩ ይታወቃል። አየህ... እንጨት ሲቆረጥ እንዳይበሰብስ መችና በምን ሰአት መቆረጥ እንዳለበት ይታወቃል። ለሰውም እንደዚያው ነው።" ብለው አቆሙ። የሰው ምን እንደሆነ ለማወቅ እና እንዲያብራሩልኝ ብፈልግም አልቀጠሉም። የሰጡኝን የአጽዋማት እና የበአላት ማውጫ መልሰው ተቀብለው ዳዊታቸው ውስጥ ከተቱ። እኔም "...የሰዉም እንደዚሁ ነው...'' የሚል እንቆቅልሽ ይዤ ወደ ቀጣዩ አመት እዘዋወር ዘንድ ግድ እያለኝ ተሰናብቻቸው ወጣሁ። የአመቱ የመጨረሻው እና እንቆቅልሹ የህሊና ድምጽ! ✍️እስራኤል ሰይፉ https://t.me/Oct13wed
128
18
እኔና ውሳኔ... ...ለመሄድ ቆርጬ ብድግ ከማለቴ መልሼ ተቀመጥኩ ከዚህ ጋር ሁለቴ ያውም ያሁን ብቻ የሌላው ቀን ቀርቶ የተመለስኩበት እንኳንስ ሊቆጠር አይታሰብ ከቶ ምን ይሆን የያዘኝ እንዳልሄድ ሚስበኝ ቆርጬ እንዳልቆርጥ አቋርጦ 'ሚያስቀረኝ? ልሄድ ያሰብሁ ድሮ ለምን እዚህ ልቅር ለራሴም አልገባኝ እንኳንስ ልናገር። እንዲህ ግራ ገብቶኝ...                         ሳልወስን ቀርቼ እንዲሁ ሳልሻሻል አመቱም አለቀ    መጣ ሌላ ፍቼ። ኤ.....ጭ! ሲያበሳጭ ቆርጦ እንደመነሳት ለምን ከንቱ ልልፋ? ካሁን ወዲህ ይብቃኝ ላቁም ሰውም አላስከፋ! ..በቃ ልነሳ ልተው መወላወል ይቆይ መነሳቴ እንደው አይቀርም ቢዘገይ  ብድግ...ቁጭ ኤ....ጭ ሲያበሳጭ! https://t.me/Oct13wed ✍️እስራኤል ሰይፉ (ለአንዱ...)
106
19
እኔና ውሳኔ... ...ለመሄድ ቆርጬ ብድግ ከማለቴ መልሼ ተቀመጥኩ ከዚህ ጋር ሁለቴ ያውም ያሁን ብቻ የሌላው ቀን ቀርቶ የተመለስኩበት እንኳንስ ሊቆጠር አይታሰብ ከቶ ምን ይሆን የያዘኝ እንዳልሄድ ሚስበኝ ቆርጬ እንዳልቆርጥ አቋርጦ 'ሚያስቀረኝ? ልሄድ ያሰብሁ ድሮ ለምን እዚህ ልቅር ለራሴም አልገባኝ እንኳንስ ልናገር። እንዲህ ግራ ገብቶኝ... ሳልወስን ቀርቼ እንዲሁ ሳልሻሻል አመቱም አለቀ መጣ ሌላ ፍቼ። ኤ.....ጭ! ሲያበሳጭ ቆርጦ እንደመነሳት ለምን ከንቱ ልልፋ? ካሁን ወዲህ ይብቃኝ ላቁም ሰውም አላስከፋ! ..በቃ ልነሳ ልተው መወላወል ይቆይ መነሳቴ እንደው አይቀር ምን ቢዘገይ  ብድግ...ቁጭ ኤ....ጭ ሲያበሳጭ! ✍️እስራኤል ሰይፉ (ለአንዱ...)
1
20
ትንሽ መሆን ግድ ነው... ...የሰርክ ጸሎት የሚደወለው 11:00 ላይ ነው። ምሁር ኢየሱስ ገዳም። ያኔ ህጻን ሳለሁ ታድያ ውስጤ ትልቅ ሰው ነበር መሰለኝ ንግግሬ ሁሉ እንደኔ ካለ ህጻን የሚጠበቅ አ
ትንሽ መሆን ግድ ነው... ...የሰርክ ጸሎት የሚደወለው 11:00 ላይ ነው። ምሁር ኢየሱስ ገዳም። ያኔ ህጻን ሳለሁ ታድያ ውስጤ ትልቅ ሰው ነበር መሰለኝ ንግግሬ ሁሉ እንደኔ ካለ ህጻን የሚጠበቅ አይነት አልነበረም። (ኧረ እንደውም ዳኛው እስከመባልም ደርሼ ነበር😁) ...አንድ ቀን ታድያ የሰርክ ጸሎት ረፍዶብኝ እየተቻኮልኩ እግሬን እታጠባለሁ። (ምን አልባት ምስባክ ሳያጠኑ ከደረስኩ ስለማልቀጣ) ልክ ግራ እግሬን ጨርሼ ቀኙን ልጀምር ስል ኤርሚ ጨ (''ጨ'' ቅጽል ስሙ ነው) እየተጣደፈ መጣና "..ዞር በል ኩታራ!'' ብሎ ገፋ አደረገኝና እጁን ታጥቦ አለፍ እንዳለ ''...ኧዪ ጊዜ ጥሎኝ እንጂ እኔም እኮ ይሄኔ ካንተ እኩል ነበርኩ.!'' አልኩት። ኦሆ! ብሎ ነጠላውን ትከሻው ላይ እየጫነ ሄደ። እኔም ' ምን አጋፋው ቆይ? እኔም እኮ ረፍዶብኛል። ተራ እንኳ ባይጠብቅ በስርአት ታጥቦ አይሄድም? አልከለከልኩት! ወይንስ ትንሽ ስለሆንኩ ነው?..' እያልኩ ብቻዬን እያጉረመረምኩ ታጥቤ ተከተልኩት። ወደ ቤተ ጸሎት። አድጌ ትልቅ ከሆንኩ በኋላ ታድያ ልክ ይህን ፎቶ የተነሳን እለት አስታወሰኝ ''...አንተ ግን ያኔ ልጅ እያለን ያልከኝን ግን መቼም አልረሳውም።'' ''...የቱን ነው?'' አልኩት እየሳኩኝ። በልጅነቴ የማልለው ነገር ስላልነበር ምን እንዳልኩት ለማስታወስ "...ያኔ እግርህን እየታጠብክ ያልከኝን። ''..ጊዜ ጥሎኝ እንጂ...' ነው ምናምን ያልከኝን'' ''..ታድያ ምን ያጋፋሃል አርፈህ በስርዓት አትታጠብም ነበር?" አልኩት ''..ኧረ ልክ ነው እኮ ያው የልጅ መልስ ስላልሆነ ገርሞኝ እንጂ'' ''..ልጅ መሆን ግድ ነው'' ተሳሳቅን ዛሬ ታድያ ልደቱ ነው። ...ታላቅየው እንኳን ተወለድክልን (አሁንማ እኩል ነን የምን ታላቅ😁) መልካም ልደት ይሁንልህ ውዱ ወንድሜ!🎂🎂🎂
92